የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋናቸውን አቀረቡ

የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ድምቀቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡
የዘንድሮ የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ምክኒያት አባገዳዎች ባስቀመጡት የሰው በቁጥር መሰረት አነስ ባለ ታዳሚ 120754652 1776632519154755 8951346557749479009 n የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋናቸውን አቀረቡድምቀቱን በጠበቀ መልኩ እንደሚከበር ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
ሆኖም ግን በዓሉን በማደናቀፍ ከተማዋን የጥፋት አውድማ ለማድረግ በርካታ የታጠቁ የጥፋት ኃይሎች ሲያሴሩ በመቆየታቸው በህብረተሰቡ እና በጸጥታ አካላት ትብብር ከነሙሉ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በህግ አካላት ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
ይህ ሁኔታም በህብረተሰቡ እና በነዋሪዎች ዘንድ ስጋት በመፍጠሩ ከጸጥታ አካላት ጀምሮ ሁሉም በየአካባቢው ሰላሙን ለማስጠበቅ በርካታ ስራዎች ሲሰራ በመቆየቱ የዛሬው የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በደመቀ ሁኔታ በሰላም ተከብሮ ውሏል፡፡
የበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም በዓሉ ካለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ከጸጥታ አካላት ጀምሮ አባገዳዎች ፣ ቄሮዎች እና ፎሌዎች እንዲሁም መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን የገለጹት ወ/ሮ አዳነች በጥፋት ኃይሎች የታቀዱ እኩይ ተግባራት ቢኖሩም ህብረተሰቡ ለንደዚህ አይነቱ ሴራ ጆሮ ሳይሰጥ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረገው ትብብር አቅርበዋል፡፡
የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በድምቀት እና በሰላም እንዳይከበር የጥፋት ሀይሎች በጀት መድበው እና ሀይል አስተባብረው ሲሰሩ እንደነበር የገለጹት ወ/ሮ አዳነች መላው በከተማዋ ነዋሪዎች፣ በበዓሉ ተሳታፊዎች እና በፀጥታ ሀይሎች ትብብር እና በተቀናጀ ስራ ሊከሽፍ ችሏል ብለዋል፡፡
የጥፋት ሃይሎች የኢትዮጵያን ብልጽግናን ለማደናቀፍ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ሰላም ወዳዱን የኦሮሞ ህዝብ እና የከተማዋ ነዋሪዎች እርስበእርስ ለማጋጨት ትልቅ ሴራ ቢነድፉም ህብረተሰቡ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር ተናቦ እና ተቀናጅቶ በመስራት፣መረጃ በመለዋወጥ እና ወንጀሎኞችን አሳልፎ በመስጠት ትልቅ ስራ መሰራቱን ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል፡፡
በነገው ዕለትም በቢሾፍቱ ከተማ ለሚከበረው የሆራ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በተመሳሳይ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ከአዲስ አበባ እና ከዙሪያዋ እንዲሁም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በባህል አልባሳት ደምቀው በአንድነት መንፈስ በጋራ ተከብሯል፡፡

120603741 1776632492488091 8145462619156291241 n የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋናቸውን አቀረቡ 120603370 1776448892506451 6826865304653719415 n የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋናቸውን አቀረቡ 120611462 1776448805839793 5625117481767420191 n የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋናቸውን አቀረቡ
ፎቶ በሀዱሽ አብረሃ/(ኢ.ፕ.ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.