አንጋፋው ፖለቲከኛና የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም አርፈዋል

Mesfin አንጋፋው ፖለቲከኛና የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም አርፈዋልአንጋፋው ፖለቲከኛና የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም አርፈዋል።   ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም! ታላቅ ምሁር፣ ሞጋች፣ ደፋር፣ ፈላስፋ፣፣እስከ መጨረሻዋ ሰአት አብዮተኛና የለውጥ ሃዋርያ!  ሰውን የማያዳሉ  ለእውነት የቆሙ የኢትዮጵያ አድባር

ነፍስዎን በአጸደ ገነቱ ለዘላለም ያኑርልን።

ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ

የአገር አድባሩና የዕውቀት ቀንዲሉ የኔታ ፕ/ር መስፍን የማረፋቸውን አሳዛኝ ዜና መስማትህን በፌስቡክ ገፅህ ከለቀከው የሀዘን መግለጫ ተረድቻለሁ።
ለኔና ለኢትዮጵያ ሕዝብ እሱ ብቻ አይበቃም።የቀብር ስርዓታቸው አገርና ወገንን በሚያኮራ መልኩ እንዲፈፀም እንሻለን።ለዚህም ስርዓቱን የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ መዋቀር አለበት።
ከዚህም በላይ በስማቸው መንገድ እንዲሰየም።ስለእሳቸው የሚዘክር ሐውልት በአዲስአበባ እንዲቆምላቸው እንፈልጋለን።ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ፋኩልታዎች አንዱ ለዘመናት በዪኒቨርስቲው ላበረከቱት አስተዋፅኦ መታሰቢያነት በስማቸው እንዲሰየም እንዲያደርጉ በትህትና እንጠይቃለን።
እባክዎን ይቺን ትንሽ ነገር በመፈፀምና በማድረግ እኛን ኢትዮጵያንን ተባበሩን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.