‹‹ዕዳ የተቀበረ የጊዜ ቦንብ!!! የኢትዮጵያ የባንኮች ክስረትና፣ የመንግሥት ውድቀት !!! ›› (ክፍል ሁለት) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

et33 ‹‹ዕዳ የተቀበረ የጊዜ ቦንብ!!! የኢትዮጵያ የባንኮች ክስረትና፣ የመንግሥት ውድቀት !!! ››  (ክፍል ሁለት)  ሚሊዮን ዘአማኑኤልለኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ጋዜጠኞችና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበርና ለቪዥን ኢትዮጵያ፣ኢሣት፣ ኢትዮ360፣ አባይ ሚዲያ ወዘተ ፤- በዘረኛው ህወሓት/ ኢህአዴግና  በተረኛው ዘረኛ ኦህዴድ/ብልፅግና ፓርቲ፣ የሃገራችን ኢኮኖሚ  ውድቀት  አዘቅት ውስጥ ከመግባቱ በፊት ለሃገርና ህዝብ ስትሉ ምስክርነታችሁን እንድትሰጡ እንጠይቃለን፡፡

ያልተከፈለ ዕዳ የጊዜ ቦንብ ነው!!!

አገሪቱ እ.ኤ.አ. እስከ ማርች 2019 ድረስ ያለባት ያልተከፈለ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ 1.5 (አንድ ነጥብ አምስት) ትሪሊዮን ብር ወይም 52.57 (ሃምሳ ሁለት ነጥብ ሃምሳ ሰባት)ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ የወጪ እና ገቢ ንግድ ሚዛን ጉድለት በየዓመቱ ከአስር እስከ አስራአምስት ቢሊዮን ዶላር ይሆናል፡፡ መንግስት ለውጭ እዳ 1.99 ቢሊዮን ዶላር ከፍሏል፡፡ 600 (ስድስት መቶ) ሚሊዮን ዶላር የተከፈለው ለብድር ወለድ ነው፡፡ 1.39 (አንድ ነጥብ ሠላሳ ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር ደግሞ፣ ዋናውን እዳ ለማቃለል፡፡ አሁን ባለው የብሔራዊ ባንክ ምንዛሬ ከተሰላ ፤የወለድ ክፍያው ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፡፡ በአጠቃላይ የውጭ ዕዳ ክፍያው ደግሞ 70 ቢሊዮን ብር ገደማ ነው፡፡  ይህን የተቆለለ ዕዳ ለመክፈል አንችልም፣ ለዚህ ነው ያልተከፈለ ዕዳ የጊዜ ቦንብ ነው የምንለው፡፡ በሃገሪቱ የሚገኙ ፋብሪካዎች፣ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች፣ አግሮ ኢንዱስትሪዎች፣ የህዳሴ ግድብ፣ ወዘተ በውጭ ምንዛሪ  እጥረት የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ጥሬ እቃዎች ማስገባት ባለመቻላቸው ከአቅም በታች በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ በአድሎና በሙስና ለተለያዩ ተቆማት የሚሠጡበት ልክስክስ አሰራር ይገኛል፡፡ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እንደ ዶሚኖ እዘጭ እንቦጭ ከማለቱ በፊት፣ የመጀመሪያውን እዘጭ አስቁም፣ ቀሪዎቹ እንቦጭ እንዳይሉ ለማዳን!!! (ለፕሮፊሰር መስፍን ወልደማርያም መታወሻ ትሁን፣ ብዙ የነፃነትና ፍትህ ብዕር ተሞጋቾች አፍርተዋልና ነፍስዎ በሠላም ታርፍ ዘንድ በፀሎታችን እናስታውስዎታለን፡፡)

ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲና የባንክ ባለሞሎቹ ይዋሻሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ጋዜጠኞች ይሄን የእዳ ጫና ተከታትለው መዘገብ፣ መጠየቅ፣ ምሁራን በመጠየቅ የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ በተለይ ቪዝን ኢትዮጵያ ምሁራንን በመጋበዝ ቃለ ምልልስ በማድረግ ተከታታይ ዜናና ሪፖርታዥ  በማቅረብ የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥትን የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ብቻ እንዲጠናቀቁ እንዲያደርግ ማንቃት ያስፈልጋል እንላለን፡፡

 • የውጭ ምንዛሪ ተመን ገበያ መር የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በፍጥነት እንድትተገብር (አይ ኤም ኤፍ) እና የዓለም ባንክ ጫና ተፅዕኖ ከማድረጉ በፊት በሃገሪቱ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ በጥቁር ገበያ የአንድ ዶላር ተመን ከ46ብር አስከ 50ብር በመመንዘር ላይ ይገኛል፡፡ የህወሓት ‹‹ልማታዊ መንግሥት ›› በብልፅግና ፓርቲ ቀጥሎል፡፡ በኦዴፓ ብልፅግና የመንግሥት መር ኢንቨስትመንት ካፒታል ተጠናክሮ ቀጥሎል፡፡ የብረት ፋብሪካ ለመገንባት 14.6 ቢሊዮን ዶላር  ግንባታ ወጪ  ለመገንባት እቅድ ተነድፎል የተጀመሩት ፕሮጀክቶች ሳይጠናቁ የህዳሴው ግድብ ሳይጠናቀቅ ሌላ ተጨማሪ ብድር ሃገሪቱ ልትወጣው ወደማትችለው ዕዳ አዘቅት ውስጥ ይከታታል እንላለን፡፡ የግሉ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ትኩረት ማጣት የውጭ ምንዛሪ አድሎዊ የሙስና አሰራር ቀጥሎል፡፡ የግሉ ዘርፍ የግብርና ታክስ ጫና፣  የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም መመናመንና የእዳ ጫና ህልውናውን ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡ የግሉ ዘርፍ ችግር  በእንዲህ እያለ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ፣ ዝዋይ፣ ጅማ፣ አርሲ፣ ባሌ፣  ኦሮሞ ያልሆኑ ባለሃብቶች ንብረት ሆቴሎች፣ ፋብሪካዎች፣ ትምህርት ቤቶች  ወዘተ መቃጠልና መውደም ከአስር እስከ አስራምስት ቢሊዮን ብር ኪሳራ አድርሶል አልፎል የብዙ ሰዎች ህይወትም ተቀጥፎል፡፡ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ፍሰት  በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ የማይታሰብ ና የማይታለም ሆኖል፡፡ የትግራይም ክልል  በኮንትሮባንድ ንግድ፣ በመሳሪያ ዝውውር፣ በህገወጥ ገንዘብ ዝውውር  የሃገሪቱ ኢኮኖሚን በማሽመድመድ ላይ ይገኛል፡፡ ሃገሪቱ በሁሉም ክልሎች ውስጥ ልዩ የፖሊስ ኃይል ግንባታ፣ የሚሊሽያ ኃይል ማደራጀት፣ ውድድር ላይ ይገኛሉ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ሁሉን ነገር በኃይል ለመፍታት በመሞከር፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል በሃገሪቱ ውስጥ ኮማንድ ፖስት በመመስረት በተለይም በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወዘተ በማሰማራት ኢኮኖሚው እንዳያንሰራራ አድርጎል፡፡
 • የኢትዮጵያ ባንኮች ያለ አንዳች ተወዳዳሪና ተፎካካሪ ስለሚሰራ፣ መንግሥት ከባህር ማዶ ባንኮች ውድድር ስለሚጠብቀው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲመዘን በሙያ፣ በብቃት፣ በክህሎትም ኃላ ቀር ናቸው፡፡
 • የኢትዮጵያ ባንኮች ትርፋቸውን በዶላር ቢያስሉት ትርፉ ኢምንት ወይም በኪሳራ እንደሚሰሩ ይረዱ ነበር፡፡
 • የኢትዮጵያ ባንኮች ሠማይ ጠቀስ ፎቆች የሚገነቡት የረከሰው ተቀማጭ ብር ከአመት አመት የመግዛት አቅሙ በዶላር ሲሰላ መሽመድመዱ ሃቅ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜት የብር የዋጋ ተመን ለውጥ አንድ ሚሊዮን ብር በዶላር ሲሰላ አንድ ዶላር በብር (5፣10፣20፣ 36 ፣ 40፣ 50) ብር በባንክ ውስጥ በተመነዘረ ወቅት  አንድ ሚሊዮን ብር ዋጋ ተመን በዶላር ሲሰላ ( ሁለት መቶ ሽህ ዶላር ፣ መቶ ሽህ ዶላር ፣ ሃምሳ ሽህ ዶላር ፣  27 ሽህ 778 ዶላር ፣25 ሽህ ዶላር፣ 20 ሽህ ዶላር ) እየወደቀ እየወደቀ ኢኮኖሚው እንደ ዶሚኖ ውድቀት እየተሸመደመደ እንደሚሄድ በቀላሉ ማንም በማስላት ሊደርስበት ይችላል፡፡

በህወሓት/ኢህአዴግና በኦዴፓ/ ብልፅግና ዘመን  የመጀመሪያው  ባንክ የቤቶችና ቁጠባ ባንክ ወደቀ፣ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰረ፣ ንግድ ባንክም ወደቀ፣ የመጀመሪያውን ባንክ ውድቀት    አስቁም፣ ቀሪዎቹን ባንኮችን ለማዳን የሚባለው ለዚህ ነው!!!

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) እና የዓለም ባንክ ጫና

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር (2010 እስከ 2013 ዓ/ም)ማስፈጸሚያ:-ኢትዮጵያ ለቀረጸችው የሶስት ዓመት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ማስፈጸሚያ ከሚያስፈልጋት 10 ቢሊየን ዶላር ውስጥ የዓለም ባንክ  ትልቁን ድርሻ ማለትም ከ6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነውን ለመሸፈን ተስማምተው ነበር፡፡ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ)  ሶስት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስን ገንዘብ በብድር ለማቅረብ ተስማምቶ ነበር። ሆኖም ‹‹የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ሊያቀርበው የነበረውን ከሁለት ቢሊየን ዶላር በላይ ደጋፍ (ብድርና ድጎማ) እንደማያቀርብና ከኢትዮጵያ ጋር በዚህ ረገድ የገባውን ስምምነት አቆርጦል፡፡››1 በተመሳሳይ በቅርቡ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልትሰጥ የነበረው 130 ሚሊየን ዶላርን እንዲዘገይ የወሰነችው ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን አቋም እንድትቀይርና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በፍጥነት እንድትተገብር ተፅዕኖ ለማድረግ መሆኑ ይገመታል።

ሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር በዋናነት (1) የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፉን ማሻሻል፣ (2) የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር እና (3) የእዳ ጫናን መቀነስ ላይ ያተኮረ ሥራን ለመስራት ያቀደ ሲሆን ተግባራዊነቱ ግን በጣም አጠራጣሪ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በዓለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ እጅ በካቴና እግሩ በእግረ ሙቅ ተጠርንፎ ታስሮል እንላለን፡፡ (4) የወጪ እና ገቢ ንግዱን ሚዛን:- የሃገሪቱን ብድር ለመክፈል የወጪ እና ገቢ ንግዱን ሚዛን ማስጠበቅን ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫው ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም እንላለን፡፡ በሀገሪቱ የፋይናንስ ስርአት ውስጥ የነበሩ ችግሮችን ለማስተካከል የገንዘብ ፖሊሲው መሻሻሉን እና የገቢ አሰባሰቡም ለውጥ እየታየበት እንደሚገኝ ቢነገርም በተጨባጭ የተገኘ ለውጥ የለም፡፡ እንዲሁም የግል ባንኮች ሲያበድሩ ከብሄራዊ ባንክ የሚገዙት የ27 በመቶ የግዴታ የቦንድ ግዢ እንዲቀር በመደረጉ ባንኮቹ የብድር ወለድ መጠንን መቀነስ ጀምረዋል፣ተገቢ ውሳኔ ነው፡፡ በተጨማሪ የግምጃ ቤት ሰነድ በቁንጽል ለተወሰኑ ተቋማት ብቻ የተተወውን ለገበያ ክፍት እንዲሆን መደረጉም ተገቢ ነው፡፡

(1) የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፉን ማሻሻል፣የሃገሪቱ መንግሥት  የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ ዘርፈ ብዙ ፈርጆች በፊሲካል ፖሊሲና ሞኒተሪ ፖሊሲ መናበብ መቻል ይገባቸዋል እንላለን፡፡

ፊሲካል ፖሊሲ፤ (Fiscal Policy) የሃገሪቱ  የግብርና ታክስ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን አፈፃፀም ፖሊሲን ያሳያል፡፡ የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ያሰላል፡፡ የመንግስትና የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን እና የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን ይቆጣጠራል፡፡  የመንግሥትና የብሄራዊ ባንክ ፊሲካል ፖሊሲ፤ የግብርና ታክስ ስርዓት ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ የግብርና ታክስ በ2011 ዓ/ም የመጀመሪያ ሩብ አመት በ10 (አስር ቢሊዮን) ብር መቀነሱ ቀይ መብራት መሆኑን መገንዘብና ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡

ሞኒተሪ ፖሊሲ፤ (Monetary Policy) የሃገሪቱ  የመንግሥትና ብሄራዊ ባንክ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ ፍላጎትና አቅርቦት በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበት መከላከልና የወለድ መጠን በመወሰን የገንዘብ ሥርዓት የሚቆጣጠርበት ሲሆን ከዓለም ዓቀፍ ኢንስቲቲውሽን ማለትም ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ እንዲሁም የሃገራቱን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የማህበረሰብ ልማት ፖሊሲዎች ጋር አዛምዶ መስራት ያካትታል፡፡ ሞኒተሪ ፖሊሲ ከሚያካትታቸው ውስጥ፤ የገቢ ፖሊስ፣ የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርት የዋጋ ቁጥጥርና የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችትን ያካትታል፡፡ ዘለቄታዊ የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ እንዲኖር የውጭ ንግድ ገቢን መጨመር፣ የዲያስፖራ የሃዋላ ገቢና የዲያስፖራ የቤት ሥራ ገንዘብ በአግባቡ መሰብሰብ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

{2} የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር/አማካይ የዋጋ ግሽበት

‹‹በአገሪቱ በተከታታይ ከፍ እያለ የመጣው የዋጋ ግሽበት ከመስከረም እስከ ሐምሌ 2012 ባሉት 11 ወራትውስጥየመቀነስምልክትእንዳልታየበትከማዕከላዊስታትስቲክስኤጀንሲየሚወጡትመረጃዎችይጠቁማሉ። ለዋጋግሽበትመጠንአለመቀነስእንደዋነኛምክንያትየሚቀመጠውበፍላጎትእናበአቅርቦትመካከልያለውልዩነትሰፊመሆኑእንደሆነየምጣኔሃብትባለሙያዎችየሚስማሙበትሃቅነው። ከማዕከላዊስታትስቲክስኤጀንሲየተገኘውመረጃእንደሚያመላክተው:-

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ በ18.6 በመቶ እና በ22.9 በመቶ መካከል ሲዋዥቅ ቆይቷል።

የምግብ ዋጋ ግሽበት ደግሞ ከ20 በመቶ ሳይወርድ ቆይቷል። ዝቅተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በጥር 2012 ሲሆን የምግብ ግሽበት መጠኑም 20 በመቶ ነበር። መጋቢት 2012 ደግሞ የዋጋ ግሽበቱ ዋጋ 26.7 በመቶ በመሆን በዓመቱ የምግብ ግሽበት ዋጋ ጣራ የነካበት ወቅት ወር ሆኖ አልፏል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበትም ቢሆን ባለፉት 11 ወራት ከ10.3 በመቶ እስከ 19.7 በመቶ መካከል ሆኖ ተመዝግቧል። ከብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በተገኘው አሃዝ መሰረት ከመስከረም እስከ ሐምሌ 2012 ድረስ የተመዘገበው የምግብ የዋጋ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እና አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ እንደሚከተለው ቀርቧል።›› (2012 ጎልተው የወጡ ምጣኔ ኃብታዊ ጉዳዮች/10 መስከረም 2020)

{3}  የእዳ ጫናን መቀነስ/የኢትዮጵያ ኮሜርሻልና ኮንሴሽናል ብድር

የቻይና መንግሥት የብድር አከፋፈል ሥምምነት፣ የኮሜርሻል ብድሮችን ወደ ኮንሴሽናል ብድር እንዲቀየሩ ስምምነት ተደርሶል፣ ከ10 እስከ 30 አመታት የብድር እፎያታ ጊዜ ውስጥ የባቡር ፕሮጀክት ብድርን እንዲከፈል ስምምነት ተደርሶል፣ በዚህ ተጠቃሚዋ ቻይና ትሆናለች፡፡ የኢትዮጵያ ብድር 2000 እኤአ 12.1 ቢሊዩን ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን 17.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለተለያዮ ፕሮጀክቶች መስሪያ አበድረዋል፡፡ ከዚሁ ውስጥ ዓለም አቀፋዊ የመሠረተልማት ግንባታ መንገድ፣ ባቡር፣ ወደብ የአንድ ሃር መንገድ የተሰኘው የቻይና መንግሥት 126 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት አውሮፓን ኤሽያንና አፍሪካን ለማገናኘት እየተገበረች ይገኛል፡፡ ቻይና መንግሥት በብድር ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ወደብ የገነባው የኤሌትሪክ ባቡር ዘለቄታዊ አትራፊነቱ ደካማ በመሆኑ ከወልዲያ ወደ መቐለ ለተጀመረው የባቡር መስመር ግንባታ ብድር አልለቀቁም ዋናውም ምክንያት የአዋጭ ጥናትና ዘለቄታዊ አትራፊነት የፒኪንግ ዩኒቨርሲተው ፕሮፌሰር ታንግ ጆያንግ ብለዋል፡፡ Its debt burden at 59% of GDP, debt distressed Ethiopia learns crucial lesson: all the same in Chinese the phrase is ‘ there is no free lunch’ The Ethiopian Observatory (TEO)… “The intensifying repayment risks from the Ethiopian government’s debt reaching 59 percent of GDP is worrying investors,” China’s mission to Africa Union…. “The sustainability of the projects is weak…[ e.g. the] Chinese-funded light railway around the capital Addis Ababa and the Ethiopia- Djibouti rail project ”… “ExIm has become more risk-averse for new projects” Researcher at China Africa Research Initiative at SAIS. ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ዘመናዊ የኤሌትሪክ ባቡር፣ በቻይና የሬል ዌይ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንና ቻይና ሲቨል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን 3.4 (በሦስት ቢሊዩን አራት መቶ ሚሊዩን) ዶላር ብድር እየተገነባ ያለው 758 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው፣ የሰውና ዕቃ ማጎጎዣ የኤሌትሪክ ባቡር አዲስአበባ ከተማን ከጅቡቲ ጋር ያገናኛል፡፡የቻይና መንግሥት ብድር ባቡሩ ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በማመላለስ እዳውን ለመክፈል በተደረገ ጥናት ዋና ሥራ ተቆራጩ በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጁ ዩ ዋን ሊ ባቡሮቹ፤ የነዳጅ ፉርጎዎቹና የሲጊናል ሲስተሞች በቻይና ደረጃ መፈብረካቸውን አስታውቆ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እዳውን ለመክፈል ባደረገው ጥናት መሠረት ባቡሩ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን በማመላለስ በተለይም ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ መሃል አገር በባቡር ለማመላለስ አንድ መቶ ያህል የነዳጅ ማመላለሻ ፉርጎዎች አዘጋጅቶል፡፡ የአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር ፕሮጀክትና ለተበደረው 2.5 ቢሊዮን ዶላር የወለድና የግዴታ ክፍያ መክፈል የጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ ግን ወደ ሥራ አለመግባቱ ይታወቃል፡፡ በሃምሌ ወር 2008 ዓ/ም 35.47 ሚሊዮን ዶላር (784 ሚሊዮን ብር) መክፈሉ ታውቆል፡፡ በ2009 ዓ/ም ጥር ወር 45 ሚሊዮን ዶላር (1.06 ቢሊዮን ብር) ለመክፈል አልቻለም፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ የኮሜርሻል ብድሮቹ ወደ ኮንሴሽናል ብድርነት እንዲቀየሩና ከ10 እስከ 30 አመታት ውስጥ የባቡር ፕሮጀክት ብድርን እንዲከፈል ተደራድረው መጥተዋል በዚህ ተጠቃሚዋ ቻይና ትሆናለች፡፡ ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ዘመናዊ የኤሌትሪክ ባቡር፣ በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት ለኪሳራ ተዳርጎል፡፡ ኢትዮጵያ ከቻይና ለተበደረችው ብድር 17.5 ቢሊዮን ዶላር የወለድ የመክፈል ሁኔታዋ  ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በትኛውን የውጭ ንግድ ገቢ ብድራችንን መክፈል እንደምንችል የተቀመጠ ነገር የለም፡፡

ለማጠቃለል የኢትዩጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረቱ በሦስቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣በኢንዱስትሪና የአገልግሎት ተስማሚ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመተግበር ለህዝብ ብልፅግናና ለኢኮኖሚ እድገት ማምጣት ይቻላል፡፡ የኢኮኖሚ ፖሊሲው ስርዓት በግብርና ታክስ፣  በመንግሥት በጀት፣ በገንዘብ አቅርቦት፣ የወለድ መጠን፣ የጉልበት ገበያ፣ ብሄራዊ ኃብትና  ሌሎች ኢኮኖሚ ዘርፎች በማበልፀግ እንዲሁም  የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ ከፍተኛውን ሚና እንዲጫወት በማድረግ፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በተወሰኑ የኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይም  በማዕድን ዘርፍ፣ በኢነርጂ ኃይል ማመንጨት፣ አየርመንገድ ወዘተ ውስጥ ብቻ እንዲወሰን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

{3.1} ‹‹ በዓመት 600 ሚሊዮን ዶላር ለውጭ ወለድ ተከፍሏል/ September 19, 2020

የመንግስት የውጭ እዳ ከ28 ቢሊዮን. ዶላር በላይ ነው!!!

በፍጥነት እየገዘፈ የመጣው የመንግስት የውጭ እዳ ባለፉት ሁለት ዓመታት ቢረጋጋም፤ በ2012 ዓ.ም ከ28.6 ቢሊዮን ዶላር ሆኗል፡፡ የውጭ እዳ ለመክፈል የሚውለው ገንዘብ፣ የአገሪቱን መንግስት የሚፈታተን ሸክም ከመሆኑም በተጨማሪ ከዓመት ዓመት እየከበደ መጥቷል፡፡በ2002 መንግስት ለውጭ እዳ 100 ሚሊዮን ዶላር ከፍሏል፡፡ በ2005 ግን የውጭ እዳ ክፍያው፣ እጥፍ ድርብ ስለጨመረ  ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ አልፏል፡፡ በዚሁ አልተገታም፤ተባባሰ እንጂ አልተቃለለም፡፡ በ2008 ዓ.ም  መንግስት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለውጭ እዳ ከፍሏል፡፡  የእዳ ክፍያ ጣሪያ የደረሰው ካቻምና ነው፡፡ የዕዳ ክፍያው፣ በ2011 ዓ.ም ከ2 ቢሊዮን ዶላር አልፏል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ሪፖርት እንደገለጸው፤ የዕዳ ክፍያ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ተረጋግቷል፡፡ መንግስት ለውጭ እዳ 1.99 ቢሊዮን ዶላር ከፍሏል – ለሁለት ቢሊዮን ትንሽ የቀረው፡፡ 600 ሚሊዮን ዶላር የተከፈለው ለብድር ወለድ ነው፡፡ 1.39 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ፣ ዋናውን እዳ ለማቃለል፡፡ አሁን ባለው የብሔራዊ ባንክ ምንዛሬ ከተሰላ ፤የወለድ ክፍያው ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፡፡ በአጠቃላይ የውጭ ዕዳ ክፍያው ደግሞ 70 ቢሊዮን ብር ገደማ ነው፡፡››

{3.2} የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት

በሃገሪቱ የሚገኙ ፋብሪካዎች፣ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች፣ አግሮ ኢንዱስትሪዎች፣ የህዳሴ ግድብ፣ ወዘተ በውጭ ምንዛሪ  እጥረት የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ጥሬ እቃዎች ማስገባት ባለመቻላቸው ከአቅም በታች በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ በአድሎና በሙስና ለተለያዩ ተቆማት የሚሠጡበት ልክስክስ አሰራር ይገኛል፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ሞኒተሪ ፖሊሲ ከሚያካትታቸው ውስጥ፤ የገቢ ፖሊስ፣ የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርት የዋጋ ቁጥጥርና የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችትን በአግባቡ በግልፅነት መጠቀምን ያካትታል፡፡ ዘለቄታዊ የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ እንዲኖርና የውጭ ንግድ ገቢን በመጨመር የሃገሪቱን ኢኮኖሚ መገንባት ላይ ያተኮረ ፖሊሲ ነው፡፡ ሆኖም የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ዶላር፣ መሬት፣ ኮንዶሚንየም  ዘረፋ ተከናውኖል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመመሪያ ውጪ ለተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች 69 ሚሊየን ዶላር ተሰጥቷል፡፡ 1 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መጋቢት አሥር ቀን 2010 ሥልጣን ከያዘ  በኋላ በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ከብሔራዊ ባንክ ደንብ እና መመሪያ ውጭ ሲባክን ነበር ። በ2010 አመት ከግንቦት እስከ ነሀሴ ወር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ከብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውጭ 69 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ለተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች እንደተሰጡ ከሰነዱ አንብበናል። ባንኩም፣ ታንኩም፣ መሬቱም፣ ፎቁም  ወያኔና ኦነግ ድርጅቶች ዶላሩን ተቀራምተውታል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ደብረፂዎንና ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ አብይ የዶለር ቅርምቱ ላይ የአንበሳውን ድርሻ ይዘዋል፡፡

 • ለመለስ ፋውንዴሽን 100 ሺ ዶላር፣ የህወሓት/ኢህአዴግ
 • ለኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ 66 ሺህ 750 ዶላር ፣
 • ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ሴንተር 500 ሺ የአሜሪካ ዶላር፣የህወሓት/ኢህአዴግ
 • ለኢዮሃ ፕሪንተር 27 ሺህ ዶላር እና
 • ለብርሃኔ ወልዱ 140 ሺ 800 ዶላር መፈቀዱን ሸገር ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የህወሓት/ኢህአዴግ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ ድልድልን አስመልክቶ በተጠቀሰው ጊዜ ከ3 ዓመት በፊት ያወጣውን መመሪያ ንግድ ባንኩ በከፍተኛ ደረጃ ሲጥስ እንደነበር ይኸው ሰነድ ያመለክታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ሀገር ገንዘብ ወይም የውጪ ምንዛሪ ድልድልን አስመልክቶ ያወጣው መመሪያ ቁጥር FXD/51/2017 ለኮንስትራክሽን ድርጅቶች የግንባታ ማሽኖች መለዋወጫ ለማስገባት ለአንድ የግዢ ማቅረቢያ ከ50,000 የማይበልጥ የአሜሪካ ዶላር እንዲመደብ ቢፈቅድም መመሪው ከወጣ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ማለትም በ1ኛው ወቅት በቁጥር 36 ለሚሆኑ በሌላኛ ወቅት ደግሞ 46 ለሚሆኑ የውጭ ምንዛሪ ጠያቂዎች ለእያንዳንዳቸው ከመመሪያው ውጪ ከ50,000 የአሜሪካዶላርበላይተመድቦላቸውወይምተሰጥቷቸውእንደነበርያገኘነውመረጃያሳያል።ከኢትዮጵያንግድባንክየወጣውእናበባንኩየቀድሞፕሬዘዳንትአቶባጫጊናየተፈረመበትይኸውሰነድእንደሚያስረዳውከሆነእንደጎርጎሮሳውያኑአቆጣጠር

 • በመጋቢት 2018፤36 ለሚሆኑ የውጪ ምንዛሪ ጠያቂዎች ለእያንዳንዳቸው ከመመሪያ ውጪ ከ50,000 ዶላር በላይ በድምሩ 19 ሚሊዮን 886 ሺ 137 የአሜሪካዶላር፣
 • በነሐሴ ወር 2018 ደግሞ ለ 46 የውጪ ምንዛሪ ጠያቂዎች በድምሩ 27 ሚሊዮን 648 ሺ 788 የአሜሪካ ዶላር እንደተመደበላቸው ያሳያል።
 • በግንቦት ወር 2018 መመሪያው የውጪ ምንዛሪ እንዳያገኙ ከፈቀደላቸው የስራ ዘርፍ ውጪ ላሉ ወይም መመሪያው ለማይመለከታቸው ቢያንስ ሸገር የሚያውቃቸው 5 ድርጅቶች በድምሩ 11 ሚሊዮን 847 ሺ 583 የአሜሪካ ዶላር እንደተሰጠ ሰነዱ ያስረዳል።
 • በግንቦት 2010 በቁጥር 10 ለሚሆኑ መኪና አቅራቢዎች ከብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ ድልድል መመሪያው ውጪ ለመለዋወጫ ማስመጫ 10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ንግድ ባንኩ እንደሰጠ (በዚህ ንግድ የተሰማሩ የህወሓት/ኢህአዴግ ድርጅት ነጋዴዎች ናቸው )በዚሁ ሰነድ ተመልክተናል።

በአቶ በቃሉ ዘለቀ እግር አቶ ባጫ ጊና ከተተኩ በኋላ የተፈፀመው አሰራር እና የውጭ ምንዛሪ ብክነት ተጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በየካቲት ወር 2011 ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ማሳወቃቸውን ሸገር ካገኘው ሰነድ ተመልክቷል።

ሸገር የተፈፀመውን ህገ ወጥ የውጪ ምንዛሪ ብክነት አስመልክቶ ጉዳዩ የሚመለከተው ህግ አስፈፃሚ አካል አስፈላጊውን ምርመራ እንዲያካሂድ ባንኩ ደብዳቤ የፃፈው በየካቲት ወር 2011 ማለትም ከዛሬ 1 ዓመት ከ6 ወር በፊት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ፤ በጉዳዩ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ምን እርምጃ ወስዶ ይሆን? ሲል የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግን ጠይቋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስምንት መቶ ሚሊዮን ብር ብድር አዲስ ለተቆቆመው የቡና ላኪዎች ማህበር መስራቾች ድንቁ ደያስ፣ አለማሁ ከተማ፣ ገምሹ (ኢሊሌ ሆቴል ባለቤት) የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ በተረኛ ዘረኛነት በአቶ ባጫ ጊና ጊዜ የተሰጠ የህዝብ ገንዘብ ነው፡፡(አንባሳደር ሆነው ተሸመዋል)

የወያኔ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ ኦነግ/ኦዴፒ ብልፅግና ዶክተር አብይ አህመድ የጦር አበጋዞች፣ በፓርቲ የዘር ንግድ ድርጅቶቻቸው መሬቱን፣ ባንኩን፣ ታንኩን፣ ወርቁን፣ ዶላሩን ወዘተ ሁሉ ዘረፉ፡፡ የወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች ሁሉን ነገር ያመቻቹላቸው የፋይናንስና ባንክ ዘርፍ ባለሙያዎችና የፖለቲካ ካድሬዎች  ሚስጥሩን በተለይም ግርማ ብሩ፣ ሶፍያን አህመድና ተክለወልድ አጥናፉ የመለስ ዜናዊ ቡችላ በመሆን ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ያስበዘበዙ አድርባይ ምሁራን በወንጀሉና በዘረፋው በተባባሪነት አገልግለዋል፡፡ ግርማ ብሩ፣ ሶፍያን አህመድ፣ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ዮሐንስ አያሌው፣ አብርሃም ተከስተ፣ይናገር ደሴ፣ በቃሉ ዘለቀ፣ ባጫ ጊና አንባሳደር ሆኖ የተሸመ፣ በሃገራችን ህግና ተጠያቂነት ሲኖር የህዝብ ተቀማጭ ገንዘብ ያለአግባብ በአድሎ በማበደር ኢፍህታዊ ሥራቸው  አንድ ቀን በሰሩት ወንጀል ይጠየቃሉ፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ የመድኃኒት አቅርት ሳይሞላለት በበሽታ እየረገፈ የውጭ ምንዛሪ ዘረፋ፣ በአድሎዊ አሠራርና የሙስና ወንጀል የባንክ ሙያተኞችና የዐብይ አህመድ መንግስት ተጠያቂ ናቸው፡፡

{4} የወጪ እና ገቢ ንግድ ሚዛን:- የሃገሪቱን ብድር ለመክፈል የወጪ እና ገቢ ንግዱን ሚዛን ማስጠበቅን ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫው ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም እንላለን፡፡ በሀገሪቱ የፋይናንስ ስርአት ውስጥ የነበሩ ችግሮችን ለማስተካከል የገንዘብ ፖሊሲው መሻሻሉን እና የገቢ አሰባሰቡም ለውጥ እየታየበት እንደሚገኝ ቢነገርም በተጨባጭ የተገኘ ለውጥ የለም፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ገቢ የተመሰረተው በግብርና ዘርፍ ኢኮኖሚ ሲሆን ግብርና ከሰማንያ በመቶ ለውጭ ንግድ(ከቡና፣ ጫት፣ ወርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ የቁም እንሰሳትና ከቅባት እህሎች ወደ ባህር ማዶ ሃገራት ትልካለች፡፡ የግብርና ዘርፍ  ሰማንያ አምስት በመቶ የሥራ እድል ፈጥሮል፡፡ በዚሁ መሠረት በ2017 እኤአ ሃገሪቱ በውጭ ንግድ 3.23 (ሦስት ነጥብ  ሃያ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር ስታገኝ፣ በተመሳሳይ  በገቢ ንግድ ወጪ 15.59 (አስራ አምስት ነጥብ ሃምሳ ዘጠኝ)  ቢሊዮን ዶላር ወጪ አውጥታለች፡፡ የሃገሪቱ የወጭና ገቢ ንግድ ሚዛን ጉድለት አስራ ሁለት ነጥብ ሠላሳ ስድስት ቢሊዮን ዶላር መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡››1 በአጠቃላይ የሃገሪቱ የወጭና ገቢ ንግድ ሚዛን ጉድለት በአማካኝ ከአስር እስከ አስራአምስት ቢሊዮን ዶላር በአመት ይደርሳል፡፡  የሃገሪቱን ብድር ለመክፈል የወጪ እና ገቢ ንግዱን ሚዛን ማስጠበቅን ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫው ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም እንላለን፡፡ በሀገሪቱ የፋይናንስ ስርአት ውስጥ የነበሩ ችግሮችን ለማስተካከል የገንዘብ ፖሊሲው መሻሻሉን እና የገቢ አሰባሰቡም ለውጥ እየታየበት እንደሚገኝ ቢነገርም በተጨባጭ የተገኘ ለውጥ የለም፡፡

{4.1} የቡና የወጪ ንግድ ገቢ፡ኢትዮጵያ በቡና የውቺ ንግድ ገቢ ስምንት መቶ ስልሳ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ገቢ በ221 ሽህ ቶን ቡና በመሸጥ ገቢ በ2017 እኤአ አግኝታለች፡፡በ2018/19 ደግሞ 239ሜትሪክ ቶን ቡና በማቅረብ በአፍሪካ ቀዳሚና በዓለም አስረኛ የቡና ላኪ አገር ሆናለች፡፡ ‹‹Ethiopia earned 866 million USD exporting 221,000 tons of coffee during its last fiscal year . Jul 11, 2017. In 2018/19, Ethiopian exports are estimated to reach 3.98 million bags of coffee (238.8 metric ton), making it, once again, the most important African coffee exporter and the tenth largest exporter in the world.Jun 6, 2019››

{4.2} የወርቅ የወጪ ንግድ ገቢ፡  ‹‹በዓመት እስከ 600 ሚሊዮን ዶላር ይገኝበት የነበረው የወርቅ ወጪ ንግድ፣ እንደ ሌሎች ምርቶች ሁሉ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ በመምጣት ላይ ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት ከወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከ30 ሚሊዮን ዶላር በታች ብቻ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ባንኩ ባካሄዳቸው ጥናቶች መሠረት በጎረቤት አገሮች ውስጥ ኮንትሮባንዲስቶች በምን ያህል ዋጋ ገዝተው በምን ያህል ዋጋ እንደሚሸጡ ለመረዳት እንደቻለ ጠቅሶ፣ ከሌሎች አገሮች ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች አካባቢም ሰፊ ጥናት በማካሄድና በሌሎች አገሮች ውስጥ ያለውን አሠራር ግምት ውስጥ በማስገባት ወርቅ የሚገዛባትን በዋጋም በመጠንም ጭማሪ ማሳየቱ ታውቆል፡፡ በሐምሌ 2012 ዓ.ም. 72 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው ወርቅ በብሄራዊ ባንክ ገቢ ሆኖል፡፡››2

{4.3} ከቱሪዝም ዘርፍ ይጠበቅ የነበረው5.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ወደ 2.1 ቢሊዮን ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

‹‹በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ከሚጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቱሪስቶች የ5.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚገኝ ቢጠበቅም፣ 541 ሺሕ ጎብኚዎች ብቻ በመምጣታቸውና የኮሮና ወረርሽኝም ባስከተለው ተፅዕኖ ሳቢያ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ብቻ መገኘቱ ተገለጸ፡፡…በተሸኘው በጀት ዓመት የተገኘው ገቢ ከዓምናውም ያነሰ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ካቻምና 2.7 ቢሊዮን ዶላር ያስገኘው የቱሪዝም ዘርፉ፣ በየጊዜው በሚነሱ ግጭቶችና በተደጋጋሚ በሚታወጁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ብሎም ኤምባሲዎች በሚያወጧቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያዎች ሳቢያ ሲታወክ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓመት በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝና በፖለቲካ ግጭቶች ሳቢያ አሁንም ከተፅዕኖ መላቀቅ አልቻለም፡፡›› 3 ‹‹ከ130 በላይ አባላት ያሉት የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማኅበር በግንቦት ወር ይፋ ባደረገው ጥናት፣ ከመጋቢት ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች በወር 35 ሚሊዮን ብር እያጡ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ …የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የተወሰዱ ዕርምጃዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን ከሥራ ውጪ አድርጎታል፡፡ በኢትዮጵያም የሚገኙ ሆቴሎች ክፉኛ በመጎዳታቸው ሠራተኞቻቸውን ይዘው ለመቆየት የሚያስችላቸው የአንድ ዓመት 6.6 ቢሊዮን ብር ከወለድ ነፃ ብድር ጠይቀው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለስድስት ወራት የሚሆን 3.3 ቢሊዮን ብር በአምስት በመቶ ወለድ ፈቅዶላቸዋል፡፡ ብድሩ በ18 ባንኮች አማካይነት ለሆቴሎች እንዲሰጥ የተደረገ ቢሆንም፣ ባንኮቹ ወለድ የማያገኙ በመሆኑ ብድሮቹን ለመስጠት ዳተኝነት እንዳሳዩ አቶ ፍትህ ገልጸው ብድሩን ያላገኙ ሆቴሎችም እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡›› (ተዘግተው የከረሙ ሆቴሎች ወደ ሥራ እየተመለሱ ነው/ሪፖርተር ጋዜጣ/27 September 2020

{4.4} ኢትዮ ቴሌኮም፡-ኩባንያው ከዓለም አቀፍ አገልግሎት 147 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቶል፡፡ “ኢትዮ ቴሌኮም ባቀረበው የ2013 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ አጠቃላይ ገቢውን ከ47.7 ቢሊዮን ብር ወደ 55.5 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ እንዳቀደ ይፋ አድርጓል፡፡ ኩባንያው ከዓለም አቀፍ አገልግሎት 157 ሚሊዮን ዶላር ለማስገባት አቅዷል፡፡ኩባንያው እንደ ሮሚንግ ያሉ የውጭ አገልግሎቶች ገበያ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ የተቀዛቀዘበት ቢሆንም፣ ከባለፈው ዓመት ካገኘው 147 ሚሊዮን ዶላር በ6.3 በመቶ ለማሳደግ እንዳቀደ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ተናግረዋል፡፡ ኩባንያው አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር ከ46.2 ሚሊዮን ወደ 52.12 ሚሊዮን ለማሳደግ አቅዷል፡፡ የሞባይል ደንበኞች ቁጥር ከ44.5 ሚሊዮን ወደ 49.7 ሚሊዮን፣ የዳታና ኢንተርኔት ደንበኞች ቁጥር ከ23.58 ሚሊዮን ወደ 27.47 ሚሊዮን ለማሳደግ አቅዷል፡፡ የመደበኛ ስልክ አገልግሎት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ቢመጣም፣ አሁን ካለበት 980,000 የደንበኞች ቁጥር ወደ 1.08 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ ታስቧል፡፡

የብሮድባንድ ኢንተርኔት ደንበኞችን ቁጥር በ215.3 በመቶ በማሳደግ ከ212,000 ወደ 669,400 ለማድረስ ታልሟል፡፡ በ2012 በጀት ዓመት የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር በ135 በመቶ በማደግ 212,000 ደርሷል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ የአገሪቱን ቴሌኮም ስርፀት ከ46.1 በመቶ ወደ 51.3 በመቶ ከፍ ለማድረግ ግብ አስቀምጧል፡፡ኩባንያው በአዲሱ በጀት ዓመት የተለያዩ የማስፋፊያ ሥራዎች በአዲስ አበባ፣ በክልል ከተሞችና ገጠራማ አካባቢዎች እንደሚያከናውን ተገልጿል፡፡ ተቋሙ 842 አዲስ ጣቢያዎች እንደሚገነባ ከዚህ ውስጥ 150 ያህሉ በአዲስ አበባ እንደሚሠሩ ተነግሯል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስና የተሻሻሉ አገልግሎቶች ለገበያ ያቀረበ ሲሆን፣ በተለያዩ አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ቅናሽ አድርጓል፡፡ በሞባይል ዳታ ጥቅል አገልግሎት እስከ 35 በመቶ፣ በሞባይል ድምፅ ጥቅል አገልግሎት እስከ 29 በመቶ፣ በሞባይል ድምፅና ዳታ ጥምር አገልግሎት እስከ 28 በመቶ ቅናሽ እንዳደረገ አስታውቋል፡፡ በሳተላይት አገልግሎት ላይ እስከ 61 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ አድርጓል፡፡ አዳዲስ ካቀረባቸው አገልግሎቶች መካከል ማይ ኢትዮ ቴል የሞባይል መተግበሪያ፣ ኢትዮ ኢኬር ዌብ ፖርታልና የሞባይል ጥቅል ዱቤ አገልግሎት ይገኙበታል፡፡”4

{4.5} የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፡- ኢትዮጵያ የኤሌትሪክ ኃይል ለውጭ አገሮች በመሸጥ (ኢነርጂ ኤክስፖርት) 66.4 (ስልሳ ስድስት ነጥብ አራት) ሚሊዮኝ ዶላር ገቢ አግኝታለች፡፡ ኢንዱስትሪዎችም ተገቢ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ከሰጠናቸው ምርቶቻቸውን ለውጭ አገር ገበያዎች በማቅረብ (Export) የውጭ ምንዛሪ ገቢ ያስገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰፊ ተልዕኮ ይዞ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡

“Ethiopia Earns over $66.4mln from Electric Power Export

 August 4, 2020  Ethiopian Monitor #Electricity#Ethiopia#Export

ADDIS ABEBA– Ethiopian Electric Power (EEP) said it has garnered over 66.4 million USD from the sale of electricity to Sudan and Djibouti in the 2019/2020 fiscal year. The amount has increased by nearly 10 million US dollars from EEP’s plan for the year. The state-run institute target was to collect 56.92 million USD. But it has collected 116.5% of its target, said in a statement issued on Tuesday. According to the statement, about 37.1 million USD was collected from Djibouti while the remaining 29.3 million USD was from Sudan. This year’s revenue from electricity sales has also shown an 11.5 million USD increase as compared to the previous year. It explained that having enough water in Dams that could produce enough electricity contributed to the success of the plan. According to EEP, the country will expand its market in the near future. Kenya also has an agreement with Ethiopia over the importation of electricity. The construction of a high-voltage transmission line and a power converter station are nearing completion to sale power to Kenya, EEP said. In addition to the three countries, Ethiopia is also in the process of establishing bilateral relations with Somaliland, Tanzania, and South Sudan, according to EEP’s statement.” 5

“የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2013 በጀት ዓመት ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ አንድ ሚሊዮን ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን ጠቁሞ፣ ከኤሌክትሪክ ፍጆታ 16.5 ቢሊዮን ብር፣ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ስምንት ቢሊዮን ብርና ከአገልግሎት ክፍያ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ለማግኘት በድምሩ 25 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱግ ግልጽ አድርጓል፡፡  የ2012 በጀት ዓመት አፈጻጸም ለአንድ ሚሊዮን ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት ታቅዶ 168,751 ወይም 16.87 በመቶ ለመፈጸም ተችሎል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት 13.75 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 11.06 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሎል፡፡  በ2013 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ስላቀዱት በጣም የተለጠጠ ገቢ (25 ቢሊዮን ብር ገቢ) ስላላቸው አስቻይ ሁኔታ ተጠይቀው፣ ‹‹ዘንድሮ ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የሰበሰብነው 11 ቢሊዮን ብር አካባቢ ነው፡፡ በቀጣይ በጀት ዓመት ደግሞ ወደ 16 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደናል፡፡ 25 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ዕቅዳችን ነው፡፡” 6

ምንጭ፡-

{1}https://www.google.com/search?source=hp&ei=KeV6X6bGLaiOlwSD6rvADQ&q=ethiopian+coffee+export+revenue+2018-2020&oq=)

{2}(https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19631/ከወርቅ የአንድ ወር ወጪ ንግድ 72 ሚሊዮን ዶላር ተገኘ/ 19 August 2020/ዳዊት ታዬ)

{3}(https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19717/ከቱሪዝም ዘርፍ ይጠበቅ የነበረው የ5.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ወደ 2.1 ቢሊዮን ማሽቆልቆሉ ተገለጸ/30 August 2020/ ዳዊት ቶሎሳ

{4}(https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19706/ኢትዮ ቴሌኮም ለውድድር መዘጋጀቱን አስታወቀ)

{5}(https://ethiopianmonitor.com/2020/08/04/ethiopia-earns-over-66-4mln-from-electric-power-export/ Ethiopia Earns over $66.4mln from Electric Power Export/By Mhret G/kristos)

{6} (https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/19702/የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቀጣይ በጀት ዓመት 25 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን ተናገረ/30 August 2020/ታምሩ ጽጌ)

 

(ማሳሰቢያ ክፍል አንድ ላይ ቁጥሮቹ ላይ ስህተት ስላለ በድጋሚ አስተካክለን አቅርበናል፡፡ ይቅርታ እንጠይቃለን