ኢትዮጵያዊያን ለሕገ መንግስሥታዊ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም የዘር ማጥፋት (ክልል) ለማስወገድ የወጣ መግለጫ 

መግለጫ

ኢትዮጵያዊያን ለሕገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም (የጎሳ ክልል ለማስወገድ) አገራችን ውስጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውን የዘር ማጥፋትን ወንጀሎች እንዲሁም የጸጥታ ኃይሎች ባንድ አንድ አካባቢዎች የዘርና ሃይማኖት ተኮር ጥቃትና ግድያዎች ተባባሪ መሆናቸውንና ፀጥታን ማስከበር አለመቻላቸውን አስመልክቶ የጎሰኝነት ስርዓት በአስቸኳይ ፈርሶ ህዝባችን ይታደግ ዘንድ ውጭ አገር በሚገኙ አገር ወዳድ ምሁራንና ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመ ድርጅት ነው። የኢህዴፌ ዋና አላማ ላለፉት 29 ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተጫነውን የጎሰኝነት ክልላዊ አገዛዝ እንዲቆምና በኢትዮጵያዊነት እሴቶች ላይ በተመሰረተ ህገ መንግሥትና መንግሥታዊ ስርዓት ህዝባችን እንዲተዳደር ለማድረግ ነው። የኢትዮጵያዊያን ለሕገ መንግሥታዊ ዲሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም ራዕይ የኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦናና መንፈስ በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ለማስረጽና በጎሰኝነት ክልላዊ አገዛዝ የታሰረችውን ታላቋን ኢትዮጵያ ነፃ ሆና ማየት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት የሆነው ራዕያችን እውን እንዲሆን የጸረ ኢትዮጵያዊነት አገዛዝን ከስሩ መንቀል ያስፈልጋል። አሁን ያለውንም ጸረ ኢትዮጵያዊ የመንግሥትና የኃይል አሰላለፍ የሚቃረን ልዩ ህዝባዊ የአደረጃጀት ስልት በመቀየስ ህዝብን ያማካለ ስር ነቀል እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንገኛለን።

ethnicኢትዮጵያን የተጋፈጧት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ቢኖሩም ድርጅታችን የችግሮቻችን ሁሉ መንስኤ በሆነው ህገ መንግሥት ላይ ትኩረት በማድረግ ከጎሰኝነት ነጻ የሆነና ኢትዮጵያዊነትን የሚያንፀባርቅ ህገ-መንግሥት ህዝባዊና ህጋዊ ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ ኢትዮጵያዊያን ለህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም (የጎሳ ክልል ለማስወገድ) አለም አቀፋዊ ትግሉን ይቀጥላል።

ኢትዮጵያዊያን ለህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም (የጎሳን ክልል ለማስወገድ) እና ኢትዮጵያዊነትን ለማስከበር የሚከተሉትን አንኳር አንኳር መርሐ ግብሮች ለማከናወን ይታገላል።

1.የኢትዮጵያዊነት ድምጽ በመሆን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተጻፈውን ህገ መንግሥትና የተዋቀረውን የጎሰኝነት ክልላዊ ስርዓትን ባገር ቤትም በዓለም አቀፍ መድረኮችም ያወግዛል እንዲፈርስም በሰላማዊና ህዝባዊ መንፈስ በጽናት ይታገላል። በምትኩም አዲስ ሕገመንግስት እንዲለወጥ በአንክሮ እንሰራለን፤፤

2.በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተጫነው ህገ መንግሥት በፖሊቲካ፣ ኤኮኖማያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ጸረ ኢትዮጵያዊነቱን ያጋልጣል፣ ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብና አለም አቀፋዊው ማህብረሰብ ያሳውቃል።

3.ከብዙ ሺ ዘመናት የአብሮነት ታሪክ፣ ባህልና ማህበራዊ ትስስራችን ጋር በማቆራኘት የኢትዮጵያዊነት እሴቶችና ህገ መንግሥታዊ መስፈርቶቹን እንዘረዝራለን፣ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም አቀፍ ማህብረሰብም እናሰራጫለን።

4.ኢትዮጵያዊነትን የሚያንፀባርቅ ህዝባዊ አደረጃጀት እንቀይሳለን፣እንዘረጋለን። በጎሰኛዉ ህገ መንግስት  ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና መሰረተዊ አንቀጾችን ነቅስን በማውጣት አደገኝነታቸውን ለሕዝብ ጭብጥ ግንዛቤ እንዲኖረው እነመክራለን፤፤

5.የኢትዮጵያን ህዝብ በአንድ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ስር ለማሰባሰብና የጥንቱን ሰንደቅ አላማችንን ለማስመለስ እንታገላለን።

6.ኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ርዕዮተ ዓለምና ህገ መንግስታዊ ስርዓት  እናስተምራለን፣ እናስተዋውቃለን።

7.እስክንድር ነጋና ሌሎችም የህሊና እስረኞች ከእስር ቤት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዓለም አቀፍ ግፊት አንዲደረግ እንሠራለን፤፤

8.ጎጠኞችና የሃይማኖት አሸባሪዎች አማራውን ፣ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ አማኞችን እንዲሁም  ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ (Genocide) ማፈናቀላቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ካለመታከት እንሠራለን። ባለፉት ለበርካታ ወራት በተደጋጋሚ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችበዘር ተለየተውነፍጠኞች” ተብለው የዘር ጭፍጨፋ ለደረስባቸው የአማራና የጉራጌ ተወላጆችና እንዲሁም የሌሎች ብሔሮች በተጨማሪም ቀሪ ቤተሰቦቻቸው ንብረታቸው ወድሞ በአሁኑ ጊዜ በየ ቤተክርስትያኑ ተጠልለው ቤተአጥ ለሆኑት ሁሉ መንግስት ባሰቸኳይ  ፍትሕ እንዲሰጥ ግፊት እንናደርገለን፤፤

9.በባዕድ ርዕዮተ ዓለምና የጸረ ኢትዮጵያዊነት ተልዕኮ አቅጣጫውን እንዲስትና ከኢትዮጵያዊነት እንዲያፈነግጥ የተደረገውን ወጣት በማስተማር ወደ ህሊናውና ኢትዮጵያዊነቱ እንዲመለስ ለማድረግ በርትተን እንሠራለን። ለሀገር ግንባታ አሰተዋጽኦ ለማድረግ ሲባል ወጣቶችና ሴቶችን የማበረታታትና የማጠናከር ተግባሮችን በህግ ከለላ ሊሰጣቸዉ ይገባል ብለን እናምናለን እንገፋለን፤፤

  1. ሕዝባችን ከድህነትና ከተመጽዋችነት እንዲላቀቅና ለዘለቄታዊ ሁለንተናዊ እድገትና ስላምን እንዲጎናጸፍ የተቻለውን አሰተዋጽኦ ለማድረግ ከህዝብ ጎን እንቆማለን እንዲሁም እናሳተፋለን፥፥ተገቢ የሆነ ብሔራዊና ሥልታዊ ሕዝብን ማእከል ያደረገ የልማት እቅድ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን እናምናለን፤፤

11.ከላይ የተዘረዘሩትን ታሳቢ በማድረግ የዘር ህገ መንግሥቱ የኢትዮጵያን አንድነቷንና ህልውናዋን እየተፈታተነ አንድ የነበረ ህዝቧን በዘር በጎጥና በሃይማኖት ከፋፍሎ ህዝብን ከህዝብ እያፋጀና በፖለቲካ በኤኮኖሚና በማሀበራዊ ኑሮ ምስቅልቅል ሁነታዎችን በመፍጠር ችግሮቹን እያባባስ በመሆኑ ሐገሪቱን ለመታደግና ከመበታተን አደጋ ለመጠበቅ የዘር ህገ መንግሥቱ መወገድ እንዳለበት እያሳሰብን፥ከመጭው ምርጫ በፊት ህዝብን ማአከል ያደረገ፤ ኢትዮጵያዊነትን ሕብረ ታሪኳንና እንቁ እሴቶቻችንን ያቀፈ ፥የአለም አቀፍ የስብዊ መብቶችን ሕጎችና ኮንቬንሽኖችን በደረጃ ያዋቀረ የዜግነት መብቶችን የእኩልነትና የዺሞክራሲ ግንባታን መሰረት ያደረገና በዘር መደራጀትን ሕገወጥ ያደረገ በተጨማሪም ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ህጋዊ ዶኩመንት (ሰነድ) እንደ አማራጭ ሕገ መንግስት በትውልደ ኢትዪጲያውያን የሕግ ባለሙያዎችና ዤጎች ባለ ድርሻዎች ተረቆ ለኢትዮያ ህዝብ እንዲቀርብ ተሳትፎ እናደርጋለን፤፤ሁኔታዎችንም በተቀላጠፈ መንገድ እንዲሳኩ ስመ ጥሩ የሆኑ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ያስተባብራል፤፤

አገርና ህዝባችንን ለማዳን ወደፊት በምናዘጋጃቸውና በምናቀርባቸው ምሁራዊ የውይይት መድረኮችና ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ባገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያላችሁት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከጎናችን እንድትቆሙ በትህትና እንጠይቃለን።

አገርና ህዝባችንን በጋራ እንታደግ።

**ኢትዮጵያዊያን ለህገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም የዘር ማጥፋት (ክልል) ለማስወገድ

1 Comment

  1. Why do we Ethiopians depend on intellectuals to give our organizations credibility where as this dependence always leads to failure from what we have seen? I suggest you descard your dependence on intellectuals who invariably have ego problems and let the cause stand on its strength alone so that everyone can support and participate in it with or without focus on educational backgrounds. I do honestly believe what one needs to participate and support is humanity and Ethiopianness not education. Time for ordinary people to lead not follow.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.