ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማሪያም መታሰቢያ የተዘጋጀች እንጉርጉሮ (ዘ-ጌርሣም)

Mesfinይዞት ተቀበረ
(ዘ-ጌርሣም)

ይዞት ተቀበረ ተራው ደርሰና
ሥጋ ለባሽ ሆኖ ማን ያመልጣልና

ዕውቀቱን
እምነቱን
ፅናቱን
ድፍረቱን
ለትውልድ ኩራትን
እጅ አለመስጠትን
ጉልበቱ ቢዝልም
ድካም ቢሰማውም
በብዕር መትረየስ
አልሞ ሲተኩስ
ሲታገል
ሲያታግል
ሲወድቅ ሲነሳ
ሲጠቁር ሲከሳ
ለግፈኞች በትር
አንዴም ሳይበገር

ይዞት ተቀበረ ተራው ደርሰና
ሥጋ ለባሽ ሆኖ ማን ያመልጣልና

ይኖር ይሆን ከቶ
በእግርሩ ተተክቶ
ትውልዱን ኮትኩቶ
ሐቅን አስረድቶ
እንዲቀጥልበት
በወረሰው ዕውቀት
አለሁ ባለ ሣምንት
ብሎ እሚቆምለት
እሱ እንድሁ አርጓል
ጉዞውን አርቋል
ነፍሱን ይማርልን
በፃድቃን ማረፊያ ነፍሱ ትኑርልን
በማለት እንፀልይ ሌላ አቅም የለነም
ሞትን አሸንፈን መመለስ አንችልም

ይዞት ተቀበረ ተራው ደርሰና
ሥጋ ለባሽ ሆኖ ማን ያመልጣልና

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.