መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የአምስት አመት ረቂቅ የልማት እቅዱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

3 1 300x200 መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የአምስት አመት ረቂቅ የልማት እቅዱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን መንግስት አገሪቱ ያላትን የመሬት ሃብት መረጃውን በአግባቡ በማደራጀትና ይዞታዎችን በማልማት እና በማስተደደር ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ ጠቀሜታ እንዲያስገኝ ለማስቻል የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ ኮርፓሬሽኑ የእርምጃዎቹ አንድ አካል በመሆን የፈደራል መንግስት መስሪያቤቶች ስልጣንና ኃላፊነት ለማሻሻል በወጣው አዋጅ 1097/2011 ተቋቁሞ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 431/2ዐ11 መሰረት ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ኮርፓሬሽኑ በመላው ሃገሪቱ ያለውን የፌዴራል መሬት ይዞታን ለማልማትና ለማስተዳደር ያመች ዘንድ የመሬት መረጃዎችን ለማሰባሰና የይዞታ ካርታ ስራ ለማከናወን ስራ በፕሮጀክት ደረጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

በትላንት እለት መስከረም 13 2013 ዓ.ም መሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን ረቂቅ የአምስት ዓመት የልማት መሪ እቅዱ ላይ ከተለያዩ የኢኮኖሚ እና አገልግሎት ነክ ስራዎች ላይ ያተኮሩ፤ ከመንግስት የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በረቂቅ የአምስት ዓመት የልማት መሪ እቅዱ ላይ በተደረገው ውይይትም ገንቢ የሆኑ ግብረመልሶች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን ፌደራል መንግስት ይዞታዎቹን ባግባቡ በማልማት ለማህበረሰቡና ለመንግስት የላቀ ጠቀሜታን በዘላቂነት ለማስገኘት እንደሚያግዘዉም ተገልፅዋል፡፡

የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዛሬ የተጀመረውን ውይይት በመቀጠልም አስፈላጊዉን ማሻሻያ በማከል ሀገር አፍ የሆነ ዉይይት በማካሄድ መሪ እቅዱን ወደስራ የሚያስገባዉ ይሆናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽንስልክ ፡

(+251) 991 96 96 96)

2 Comments

  1. ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ ?መንገሰት ዬገጠረ መሬትን ምንይላል ?።1980ወቹ ወዲህ የተወለደዉ ልጅ መሬት ይፈልጋል ፡ መሬት ካለወ የሌለወ ይበልጣል ስለዚ መንገሰት አይተህ ፈረድ የገጠረ ተወላጅ በዬኩል መሬት ተጬቁንዋል ፡ መሬት ለሃብታም ተሰቶ ሃብታም ከተማ ገባ የገጠረ ወጣት የሃብታም ልጅ አሳዳጊ አስተማሪ ሆነ መንገስት ፈጣሪህን ይዘህ ለህሊናህ ፈረድ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.