አውቶብሶች ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ታግደዋል?

211ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ የሚያመሩ መንገደኞች ወደ ከተማው መግባት ባለመቻላቸው እየተጉላሉ እንደሆነ መረጃው ደርሶን እንድናጣራ በርካታ መልዕክቶች ደርሰውናል።

ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ መንግስት እየወሰደ ባለው የጸጥታ ቁጥጥር አውቶብሶች ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ እንዳልሆነ ኢትዮዽያ ቼክ ያነጋገራቸው የኤፍ ኤም ባስ፣ የአባይ ባስ፣ የዘመን ባስ እና የጎልደን ባስ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች አረጋግጠውልናል።

ኢትዮዽያ ቼክ ያነጋገራቸው አንድ የአውቶብስ ሹፌር ወደ አዲስ አበባ ያመሩ የነበሩ አውቶብሶች ባሉበት እንዲቆሙ መደረጉን ተናግረዋል።
ከግሸን ክብረ በአል ሲመለሱ ሸኖ ከተማ ላይ እንዲቆሙ የተደረጉ፣ ሆሳዕና ለመስቀል በአል ሄደው ሲመለሱ አለምገና መግቢያ ላይ እንዲቆሙ የተደረጉ እንዲሁም ከአርባ ምንጭ፣ ወላይታ እና ከሌሎች ስፍራዎች ሲጓጓዙ ቡታጅራን አልፈው ሌመን የምትባል ከተማ ላይ እንዲቆሙ የተደረጉ በርካቶች እንዳሉ መረጃዎች ደርሰውናል።

ህፃናትን የያዙ፣ አረጋውያን፣ እና ህመምተኞች ጭምር በመንገድ መዘጋቱ ምክንያት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ እና የት ማደር እንዳለባቸው እንኳን እንደማያውቁ መረጃ ለኢትዮጵያ ቼክ ሰጥተዋል።

ኢትዮዽያ ቼክ

4 Comments

  1. ለአንድ ሙትቻ ማነው እሬቻ በዓል ሀገር ይታመሣል። ከየት የመጣ ያገር አስተዳደር ፈሊጥ እንደሆነ እነዚህ ጀዝባዎች ቀናቸው ደርሶ በፍልጥ ሲነረቱ ይናገሯታል። አገር ሢያረጅ ጃርት ያፈራል መባሉ እንዴት ትክክል ነው?

  2. ትላንትና የኦርቶዶክስ ክርስትና በአል እንዳይከበር ያዘዘ አመራር ዛሬ ኢሬቻ እንዲከበር ያዘዘው የነሽመልስን የበላይነት ለማረጋገጥ ታስቦ የተወጠነ ነው? የሚያሳዝነው አመራሮቹ በሙሉ ወይ ክርስቲያን ወይ እስላም ናቸው ታድያ ሁለቱም ሀይማኖቶች ከኢሬቻ ተጻራሪ ናቸው። እነዚህ መሪዊች ግን በጣም devotion ለሚያስፈልገው የክርስትና እና እስልምና እምነት እንኳን ግድ ስለሌላቸው በአሉን ሊታደሙ ተዘጋጅተዋል። እንግዲህ አባዱላ ገመዳን አብይ መሀመድን ለማ መገርሳን ዳውድ ኢብሳን ሌንጮ ለታ/ባቲን የመሳሰሉትን ለዚህ ባእድ አምልኮ እያጓሩ ዛፍ ቅቤ ቢቀቡ ልትገረሙ አይገባም። ሰሞኑን መከረኛው የአዲስ አበባ ህዝብ ለቅቤ ካላዋጣህ ተብሎ ቄሮ የተባለ መንጋ ቁም ስቅሉን ሲያበላው ነበር።ባጭሩ ኢሬቻ ኢ አማኞች የሚያከብሩት የዛር አምልኮ ነው። ከክርስትና እና እስልምና በጣም በተጻራሪ የቆመ ሀይማኖትም ጭምር ነው። እንዲህ ነው የቁልቁለት ጉዞ ማለት። በእርግጠኝነት እስላሞች አህመዲን ጀበል ለመወደድ ብሎ ቢቀሰቅሳቸውም እንደማይሄዱ ማረጋገጫ መስጠት ይቻላል።

  3. Many passengers are lost in the wilderness of Oromia while walking starting from the border of Addis Ababa and Oromia, all the way back to where they came from.

  4. Irecchha = Parade

    Bekele Gerba had huge potential but he squandered his potential by aligning with the Dembi Dolllo University student’s abducters . Three hundred plus days had passed since the Dembi Dollo students had been abducted , giving the Bekele Gerba’s legal team a leverage to negotiate a deal with the prosecutor , without this deal it seems the whereabouts of the students is not known with three hundred days passing, with no clue known by the students families or by the government’s security apparatus hostage negotiators search professionals to where the students are .

    Jawar is firing six of his lawyers letting only six of his lawyers represent him because twelve lawyers at the same time representing Jawar shown that he is giving directions to his lawyers to do things not related to his imprisonment.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.