‹‹ ጦር ይሠበቃል ወይ፣ ጋሻ ለሌለው ሰው!!!›› ‹‹ ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!›› ፀ/ትፂዮን ዘማርያም

ET32‹‹ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!››

‹‹የክልል ልዩ ታጣቂ ኃይል ይፍረስ፤ በዘር ተደራጅቶ፣ በዘር የታጠቀ፣ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል!›› ያሬድ ሀይለማርያም

ኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የክልል ሥልጣንና ተግባር ‹‹የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል ፣ይመራል፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፡››  ይላል አንቀጽ 52፡፡ በህገ-መንግሥቱ  መሠረት ክልሎች የፖሊስ ሠራዊት ኃይል ብቻ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ( ትህነግ) ህገመንግሥቱ በመጣስ ክልሎች  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀቶች  እንዲኖራቸው አደረገ፣ ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ በመሄድ በክልሎች መኃል ተጨማሪ ኃይል የማሰባሰብ ክልሎች እርስበእርሳቸው የጎሪጥ እንዲተያዩ አደረጋቸው፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዘርና በብሔር አደረጃጀት ከፋፈለው፣ ሸነሸነው፡፡ ወያኔ/ኢህአዴግና ኦዴፓ ብልጽግና የሠራዊቱን  ሃገራዊ ፍቅሩንና ብሄራዊ ክብሩን በማዋረድ ሠራዊቱን በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን በመቀስቀስና የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት  ሃገሪቱን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ሊያፈርሳት እየጣረ ይገኛል፡፡ የወያኔ/ኢህአዴግና ኦዴፓ ብልፅግና  የፖለቲካ ሴራ ለስልጣኑ ሲል ሃገር በማፍረስ መከላከያ ሠራዊቱንና የፖሊስ ኃይል በዘርና በብሄር በመሸንሸን ሃገራዊ ተልዕኮውን አንዲሸረሸር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

‹‹የጎሳ ፖለቲካ ጡዘት ሰማይ በነካበት እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገር ውስጥ በብሔር የተዋቀረ የክልል ታጣቂ ልዩ ኃይል ወይም ሚሊሻ ማደራጀት ማለት የተጠመደ ፈንጅ በጀርባ አዝሎ እንደመዞር ነው። ክልሎች በአገር ውስጥ ያሉ አገሮች ሆነው ተዋቅረዋል። በዛ ላይ አወቃቀራቸው ቋንቋና ብሔርን መሰረት ያደረገ ነው። የብሔር ፖለቲካው እያመሳት ላለች አገር በብሔር የተደራጁ ታጣቂ ኃይሎች እያሰለጠኑ እና እያስታጠቁ በየክልሉ ማስቀመጥ ካየነው በላይ ብዙ ግፍ እንድናይ እና ኢትዮጵያንም በቀላሉ ወደ ዘር ተኮር ግጭት ከመውሰድም በላይ የአክራሪ ቡድኖች መፍለቂያነት እና ወደ ሽብር ቀጠና ሊለውጣት ይችላል።

የትግራይ ክልል ወታደራዊ ትዕይንት ባደረገ ማግስት በርካታ የትግራይ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ የታጠቀ ኃይል ወደ አማራ ክልል ድንበር በማስጠጋት አላማጣ፣ ራያ ቆቦ፣ ጨርጨር  አካባቢ እየሰፈረና ምሽግ በመቆፈር የጦርነት ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ወንድማማቾችን በጦርነት የማፋጀት የፖለቲካ ፖሊሲና ሴራ  በማጋለጥ የትግራይ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ  የኢትዮጵያን ጦር ለመቀላቀል ወደ አማራ ክልል እየገቡ እንደሆነ ታውቆል፣ ለዚህ ነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ‹‹ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!›› የሚሉት፡፡ ህወሓት /ኢህአዴግ በዘርና ቌንቌ በማካለል በአንድ ዘር ላይ የተዋቀረ የፖሊስ ኃይል፣  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ በማስታጠቅ በክልሎች መኃል የማያባራ የድንበር ግጭትና ጦርነት የሰው እልቂት፣ የንብረት ውድመትና በወንድማማቾች ጦርነት ደም በከንቱ ሲፈስ ቆይቶል፡፡

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የመከላከያ ወታደራዊና የፖሊስ ሠራዊት ትዕይንት በማድረግ የኦነግ/ኦዴፓ/ ኦህዴድ ብልጽግና ፓርቲ ድብቅ አጀንዳ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅምና አዲስ አበባ የኦሮሞ ክልል አካል ነው የሚል እብሪት በተረኝነት የኦሮሞ የዘር ፖለቲካ ሴራ እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ አከርካሬው ይመታል፡፡

ማጠቃለያ  ከህወሓት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራን ለመበጣጠስ የወያኔን ህገ-መንግስት በአዲስ ተክቶ ይሄን የአባላሽኝ ዘመን የኦነግ፣ የኦነግ ሸኔና ኦፌኮን የዘርና የኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) አስወግደን አዲሲቷን ኢትዮጵያ በእውነትና በሃቅ መምራት ይጠበቅብናል፡፡ በኢትዮጵያ የዘርና የኃይማኖት ፍጅትና ዘርፈ ብዙ ሽብርተኛነትን ለማስወገድ ፡-

  • አንደኛ ከክልል ፖሊስ በስተቀር ያሉ የክልል ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀትች ሙሉ በሙሉ ከክልሎች እጅ አውጥቶ በፌደራል መዋቅር ስር ማድረግ፣
  • ሁለተኛ በብሔር የተዋቀረውን የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ በመበታትን ወደ ሁሉም የአገሪቷ ክፍል ማሰባጠር እና በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ ያለው ታጣቂ ኃይል ከሁሉም ብሔር የተወጣጣ እንዲሆን ማድረግ፣
  • ሦስተኛ በየክልሉ ያለውን ስብጥር ኃይልን በበላይነት የሚመሩትንም አዛዦች እንዲሁ በተሰባጠረ መልኩ ማዋቀር፣
  • አራተኛ ይህን ኃይል በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አይምሯቸው ውስጥ ያለውን የብሔረተኝነት ስሜት በሂደት እንዲቀይሩና ያለመድሎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ደህንነት ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ።

ክልሎችም ያንጃበበውን አደጋ ከወዲሁ አጢነው ለዚህ ለውጥ መሳካት ካልተባበሩ በዘር ያደራጁት የታጠቀ ኃይል ተንሸራቶ አክራሪዎች እጅ የወደቀ ዕለት የመጀመሪያዎቹ የጥቃት ኢላማዎች እነሱ መሆናቸውን ሊያጤኑት ይገባል። በዘር ተደራጅቶ በዘር የታጠቀ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል። ይህን ለማድረግ ግን ወሳኙ ነገር የአገዛዝ ሥርዓቱ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ያንጃበበውንም አደጋ በበቂ ሁኔታ መረዳትን ይጠይቃል። ይሄን የተጠመደ ፈንጂ ሳያመክኑ በጀርባ አዝለው እየዞሩ ኢትዮጵያ አትፈርስም ማለት ብቻውን አደጋውን አያስቀረውም።›› የብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር አብይ አህመድ ይሄን ምክር ተጠቅመው የኢትዮጵያን እናቶች፣ ህጻናትና፣ ሁሉን ዜጎች ከዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀኖሳይድ) ሊታደጉት ይገባል እንላለን፡፡ በሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ተከትሎ መቶ ስልሳ ሰባት ሰዎች ህይወት መጥፋት ቤተሰቦች ሳያፅናኑና ለወደመው ንብረት በተለይ የሻሸመኔ ከተማ መቃጠል ለመርዳት በሃገር አቀፍ ደረጃ የእርዳታ  ገበታ ሳያዘጋጁ አዲስ አበባ ለማስዋብ የአምስትና አስር ሚሊዮን ብር የገበታ ድግስ ማዘጋጀት ቅድሚያ ለማን ይሰጥ? ከተማ ከመገንባት በፊት የቄሮ ህሊናን መገንባት ይቅደም፡፡

 

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዐብይ አህመድ  ሪፓብሊካን ጋርድ ገነባ!!! ለህዳሴ ግድብ የፌዴራል ጋርድ ልዩ ኮማንዶ ጦር ከሁሉም ክልሎች የተወጣጣ ጦር መገንባት አስፈላጊ ነው እንላለን !!!

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዘርና የኃይማኖት ፍጅትን ማስቆም ያልቻለ መንግሥት ስለሆነ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፀጥታና ደህንነት ማስጠበቅ አይችልም!!! እውቀትም ብቃትም የለው!!!

 

 

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.