አቶ መለስ ዜናዊና ጋዜጠኛ አበበ ገላው፤ የተቃራኒዎች አንድነትና ትግል ህግ ማሳያ – ከበየነ ከበደ

mele and abeመኢሶንና ኢሕአፓ ለስልጣን አልበቁም እንጂ እውቀታቸውና ንቃታቸው ከፍ ያለ ነበር። የሁለቱ ፓርቲዎች አብዛኛው አባላት በወቅቱ ተራማጅ የነበረውን ማርኪስዚምሌኒኒዝምና ተያያዡን ፍልስፍና ጠጥተውታል። መቀሌ በፈረጠጡት ባንዳዎች ተጠፍጥፎ የተሠራውን ኢሕአዴግ ስንመረምር – አብዛኛዎቹ አባላት እንኳንስ ለመኢሶንና ኢሕአፓ እጩነት ይቅርና ለንዑስ ማህበራት ግልጋሎት አይመጥኑም ነበር። ቅሚያ፣ ራስ ወዳዶድነትና ሙሰኝነት ብቻ አይደለም የአብዛኛዎቹን ብቃት ወደ ዜሮ ያወረደው፤ አቋማቸው ራሱ ለበታች አካል ካድሬነት እንኳን ስለማያዘጋጃቸው ነው። ስብሃትና መለስ እነዚህን አባላት ጠፍጥፈው የሠሩት ሳያውቁ ቀርተ አይደለም፣ ለመቶ ዓመት በጫንቃችው እንዲሸከሟቸው ዘይደው እንጂ። ኢሕአዴጎች ንግግር ያሳመሩ ይመስላቸዋል። በዓረፍተ ነገሮች መሃል ጣል ጣል በሚያደርጓት የጓዳ ቋንቋ (jargon) አዋቂ ታስመስላቸዋለች እንጂ በንድፈሃሳብና ተግባር መካከል ያለውን ተዛማጅነት ፈጽሞ አይረዱም።

ዲያሌክቲካዊና ታሪካዊ ቁስ አካልነት” የምትለዋ የፍልስፍና ክፍል ብዙ ታስረዳለች ። በተለይ ደግሞ የተቃራኒዎች አንድነትና ትግል ህግ” “የሻሪ ሽረት ህግ፣ ከዓይነት ወደ ጥራት ሽግግር ህግ” የሚሉትን ክፍሎች ጥሩ የፖለቲካ ግንዛቤ ያስጨብጣሉ። መለስና ስብሃት እነዚህን የመሳሰሉ ማህበራዊ ሳይንሶች በማኦዪዝም ለውሰው የበታች አባላቱን ውሸት ጋቱ። አባላቱ ሳያስቡ ከተነከሩበት ምዝበራና ሌብነት ተጠያቂነት ለመዳን ውሸትንና እንደ ማደናገርያነት ሃሰትን እንደ ማፍዘዥያነት ሲጠቀሙ ኖሩ። መናገር ማወቅ የሚመስላቸው የኢሕአዴጉ አብዛኛው አባላት ሞኞች ነበሩ። ንግግራቸው ሁሉ ከተግባር ስለማይቀዳ ሃገሪቱን መቶ ዓመት ወደ ኋላ ጎተቷት። ፍሬቢስ ሽንገላና የውሸት ትርክት አዳማጩን ለጊዜው ያደናግር (confuse) እንደሆን እንጂ መጨረሻው ዓዕምሮን አበስብሶ ከንቱ ማድረግ መሆኑን እስካሁን ያልተረዱ የኢሕአዴግ አባላት አሉ።

ባንድ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ የዓዕምሮ ደሃው፣ ደረቁና ሊሞት አንድ ሃሙስ የቀረው አቶ መለስና ንቁው ጋዜጠኛ አበበ ገላው አብረው ታድመዋል። አበበ እንዴት አዳራሹ መሃል ተስተካክሎ እነደተቀመጠ አላውቅም፣ ግን ስትራቴጂያዊ ቦታ አያያዙ አስገራሚ ነበር። ለአጭር ደቂቃዎች ከድምጽ የፈጠነው የድምጹ ሞገድ የአቶ መለስን አሮጌ ጭንቅላት ደርምሶ እንደገባ የተረዳሁት ስለ ሚሳይል አወነጫጨፍ አንድ የፊዚስክ ምሁር ቀለል አድርጎ ሲያስረዳኝ ነው። በሁለቱ ተቃራኒ ሥጋ ለባሾች መካከል ያለውን ቀጥተኛ መሥመር ድምጹ ተወንጭፎ ሄዶ ዒላማውን እንዲያደባይ አስችሏል። አሮጌው አቶ መለስና ተራማጁ ጋዤጠኛ አበበ ገላው የጨቋኝና የተጨቋኝ መደቦች ምሳሌ ናቸው። ወዲ ባንዳው አቶ መለስ ሺህ ጨቋኞችንና ቅኝ ገዥዎችን ወክለው እስብሰባ አዳራሹ መጥተዋል። አበበ ገላውም ዕልፍ ዓዕላፍ ተመዝባሪዎችን፣ እስረኞችንና የነጻነት አርበኞችን ወክሎ አዳራሹ ገብቷል። የጨቋኙ ወኪል ተዘናግቷል፣ የተጨቋኙ ወገን ግን ንቁ ነበር። መለስ ዜናዊ አምባገበን ነው፣ እስክንድረ ነጋን ጨምሮ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም የግድያ ወንጀል ይቁም፣ የሚለው ድምጽ የጨቋኙን የበሰበሰ ጭንቅላት ጠርምሶ አወላግዶ ቁልቁል ቆለመመው። አቶ መለስና ሕወሃት የበቃላቸው አርብ 10 ግንቦት 2004 ዓም ያችን ዕለት ነበር። ዕለቲቱ የታጋዮችን ሁለገብ ትግል ይበልጥ አፈርጥማ አንዳንዴ አዝጋሚ አንዳንዴ ደግሞ አብዮታዊ በሆነ ስልት እየተመራች ከብዛት ወደ ዓይነት ለውጥ ደረጃ ተሸጋግራ 21 መጋቢት 2010ዓም ሥርዓት ሻረች።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢሬቻው ማን ተጠቀመ? ማንስ ተጎዳ? - አሊጋዝ ይመር

በስባሳው ሕወሃት ወደ መቀሌ ከመፈርጠጡ በፊት በስድስት የጣዕረሞት ዓመታት ተሰቃይቷል። አንዳንዶች አልገባቸውም እንጂ አቶ ስብሃት በስብሰናል እንታደስ” ሲሉ በስብሰናል እንፈርጥጥ” ማለታቸው ነበር። የበሰበሰው ሕወሃት ዶላር ወዳከማቸበት ሃገር መሸሽ ተስኖት – ነገ ተነገ ወድያ – ማጅራቱን ተይዞ ለሕዝባዊው ፍርድ ቅርብ እሆነበት መቀሌ ፈረጠጠ። ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይ፣ ወዘተ፣ እንደ ኮሎኔል መንግስቱ እንኳን ራቅ ማለት ያልቻሉት እግዚአብሄር አሽመድምዷቸው ነው። ቢሸሹም የዕልፍ ዓዕላፍ አርበኞች ድምጽ ይጠብቃቸዋል። ሕወሃቶች እንደ ኮሎኔል መንግሥቱ ሃገር ወዳዶች አልነበሩም። ኮሎኔል መንግሥቱ አምባገነን ቢሆኑም አይሰርቁም። ሕወሃቶች ለየት ያሉ ናቸው። ሕወሃቶች ሃገር ጠል፣ ጨካኝ መዝባሪዎች፣ ዘረ ፈጆች፣ አታላዮች፣ ሴሰኞች፣ ዕዳ አስታቃፊዎች፣ ውሸታሞች፣ ትውልድና ሃገር ገዳዮች ነበሩ።

ሁልጊዜ ለውጥ አለ። ለውጡ ለደጋጎች ውስጣዊ እርካታ ሲጨምር ለክፉዎች ደግሞ ውድቀት ነው። አሁንም አልመሸመ። ቀማኛው ሥርዓት አግዞት ባለሃብት የሆነ መዝባሪ ሁሉ ኃብቱን በሰላም ለሕዝብ ቢያስረክብ ማለፍያ ነው። ደልቶኛል፣ ገንዘብ ሰብስቤአለሁ፣ ሕንጻ ገንብቻለሁ፣ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ መጦርያ አለኝ፣ አሜሪካ እኖራለሁ፣ ብሎ የሚኩራራ ሙሰኛ ሁሉ ነገ በሻሪ ሻሪ ዲያሌክትካዊ ህግ ጭንቅላቱ እንደ መለስ ይቆለመማል። ቢደበቅም ኅሊናው ጎትቶ ያወጣዋል። በሻሪ ሻሪዋ መዶሻ አናቱ እንዳይመታ የሚፈልግ ሁሉ ሊያስተውል ይገባል። የጠፉት ሕንጻዎች ባለቤት የሆናችሁ ሁሉ ብቅ ብላችሁ ለሕዝብ ተናዘዙ። ቀማኛው ሥርዓት ያገዛችሁ ሞኞች ሁሉ አላግባብ የገነባችሁትን ቪላ፣ ሕንጻ፣ ከድሃዪቲ ጉሮሮ ነጥቃችሁ የገዛችሁትን ዘመናዊ ተሽከርካሪ ለሕዝብ አስረክቡ። ዛሬ ላይ ያስገመገመው ለውጥ አስደንግጧችሁ የምትቅበዘበዙ የመንግሥት ሠራተኖችና ጉዳይ አስፈጻሚ ተብዬዎችም አደብ ግዙ። ምን ይፈይዳል በሃገር ሃብትና በሰው ድካም ብላክ ሌብል ውስኪ ቢጠጣ፣ ጮማ ቢቆረጥ፣ ቤት ቢሰራ፣ መኪና ቢነዳበሃቅ የተገኘ ቁራሽ እንጀራ ያጠግባል። ቅሚያና ምዝበራ ያስተማሩት ሕወሃቶች ሞተዋል፤ ይናገራሉ እንጂ በድን ናቸው፣ ይንቀሳቀሳሉ እንጂ አናታቸው ተፈረካክሷል፣ ቪላ ገነቡ እንጂ ቤታቸው ዋሻ ሆኗል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወቅታዊ ጥሪ - በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር አተባባሪ ኮሚቴ

ሁሉም ነገር ይፈሳል (flows)፣ ሁሉም ነገር ይለወጣል (changes)፣ አንዳች የቆመ ወይም የማይንቀሳቀስ ነገር የለም (nothing absolutely stagnant)። ነባራዊ ሁኔታው (objective condition) ወደፊት የሚያንደረድረው ታሪክ ለውጥ (change) ያመጣል። አሮጌው፣ ያረጀው ያፈጀው (archaic) ሥርዓት በሻሪ ሻሪ ህግ (negation of negation) ይሻራል። ለውጡ አንዳንዴ ዝግመታዊ (evolutionary) አንዳንዴ ደግሞ እመርታዊ (leap) በመሆን ከብዛት ይልቅ የዓይነት (from quantity to quality) ለውጥ ያመጣል። አዲሱ ሥርዓትም እያደር እያረጀ ለሌላ አዲስ ሥርዓት ቦታውን ይለቃል።

ሥርዓተ ማህበር ሲበሰበስ ጊዜውን ጠብቆ ለአዲሱ ሥርዓት ቦታውን ይለቃል። ጨቋኝና ተጨቋኝ፣ መዝባሪና ተመዝባሪ፣ ተቃራኒዎች በሥርዓተ ማህበሩ ውስጥ አብረው ይኖራሉ። አብረው የሚኖሩት እየታገሉ ነው። በሁለቱ ተቃራኒ መደቦች መካከል የማያቋርጥ ግጭት አለ። ትግሉ በአሮጌው ሥርዓት ከርሰ መቃብር ላይ አዲስ የኤኮኖሚ ሥርዓት ይወልዳል። አዲሱ ሥርዓት አሮጌውን ሥርዓት ሽሮ ከዓይነት ወደ ጥራት ለውጥ ይሸጋገራል። በሞተው ቀማኛው ሥርዓት ከርሠ መቃብር ላይ አዲስ ዓይነት ሥርዓት ይገነባል እንጂ አሮጌው ሕወሃት ዳግም አያቆጠቁጥም።

ከወያኔኢሕአዴግ ጋር የተደረገው ትግል ሕዝባዊ ትግል እንጂ ግርግርና ማደናገር (confusion) አይደለም። እነ ወዲ ነጋን – የሻሪ ሻሪ ህግ ጊዜውን ጠብቆ ነው የቆለመማቸው። ቢሆንም ፋታ የሠጣቸው አዲሱ ጥገናዊ ” አስተዳደር እንዲርመሰመሱ አድርጎላቸዋል። ይህ የቅራኔዎችን ትክክለኛ አያያዝ (correct handling of contradictions) ዘይቤ የዘነጋው ዳተኛ አመራር በአፋጣኝ ሊስተካከል ይገባል። ቅኝ ገዥዎች ሳይቀር ክፋታችሁ የተጋነነ ነው” ያሏቸው ሕወሃቶች የግፍ ሥራቸው ነው ያሽቀነጠራቸው። ከሞተ ስምንተ ዓመት የሞላው ክፉው ሕወሃት በእርግጥ ውቃቢው አልሞተም። ውቃቢው ዞሮ ተሽከርክሮ የፌደራሊስት ኃይሎች ጥምረት ነን” ባዮቹ አንግት ላይ እንደ ጦስ ጥምቡሳስ ተጥለምልሞ ተቆልሏል። ኢትዮጵያ ከመስከረም ሃያ አምስት በኋላ መንግሥት የላትም” ያለው የሕወሃት ውቃቢ በእርግጥም ፌዘኛ ነው። ኢትዮጵያ እንዲህ ዋዛ፣ ከመንግስትም በላይ ታላቅ ሕዝብ፣ ቆራጥና ጽኑ ሠራዊት፣ አገር ውዳድ አርበኞች አሏት – ለክብሯ የቆሙ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ፍቅረኛሞች በአዲስ አበባ - [አሪፍ የፍቅር ታሪክ)

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃል።

.ከ – 20 መስከረም 2013 ዓም

1 Comment

  1. Meles Zenawi never held a hundred birr note until his father Zenawi Asres handed a hundred birr note to Meles Zenawi few years before Meles’s passing in this new millennium.which shows that Meles Zenawi did not concern himself in painting pictures on the birr note he came up with as the current PM Abiy Ahmed did concern himself in coming up the best display design on the new birr notes.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.