በመጨረሻም ታላቁ ሰው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

በመጨረሻም ታላቁ ሰው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተወካዮቻቸው፣ የኢሰመጉ አመራሮች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና አፍቃሪዎቻቸው በተገኙበት በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
120999445 10223851844823089 8968558971835030966 nጀግናችንን ሸኘን፤ ቀብሩም ክብራቸውን እና ሥራቸውን በሚመጥን መልኩ ተከወነ።
ኖሮ መሞት ምን እንደሆነ በተግባር ያሳዩኝን አባቴን ፕሮፌሰር መስፍንን በአካል ተገኝቼ ለመቅብር በመቻሌ ፈጣሪን አመሰገንኩ። ኖሮ ላለፈ ሰው ሞት ጥሩ እረፍት ነው። ይብላኝ ለኛ ለቀረነው ከእድሜያችን ውስጥ ከኖርንበት ያልኖርንበት ዘመን ሚዛን ለሚደፋው። በፍርሀት ቆፈን ለተያዝነው፣ በንዋይ ፍቅር ለዋልነው፣ ሆዳችን ያባውን ለመተንፈስ ብቅል መቅመስ ግድ ለሚለን፣ አንገታችንን እንደ ሰጎን አሸዋ ውስጥ ቀብረን ለግፍና ለግፈኞች የዝምታ ድጋፍ ለምንቸረው፣ ላለፈ ላገደመው ሹመኛ ሁሉ ጭብጨባና ፉጨት እየለገስን ስልጣን መባለጊያ እንዲሆን ላደረግነው፤ ይብላኝ ለኛ ሰው ሆኖ መኖርን በርቀት እያየን በእድሜ ጠገብ ጉዞ ሳንኖር ለምናልፈው። ፕሮፌሰር እነዚህን ሁሉ አሸንፈው፤ ሰው ሆነው ኖረው ሰው ሆነው ያለፋ ናቸው።
ሰው ሆኖ፣ እንደሰው ተከብሮ፣ ለሰው ክብር ሲል ተገፍቶና ተዋርዶ ከሰውነት ጸጋ ሳይጎድል ሰው እንደሆነ ለማለፍ የወደደ ሁሉ የጋሽ መስፍንን ዱካ ይከተል።
ከሰውነት ከመጉደል ያውጣችሁ!
የጋሽ መስፍንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን!
ያሬድ ኃይለማርያም
PhotoGrid 1601986486489 PhotoGrid 1601986523682 PhotoGrid 1601986505198
ተጨማሪ ያንብቡ:  እርዱን ፍረዱልን አንልም፤ በነፃነት ተጋድሎአችን አይግቡብን! - ከጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.