ይድረስ ለቀድሞ የወያኔ አመራር ቡድን አባሎች አክሱም ሆቴል: መቀሌ

ይድረስ ለቀድሞ የወያኔ አመራር ቡድን አባሎች
አክሱም ሆቴል: መቀሌ
የትግራይ ክልል: ኢትዮጵያ

meles and susnክፍል ሁለት፡:  በሃሰተኛ ውንጀላ የመሳሪያ እና የኢኮኖሚ ማዕቀብ በማስጣል በኤርትራ ላይ ያደረሳችሁት ጉዳት

“የኢሳይያስን ጉሮሮ ማነቅ የሚቻለው አሜሪካና ሌሎች ተባብረው ኤርትራ ላይ የገንዝብ ማዕቀብ ሲጥሉ እንዲሁም ከሌሎች አገራት በተለይም ከቃጣር መንግስት የምታገኘው የገንዝብ እርዳታ ሲቋረጥ ይሆናል።ሌላው ለመንግስት ከፍተኛ የገቢ ምንጭ የሆነውን አሜሪካ ከሚገኙ ኤርትራውያን የሚላከውን

ገንዘብ ማስቆም ነው”። መለስ ዜናዊ (ግንቦት 2009 እ.ኤ.አ)

1. በክፍል 1 መጨረሻ ላይ ያሰፈርኩት የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ለማስቀየር በናንት ክስ አቅራቢነት የአሜሪካ መንግስት በተባበሩት መንግስታት ድርጀት የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ላይ ያደረገውን ከፍተኛ ጫና የሚያወሳ ነበር፡በወቅቱ በአሜሪካን ስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳይ ከፍተኛ ባለስልጣንየነበሩት ጃንዳይ

ፍሬዘር በታህሳስ 2006 (በእ/ኤ/አ) ወደ ኢትዮ-ኤርትራ ድንብር ዘልቀው አዲግራትንና ዛላምበሳን ጎበኙ። ቀጥለውም በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሄሊኮፕተር ባድመ ደርሰው በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባል አስተርጓሚነት (ምናለ ገለልተኛ የሆነ አስትርጓሚ ከአኤምባሲያቸው ቢጠቀሙ) በቅድሚያ በናንተው ከተመረጡ የባደመ ነዊሪዎች ጋር አጭር ቆየታ አደረጉ።

ከአጭር ቆይታ በኋላ፡ “የባድመ ነዋሪዎች ከፍተኛ የኢትዮጵያዊንት ስሜትና ማንነት እንዳላችው ተገንዝቢያለሁ፡ አቶ መለስ ዜናዊም ለምን የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ለመቀበልና ለመተግበር እንደተቸገረ ጥሩ ግንዛቤ አግኝቻለሁ”፡ ሲሉ ገለጹ ። ቀጥለውም የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሚሽን

(UNMEE) ከፍተኛ ባለስልጣን ጆሴፍ ላጉየላ ጋር ሲገናኙ ” አከራካሪ የሆነውን ባድመን ለኤርትራ የሰጠውን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ የባድመ ነዋሪዎች ኢፍትሃዊና ሚዛን የጎደላው ነው በማለት አጥብቀው እንደሚቃወሙት በጉብኝቱ ሊረዱ መቻላቸውን፤ ሰለዚህ “ጉዳዩ የሚመለከታችው ሁሉም አካላት የድንበር ኮሚሽኑ ጭምር አቋማቸውን ማላላት ይኖርባቸዋል” የሚል ድምዳሜ ሰጡ ።

የሚያሳዝነው አሜሪካዊቷ ከፍተኛ ዲፕሎማት ጉዳዩ የብዙ ሰው ህይወት የቀጠፈ መሆኑን ባለ መገንዘባችው ብቻ ሳይሆን ስለጉዳዩ ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው ሌሎች ዲፕሎማቶች ለዓመታት ሞክረው ያልቻሉትን በ30 ደቂቃ ጉብኝት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው ነው፡ የኤርትራ መንግስት ጉብኘቱንና የሰጡትን አስታያይት በጥብቅ ወቀሰ፡፡

2. አምባሳደር ላጉየላም “በባድመ ያነጋገርሻቸው ነዋሪዎች በመንግስት የተመለመሉና የመንግስትን አቋም የሚግልጹ ናቸው፤ ሆኖምየድንበሩ ውሳኔ ሳይተገበር በሁለቱ ሃገሮች መካከል ስለ ሌላ ጉዳዮች መነጋገር የሚችሉ አይምስለኝም፡ የድንበር ውሳኔው በተግባር ላይ ከዋለ ግን የሁለቱ ሃገሮች የስላም ሂደት ሊሻሻል እንደሚችልና የአሰብን ወደብ ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት እንደምትችል ኤርትራ ገልጻልኛለች” የሚል

አስተያያት ሰጡ።ጃንዳይ ፍሬዘር ከባድመ ወደ አዲሳ አበባ ተመልሰው ከጠ/ሚንስተር መለስ ዜናዊ ጋር ስብሰባ ተቀመጡ። ስለጉበኘቱ ከተነጋገሩና ሃሳብ ለሃሳብ ከተቀያየሩ በኋላ የድንበሩ ኮሚሽኑን ውሳኔ ለማስቀየር መወሰድ ሰላለባቸው እርምጃዎች ተስማሙ። ይህ ሴራ (በክፍል 1 እንደተገለጸው) በአምባሳደር ቦልተን እምቢተኛነት ልክ እንደሌሎቹ ሙከራዎች ፍሬ አልባ ሆኖ ቀረ።

3. በመቀጠል የኤርትራን መንግስት ከስልጣን ለማስውገድ ሶስት ዘዴዎች ተጠቀማችሁ፡ አንደኛ ኤርትራውያን ወጣቶች ላይ በማነጣጠር አገር ለቀው ወደ ኢትዮጵያና ሱዳን አንዲወጡ በማባበል “ወደ

ስደተኝ ካምፕ ከመጣችሁ በአጭር ጊዜ አሜሪካ፣ አውስትራሊያና አውሮፓ ትሄዳላችሁ” የሚል ፕሮፓጋንዳ ነዛችሁ። ዋናው ዓላማው የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት አንዲዳክም ሲሆን፣ ድንበር ተሻግረው የስደተኞች ካምፕ የደረሱ ወጣቶችን የኤርትራ መታወቂያ ካርዳቸውን ነጠቃችሁ።በቀማችሁት የመታወቂያ ወረቀት በመጠቀም የትግራይ ተወላጆችን በኤርትራውያኑ ስም ወደ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራሊያ በሠፈራ ፕሮግራም ለመላክ እንደተጠቀማችሁበት የአደባባይ ሚስጥር ነው ፡፡

4. ሁለተኛ የተቃዋሚ ቡድኖችን አደራጃችሁና አስታጠቃችሁ። ቁጥራቸውም አሥራ ሶስት ደርሰው ነበር። ሥስቱ እስላማዊ ግንባሮች እና ሁለት የብሄር ድርጅቶች ሲሆኑ ስምንቱ ከቀድሞ ጀብሃ የወጡ እና አዳዲስ

ሕብረ-ብሄራዊ ድርጅቶች ናቸው። የተቃዋሚ ቡድኖቹ ዋና አላማቸው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ከስልጣን ለማውረድ እንደሆነ በወቅቱ በኢትዮጵው የአሜሪካ አምባሳደር ለነበሩት ያማሞቶ ገልጸውላቸዋል።

በኤርትራና በውጭ አገር በሚገኙ ኤርትራውያን ዕይታ የተቃዋሚ ብድኖቹ የወያኔ መጫወቻ አሻንጉሊት ሆነው በመቆጠራቸው ይኽም በሕዝብ ዘንድ ቀባይነት ለማግኘት ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረባቸውም ለያማምቶ በግልፅ ተናገሩ። የአሜሪካው አምባሳደር አዲስ አበባ በተደረገው የተቃዋሚዎች ጉባኤ በታዛቢነት ለመሳተፍ ወይንም መልዕክት ለማስተላለፍ ፍላጎት ማሳየታቸው አስገራሚ ነበር፡ ለዚህም የስቴት ዲፓርትመንትን ፍቃድ ጠይቀዋል።

5. በስደተኞች ካምፕ የሚገኙትን የሳዋ ሰልጣኝ ወጣቶች ለመመልመል አቶ ስብሃት ነጋ የስደተኞች ካምፕ

ሄደው ገለጻ ሲያደርጉ ”ብዙዎቻችሁ በሳዋ ወታደራዊ ስልጠና የቀሰማችሁ ወጣቶች ስለሆናችሁ የኤርትራ ተስፋ እናንተ ናችሁ፡፡ ስለዚህ ተደራጅታችሁ የኤርትራን መንግስት ለመገልበጥ ተንቀሳቀሱ፡ አስፈላጊውንም

እርዳታ እናደርግላችኋለን” አሉ፡ ቀጥለውም የአሜሪካ መንግስት የሻዕቢያን መንግስት ለማዳከም ኤርትራ ላይ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ፣ ኤኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያው ማዕቀብ (sanction) ለማድረግ መዘጋጀቱን ገለጹ። ወያኔም ለተቃዋሚ ድርጅቶች አስፈላጊውን መሳርያና ሥልጠና በመስጠት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሻዕብያን መንግስት ከሥልጣን ለማስወገድ እንደተዘጋጀም በስደተኛ ካምፕ ላሉት ኤርትራውያን ወጣቶች ነገሩ።

የዚህ መዳረሻ ዓላማው የኤርትራን መንግሥት መጣል ብቻ ሳይሆን በኤርትራ በብሄር ላይ የተመሠረተ የክልል ፌዴራሊዝም ሥርዓት መመስረት ነው፡፡ወጣቶቹም ይህን በመገንዘብ ጭምር ሊሆን ይችላል

በድፍረት ”እኛ ከአገር የወጣነው ውጭ ሃገር ሄደን ኑሯችንን ለማሻሻል እንጂ ጦር መሳሪያ አንስተን ያስተማረች ሀገራችንን ለመውጋት አይደለም” የሚል መልስ ሲሰጡ ሽማግሌው አቦይ ስብሀት በመናደድ “የሻዕቢያ መርፌ የተወጋችሁ ለመሆናችሁ ማረጋግጫ ነው” በማለት ቦታውን ለቀው ሄዱ፡፡

የቀድሞ የወያኔ መሪዎች ማወቅ የተሳናችሁ ትልቅ ሚስጥር ስለሳዋ ስልጠና ማዕከል ነው ፡ በሳዋ ከሁሉም ብሄሮች የተወጣጡት ምልምል ወጣቶች ከአካዳሚያዊና ወታደራዊ ስልጠና ከመቅሰም ባሻገር በ18 ወራት ሳው ቆይታቸው የእርስ በርስ መከባበርና መቻቻል፣ የአብሮ መኖር አመለካከት ማዳበራቸውና አንድነታችው ነው። ለኤርትራ ላዓላዊነት መከበርና ለሀገሪቱ ሠላምና መሪጋጋት ሳዋ ከፈተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ የሚያጠያይቅ አይደለም።

6. ሶስተኛ የኤርትራን መንግስት ከስልጣን ለማስወገድ እንዲረዳ በሀሰት ክስ የመሳርያና የኤኮኖሚ ማዕቀብ

ለማስጣል ተሯሯጣችሁ፡፡ የፕረዝደንት ኢሲሳያስ መንግስት ለሶማሊያውን ሽብርተኛ አል-ሸባብ ወታደራዊ ትጥቅ ያቀብላል ብላችሁ ኤርትራ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ተማጸናችሁ። በፕረዚደንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው በወቅቱ የተሾሙት አምባሳደር ሱዛን ሪይስ ለዚህ ዋናው ተዋናይ ነበሩ። በ2009 የኢትዮጵያ ጐብኝታቸው ከጠ/ሚኒስተር መለ ዜናዊ ጋር ጋር ረጅም ስዓት የፈጀ ስብሳባ ተቀመጡ። አቶ መለስ በቀጠናው ስለሚገኙት እያንድንዱ አገር (ኤርትራ፣ ሱዳን፡ ደቡብ ሱዳን፡ ሶማልያ) ፖለቲካዊ ሁኔታ ዝርዝር ትንታኔ ስጡ፡፡ የኤርትራ መንግስትና ኤርትራ የምታስታጥቀው የሶማሊያው ሽብርተኛ ቡድን አል-ሸባብ ለኢትዮጵያ ፀጥታ ዋናው ስጋት መሆኑንና ይህን ተግባር ለመቅጨት መወስድ ያለባቸውን እርምጃዎች በዝርዝር አስቀመጡ።

7. ከአቶ መለስ ምክሮች በተለይ ትኩረቴን የሳበው “የኢሳያስን ጉሮሮ ማነቅ የሚቻለው አሜሪካና ሌሎች ተባብረው ኤርትራ ላይ የገንዝብ ማዕቀብ ሲጥሉእንዲሁም ኤርትራ ከሌላ አገሮች በተለይ ከቋጣር የምታገኘውን የገንዝብ እርዳታ እንዲቋረጥ ማድረግና ለመንግስት ከፍተኛ የጋቢ ምንጭ የሆነውን አሜሪካ

ከሚገኙ ኤርትራውያን የሚላከውን ገንዘብ ማስቆም” ፡ ቀጥለውም “አሜሪካ በሚስጥር ኢሳያስን በማነጋገር ጠባዩን እንዲቀይር ለማድረግ መሞከር፡ ካልሆነ የእግዳ ዱላ እንዳሚጣልበት አሳስቦ የሚሰጠውን መልስ ማየት፡ ማንኛውም በይፋ የሚሰጥ መግለጫ ይሁን ማስፈራርያ ከኢሳያስ ጋር ሊሰራ አይችልም። የማያቋርጥ

ወታደራዊ ጫናና ከባድ የኤኮኖሚ ማዕቀብ ኤርትራ ላይ ከተደረግ ግፊቱ ውጤታማና የተፈለጋውን ውጤት ሊያመጣ ይችላል” አሉ።

ኤርትራን ለማንበርከክ ይህን ሃሳብ ነበር መለስ ዜናዊ ለአሜሪካዊቷ ሱዛን ራይስ ያማከሩት። ይኽ ከሆነ ከጥቂት ወራት በኋላ የኤርትራ መንግሥት በሶማሊያ አልሸባብን ይረዳል፡ ከጅቡቲ ጋር አወዛጋቢ ከሆነው

ድንበር ወታደሮቻን ለማወጣት ፈቃደኛ አይደለም በሚል የሃስት ክስ በታህሳስ 2009 (እ/ኤ/አ.) የተባበሩት መንግስታት ሰኩሪቲ ካውንስል በኤርትራ ላይ የመሳርያና ኤኮኖሚያዊ ማዕቀብ ጣለ። ይኽ በቁጥር 1907 የሚታዋቀው ማዕቀብ የጦር መሣሪያ ግዢ ዕቀባ ፣ የከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣኖች ላይ የጉዞ እገዳና የአንዳንድ የሀገሪቱን የፖለቲካና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ሀብት ማገድን ያጠቃልላል።

8. ይህ ኤርትራ ላይ የተጫነው ዐሥር ዓመታት ያሥቆጠረው እገዳ በአገራችን ኤኮኖሚና በመሠርተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱየሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም። ያስጣላችሁብን እገዳም ሆነ የተቃዋሚ ቡድኖችን ማስታጠቅ የፈለጋችሁትን የመንግስት ግልበጣ ሳይመጣ እንደሌሎቹ እርምጃዎች ሁሉ ይኽም ከሽፎ እናንተ ቀድማችሁ የአራት ኪሎውን ቤተመንግስት ተነጥቃችሁ ወደ መቀሌ ሸሻችሁ። ዋናው

ሕልማችሁ በአንድ ኤክስፐርት አገላላጽ “Somalizaiton of Eritrea” ማለት የኤርትራ መንግሥትን ኣዳክሞ ከስልጣን ማስወገድና ኤርትራን እንደሶማሊያ በመፈረካስከስ የጅሃዳዊ ሽብርተኝነት መናሓርያ ማድረግ ነበር ፡፡ ግን አልተሳካላችሁም !!

ዋናው ምክንያቶች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስማዕታት በመክፈል የኤርትራ ህዝብ ሉዓላዊነቱን ለማስከበር ስለመከተ፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት ሕዝቡ ግፊትን የመቋቋም ችሎታውንና በቁርጥኝነቱ በአላማው ጸንቶ

የመቆየት ባህሉን በመጠበቁ ነበር። በኤኮኖሚና ማኅበራዊ ሴክተሮች መንግሥት የወሰዳችው “ቀበቶ የማጥብቅ” ወሳኝ እርምጃውችም ኤርትራ በናንተ ሳቢያ የተጣለባትን ዕገዳ እንድትሻገረው አግዟታል።

9. የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የድንበር ኮሚሽንን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተቀበለው

በኤርትራ ታሪካዊ ጉብኝት አደረጉ። በሐምሌ 9 2018 (እ.ኤ.አ) የኤርትራው ፕረዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የስላም ውል አሥመራ ተፈራረሙ፡፡ በዚሁም በሁለቱ አገራት መካከል ለሃያ ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ማብቃቱን አወጁ። እናንተ ለዐስራ ስምንት ዓመት መቀበል አሻፈረኝ ያላችሁትን የድንበሩን ውሳኔ በአጭር ጊዜ በመቀበላቸውና በሁለቱ አገሮች መካካል ለሰፈነው የሰላም ተስፋ ዓለም አቀፉ ማህበረስብ በማድነቅ ለዶ/ር ዐብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ሰጣቸው።

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ፎርማጆ በዶ/ር አቢይ አሕመድ ደጋፊነት ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ ቤት ማዕቀቡን እንዲያነሳ ጥሪ አቅርበው ዐሃስር ዓመት ኤርትራ ላይ ያስጣላችሁት ማዕቀብ በየካቲት 2019

(እ/ኤ.አ) ተነስቷል። ቀጥሎም በትግራይ ያቋቋማቹኃቸው የስደተኛ ካምፖች በ ዶ/ር አብይተዘጉ፡ ምንም

ቁም ነገር ሳያደርጉ ለአስራ ስምንት (18) ዓመታት እናንተ ስር ተወሽቀው የኖሩት የተቃዋሚ ቡድኖች

(ከናተው ጋር መቀሌ ከሰፈሩት ሁለት በቀር ) ጓዛቸውን ጠቅልለው ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተውል። አነዚህ

በ2018 በአሥመራ የተፈረመው የስላም ስምምት ተጨባጭ የመጀመርያ ውጤቶች ናቸው።

10. ከአራት ኪሎ ቤተ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ግፊት ስልጣን ለቃቹህ መቀሌ ከሰፈራችሁም በኃላ ከኤርትራ ጋር ያለው ፍጥጫ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር የተዘጋጃችሁ አለመሆናቸውም በግልጽ ይታያል፡፡ ባላችሁበት ሁኔት ሁለት አማራጮች ያላችሁ ይመስለኛል። አንደኛው ባለፉት ሃያ ዐመታት በያዛችሁት እምቢታ በመቀጠል የኤርትራ መንግስት ከፌደራል መንግስት ጋር በመተባብር በጦር ሊያጠቃን ነው በሚል ሃስት ፕሮፖጋንዳ የትግራይን ህዝብ እንደ ሆስቴጅ በመያዝ ወደ አላስፈላጊ ዳግማዊ ደም መፋሰስ መግባት ነው።

ሁለተኛ፡ ለቀድሞው የእምቢታ አቋማችሁ ምርኮኛ ከመሆን ተላቃችሁ የትግራይ ህዝብ ከጎረቤት የኤርትራ ህዝብ ጋር በሰላምና በመከባብር እንዲኖሩ በማሰብ በቅድሚያ የድንብር ኮምሽን ውሳኔ መቀበልና ከሉዓላዊ የኤርትራ መሬት መውጣት ነው። ላለፉት ሃያ ዓመታት ያመለጣችሁን ዕድል ይህን ታሪካዊ እርምጃ መውሰድ በሁለቱ መንግስታትና በኤርትራና በትግራይ ህዝብ መካከል ለወደፊት በሰላምና በመከባበር እንዲኖሩ የሚያስችል የመጀመሪያው ታሪካዊ ምዕራፍ ሊሆን ይችላል።

11. ይኽን ቆራጥ እርምጃ ከወሰዳችሁ የኢትዮ-ኤርትራ አዲስ የሰላም መዕራፍ በመክፈት ባለፉት ሃያ ዓመታት የባከነውን ጊዜ ባፋጣኝ ለመተካትና ህዝቦቻችንን ከድህነት ለማላቀቅ ወሳኝ ሚና መጫወት ትችላላችሁ።በተለይም ለወጣቱ ሰፊ የሰራ ዕድል የሚጥሩ የኤኮኖሚና የልማትፕሮጀክቶች እንዲሁም በደንብር አካባቢ ለሚኖሩ ለተጎዱት የሁለቱ ሃገራት ህዘቦች ኑሮ ለማሻሽል ሰፊ በር ይከፍታል ። ይኽን ሳታደርጉ የጦርነት ጥሪ ማስተጋብቱን እንደድሮው ከቀጠላችሁ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ከፍተኛ ውጥረትና ደም መፋሰስ ሊያስከትል ይችላል። ከዚህ ሳትታቀቡ እንዲሁ ከኤርትራ ጋር ቅርብ ግንኙነት እንፈልጋለን በማለት የምትደሰኩሩት ለህዝብ ግንኙነት ፍጆት ካልሆነ በስተቀር ለሁለቱ ጎረቤት ህዝብ በሰላም የመኖር ዕድል ምንም ፋይዳ አይኖረውም ።

“በኤርትራውያንና በኤርትራ ላይ የፈጸመችሁትን ግፍ አልረሳነውም፡ እንዴት ይረሳል !!

ሰዓረ ተስፋይ

ዋሽንግተን ዲ.ሲ.

2 Comments

 1. ወይ የቀን ጎዶሎ አለ የትግሬን ጥላ ፈርተህ እንዳልሸሸህ ዛሬ ለትግሬ ቀጭን ትእዛዝ መስጠት ጀመርክ? ከጽሁፍህ እንደተረዳሁት1. ትግሬዎችን ክፉኛ ፈርተሀቸዋል 2. የሰላሙ ሁኔታ ተመቻችቶልህ ትግሬዎችን ተክተህ ኢትዮጵያን ለመጋጥ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነህ።
  መቀሌ መሸጉ ገላ መሌ ከስፔስ የመጡ አድርገህ የምትስላቸው የትግሬ መሪዎች ከትግሬው ኢሳይያስ አፈወረቅ ጋር አብረው ያደጉ የሰሩ መሆናቸውን ማስታወስ መልካም ይመስለኛል። የሚያሳዝነው የኤርትራ ወጣቶች የሚሰደዱት የአረመኔው ኢሳይያስን ግፍና ጭቆና ለማምለጥ ሳይሆን ትግሬዎች ባቀነባበሩት ሴራ ነው ትለናለህ ምን አይነት ሞራል ይዘህ ነው ኢትዮጵያውያኖች ዘንድ መድረስ የምትፈልገው?

  ኢትዮጵያውያን እንደ እናንተ ብን ብን ሳንሆን በእርጋታ ማሰብ የምንችል ህዝብ ነን። የሚገርምህ ይሄ ሁሉ እሮሮ የምታሰማን በተንኮለኞቹ በሻቢያ እና ህወአት የመጣ ነው ቻሉት የስራችሁ ውጤት ነው። ነገር ግን ይሄ ለፖለቲካ ፍጆታ ያነሳኸው ተረት አንዱም ሚዛን ስለማያነሳ ተረቱን ለኤርትራውያንና ለትግሬዎች ብትችል በኤርትርኛ ካልሆነም በትግሪኛ ላክላቸው ይህ ከእኛ ጋር ተያያዥነት የለውም። ብዙ የምንጠቀምበትን መድረክ እየመጣችሁ ሙሾ አታውርዱብን።

  እዚህ ላይ ያንተ ፍላጎት ትግሬዎች በእውቀት ማነስና ወደፊት ኤርትራ ጋር አንድ ሁነን እንኖራለን ከሚል እሳቤ ያለተከራካሪ የሰጡት የኢትዮጵያ መሬትና የባህር በር እስከ ወዲያኛው በሰላም እንጠቀምበታለን በኢትዮጵያም ሂሳብ ሲንጋፖር እንሆናለን የሚለውን ቀልድህን ተወው ትውልዱ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ያደረግህበትን አልረሳውም።

  ባጠቃላይ ትርክቱ የሻቢያና የህወአት ጉዳይ በመሆኑ ህወአትም እንክትክታችሁን ስላወጣው ዳግም አገርና ሰው የመሆናችሁ ነገር እስከ መጨረሻው ስላከተመ ጉዳዩን በዚህ ቋጭተነው ካሁን ብሁዋላ በሁለት ቢላ የምትበሉ ኤርትራውያን ከበረከት ሐብተ ስላሴ ጨምሮ ክብር ካላችሁ ኢትዮጵያ ውስጥ የቀራችሁ ነገር ስለሌለ አትምጡብን እያልን መጽሀፍም ባማርኛ ጽፋችሁ ግዙን የምትሉን ሽያጭ ሳይሆን ገንዘብ ልመና አድርገን ስለምንቆጥረው አትምጡብን እንላለን።
  የኤርትራ ነዋሪ ትግሬውን ኢሳይያስ ወዶ አፍቅሮ ነው የሚኖረው ካልከን ሽህ አመት ያንግስልህ።
  አበቃሁ ባለህበት ኑር

 2. ምን ይመስላል? ጎበዝ እነ አጼ ሐይለ ስላሴ በተቀመጡበት ወምበር ይሄ ጉጭማ ይቀመጥበት ኢትዮጵያን በዚህ ሰዉ ይወከሉ? እዉነትም ክፉ የቀን ጎደሎ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.