ደቡብ ምዕራብ 11ኛ የኢትዮጵያ ክልል እንዲሆን ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ ተወሰነ

ahmed የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች 11ኛ የኢትዮጵያ ክልል መሆን እንዲችሉ በምርጫ ቦርድ አስፈጻሚነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወሰነ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው በአጀንዳነት ከተመለከታቸው አበይት ጉዳዮች መካከል አንዱ የደቡብ ምዕራብ ክልል ጉዳይ ነው።

የምክር ቤቱ የሕገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሕዝቦች ያቀረቡትን ክልል የመሆን ጥያቄ አብራርቷል። የኮሚቴው ጸሓፊ አቶ ወርቁ አዳሙ እንዳሉት የከፋ፣ የቤንች ሸኮ፣ የምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮና ሸካ ዞኖች እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳ በጋራ ክልል ለመመስረት መወሰናቸውን ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል።

የዞኖቹ ምክር ቤቶችና ልዩ ወረዳው አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው መቅረባቸውን የገለጹት አቶ ወርቁ አራቱ ዞኖችና ልዩ ወረዳው ውሳኔውን በሙሉ ድምጽ ያጸደቁ ሲሆን አንዱ ዞን በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል ብለዋል።

ዞኖቹ ከኢህአዴግ መንግስት በፊት በአንድ ጠቅላይ ግዛት ስር የነበሩና ተቀራራቢ ቋንቋ፣ ባህልና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እንደሚጋሩም ገልጸዋል ነው ያሉት።

ቋሚ ኮሚቴው በሕገ መንግስቱ መሰረት ክልል የመሆን ጥያቄው መቅረቡን ካረጋገጠ በኋላ በዛሬው እለት በምርጫ ቦርድ አስፈጻሚነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አባላት አቅርበዋል።

ኢዜአ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን የሰላምና የትብብር አድቮካሲ ግሩፕ ፤በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

6 Comments

 1. ሲልጤ ከጥቂት አመት በፊት አረብ ነኝ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ እንደወጣ አስታውሳለሁ ዛሬስ ምን ዞን ሊሆን ይሆን? አይ የቀልድ ጊዜ አገር ላይ እንዲህ ይቀለድ?

 2. “ዞኖቹ ከኢህአዴግ መንግስት በፊት በአንድ ጠቅላይ ግዛት ስር የነበሩና ተቀራራቢ ቋንቋ፣ ባህልና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እንደሚጋሩም ገልጸዋል ነው ያሉት።”

  ላስረዳ ይፈቀድልኝ፡
  ይህ ክልል መሬት ሲወርድ በደርግ መጨረሻ ዐመታት “ከፋ” ከፍለ ሃገር የሚባለው ነበር፡፡ በጃንሆይ ጊዜ ደግሞ “ከፋ ጠቅላይ ግዛት ሲቀነስ ጂማ” ማለት ነው፡፡ ጂማ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ ጂማ ያለእነዚህ ጎረበቶችዋ አያምርባትምም ኢኮኖሚካሊም አንሰራርታ የቀድሞ የስልጣኔ እና የዘመናዊነት ማማዋ ላይ መመለስ አትችልም፡፡ አቢቹ ዘ ብሄረ ጂማ ይህንን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ኮንታ እና ዳውሮን በጎበኘ ጊዘ ምን አለ? “እናንተ የኛ የጂማዎች ኩራት”። ካፍቾ ከአባተ ኪሾ ወይም ርስቱ ይርዳው ይበልጥ ልቡ ለአቢይ ለዐብይ ይቀርባል፡፡ የዚህን ትርጉም የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ምን እንደታሰበም ታሪክ ለሚያውቅ ሰው ግልጥ እና ግልጥ ነው፡፡ ኮይሻ ለመዝናናት ለመሄድ በጂማ በኩል ማለፍ ይጠይቃል፡፡ በወላይታ ሶዶ በኩልም መሄድ ይቻላል ግን በጣም ይርቃል፤ አይመችም፡፡

  • ከድር ሰተቴ ብዙ የታጨቀ ሀሳብ አቅርበሀል ፈታ ብታደርገዉ ወገን ይማርበታል ሰዎቹ በዚህ ሰዉዬ አማካይነት ጉድ ሳይሰሩን አይቀሩም።

 3. This area generates the most foreign currency amount through export of coffee and khat compared to all the foreign currency amount which the other parts of Ethiopia generate through export. With the evergrowing international foreign aid cuts this region is bound to become the backbone supplier of the Ethiopian national banks foreign currency needs .

  • In the following few years right after the 1974 revolution some farmers around the city and the weavers in the city saw their lives changed. The irrigation farmers that provided fresh vegetable every morning 365 days a year even bought their own trucks instead of renting and the TEFF farmers made extra money in off seasons selling fire wood on pack animals they owned. The weavers did not feel stigmatized any more and traditional attire was in fashion thanks to the likes of ETYE (General Aman Andom’s sister) some even bought their own Lada and Fiat 24 taxis and made even more money. Though these people were of different language groups they were all devout Orthodox Christians and on TIMQET DAY at their local churches they were celebrating with their cultural songs and dances more enthusiastically and the city people were happy for them.

   I think they didn’t have to pay in the ‘supply chain of economics’ any more except for taxes. The benefit of their labor went directly to them and that was why their lives changed.

   Likewise the coffee and khat at farmers might see their lives changed when they demand benefits in the form of resource allocations from the federal government and the banks.

 4. @anonymous
  ጭራሽ አልገባህም/ሽም፡፡ በተቃራኒው ነው ያስብከው/ሽው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.