ከእውነት ጋር በመራመድ  ከጠ/ሚኒሥትራችን ነፍሥ ጋር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከቆምን ነጋችን እጅግ ያማረ ይሆናል። – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

abiy 4 አሁን ያለው  የሀገሬ መንግሥት ፣አሻጋሪ መንግሥት ነው። ይህ አሻጋሪ የሆነው “የለውጥ መንግሥት” በህዝባዊ ተቃውሞ ታግዞ  ከ27 ዓመት በፊት የነበረውን  ፣በወያኔ ኢህአዴግ  የሚመራውን  መንግሥት እርካቡን በዘዴ ተቆናጦ መንበሩ ላይ የተቀመጠ።

መንበሩ ላይ የተቀመጠው” አሻጋሪው የለውጥ “ ፣መንግሥትም በእቅድ፣በዘዴ ና ጥበብ በተሞላበት ብልሃት ሀገርን እየመራ ነው።

ይህ እውነት ነው።  የአሻጋሪው መንግሥት መሪ ሀገርን ከጥፋት ያዳነ መንግሥት ነው።የለውጡ መንግሥት  ሀገሬ በባንዳዎችና ሤረኞች እንዳትገነጣጠል ና ጥንታዊ ታሪኳ ከምድረ ገፅ እንዳይደመሠሥ ጥበብ በተሟላበት ዘዴ  ተጠቅሞ የፀረ-ኢትዮጵያ ሴራዎችን ግንባር ቀደም ሆኖ  አክሽፏል።  ይህንን እውነት መካድ አይቻልም።

አሁን ያለው የሀገሬ መንግሥት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር መሆኑን በተግባር ያሥመሠከረ መንግሥት ነው።በመሆኑም ሀገሬ በለውጡ ፣ጥንቃቄ በተሟላበት  ሂደት ና ዛሬ በደረሰበት ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሊመኩ ይገባል። ሀገሬ  የፈጣሪ ፈቃድ ፣ከእርሥ በእርሥ ፍጅት ወይም እልቂት የተረፈችው  ፣ ብሩህ አእምሮ ያለው ፣አሥተዋይ፣አርቆ አሳቢ፣ከፊቱ የተደቀኑ ችግሮቹን ፣በጊዜ፣በቦታ፣በሁኔታ ላይ ተመሥርቶ የሚፈታ ጥበበኛ መሪ ሥላጋጠማት ነው።

በዚህ በጥበበኛ፣አሥተዋይ፣ይቅርባይ እና ተጠንቅቆ ተራመጅ መሪ ዜጎች ሁሉ ሊኮሩ ይገባል። ትሁት፣ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ና ሠርቶ የሚያሠራ መሪ ማግኘት በራሱ የሚያኮራ አይደለም እንዴ?(ሠርቆ መክበር እንደ ፅድቅ በተቆጠረበት 27 ዓመት ሥራዎችን ያለሙሥና እንዴት መሥራት ና በታቀደለት ጊዜ መፈፀም እንደሚቻል ማሣየት አንዱ የለውጥ ማሥተማሪያ መንገድ ነው።)

በበኩሌ ለምን ጥቂቶች በጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር)  ትህትና ራሥን ዝቅ ማድረግ እንደሚበሳጩ እና እንደሚጨረጨሩ አይገባኝም። …ሙሥና በበዛባት ሀገር በአንድ ዓመት ትንሽ ፈቀቅ ባለ ጊዜ ፣በእንጦጦ ተራራ ና ቤተመንግሥት ልዩ፣ፕሮጀክት ፣ያሣዩንን አዲስ አበባን እንደሥሞ “አዲስ አበባ” የማድረግ ሥራ ሊወደሱና ሊሸለሙ ሲገባቸው አለአሥፈላጊ ትችት ከአንዳንድ አለአመዛዛኝ ምሁራን ሲሰነዘርባቸው ያሥገርመኛል።

ገና ተቋማት በወጉ ባልተደራጁበት፣የሰው ያለህ በማለት፣ “ኃቀኛ ሰው በቀን ብርሃን በፋኖሥ በሚፈልጉበት” ና አሻጋጋሪነታቸውን አክብረው ያለእረፍት በቅንነት እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ታማኝ ሆነው፣ሰው እየፈለጉ ከጎናቸው በማሠለፍ፣ጠንካራዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት በብርቱ እየደከሙ ባሉበት በዚህ ፈታኝ በሆነ ፣ ትዕግሥት ገዜ፣ሥፍራ እና ቦታን ተገን አድርጎ መንቀሳቀስ በሚያሥፈልግበት ወቅት  ያለ አመዛዛኝና አሥተዋይ ህሊና አፍ እንዳመጣ አሉታዊ አሥተያየት መሥጠት ተገቢ አይመሥለኝም።

በዚህ አርቆ አሥተዋይ ዜጎች ፣የለውጡን ዓላማ ከግብ  ለማድረሥ፣በሚጣጣሩበት ወቅት፣ በዚህ ከፍተኛ ትእግሥትን በሚጠይቅ፣ የዴሞክራሲ ምህደሩ በመሥፋቱ ፣ የተነሳ ከውጪ  የገባ ና በውሥጥ ያለ ወግ የሌለው ፖለቲከኛ ፣ለፖለቲካ ሥልጣን” በሤራ ፖለቲካ” አማካኝነት  እንዲፈነጭ በተፈቀደበት በዚህ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ብቻ ሥልጣን መያዝ በሚቻልበት፣ግልፅነት በሠፈነበት፣   የለውጥ ወቅት፤ “እእምሮ የጎደላቸው ፣በአንድ ቀን ጀንበር ያለአንዳች ችሎታ፣ በድራማ  “ሜሲን እና ሮናልዶን” ሆኜ ባሎንዶር ካልተሸለምኩ ሞቼ እገኛለሁ።”የሚሉ ሰዎች”እዚህም እዚያም መብዛታቸው እና ለጠ/ሚ ቅንነት፣ረህራሄ ና ፍቅር ለተሞላው ሥራ እውቅናና ምሥጋና ከማቅረብ ይልቅ ፣ከዘረፋችን አሥተጓግለውናል እና በሤራ ከሥልጣን ወርደው እኛ ዘራፊዎቹ ና የሰብአዊ መብት ረጋጮቹ ሥልጣን እንያዝ ማለት በእውነቱ የሤጣንን የጥፋት ና የእልቂት መዝሙር ደጋግሞ እንደመዘመር ይቆጠራል።

የጠ/ሚ  አብይ አህመድ ነፍሥ  የእልቂት እና የጥላቻ መዝሙርን  እጅግ የምትጠየፍ በእውነት መንገድ የምትጓዝ ናት።የዚህ እውነት መገለጫም፣ ከወንድሞቻችን እና ከእህቶቻችን  ከኤርትራውያን ጋር በልባዊ ፍቅራቸው መልሰው በፍቅር እንድንቀራረብ ማድረጋቸው ነው። በዚህ ድርጊታቸውም፣ ፍቅር እንደሚያሸንፍ በተግባር አሳይተዋል።(ሎሬት፣ፀጋዬ ፍቅር በተሞላበት ግጥሙ ፣ኤርትራና ኢትዮጵያ የአንድ ሣንታም ሁለት ገፅታዎች መሆናቸውን ደጋግሞ ማብሰሩንም አንዘንጋ)

ከዚህም በላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለተለያዩ ሀገር አፍራሽ ሤራዎች ሳይበገሩ ፣በጊዜ፣ በሥፍራ እና በሁኔታ እየታገዙ በጥንቃቄ በመራመድ አሻገሪነታቸውን በተግባር  የሥመሰከሩ ከፍተኛ ትዕግሥትና አሥተዋይነትን ገንዘባቸው ያደረጉ የለውጡ መሪ ናቸው።ጠ/ሚነስትሩ ያለጊዜው፣ያለሥፍራው፣ እና የለሁኔታው አሥገዳጅነት  አንዳችም የማረምያና የማሥተካከያ እርምጃ አልወሰዱም። ሀገር በታኝ ፣ቅጥረኛ ና ባንዳዎችን ከህግ በላይ ያለመሆናቸውን ያሣዪዎቸው ፣በጊዜ፣በሥፍራ ና በሁኔታ ላይ ተመሥርተው መሆኑንን ልብ ይሏል።ከአንድ ዓመት በፊት ይህንን እርምጃ ቢወሥዱ ምን እንደሚፈጠር  ማንም አሥተዋይ ሰው ለመገመት አይከብደውም ።(…)

ጎበዝ እንረጋጋ።አፍ እና የውሸት ፕሮፖጋንዳ የመንዛት ችሎታ አለን ብለን የግል ጥቅማችንን በማየት ብቻ የዳቢሎሥ ሥራን አናበረታታ። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በማቋቋም ፣ሥለ ሰዎች መብት መሟገት ሲገባን ወይም በየቢሯችን ሥለድርጊቱ መግለጫ መሥጠት ሲገባን ፣ ልክ እንደ ህጋዊ መንግሥት ፣ያለህግ አግባብ እየዞርን፣ ሰውን ከሰው   ጋር ለማባላት ፣በቋንቋ መከፋፋልን እያወገዝን በቋንቋ እየከፋፋልን ሁከትና ሽብር ለመፍጠር እና ርካሽ ተወዳጅነትን ለማግኘት አንጣር። የቃላት  የተሥፋ ዳቦ በመቸርቸርም  የደሃውን ሆድ በከንቱ አናሥጩህ።

ባለፉት 27 ዓመታት ፣በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች ሙሥና ወይም ሥልጣንን በመጠቀም የሀገርን እና የህዝብ ሀብት እንዲሁም ህዝቡን፣ የመሥረቅ፣የመበዝበዝ ና የማሥበዝበዝ እንዲሁም መሬትን በመቸርቸር የመክበርና በአንድ ቀን ጀምበር ከባለ ሚሊዮኖች ተርታ የመሠለፍ ተግባራትን በመፈፀም፣እኛ እየጠገበን በሽታው የደሃውን ያልበላ አንጀት ማሥጮኻችንን አንዘንጋ!!

ዛሬም የዘረፋ    ሠንሠለታችን ሙሉ ለሙሉ ባለመቆረጡ ይህ   ፀያፍ ተግባራችን ቢቀጥል አያሥገርምም።ለምን ቢሉ “እንሰር ብንል ድፍን አዲስ አባባ ለእሥር ቤትነት አይበቃም ።”የሚለው መልሥ በቂ ነውና!  የሁን እንጂ በጊዜው፣በሥፍራው እና በሁኔታው አመቺነት ሁሉም ሌባ ቅጣቱን እንደሚያገኝ አትጠራጠሩ።ጠ/ሚኒስትሩ ማንም ይሁን ማ ሌባውን፣አጭበርባሪውን፣ሥግብግቡን፣በሰው ደም የሠከረውን ወዘተ።በትክክለኛው ጊዜ፣ሥፍራና ለህዝብ ግልፅ በሆነ ሁኔታ የሥራውን እና የእጁን እንዲያገኝ ያደርጋሉ። ይህንን እያደረጉ እንዳለም በበኩሌ እያሥተዋልኩ ነው።ባለማሥተዋል አፋችን እንዳመጣ የምንናገር ኋላ በውርደት አንገታችንን መድፋታችን አይቀርም።ይህ ቅሌት እንዳይከሰትብን  ከሥድ ንግግራችን እንቆጠብ።

ሥድ ንግግር ምን ይረባል። አንድ የክልል መንግሥት አመራር በሥድነት፣መከላከያን ጭምር እያነሳ በምርቃና ይሁን በሥካር ያለሀፍረት  ሲናገር ሥንሰማ ይህ ግለሰብ፣የአንድ ትልቅ ህዝብ አመራር ዓባል መሆኑ ያናድደናል።የኢትዮጵያ ኩራት የሆነው ያ ታላቅ ህዝብ ግን ቀኑ ሲደርሥ የራሱን ፍርድ እንደሚሰጠው በመዘንጋቱ ግን የዋህነቱ ያሳዝነናል። ሰው ለከርሱ ብሎ ከመሥመር መውጣት አልነበረበትም።ዞሮ፣ዞሮ ሞት ላይቀር በእንዲህ ዓይነት ማሥመሠል መኖርን መምረጥ በራሱ ሞት ነው።

ለገንዘብ እንጂ ለሰው ቅንጣት ፍቅር ከሌላቸው ጋር አብሮ፣ህዝብን በምላሥ እያታለሉ ፣ለእልቂት ማሠናዳት የፋሺስት ተግባር ነው። ይህንን ለመተግበር የቆረጡ፣ጨካኝ ነፍሰ ገዳዮች፣ባንዳዎች፣የፍቅርና የአንድነት ጠላቶች ፣ሥግብግቦች ና አይጠረቄዎች የእጃቸውን የሚያገኙበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን እገምታለሁ።

እነዚህ ራሳቸው ለይቶላቸው፣በኢትዮጵያ መንግሥት ሥር መሆናቸውን ዘንግተው የኢትዮጵያን ኩራት የመከላከያ ሠራዊታችንን ንቀው፣ የኢትዮጵያን ጠ/ሚ መሥደብ የጀመሩ ግለሰቦች ፣በእርግጠኝነት ነገ፣ተነገወዲያ ራሳቸውን እንደሚረግሙ አትጠራጠሩ።

እነዚህ ንዋይ ያሣወራቸው፣ቮድካ ያሳበዳቸው ሰዎች፣ትላንት በብዝበዛ፣በመሬት ወረራ፣በሙሥና የተካኑ ሰዎች ነበሩ። እነሱ ከቶም ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ሊወዳደሩ ይቅርና የጫማቸውን ክር ማሠር አይችሉም።

ጠ/ሚ  አብይ አህመድ እኮ፣ በታላቅ ፖለቲካዊ ጫና ውሥጥ ሆነው፣ በ2 ዓመት በ5 ወር ውሥጥ  ግንባር ቀደም በመሆን   ሠርተው በማሠራት ያሥገኙት ሥኬት ብቻ ለታላቅነታቸው ምሥክር ነው ። ይህንን እውነት እያሥተዋልን እንዴት የሃያ ሰባት ዓመት በዝባዥ እና ከፋፋይ ገዢዎቻችንን ከአገልጋይ መሪያችን ጋር እናወዳድራቸዋለን?

ባለፉት ሃያሰባት ዓመታት   ይህቺ ሀገር  በመንግሥት ሌቦች ብዛት የታወቀችና የሙሥና ጫካ የገነባች ነበረች።ይህንን ጠ/ሚ መለሥ ዜናዊ (ነፍሳቸውን ይማረውና) ተናግረው ነበር።(ሰውዬ አንተ መለሥን ልትሰድበው ትችላለህ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ሥነ ምግባሬ አይፈቅድልኝም።”በኢትዮጵያ የዘረኝነትን ፈንጂ ማነው የቀበረው?” ብትለኝ ግን ህወሃት/ ኢህአዴግ ነው።በማለት እመልሥልሃለሁ።አንድን ሰው ብቻ ተጠያቂ አላደርግም።)

በመጨረሻም በዚህ አሥተማሪ  ግጥምሜ አንባቢዎቼን በክብር እሠናበታለሁ።

 

ይድረሥ ለሀገሬ መንግሥት

ይድረሥ ለሀገሬ መንግሥት

የ2013 መልዕክት
እንኳን አደረሳችሁ
መንግሥት የሆናችሁ።

እናንተም እኛም
በመሀፀን
መንግሥትና ህዝብ አልተባልንም።
ግና…

ሁላችንም፣ራቁታችንን ተወልደን
ራቁቱን በተወለደው ታቅፈን።
ይህንን እውነት እናውቃለን
ሆኖም እንዘነጋዋለን

“ሀሌም የሚሞተው
በሬሣ ሣጥን የተከተተው።”

ነው፣እያልን ለመቅበር እንሰለፋለን
ሁላችንም፣የሞት ሠልፍ መሠለፋችንን…
ፍፁም ዘንግተን…
ተረግዘን እንደተወለድን ረሥተን
የፈጣሪ ረቂቅ ሥራ መሆናችንን ክደን

ከጥቃቅንነት ወደግዙፍነት

ከእሥፐርምና እንቁላል ወደ ፅንሥነት

ከዛም ወደጨቅላነት እንደተቀየርን

በምጥ እንደተወለድን

ወይም፣

ከማህፀን እንደተላቀቅን፣ በኦፕሬሽን።

በማሥተዋል ሥላላወቅን።

ደሞም በዘመነ ጮርቃነት

በህሊና ፍቅር በነገሰበት

በፍፁም የዋህነት ፣ሰውን ሁሉ ወደን

እየዳህን በማንም ታቅፈን።

በማንም ተሥመን።

“እንትፍ!እንትፍ!

እደግ ተመደግ።” ተብለን

ለአዋቂነት እንደበቃን

ፈፅሞ እንረሳለን።

ትላንት፣

ሳናፍር ፣በእርቃናችን

ቀየውን አዳርሰን

“የማነው?የማናት? ድንቡሼ !” ተብለን

እንዲያ ያለሃሳብ ሥንውተረተር

ያለ ሥጋት ሥንዞር

ለእኛ ሁሉ ወዳጃችን ነበር

የሚመሥለን የሚያየን በፍቅር።

ህፃን ነን እና ምን እናውቃለን

ራቁት ነን እና የተደበቀ የሌለን።

ካደግን በኋላ ፣

ከጎለመሥን በኋላ ፣

ተነኳልና ምቀኝነት

እውነትና ውሸት

ጥላቻና ፍቅር

ተራ ነገርና ምሥጢር…

ቀሥ በቀሥ ከትልልቆቹ በመማር።

እንሆ ዛሬ ብዙዎቻችን …

የራሳችንን…

አጥር ገነባን።

ጥቂቶቻችን ደግሞ ፣በነገሩ ቆዝምን

የትላንት ልጅነታችንን ሥላሥረሳን።

ይህ እነሱ እና እኛ

ልክ እንደ ድንገተኛ

በጥፊ እንደሚያጣምም መጋኛ

አጣሞን እንዳንግባባ በሰውኛ

አድርጎን ተሳዳቢ ነውረኛ

የከፋፋይ፣የነጣጣይ ዘረኞች ቅጥረኛ

ሳናሥበው በ27 ዓመት ውትወተው ሥላደረገን

የዘረኛው ከፋፋይ አጥር ዛሬ ሥንነቃ እጅግ አናደደን

ክልል አጥር፣በቋንቋ፣በጎሣ ና በነገድ ሥለለየን።

ይህም ብቻም አይደል

ያመጣብን የቋንቋ አጥር መከለለ።

የትላንት ህፃንነታቸውን የዘነጉ

ዜጋን በቋንቋው ባዳ የሚያደርጉ

ከፈጣሪ መሬት የሚያሳድዱ

አውሬ ሆነው አጋድመው የሚያርዱ

እንዲፈጠሩ በማድረጉ

ሰው ተገፏል ክብሩና ማእረጉ።

ይህንን ሀገራዊ ገዳይ ወረርሺኝ በማየት ፈራን

የትላንት የህፃንነት ፍቅራችንን አሥበንም አለቀሥን።

ዛሬ በሀገሬ

በሠፈር መንደሬ

የትላንት ህፃንነታቸውን የዘነጉት

ሰውነታቸውን የካዱት

ወደ አውሬነት የተቀየሩት

የሚያደርጉትን የጭካኔ ተግባር እያየን

ፉከራቸውን እየሰማን

“ኑ፣እንውረድ

ዘር እና ኃይማኖት …

ቋንቋና ማንነት

እየለየን፣ሰው እንረድ።

መቃብር እስከምንገባ ፤

መቃብር እናሥገባ!

ሆነን የዳቢሎስ ወታደር ፤

እንፍጠር የሬሣ ክምር።

በጥይት ፣ በሜንጫ ና ገጀራ

አሥከሬን እንደርድራ።”

ሲሉ ዛሬም በአውሬነት

ኢትዮጵያን እንዳያጠፏት

እጅግ ፈራን !

ለትውልዱ ሠጋን !

የትም የምንሰማው የቋንቋ ንግሥና

ለሰው ሰውነት ሥለማይሆን ጤና

ትላንት ተመሥክሯልና አውዳሚነቱ

አያሥገርምም ቢነግሥብን ፍርሃቱ።

ዛሬሥ ታይቶ የለ ዘግናኝ ጭፍጨፋው ያለማባራቱ ?

ይህንን እኩይ ድርጊት

ትላንት በፊትአውራሪነት

ከ2010 እሥከ 2012 ዓ/ምህረት

የጭካኔ ተግባራትን ሲፈፅሙና ሲያሥፈፅሙ

ሰውን በቋንቋውና በኃይማኖቱ ሲገድሉ

ንብረትና ሀብቱን ሲያወድሙ…

ነበር ተሸሽጎ ፣ በሰው ደም የታጥበው እጃቸው

ኃጫሉ እንደ እየሱስ በሞቱ ባያጋልጣቸው !

የጥፋት ፊታውራሪዎቹ ብዙ ነበር እቅዳቸው

የኢትዮጵያ ዓምላክ ባያጨናግፍባቸው።

እናም በ2013 ዓ/ም ፣መንግሥት ይንቃ

ሰው የሆነው ዜጋ፣ በቸልተኝነት እንዳያሥጠቃ።

ሥርዓቱንም ይፈትሽ የልዩ ኃይሎችን ምልመላ

ከለላ  እንዳይሆን ጅብ ተመሣጥሮ ሲበላ።

መሥከረም 12/2013 ዓ/ም

(መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ )

 

 

7 Comments

 1. What a very distorted and misleading theoretic ! Are you talking about the country exists in this planet and particularly in Africa in which millions and millions of citizens live with all kinds of brutal and tragic ways of lives or the country you created in your own delusional and illusional world or mind ?
  You have the right to say anything you may believe about the guy ( the prime minister) who is dangerously cynical and hypocritical . But I do not think that we have the right to be advocates and glorifiers of a politician who horribly failed when millions and millions of innocent citizens have been victims of genocide and forced displacements in their own country .

  I am sorry to say but I have to say that it is a very stupid way of political thinking to praise uncritically the politician (the prime minster) who is making the very critical branch of government ( the judiciary ) the very instrument of the dirty or cheap political agenda and practice!

  Yes, it is a political idiocy to preach the people to be captives of the very cynical and misleading rhetoric by a prime minister who has , unfortunately multi -faceted and highly contradictory political personality !

  Believe or not, as we are not talking about Abyi or any other cadre but about a system, there is no way out to a true democratic system without rooting out this critically ill and criminal continuation of EPRDF by simply changing its name to the called Prosperity !

 2. “የጠ/ሚ አብይ አህመድ ነፍሥ የእልቂት እና የጥላቻ መዝሙርን እጅግ የምትጠየፍ በእውነት መንገድ የምትጓዝ ናት።”
  We need more of your likes in this Zehabesha site that has become a platform for hate mongers, twisted minds, and those who do not even know the key priority challenges to sustain the Ethiopian nation. Go..go… brother Mekonen! believe me the tens of millions “silent majority” are with you, it is only that they don’t make noise!

 3. Liji Kedir, nobody with his or her right mind simply hate people because of their personal behaviors and their own way of lives at all!! But it is the right thing to hate and get rid of their dirty and deadly political behaviors and practices that are destroying the very fabrics of the people and make them ( the people) kill each other in order to get their ethnocentric political power of narcissism ! If you are saying that to hate those politicians who have blood of innocent citizens in their hands and try to continue politics as usual is hate monger , so be it ! I do not know what else you hate if you do not hate the very horrible killings of so many innocent Ethiopians ?
  Let me reiterate that if holding a prime minister who keeps preaching not only empty words but also highly misleading preach while innocent people are victims of genocide Is wrong , you desperately need to take deep breath and go back to your very common sense humanity !
  Good luck bro !!!

 4. እንዴ፣ እንዴ፣ … እንዴት ያለች ጽሑፍ ናት በል! ለመሆኑ መቼ ነው የተጻፈችው? ጸሐፊው የት ሆኖ ይሆን የጻፋት? እንኳን አነበብኳት፤ እንኳንም አላመለጠችኝ! ኧረረረ… ለካንሥ እንዲህም ይጻፋልና!
  የጸሐፊውን እጅ ቁርጥማት አይንካው፤ ባለፉት 2.6 ዓመታት ገደማ አፄ ናርሲሰስ ዶር. አቢይ ሀገራቸውን ለማበልጸግ በተለይ ኦሮምያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ፣ አማራ፣ “ፊንፊኔና ዙሪያዋ”፣ ጋምቤላና ሐረሪ በሚባሉ ክልሎች ውሥጥ የሚኖሩ “በረሮዎች”ን ከነምድራዊ ሀብት ንብረታቸውና የእምነት ቅርሣቸው ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከመሠሎቻቸው ጋር ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረት እንኳንሥ በዚህ ጽሑፍ የተገለጸ ሙገሣ ሁለተኛ የኖቤል የሠላም ሽልማትም ሲያንሥ ነው! ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ መሆኑን በግልጽ የሚያሣይ ድንቅ ጽሑፍ። ሣይደግሥ አይጣላም፤ እኔን መሠል ከእውነት የተጣላ እንከፍ ጸሐፊ ተብዬ አዘውትሮ የሚያጠለሸውን የክቡር ወንዑድ ጠ/ሚንስትራችንን ሥም ከፍ አድርጎ የሚሰቅል እንዲህ ያለ ሰው ማግኘት መታደል ነው። …

 5. This narrative by mekonen is very distaseful given the realities in the country. What kind of person would accept the ethnic cleansing as headed by abiy, unless they are participants in the exercise itself. This kind of denial and distortion of reality is the formula the current govt uses to sustain itself so is easy to see mekonen if that is his real name might be a member of this govt or is an individual who is trying to get ahead with the govt over innocent people blood. This is unethiopian, inhuman and selfish to say the least. Mekonen i would ask you to stand in front of the mirror and see what kind of a selfish inhuman person you are. To all others I would like to say i or others have anything personal with abiy or anyone for that matter but our arguments are based on what they stand for and what they represent. We can not accept anyone who believes in ethnic cleansing, inhumanity, lies and misrepresenting the truth, false pretense, denial etc. etc. all these characterize the abiy leadership and that is the brutal truth.

 6. Mekonnen:

  How do you defend the fact that Abiy Ahmed ignored the death of thousands of Amharas in the socalled oromia and benshangul regions? Did he ever admit that there was genocide against Amharas and non-amhara orthodox christians? Did he stand by the side of the victims and try, as a leader, to lift the spirits of these victims?

  How do you defend the imprisonment of Eskinder Nega just to make the wild animals in the name of kero to be happy?

  I respect your stand to supoort of Abiy Ahmed, but for me, this guy is a fake, pretentious person who has a clear anti-
  Amhara and anti-orthodox stand.

 7. INSA did not harm a single Ethiopian person while it was under Dr. Abiy Ahmed. Not one person came forward in social media or charging legally in courts with evidence blaming INSA of commiting a crime . Never backed up by evidence. It is just rumor fake news .

  Not Abebe or any other person ever came forward stating dates and events when INSA silenced or harmed any Ethiopian while Dr. Abiy was leading the agency.
  No proof or evidence was never seen till.this day. So it is just a campaign politically motivated stunt.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.