የዘር መታወቂያ ካርድ የሚሠጡ የንግድ ፓርቲዎችና የጦር አበጋዞች ሠራዊት ይወገዳሉ!!! – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

et 22የደብረፂዮንና የዐብይ ዘረኛ የጦር አበጋዞች መንግሥት አደረጃጀት፣ፍልሚያና ፍፃሜ!!!

ዐብይ ሪፓብሊካን ጋርድና መከላከያ ሠራዊት የኦሮሚያ ልዩ የፖሊስ ኃይልና ሚሊሽያ አላቸው !!!  ደብረፂዮን አጋዚ ጋርድና አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽህ ጦር አላቸው!!! አብዲ ኢሌ ሄጎ ጋርድና ልዩ የፖሊስ ኃይልና ሚሊሽያ አርባ ሽህ ጦር ነበራቸው፡፡ አብዲ ኢሌ፣ደብረፂዮንና ዐብይ አንድም ሁለትም ሦስትም ናቸው፡፡  የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዘብ የሚቆምለት ህዝባዊ ፌዴራላዊ  ጋርድ፣ ልዩ ኮማንዶ ጠባቂ ጦር አልተገነባለትም ከሱዳን ድንበር አርባ ኪሎሜትር ላይ ሲገኝ የሽምቅ ተዋጊዎች የዘርና የኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) የሚያደርጉበት አካባቢ መሆኑን ሁሉም ያውቃል፡፡ የዘር መታወቂያ ካርድ የሚሠጡ የንግድ ፓርቲዎችና ሠራዊት ባላቸው አገር የበለጸገ አገር በዓለም ላይ የለም፣ የዘር፣ የብሄርና፣ቀለም ልዩነት፣አስተሳሰብ ኃላቀር ያልሠለጠኑ ሰዎች አመለካከት ነው፡፡ በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን የወጣቶችን ህሊና አይመጥናቸውም፣ በግሎባላይዤሽን የመረጃ ዘመን ዓለማችን እንደ አንድ መንደር ናትና  የዘርና የኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) ፈፅሞ መደበቅ አይቻልም፡፡ በህግ ሉዓላዊነት የእናቶች ዕንባ ይታበሳል! በምግብ እራሷን ያልቻለች አገር በጦር መሣሪያ ህይወት መቅጠፍ እንጂ እህል አታበቅልም፡፡ ሁሉም በዓለም አልፎል…ጊዜ ለሁሉ!!! የአዲስ አበባ ወታደራዊ ትርዒት በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በወለጋ ይደገም!!!

የህወሓት/ኢህአዴግና የኦዴፓ ብልጽግና ዘረኛ የጦር አበጋዞች መንግሥት አደረጃጀትና ፍልሚያ!!!

ከግንቦት 20 ቀን 1983ዓ/ም በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ገቡ፣ የሻብያ፣ የወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች ወታደሮች በዘር የማንነት መታወቂያ የተሠጣቸው ከኤርትራው አፋቤት በርሃ፣ ከትግራይ ደደቢት በርሃና ከወለጋ በርሃ የብሄር  የዘር ንግድ ድርጅት ወታደራዊ ሥልጠና በማግኘት፣ የዘርህ ግንዳቸው ተጣርቶ መታወቂያ የተሠጣቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ነፃ ስንወጣ  በየክልልህ የመንግሥት ሥራ ትመደባለህ፣ ውታደርና ፖሊስ ሆነህ  ትመለመላለህ በሚል ሠበካ የተመለመሉ ሽምቅ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡ ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ‹‹የዘር ማንነት መታወቂያ የሚሠጡ  የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ናቸው፣ አመሰራረታቸውም ዘር ተኮር ነው፡፡ በግለሰብና በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የዘውግ/ የብሄር/የዘር የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ  ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የሚጭኑበት ስርአት ነው፡፡ የጦር አበጋዞቹ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም  ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡ ዘመነ ጦር አበጋዝ፣ ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የጦር አበጋዞች መንግስት ወደ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ)  የጦር አበጋዞች መንግስት  በትረሥልጣኑን ለማራዘም ያሸጋገረበት የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተስፋ ባለመቁረጥ አሁን ደግሞ ከመቐሌ ምሽጉ ስፖንስር በሚያደርገው ገንዘብና መሣሪያ ለኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) የጦር አበጋዞች መንግስት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተለይ በወለጋ፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ወዘተ ትጥቅና ስንቅ በማቅረብ ሠላም በማደፍረስ ላይ ይገኛሉ፡፡

የጦር አበጋዝ ማለት በዘር ግንድ ላይ የተመሠረተ የግል ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት፣ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም፣ ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ስም፣ ኦብነግ በኦጋዴን ህዝብ ስም፣ ሲአን በሲዳማ ህዝብ ስም በዘር የተደራጀ ጦር በመገንባት ሌላውን ዘር በማግለል የራሳቸውን ግዛትና መንግሥት በሌላው ላይ ለመጫን የተደራጀ ኃይል ያቆቁማሉ፡፡  የጦር አበጋዝ ማለት  ለግል ጥቅም ስልጣንና ኃብትን የሚያካብት ተዋናይ ሲሆን በአንድ ሃገር፣ ያለው መንግስትና መንግስታዊ መዋቅሮች ጠንካራ ባልሆነበት አካባቢ የሚፈለፈል ነጻ አውጪ፣ ንቅናቄ የጦር አበጋዝ ነው፡፡

‹‹የፖለቲካ የማንነት ጥያቄ›› Identities Politics፣ በአፍሪካ የዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት ፅንሰ ሃሳብ ዋነኛና አንገብጋቢ ጥያቄ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ዘውጌ ብሄረተኛነት፣ ‹‹በማህበራዊ ጭብጦች ላይ ሳይሆን፣ በዝርያ፣ በወገን መመሳሰል ላይ የተመሠረተ ብሄርተኛነት››ነው፡፡(አንዳርጋቸው ፅጌ ገፅ 310) በዘመነ-ጦር አበጋዞች በጎሳ፣ በነገድ፣ በዘር፣ በዘውግ፣ በክልል (የደም ግንኙነት፣ የዘር ሃረግ፣ የቌንቌ፣ወዘተ) ላይ የተከለሉና የተመሠረቱ የጦር አበጋዞች አንድ ዘርን  በውትድርና በመሠልጠን፣ በማደራጀትና ተዋጊዎች በመመልመልና በሌሎች ዘሮች ላይ በመነሳት፣ የማንነት ጥያቄን ሽሮ መብሊያቸው አደረጉት፡፡ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም፣ ማኦይዝም ቀመስ የሆኑ የጦር አበጋዞች በስመ ሶሻሊዝም የብሄር ብሄረሰብን ጥያቄ በማራገብ  ደቀ መዝሙር የነበሩ ጀሌውን ህሊና አጠቡት፡፡ የጦር አበጋዞቹ እልፍ አእላፍ ገበሬዎችን በወታደርነት በመመልመልና አንዱን ዘር በሌላው ዘር ላይ ጥላቻ በመቀስቀስ፣ የራሳቸውን ታማኝ ጦር ማደራጀት ቻሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ  የማንነት ጥያቄ ኢንተርፕሬነር ፈላስፎች ሆኑ፡፡ በኢትዩጵያ ውስጥ በዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት  በጉጠኛነት፣ በዘውገኛነትና በዘር ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች መኃል፤ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ (ህግሓኤ)፣ ኤርትራ አርነት ግንባር (ኤአግ)፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሓት)፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ እስላማዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦእነግ)፣ ምዕራብ ሶማልያ ነፃ አውጭ ግንባር (ምሶነግ)፣ በሱማሌ (ኦኤንሌኤፍ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ በጋንቤላ ነፃ አውጪ ግንባር (ጋነግ)፣ የሲዳማ አርነት (ሲአን)፣ ቤኒ-ሻንጉል ነፃአውጪ ግንባር፣ አፋር ነፃ አውጭ ግንባር (አነግ) ወዘተ ማዕከላዊውን መንግስት በማዳከም የፖለቲካ ስልጣን የሚቆጣጠሩበት ስርዓት ሆነ፡፡ በዘመነ-ጦር አበጋዞች በነፃ አውጭ ስም፣ በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ የግላቸው ሎሌ ጦር ሰራዊት ለራሳቸው ጥቅምና ስልጣን በማደራጀትና በመመልመል በብሔራቸው ስም ስልጣን ለመያዥ ይታገላሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ በግለሰቦችና በተለያዩ ቡድኖች ላይ ጥላቻን በመፍጠር የራሳቸውን የጦር ሰራዊት በማቆቆም ጥቅማቸውን ያስጠብቃሉ፡፡ እንደ ቶማስ ገለፃ ከሆነ፣ የጦር አበጋዞቹ ሚና የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት ጋር ይወዳደራል፣ በዛም የዘርህ ግንድ ተጣርቶ መታወቂያ ይሰጥህና ውትድርና ትመለመላለህ ማለት ነው፡፡

‹‹የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት አመሰራረቱ፣ በግለሰብና በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ  ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የሚጭኑበት ስርአት ነው፡፡ የጦር አበጋዞቹ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም  ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡››

ከወያኔ ኢህአዴግ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የተረኛነት የዘር ፖለቲካ፡-

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ፅ/ቤት፣ በኦሮሚያ ፖሊስ ዋና ፅ/ ቤቱን አዲስ አበባ ተደርጎል፣ ማዕከላዊ እዙ አዲስአበባ ሆኖ በመላ ኢትዮጵያ ፀጥታ የማስከበር ኃላፊነት ለኦሮሚያ ፖሊስ ተሰጥቶል፡፡ የኦህዴድ/ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ከወያኔ ኢህአዴግ ዘረኛ የጦር አበጋዞች መንግሥት የቀሰመውን ዘረኛ የተረኝነት አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለመጫን እየታገለ ይገኛል፡፡ ወያኔ በህዝብ የተጠላው በአንድ ዘር ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ፖሊስ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ እያለ በክልሎች የዘር ፖለቲካ በመትከልና በከፋፍለህ ግዛው ብሂል በመጠቀም ለሃያ ሰባት አመታት ገዝቶ ወደቀ፡፡ ዛሬ ኦዴፓ ብልጽግና የራሱን የጦር አበጋዞች መንግስት በመገንባት ላይ ተጠምዶል ከወያኔ ውድቀት መማር አልቻለም፡፡ ወታደራዊ ሳይንስ ዓለም አቀፋዊ ሙያ ሆኖ ለአንድ አገር ይቆማል እንጂ ለይቶ ለአንድ ዘር የመቆም ቃል ኪዳን ገብቶ አያውቅም ለዚህ ነው  ‹‹ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!››የሚባለው፡፡

በኦሮሚያ ክልል የኦሮሚያ ፖሊስ ስልጠና ለ30ኛ ጊዜ በብዙ ሽህዎች ተመርቆል፡፡ ከሜቴክ የ300 ሽህ የክላሽንኮብ መሣሪያ ከአንድ ሚሊዩን ጥይቶች ለኦሮሚያ ክልል ማስታጠቅ የዘረኝነት ፖለቲካ ለዘር ፍጅት  ዝግጅት አንድ እርምጃ መሰናዶ ነው እንላለን::  የአዲስ አበባ ህዝብ የሞግዚት አስተዳደር ያበቃል !!! የአዲስ አበባ ህዝብ ለመብቱና ነፃነቱ የአልገዛም የእንቢተኝነት ትግሉን በተደራጀና በሰለጠነ ኃይል ይቀጥላል!!! አዲስ አበባ የሁሉም ክልሎች የጋራ ሃብት ናት፡፡ የሱማሌ፣ የአፋር፣ የጋምቤላ፣ የሀረሪ፣ ቤኒሻንጉል፣ የደቡብ፣ ሲዳማ፣ ትግራይ፣ አማራ፣ የኦሮሞ ህዝብ በጋራ ይሄን የኦዴፓ/ ኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ለማድረግ የሚታሰብ ሳጥናኤላዊ ሥራ በአጭር ጊዜ በህዝባዊ እንቢተኝነትና አልገዛም ባይነት ይገረሰሳል፡፡ ዶክተር ዐብይ አህመድ ለኢትዮጵያ ህዝብ የገቡትን ቃልኪዳን ጠብቀው የመጨረሻ እድልዎን እንዲጠቀሙበት እንመክራለን፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ የወደፊት እቅድ  የኦሮሚያን ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ከኢትዮጵያ የሚችለውን ያህል እንደ ወያኔ ዘርፎ ለመገንጠል ማመቻቸት ይሆናል፡፡ የአብይን መንግሥት ለመጣል ከተንቀሳቀስክ ኦሮሚያ ትገነጠላለች አብራም  አዲስ አበባ ይዛ ወደ ሰማይ ታርጋለች በሚል የፖለቲካ ግርዶሽ የህዝቡን ዓይን በመጋረድ አስተዳደራቸው ይቀጥላል፡፡ አዲስ አበባን ከተማ በኦሮሚያ ስነ-ህዝብ ፕወዛ አጠንክሮ በመቀጠል አንባገነናዊ አገዛዙ ዓይን ያወጣ አንባገነን ዘረኛ የጦር አበጋዝ መንግስት ይመሠርታል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አንድ ሜትር ካሬ ቦታ ሦስት መቶ ሽህ ብር እያወጣ መሬት በመሸጥ ከወርቅና ዘይት መዕድን የበለጠ መዛቅ መቻሉን ከህወሓት/ ኢህአዴግ የተማረው ኦዴፓ ብልፅግና በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ድርድር የለውም፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ካርታ አዲስ አበባን ጠቅልሎ እንዲቀጥል ለማድረግ ህገመንግሥቱን እነ ዶክተር አብይ አህመድ መቀየር አይሹም፡፡

ኦነግ/ኦህዴድ/ ኦዴፓ አዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነው ሲሉ አንድም የእነሱ የሆነ አሻራ የጠፋ ኪነ-ህንፃ፣ ብርቅና ድንቅ ቅርሳ ቅርሶች፣ መንግሥታዊ ተቆማት የተገነባ ህንፃዎች፣ ወዘተ ለላንቲካ ያህል በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ማሳየት በተቻላቸው ነበር፡፡ በ1889 እኤአ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና መዲና ሆና በዳግማዊ ምኒሊክ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያና ግርማዊት ንግሥተ ነገሥታት እቴጌ ጣይቱ ቡጡል ተቆረቆረች፡፡ ከዛ በፊት ያለውን የአዲስ አበባ ታሪክ በበራራ መጽሃፍ ያንብቡ፡፡ በዛ ዘመን ታላቁ የዳግማዊ ምኒልክ ቤተ-መንግሥት፣ ዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርት ቤት፣ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል፣ የምድር ባቡር ጣቢያና የባቡር አገልግሎት፣ ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ወዘተ ሁሉ ሥልጣኔ በእሳቸው ዘመን የገባ ነበር፡፡ ታላቁ የዳግማዊ ሚኒልክ ቤተ-መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ኃብትና ቅርሳችን በመሆኑ ኢትዮጵያዊ መሪዎች ዘር ማንዘር ሳትመርጥ፣ ከቀ.ኃ.ሥ፣ ኮነሬል መንግሥቱ ኃለማርያም፣ መለስ ዜናዊን፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዶክተር አብይ አህመድን  በመሪነት አስተናግዳለች፡፡ አዲስአበባ የዛሬ 131አመታት በፊት በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና ተቆረቆረች፡፡ የሸዋ ክፍለሃገር ዋና መዲና ተባለች፣ በሸዋ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ወዘተ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና ናት፡፡ ‹‹ኦሮሞ ለመናገር በሚከብድ ደረጃ ችግር ውስጥ እንዲገባ በቅኝ ገዥው ሥርዓት ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል ጉዳት ደርሶበታል፡፡›› ዶክተር አብይ አህመድ እያለ በኦሮሙኛ ቌንቌ ለኦሮሞ ተናጋሪዎች ያወራል፡፡እንዲህ ዓይነት አስተምሮት ከአንድ መሪ የማይጠበቅ እንደዛ ለመደረጉ ማስረጃና መረጃ የሌለው ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡

አዲስ አበባ እንደ ሻሸመኔ አትቃጠልም!!! የአዲስ አበባ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ጋርድ ሁሉም ህዝብ ከቀበሌው፣ ወረዳው፣ ክፍለ ከተማው ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ ህብረተሰቡንና ንብረቶቹን መጠበቅ ሓላፊነትና ግዴታ አለበት፡፡  ዶክተር አብይ አህመድ ‹‹ሪፓብሊካን ጋርድ›› ገንብቶ የእራሱን ፀጥታና ደህንነት ቤተመንግስቱንና መናፈሻዎቹን ማስጠበቅ ችሎል፡፡ ሰማንያ ሰባት ሰዎች ሲታረዱ ዝምታ፣ መቶ ሰማንያ ሰባት ሰዎች ሲታረዱ ዝምታ ብሎም አጣጥሎ ምንም እንዳልሆነ ነካክቶ ማለፍ የሞራል ውድቀትና የህሊና ልሽቀት፤ የግብርገብነት ደዌ ነው እንላለን፡፡   አረመኔዎቹ ፅንፈኛ ቄሮዎች ሰው ሲያርዱ፣ ሴቶች ሲደፍሩ፣ ንብረት ሲያወድሙ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል ሊታደገው አልቻለም፡፡ ደሞዝ የሚቆርጥለትና ቀለብ የሚሠፍርለት ደሃው ህዝብ ሲታረድና ንብረቱ ዶጋ አመድ ሲሆን ይመለከቱ ነበር፡፡  ከእንግዲህ ለአዲስ አበባ ሁሉም ዘብ ይቆማል!!!…..  ‹‹ ዘጠኝ ሞት መጣ ቢለው አንዱን ግባ አለው!!! ›› የአዲስ አበባ ልጆች፡፡

የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ግድቡ ከሱዳን ድንበር  አርባ ኪሎሜትር ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ በአማፂዎች የሚደረግ ተደጋጋሚ የዘር ጭፍጨፍ ቅጥረኞች ከግብፅ፣ ከሱዳንና ከሃገሪቱ ወዳጅ ያልሆኑ ሃገራት የፖለቲካ ሴራ የህዳሴግድቡ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ስለሚችል በአስቸኮይ እንደ ሪፓብሊካን ጋርድ፣ለህዳሴ ግድብ የፌዴራል ጋርድ ሊገነባ ይገባል እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ በላይ የወጣበት የሃገሪቱ አንጡራ ንብረት በመሆኑ በቆሚ በፌዴራል መከላከያ ሠራዊት ወይም በፌዴራል ጋርድ ጥበቃ ልዩ ኃይል በዓየርና በምድር የጥበቃ ተግባርን ለመከወን የሁሉም ክልሎች የሰው ኃይልና የጋራ በጀት መገንባት ይኖርበታል፡፡ የህዳሴ ግድቡ በአስተማማኝ የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ መገንባት አለበት እንላለን፡፡

የዐብይ ሪፓብሊካን ጋርድ እንደገነባ ሁሉ ፣ የህዳሴ ግድብ በፌዴራል ጋርድ ልዩ ኮማንዶ ጦር ሊገነባ ይገባል እንላለን ይህን ስንልም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሽምቅ ተዋጊዎች በተደጋጋሚ የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋ ስላደረጉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል ካለ ስለማይቆጠር  በሁሉም ክልሎች የተወጣጣ  አዲስ የፌዴራል ጋርድ እንዲቆቆም እንጠይቃለን፡፡ የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ የህዝብ አንጡራ ኃብት በመሆኑ ከደሃው ህዝብ በመዋጮ የተገነባ ግድብ በመሆኑ የግድቡን ፀጥታና ደህንነት መጠበቅና ዋስትና መስጠት የብልፅግና ፓርቲ  ቀይ መሥመር ነው እንላለን፡፡ በግድቡ ላይ ጥቃት እንዳይፈፀም በንቃት መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ በግድቡ አካባቢ ሽምቅ ተዋጊዎች እንቅስቃሴ መቆም ግድ ይላል፣ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲን መንግሥት የግድቡን ፀጥታና ደህንነት ያስጠብቅ እንላለን፡፡ የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ለሃገሪቱ የሚያስገኘው ገቢ ትንበያ (Revenue Projection) በግልፅ የተቀመጠ ጉዳይ ስለሆነ የፕሮጀክቱ ጥቅምና ጉዳት (Cost-Benefit Analysis) ስሌት በጥናቱ መሠረት ካልተተገበረ የአዋጭነትና ትርፋማነት ጥናቱ ከንቱ ሆኖ ስለሚቀር የግድቡ ፕሮጀክት የድርድሩ ቀይ መሥመር ለመንግሥትና ለተደራዳሪዎች አይነኬ ውሃልኮችን ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረግ የምሁራን ኃላፊነት ነው እንላለን፡፡ የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ፣  ከመጋቢት 24 ቀን 2003 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ/ም የዘጠኝ  ዓመታት ጉዞና እውነታዎች ውስጥ የሚያመነጨው የሃይል መጠን 6 ሺ 450 ሜጋ ዋት፣ለመገንባት የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን  5 አምስት ቢሊዩን የአሜሪካ ዶላር በላይ የግንባታ ወጪ ሲኖረው፣ በ2023 እኤአ አንድ ቢሊዩን ዶላር በዓመት ለሃገሪቱ የውጪ ምንዛሪ ከኤሌትሪክ ሃይል ሽያጭ  ያስገኛል ተብሎ ተተንቡዩል፡፡  የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ያልተጠበቀ ምን  ይጠበቅ፡፡

 

ለዚህ ነው  የዐብይ እራሱን ለመጠበቅ ሪፓብሊካን ጋርድ እንደገነባ ሁሉ ፣ የህዳሴ ግድብ በፌዴራል ጋርድ ልዩ ኮማንዶ ጦር ሊገነባለት ይገባል እንላለን፡፡

 

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዐብይ አህመድ  ሪፓብሊካን ጋርድ ገነባ!!! ለህዳሴ ግድብ የፌዴራል ጋርድ ልዩ ኮማንዶ ጦር ከሁሉም ክልሎች የተወጣጣ ጦር መገንባት አስፈላጊ ነው እንላለን !!!

 

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዘርና የኃይማኖት ፍጅትን ማስቆም ያልቻለ መንግሥት ስለሆነ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፀጥታና ደህንነት ማስጠበቅ አይችልም!!! እውቀትም ብቃትም የለው!!!

የአዲስ አበባ ወታደራዊ ትርዒት በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በወለጋ ይደገም!!!

ወይ ጊዜ ወይ ዘመን፣ ወይ ዘመን ወይ ወራት፣ የአንበሣን ቡችላ ሚዳቆ አባረራት!!!

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.