የሸዋ ኦሮሞ ላይ የተመዘዘ ሁለት ሰይፍ – ከተማ ዋቅጅራ

ሰው ሆኖ እንደሰው ማሰብ ሲሳንህ ከባድ ነው ፣ እንደ ሰው ቁመና ኖሮህ እንደ ሰው አለማሰብ በሽታ ነው፣ እንደ ሰው አእምሮ ሰጥቶህ እንደ ሰው ማሰብ ካቃተህ ካንሰር ነው።
shewaየሸዋ ምድር የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የጉራጌ፣ የሃዲያ፣ የከንባታ፣ የወርጂና፣ የሌሎችም መኖሪያ ምድር እና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንብርት ናት ።
የሸዋ በደል የጀመረው 1983 አመተ ምህረት ላይ ነው። ሸዋን በዘር የተደራጁት ጽንፈኞቹ ህዋትና ሸኔ ለምን ይጠሉታል ብላቹ ጠለቅ ብላችሁ ብትጠይቁና ብትመረምሩ የምትደርሱበት ጭብጥ ህውአት ሸዋን የምትጠላው የሸዋው ንጉስ ንጉስ ምንሊክ ሰሜን ላይ የነበረውን የመንግስታቶችን ሃይል ሰብሮ ወደ መሃል አምጥቶ በመትከሉ  ምክንያት ሰሜኑን ያደኸየው ምንሊክ ነው ብለው በማመን ዘረኞቹ ለፖለቲካ ትርፍ ብለው የውሸት ትርክት በመንገራቸውና ይሄንንም ታሪክ ህዝብን ለማታለል ስለተጠቀሙበት ነው።
ኦነግ ሸኔ ደግሞ ኦርቶዶክስ ክርስትናን በግድ ኦሮሞ እንዲቀበሉ ያደረጉት የኦሮሞን ህዝብ ሰብስቦ ከዚህ መለስ ገብረ ማርያም ከዚህ መለስ ደግሞ ወለተ ማርያም ብሎ ኦሮሞን ክርስትና እንዲቀበሉ ያደረገውና ክርስትናን ያስፋፋው ምኒልክ ነው በማለትና ይሄንን የውሸት ትርክት ለፖለቲካ ፍጆታና ለድብቅ አላማቸው ማሳኪያ ስለተጠቀሙበትና የአኖሌ የውሸት ትርክት በመጨመር የኦሮሞ ማህበረሰብን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንዲገባ አድርገዋል።
የአኖሌ ሃውት የሚመለከተው ነፍጠኛውን ነው። ይቺ ኮድ ደግሞ ከአማራው ማህበረሰብ በተጨማሪ የሸዋ ኦሮሞን እንደሆነ ላሰምርበት እወዳለው ። በምንሊክ ግዜ  ወደ ተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል የዘመተው  ከ80% በላይ በጎበና ዳጬ መሪነት የሸዋ ኦሮሞ ነበረና ነው ለዚህም ማሳያ በሸዋ ኦሮሞ ሽማግሌዎችና በአርሲ ኦሮሞ ሽማግሌዎ መካከል በቅርቡ በሬ ታርዶ የእርቅ ፕሮግራም እንደተደረገ የሚታወቅ ቢሆንም ቅሉ እነዚህ ዘረኞች ግን የሸዋ ኦሮሞም ቶኩማ ኦሮሞ በሚል ማደንዘዢያነት  ሳያስበው ቃስ በቃስ በማጥፋት ላይ ናቸው። ለዚህም ማሳያ በዚህ 27 + 3 አመት ውስጥ በከፍተኛ ሁሌታ እየተገደለና እየተፈናቀለ ያለው ከአማራው ከክርስትያኑ ባልተናነሰ የሸዋ ኦሮሞ ነው። ምክንያቱ ደግሞ የሸዋ ኦሮሞ በአገሩና በሐይማኖቱ የማይደራደር  ጀግና ነውና ነው። ጀግናን ደግሞ ጠላት ፊት ለፊት ገጥሞ ማሸነፍ ስለማይችል አንድ ነን በሚል ሽፋን ሸፋፍኖ በማቅረብ ማጥፋት የምትለውን የፈሪዎች ፖለቲካ በመከተል እየሰሩበት ነው። ደግሞም በግዜ ካልተነቃ አደገኛ የሆነ አካሄድ ነው።
በህውአት ዘመን አዲስ አበባን የተለያዩ የኦሮሞ ልጆች መርተውታል ነገር ግን አንዱም የሸዋ ኦሮሞ  የለም ። ምክንያቱም ደግሞ በኢትዮጵያዊነቱና በሐይማኖቱ  ስለማይደራደር ለሚፈልጉት አላማ የተመቸ ስላልሆነ ነው።
ኦነግ ሸኔ 4ወይም 5 በኦሮሞ ስም ያቋቋመው ፓሪቲዎች አሉት ነገር ግን በአንድም ውስጥ የሸዋ ኦሮሞ ሊቀመንበር በመሆን የመሪ ቦታ አይሰጠውም ይህ የሚያሳየን በሸኔዎች የሸዋ ኦሮሞ ጎበና ዳጬ ነውና ነው። በሸኔዎቹ ጎበና ዳጬ ማለት ኦሮሞን የከዳ ወይንም ባንዳ እንደማለት ነው።
የሸዋ ኦሮሞ ሙሁራን ፖለቲከኞች የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች አክቲቪስቶችና ተሰሚነት ያላችሁ ማህበረሰቦች ቶኩማ ኦሮሞ በሚለው ሽፋን ውስጥ ምን እንደሚከናወን እና እነማን ምን እየሰሩ እንደሆነ መከታተልና የሸዋ ኦሮሞ ከመጣበት ጥፋት መታደግ ይጠበቅብናል። ሙሁራኑ እና ፖለቲከኛው በሸዋ ግዛት ውስጥ ቦታዎችን ከሌሎች ወንድም ብሄሮች ጋር በመነጋገር የመሪነት ቦታውን መቆጣጠር ይገባል። ይሄ ግድ ነው። በሸዋ ክልል ውስጥ የሚሰሩት ወንጀሎች በሙሉ የሸዋ ኦሮሞ ተጠቂ ሆኖ ሳለ ነገር ግን በስመ ኦሮሞ በሌላ ማህበረሰብ እየተጠላና እንደ ጠላትነት እየታየ ስለሆነ በአትክሮት ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ስለዚህ በሰበታ፣ በሱሉልታ፣ በሰንዳፋ፣ በአንቦ፣ በሸኖ፣በቢሾፍቱ እና በመሳሰሉት የሸዋ ግዛቶች በሙሉ የራሱ የአካባቢው ተወላጅ ማስተዳደር አለበት።  የራስ የሆነ ሰው ሃላፊነት ስለሚሰማው ወገኖቹን አሳልፎ ለአደጋ አገርን ደግሞ ለጥፋት አይጋብዝምና ነው።
ይህ ካልሆነ ግን እነዚህ በኦሮሞ ስም የተደራጁት ጽንፈኞቹ በኦሮሞ ክልል ውስጥ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ዘግናኝ ግፍ እየተሰራ ስለሆነ በዚህም ምክንያት በሌሎች ማህበረሰብ ባጠቃላይ ኦሮሞ አራጅና ጨፍጫፊ አረመኔ ተደርጎ እየተሳለ ስለሆነና የተሰራው ወንጀል በአለም ፍርድ ቤት ጭምር በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ ማህበረሰቡ ተረጋግቶ መኖር የሚያስችል ሁኔታዎችን ስለማይፈጥር ወደ በቀልና በደልን ወደመመለሱ ከተገባ አጥፊዎቹ ሳይሆኑ የሚጠቃውና የሚጎዳው ምንም የማያውቀው በስመ ኦሮሞ የሆነውና በስሙ በተነገደው የሸዋ ኦሮሞ ነው። የሸዋ ኦሮሞ የገጠመው አደጋ ከሁሉ የከፋ ነው። ቶኩማ ኦሮሞ በማለት አንድ ነን ብሎ ወደ ሸኔዎቹ ቢሄድ ሸኔዎቹ ጎበና ዳጬ ብለው በሰይፍ አሁንም እንደሚገሉት ይገደላል ወደሌላው ማህበረስብ እንዳይሄድ ደግሞ በስሙ በተፈጸመ ወንጀል ሌላው ማህበረሰብ እንደ ገዳይና አረመኔ ቆጥረውታል። የጨነቀ ነገር ከፊታችን እንዳለ አውቀን ከአደጋው ለማምለት በግዜ በስማችን ከሚነግዱ እና በወገናችን ላይ ከሚመጣብን አደጋ ለማምለጥ በሸዋ ምድር ላይ የስልጣን ቦታውን በመያዝ የሸዋ ኦሮሞ አገሩን ሃይማኖቱን እና ወገኑን ጠባቂ እንጂ ገዳይ ወይንም አገር አጥፊ እንዳልሆነ ማሳየት ይጠበቃል። ይሄንን ማሳየት  ካልቻልን የሸዋ ኦሮሞ ከባድ ግዜ እንደሚመጣበት መናገር ነብይ መሆን አይጠይቅም።
ከሚናገረው ዝም ያለው ህዝብ እጅግ ይበዛል፣ አገር ለማፍረስ ከሚቅበዘበዘው ይልቅ አገር ለመጠበቅ የሚነሳው ህዝብ አስፈሪ ነው፣ በዘርና በሃይማኖት ከረጢት ውስጥ ተደብቀው ድብቅ አላማቸውን ለማሳካት ከሚውተረተሩት ይልቅ የሚሆነውን እና እየሆነ ያለውን እየታዘበ ያለው በብዙ ሚሊዮን ይበዛል።
እነዚህ የዘርና የሃይማኖት ነጋዴዎች በዘርና በሃይማኖታቸው ተደራጅተው የመንግስትን ስልጣን እየተቆጣጠሩና መቆጣጠር እንዳለባቸው በግልጽ እየተናገሩ ለዚህም እየሰሩ ኦርቶዶክሳዊያኑን ግን የመንግስት ስልጣን መያዝና ወደ ስልጣን እንዳይመጣ ፖለቲካና ሃይማኖት አንድ አይደሉም ይሉሃል። ሁሉም ቦታ ብትሄድ ግን በሃይማኖትና በዘር ተደራጅተው ስልጣኑን በመያዝ ለኦርቶዶክሳዊያኑ እልቂትና ሃይማኖታዊ መብቱን እንዳይጠቀም አደጋ የሆኑበት። ሁሉም የሚመለከተው በሙሉ መቅለስለስና ዝም ከማለት ወጥተን  ደፍረን ወደፊት ወደመሪነት ቦታው መምጣት አለብን ካለበለዛ ለሚመጣው አደጋ የኛም ዝምታን ወገናችን ላይ ለሚፈጠረው አደጋ  ከተጠያቂነት አያድነንም።
የኔ ቋንቋ ተናጋሪ ብሎ መዘናጋት የለብንም ማንም ይሁን ማንም አካባቢዊን መጠበቅና ማስተዳደር ያለበት ያካባቢው ሰውና ያካባቢው ማህበረሰብ ያመነበትና የመረጠው መሪ መሆን አለበት።
ኦርቶዶክ የሚበዛበት ቦታ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆነ የእስላም አማኝ በሚበዛበት ቦታ የእስልምና ተከታ የሆነ ሰው ፕሮቴስታንት በሚበዛበት ቦታ የፕሮቴስታንት አማኝ የሆነ ሰው ሆኖ በማህበረሰቡ የታመነ እና ብቃት ያለው ሰው በመሆን አካባቢውን እና ሃይማኖቱን ከአደጋ የሚጠብቅና የሚያስጠብቅ መሆን አለበት።
ለሚሳለ፣ ሸዋ 89% የኦርቶዶክስ አማኝ ነው ፣ አዲስ አበባ 83% የኦርቶዶክስ አማኝ ነው፣ አማራ 89% ኦርቶዶክስ አማኝ ነው አፋር 97% የእስላምና አማኝ ነው ሱማሌ 99% እስላምና አማኝ ነው ትግሬ 95% ኦርቶዶክስ አማኝ ነው ደቡብ 40% ፕሮቴስታንት አማኝ ነው ወለጋ 50 %  ፕሮቴስታንት አማኝ ነው……እያለ ይቀጥላል።
ማስታወሻ ለመንግስት ፦ በአዲስ አበባ ዙሪያ ለተነሱ የሸዋ ኦሮሞ ካሳን በተመለከተ  ከአዲስ አበባ ለተፈናቀሉ አዲስ አበቤዎች ማስታወስ ያልተቻለው ለምንድን ይሆን? ስለዚህ ኮንደሚኒየሙ ፖለቲካ አጀንዳ አለው ማለት ነው።
ከአዲስ አበባ ዙርያ በመንግስት ስልጣል ባሉ ሰዎች ዘራፊነትና ማጭበርበር በግፍ ለተነሱት ገበሬዎች አሁንም በመንግስት ዘራፊነትና አስገዳጅነት የደሃን ህዝብ ንብረት ስልጣንን ተጠቅሞ በመዝረፍ ለተፈናቃይ ገበሬ በመስጠት ለምስኪኑ ሸዋ ኦሮሞ ወዳጅነት ወይንስ ጠላትንት? በግዜው ስልጣን ላይ ስለሆናሽሁ የበሰለ ካድሬ ማከማቻ ቦታ ስትፈልጉ ኮንደሚንየም አገኛችሁና በገበረው ስም የማይገባውን ለካሳውም ተመጣጣኝ ያልሆነ ቦታ የሌለው ቤት በመስጠት የናንተ የፖለቲካ አላማ ለግዜ ሊሳካ ይችል ይሆናል ነገስ… ስልጣኑን ስትለቁትስ የኔ የሚለው ማህበረሰብ ንብረቱን መጠየቁ ይቀራልን ለምንድነው በሸዋ ኦሮሞ ስም ወንጀል በመስራት የሸዋ ኦሮሞን ማስመታትና በሌላው ማህበረሰብ ማስጠላት የተፈለገው። በሸዋ ኦሮሞ ስም መቆመር በግዜ በቃችሁ ሊባሉ ይገባል። ይሄም ጥቆማ ነው ለሚመለከተው።
ገበሬውን መጥቀም ከተፈለገ  መጀመሪያ ገበሬውን አፈናቅሎ ለከፋ መከራ የዳረጉትን የመንግስት ባልስልጣንን በመያዝ ወንጀል የሰሩትን ሰዎች እነዚህ ናችው ያፈናቀሉህና ለችግር የዳረጉህ እነዚ ናቸው ተብሎ ለህግ ማቅረብ እና ተመጣጣኝ ፍርድ ማስፈረድ። በሁለተኛ ደግሞ ገበሬዎቹ በተነሱበት አካባቢ ከ200-300 ካሬ ሜትር ቦታ በመስጠት  ቤት ሰርቶ  መካስና ማቋቋም ሲገባ የደሃውን ንብረት ዘርፎ ግዜአዊ የፖለቲካ ትርፍ በማስብ የሚሰራው መንግስታዊ ወንጀል  ለገበሬው ጠላትነትን እንጂ ወዳጅነተን አያገኝበትም።
ግዜው ከባድ ስለሆነ ይሄ ግዜ አልፎ በአገራችን ህዝብ መሃል መተማመን መጥቶ ፍራቻ እስኪጠፋ ድረስ በራሳችን ሰውና አብላጫ የሃይማኖት ቁጥር ያለው ሃይማኖት አካባቢውን ማስተዳደር አለበት አዲሳባን ጨምሮ የሸዋ ግዛቶች በሙሉ ሃይማኖቱን የሚያስከብርና ህዝቡን የሚያውቀውና የመረጠው ብቻ መመራት አለበት። ይሄንን ከባድ የመከራ ዘመን ከታለፈ ማንም ይሁን ማን ኢትዮጵያዊ የሆነ ከሆነ ችግር የማይሆንበት ግዜ ይመጣል እስከዛው ግን እነሱ ለጥፋታቸው የሚፈልጉትን እንዲሰሩ በፍጹም መፍቀድ የለብንም እላለው።
ከተማ ዋቅጅራ

4 Comments

 1. ከተማ ዋቅጅራ እናመሰግናለን በእርግጥ ነዉ ጁዋርና የእሱ ደቀ መዝሙሮች ቄሮዎች ለሸዋ ኦሮሞ ቀና ልብ የላቸዉም እዚህ ላይ የማይባል መጥፎ መጥፎ ስም ይሰጡታል አያስጠጉትም። ይህ እንዳልከዉ በሁለት ምክንያት ነዉ ከእነሱ በተሻለ ሁኔታ ኢትዮጵያ ሀገረ ምስረታ ላይ አሻራዉ አለ የኢትዮጵያም ምልክት ነዉ። ግራ የገባዉ ነገር ግን እነዚህ ወሮበሎች ሲወራጩ እስከ ዛሬ ዝም ብሎ መመልከቱና በስሙ ይህ ሁሉ ግፍ እንዲሰራ መፍቀዱ ነዉ። ምንም ፊን ፊን ቢሉም የሸዋ ኦሮሞ ፍቃድ ካልሰጣቸዉ የትም አይደርሱም።

  ሀይማኖቱን በተመለከተ ድብቅ የለዉም ጁዋር መሀመድ ክርስቲያን ቀና ሲል አንገቱን እንመታለን ብሎ ቀደም ብሎ ጂሃዳዊ አዋጁን ባወጀዉ መሰረት መመሪያዉን እየተገበሩ ነዉ። ግራ የገባ ነገር ግን ርእሰ ብሔሩ ይህ ሁሉ ሰቆቃ በሰዉ ልጅ ላይ ሲፈጸም ተዉ ማለትም ማስቆምም ተስኖት ማቾቹን ሲኮንን ነዉ። አሁን በዚህ ሰሞን እንኳን እነዚህ ሰዎች በመታሰራቸዉ የተገኘዉ አንጻራዊ እረፍት ለድክመቱ በቂ ማሳያ ነዉ ቀደም ብሎ እርምጃ ቢወሰድባቸዉ አገርም አገር ይመስል ነበር። ሰዎች በሀይማኖታቸዉና በዘራቸዉ እየተመነጠሩ ሲገደሉ የዘርና የሀይማኖት ማጥፋቱን ዘመቻ እሱና አባ ዱላ ግጭት ብለዉ ወንጀሉን ያሳንሱታል።ባጠቃላይ ዛሬ ከባጥ በላይ ከሚጮኸዉ መንጋ ያንተን መሳይ ወገኖች አገር አገር ሁና እንድትኖር ትልቅ አስተዋጽኦ ስለምታበረከቱ በትጋት በጥረት ለሀገራችን እንቁም እላለሁ። ይህ የጨረባ ተዝካር ማለፉ አይቀርም።

 2. እውነተኛ ታሪክ ትቀበራለች እንጂ አትሞትም፡፡ ድሮ ድሮ “ሸዋ ባላመጠ በዓመቱ ይውጣል” ይባል ነበር፡፡ ነገር አዋቂነቱን ለማሳየት መሰለኝ፤
  ለማንኛውም የህይል አሰላለፍ መደቡ የታወቀ ነው (ለሚያውቅ)፡፡
  1። ወለጋ፣ 2፡ ጂማ፟ ኢሉባቦር፡ 3፡ አርሲ ባሌ ህረር፡ 4፡ ሽዋ 5፡ ቦረና፡ ቋንቋ ብቻውን አንድ አያደርግም፡፡ ከሶማሊያ በላይ ማን ምስክር አለ? That is what the former Ayatollah missed. የኢትዮጵያን ስሪት በደንብ ሳያጤኑ የሞቅ ሞቅ ፖለቲካ ዉስጥ ገብቶ መንቦጫረቅ ዋጋ ያስከፊላል።
  አሰላለፍ፡
  ህ/ መደብ#3 ብቻ ነው አብይን የሚገዳደር፡፡
  2/ መደብ #1 አቢይን ወዶት ሳይሆን ከመደብ #3 ጋር ስለማይስማማ ነው፡፡
  3/ በህይማኖት ቢሆን መደብ#2 እና መደብ#3 አንድ መሆን ነበረባቸው፡፡ የመደብ#3 ከአብይ ጋር መሆን “በቃ ልጃችን ንው” ቢሉም ይችላሉ። ግን እሱ አይደለም፡፡ ይቅር!
  3/ መደብ#4 በህይማኖት ምክንያት ክመደብ#3 ጋር ሊስማማ እንደማይችል አሁን ስለገባው (በሻሸመኔ ምክኛት) በመሪነት የመሰረታትን ኢትዮጵያን ለማዳን የበለጠ ህላፊነት እንዳለበት ተረድቶታል፡፡ ሸዋ የጀግኖቹነ ታሪክ ያለ ይሉኝታ እና መሸማቀቅ በኩራት ወደ አደባባይ ማምጣት አለበት፡፡ አለያማ ጀግናው ራስ አበበ አረጋይን (የራስ ጎበና ዳጨ የልጅ ልጅ) የትግራይ ሰው ነበሩ (አረጋይ የሚለውን ስም በማየት!) ብሎ የሚያስብ ትውልድ ተይዞ ወዴት መድረስ ይቻላል? ለማንኛውም ለኢትዮጲያ ሲል መደብ#4 ከአብይ ጋር ዪሰለፋል (ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተገፍተው ኤክሴፕሽን ሊሆኑ ችለዋል!)።

  በነገራችን ላይ “ሸዋ” ሲባል ኦሮሞ ወይም አማራማለት አይደለም፡፡ በዋናነት ሁለቱ እየተዋጉም እየተጣሉም እየተጋቡም እየተዋለዱም የገመዱት ዘመን የተሻገረ ዉሁድ (ወልመካ) ማንነት ንው፡፡ እስቲ እነዚህ ዐረፍተ ነገሮች ኦሮሚፋ ይሁኑ አማርኛ ንገሩኝ፡ “መስታወቂያ ኪያ ነተቀበሌ”፤ “አኒ ደስ ናጀዴ”
  Hey, how about a political grouping something like, “Shoan Restoration/Renaissance Party” ?

  • correction:
   3/ ………የምደብ#2 ከአብይ ጋር መሆን “ብቃ ልጃችን ነው”……ብሚለው ዪተካ። (ምደብ#3 ሳይሆን መደብ#2 ተብሎ ይነበብ። ይቅርታ!

 3. When the radical ethnic politicians accuse Shewa Oromo of being the Orthodox faith, they forget their faith too is not necessarily invented by them. IRRETCHA too is mainly a Shewan Oromo tradition and besides Orthodox is in Greece, Former USSR, Cyprus, Bulgaria among others and not necessarily invented in Ethiopia. Why should there be Oromo Orthodox church if there is no Oromo Protestant church? Ethiopian Muslim has strong bond with other Ethiopian Muslim that doesn’t speak the same language and that is a good thing. If it is okay to use Arabic in our Mosques why not Geez in our Orthodox and Catholic churches? Orthodox Oromo is known for having deep attachment to Ethiopia. The list of Orthodox Oromo colonels and generals that fought for their country is very, very long. This is not to mean Orthodox of other language groups or Oromos of other Christian or Muslim faith didn’t fight for Ethiopia. But in SELALE alone the staggering number of well known Ethiopian warriors for generations is amazing. ABICHU-GELAN-GELA was a beloved children’s song when I went to KG as much as HAYLEMARYAM MAMO YETTORU GEBERAE. We had no idea who those people were but it was nice to remember the war heroes of Ethiopia while we still had our angle-like innocence.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.