የብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ አስቂኝ  ጭውውት በOMN – አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

Birhaneብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ የሚባለው ዐይነ ደረቅ አክራሪ ብሔርተኛ “አማርኛ በኢትዮጵያ 29 በመቶ ብቻ ተናጋሪ ሲኖረው ኦሮምኛ ግን 71 በመቶ ነው፡፡” እያለን ነው፡፡ የት ሄዶና መቼ ይህን ጥናት እንዳደረገ አልገለጸም፡፡ ስድስት ሚሊዮኑን ትግሬ፣ ስድስት ሚሊዮኑን ሶማሌ፣ ስንት ሚሊዮኑን ደቡቤ፣ ስንት ሚሊዮኑን ሽናሻ፣ አገው፣ አኙዋክ፣ በርታ፣ ጉሙዝ ወዘተ. ከአማርኛው ይሁን ከኦሮምኛው የቋንቋ ቅርጫት በየትኛው ውስጥ እንደከተታቸውም አልጠቆመም – ፍጹማዊ የኅሊና መታወር ማለት ይቺ ናት እንግዴክ፡፡ በዚህ ሰውዬ ጥናት መሠረት – ይህንን ከእንስሳም የወረደ ስብዕና ሰው ብሎ መጥራት እንኳን ይቸግረኛል በውነቱ –  ከኢትዮጵያ ሕዝብ 71 በመቶው ኦሮሞ ሲሆን 29 በመቶው ደግሞ አማራ ነው፡፡ አዲዮስ ሸዋ! አዲዮስ የለማ አገር ቅምብቢት! አዲዮስ ትላልቅ ከተሞች! አዲዮስ ጎንደር፣ ወሎና ጎጃም! አዲዮስ ፊን… ማናት አዲስ አበባ!

በጣም አስቂኙ የዚህ ጅል ሰውዬ ድርጊት ይህን ነገር መናገር የነበረበትና ያለበት “ብዙ አድማጭ” ባለው ወይም እንዳለው በራሱ ጥናት በደረሰበት በኦሮምኛ ቋንቋ መሆን ሲገባው በአማርኛ መሆኑ ነው – ሊያውም ጥርት ባለች አማርኛ! አማርኛን የሚችለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 29 በመቶ ብቻ ሆኖ ሳለ ለዚያውም በጽንፈኛ ቲቪ እንዴት በአማርኛ እንደሚናገር ራሱ ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ በጥናቱ እውነትነት አልተማመነም ማለት ነው፡፡ ራሱ ያላመነበትን ጥናት ደግሞ እኛን ሊያሳምን መድከም አልነበረበትም፡፡ ከዕውቀት የጸዳ ባዶ ጭንቅላት፡፡

በዘረኝነት መንፈስ ካበዱ አይቀር እንደዚህ ነው፡፡ የምን ትዝብት፣ የምን ይሉኝታ፣ የምን ትምህርትና ዕውቀት፣ የምን ምናምን… ለያዘው ክርክር  ማሸነፊያ መስሎ የታየውንና አፉ ላይ  የመጣለትን ብቻ መዘላበድ ነው፡፡ እነዚህ አክራሪ ኦሮሞዎች ግዴላችሁም አክራሪ ትግሬዎችን ሊያስከነዱና የተፋነውን ሊያስናፍቁንም ነው መሰለኝ፡፡ ይሄው የፈረደበት አማራ “አንዱን ካላዩ አንዱን አይሰዩ” (አያመሰግኑ?) የሚለው “ወደው አይስቁ” ጋር ተዳምሮ በጣም ትክክል ነው፡፡ ለነገሩ ጅል አይሙት እንዲያጫውትም ይባላልና እንደዚያ ነው ነገሩ፡፡

እኔ በመሠረቱና እንደእውነቱም ከሆነ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ 29 በመቶ ሆነ 0.01 በመቶ ጉዳየ አይደለም፡፡ አንድን ቋንቋ ከተናጋሪው ማንነትና ምንነት ጋር በማያያዝ በሥነ ልቦና ደዌ ለማይቸገር ሰው ይህ ነገር ተራ ነው፡፡ አማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ ወይም ኦሮምኛ መገልገያ መሣሪያ እንጂ እንደአክራሪ ብሔርተኞች እምነት በአንድ በዘር ሐረግና በደምም ሆነ በንክኪ በማይወረስ ተራ የመግባቢያ መሣሪያ ይህን ያህል በማያባራ አርማጌዴዖናዊ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቆ ለያዥ ለገራዥ ማስቸገር የበሽታ እንጂ የጤንነት ምልክት አይደለም፡፡ እናም ችግሬ እሱ ሊሆን አይችልም፡፡ በዓለም ያለው ወደ ሰባት ሽህ ገደማ የሚገመተው ቋንቋ ሁሉ የኔ(ም) ነው – ኦሮምኛ ይቅርና፡፡

… ግን ግን ኦኤምኤን ራሱ ለምን በአማርኛ ይናገራል? ለ29 መቶኛ ሕዝብ ለመድረስ ይህን ያህል ለምን ተጨነቀ? ትግራይ ቲቪስ ለምን በአማርኛ ይናገራል? ዋሽንግተን ዲሲ ለምን አማርኛን አምስተኛው ኢፊሴየል ቋንቋ ያደርጋል? ጀርመንና ብዙ ያደጉ የአውሮፓና አሜሪካ ሀገራት ለምን በአማርኛ የከፍተኛ ትምህርት መርሐ ግብሮችን ይሰጣሉ? ሰሞኑን ደግሞ ቻይና ለምን አማርኛን በዲግሪ ደረጃ እንዲሰጥ ወሰነች? ወያኔዎችና ቱባ ቱባ የኦህዲድ ባለሥልጣኖች ለምን ልጆቻቸውን በአማርኛ ያሰለጥኗቸዋል? አሰለጥ የዘር ፖለቲከኞች ለራሳቸው የሚመርጡትን ነገር እንወክለዋለን ለሚሉት ወገን ለምን ይከለክላሉ? እነጃዋር አማርኛን ምናልባትም አማራ ከሚባለው በበለጠ ለምን ይራቀቁበታል? እነፀጋየና ሕዝቅኤል ለምን በሚጠሉት ቋንቋ በአማርኛ ይናገራሉ? የፌዴራል መንግሥት፣ ስብሰባዎችን በኦሮምኛ ወይም በእንግሊዝኛ ለምን አያደርግም? ፌዴራሊስት ተብዬዎቹ ለስብሰባም ሆነ ለሆነ ጉዳይ ሲገናኙ ለምን አማርኛን መርጠው ይጠቀማሉ? የየጁው ራስ አሊ፣ ትግሬው አፄ ዮሐንስ፣ አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ምኒልክ፣ አፄ ኃይለ ሥላሤ፣ ኮ/ል መንግሥቱ፣ አፄ መለስ ዜናዊ … ሌሎችም ቀደምትና የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ገዢዎች አማርኛን የተገለገሉት የአማራ ሕዝብ እግራቸው ሥር ተደፍቶ “እባካችሁን ይህን ጉሮሮ የማይቧጥጥ፣ ድድ የማያሳብጥ፣ ከንፈር የማይጎረብጥ፣ ለጽሑፍና ለታሪክ ድርሳን የሚመች አማርኛ ቋንቋየን ተጠቀሙ!” ብሎ ለምኗቸው ይሆን?  ማን ያውቃል! እንደአሁኑ የአክራሪ ኦሮሞዎች መቅነዝነቀዝ ከሆነ በርግጥም ያስብላል – እባካችሁን እነዚህ ቂሎች ስለቋንቋና ማኅበረሰብ ምንነትና ዘፈቀዳዊ ግንኙነት እንዲያነቡ ምከሯቸው፡፡

ተቃራኒውን ልንገራችሁ ይልቁንስ፡- አማራነት በውድም በግድም የተለጠፈበትና ይህን ከኢትዮጵያዊነት ማዕረግ የወረደ ልጠፋ አምኖበትም ሆነ ሳያምንበት የተቀበለው ሕዝብ በጉልበቱ ተንበርክኮ “አማርኛ የሥራም ሆነ የጋራ ቋንቋ እንዳይሆንብን መንግሥት ዐዋጅ ያውጣልንና እኛንም ያሳርፈን” ብሎ ቢለምን አይሣካለትም፡፡ ምክንያቱም ተወደደም ተጠላ አማርኛ የ86 ነገዶች የጋራ መግባቢያ የሆነው በዐዋጅና በጦርነት ሳይሆን ለበርካታ ምዕተ ዓመታት በተደረገ የርስ በርስ መስተጋብርና ማኅበረሰብኣዊ ስምምነት ነው፡፡ ዛሬ ተነስተህ፣ “ሁሉም በጄ፣ ሁሉም በደጄ” ብለህ ወጧ እንዳማረላት ሴት ከአውሮፓ አሜሪካ እያሽቃነጥክ “የኔ ቋንቋ አገሩን ይግዛ” ብትልና በጠበንጃና በቀስት ሕዝብ ብታስፈጅ ያገኘኸውን ዕድል አበለሻሽተህ የታሪክ ተወቃሽ ትሆናለህ እንጂ እውነቱን ልንገርህ ምንም አታመጣም፡፡

ኧረ ግን ብርሃነ መስቀል አበበ ራሱ ስሙን ለምን አይቀይርምና “ፈይሣ ጉርሜሣ ሰኚ” አይባልም? ትግልን መጀመር የሚያምረው ከራስ ነዋ! ማን በዚህ ስም እንዲጠራ አስገደደው? … እነፀጋዬ ገ/መድኅን ዋቀዮ፣ እነፊታውራሪ ኃ/ጊዮርጊስ ዲነግዴ፣ እነጄኔ. ደምሴ ቡልቶ፣ እነጄኔ. ጃጋማ ኬሎ፣ እነጄኔ. ታዬ ባልኬር፣ እነሽመልስ ማነው እነአብዲሣ አጋ፣ እነበዓሉ ግርማ፣ እነጥላሁን ገሠሠ፣ እነጄኔ. መርዳሣ ሌሊሣ፣ እነለማ ጉያ፣ እነለማ ጉተማ፣ እነደበላ ዲንሣ፣ ስንቶቹን ጠርቼ (አማሮች ግን እነማናቸው በል? የትስ አሉ በሀገራችን ታሪክ? እ? ) … እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ወገኖቻቸው ጋር ለዘመናት የገነቧትን ሀገር፣ ወፍ ዘራሾች ድንገት ተነስተው በ30 እና በ40 ዓመታት ውስጥ ያፈርሷታል ማለት ዘበት ነው፡፡ ሙከራው ግን ብዙ ጠባሳ አያሳድርም ማለት እንዳልሆነ በግልጽ እያየን ነው፡፡ ለማንኛውም “አባት ሳለ አጊጥ ጀምበር ሳለ ሩጥ” ነውና እነውድ አክራሪዎች ሆይ፣ አሁን አራት ኪሎ የተገሸረው ሰውዬ ሳያመልችጣሁ ቶሎ ቶሎ ሩጡ! በርቱ!!

5 Comments

 1. ወይ አምባቸው ጥናት አድርግ ብለህ ለምን ታስቸግረዋለህ እነማን አጥንተው ነው? የሚያጠኑላቸው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገ/አብ ናቸው የትምህርት ደረጃውን ዘንግቼ እንዳይመስልህ። እንደው ሳቅ ሲያምረኝ አቻምየለህና ቴዎድሮስ ጸጋዬ ስለ አንዳርጋቸው መጽሀፍ ያደረጉትን ውይይት እሰማለሁ አሁንማ ቃል በቃል ሳልይዘው አልቀርም።
  እንደ አበበ ሳኒ አንዳርጋቸው ጽጌ በአድዋ ጦርነት እስላሞችን እየለዩ አይቀብሩም ብሎ የምንሊክን ስራዊትና ንጉሰ ነገስቱን ይከስሳል።
  ነገሩ ያገኘው ሬይመንድ ከተባለ እንግሊዛዊ ከጻፈው መጻፍ ነው ሰውየው በስለላ ስራ ተይዜ የተባረረ ነበር። ይህን መጻፍ ያንብብ አያንብብ እንደተጠበቀ ሁኖ ሬይመንድ መረጃውን አገኘሁ የሚለው ከሌላ ጸሀፊ ነበር ያ ጸሀፉ አደዋ የደረሰው ከጦርነቱ ከአምስት ወር በሁዋላ ነው። እግዚአብሄር ያሳይህ ነብስህ ሳይወጣ አሞራና ጅብ ይቀራመትሀል 5 ወር እንኳንስ የሰራዊቱ ሀይማኖቱና ነገዱ ሊለይ ቀርቶ የሰው አጽሙም ከተገኘ እድል ነው።

  ሲፈርድበት አጼ ምንሊክ ቡኒ ከተባለው አያቴ 20000 ላም ወስደውበታል ማለት መቼም አቻም የለህ ታምሩ ሰው ሲዋሽ አይወድም መናፍስት ጠርቶ ሳያናግርም አይቀርም። ከአንዳርጋቸው እስከ ቡኒ ያለውን ትውልድ በ25 አመት ብቻ አባዝቶ ቡኒ የኖረው የአጼ ምንሊክ አያት ሳይወለዱ ሁኔ ተገኘ። ቅሌት ይሉሀል እንዲህ ነው ስለ መጽሀፉ ገለጻ ስጥ አቻምየለህ ጋር ተብሎ ቢጠየቅ በጠራራ ጸሀይ ያለ ፍርድ ረሽኑኝ እንጅ ቴዎድሮስና አቻምየለህ ፊት አልቀርብም አለ እነሱም አፍረው ተውት።

  ለነገሩ ዶር ብርሀኑም ልደቱ አያሌው ጋር ቀርበህ በተለያዩ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ምልከታህን ስጥ ቢባል እጅና እግሬ ታስሮ ወደ ገደል ብጣል ይሻለኛል ብሎ እምቢ አለ። አበበ ታድያ ምን በወጣው ጥናት ያድርግ ባዶ የሆነ የቄሮ ትውልድ አለለት የፈለገውን መበጥረቅ ህገመንግስቱ የሰጠው መብቱ ነው ላለመዋሸት የሚይዘውም የሞራል ልጓም የለውም። ባለፈው ህዝቅኤል ሲናገር ኦሮሞ ከውሀ ነው የወጣው ዋቆ ጉራቻ ዞር ብሎ ሲያየው ሴት ፈጠረለት አለ እንግዲህ ያልኩላህ ሁሉ ሚዲያው ላይ ታገኘዋለህ። እኛ ብንለው አንድ ከተማ ያወድሙ ነበር። ዝም ብሎ መሳቅ ነው ምን ይደረጋል።

 2. አምባቸው ብዙ የምታውቅ ሰው እነዚህን ሰዎች ለምን ታስቸግራቸዋለህ ጥናት አድርጉ ብለህ። አስመሮም ለገሰና ተስፋዬ ገ/አብ ያጠኑላቸዋል እነሰም ሳያላምጡ ይውጡታል ቀጥሎም ወደ ተከታዮቻቸው ይልኩታል። የጥናትን ነገር ካነሳህ አንዳርጋቸው ጽጌ አህያ የማይችለው መጽሀፍ ጽፎ በዚህ ልክ የተጻፈ የታሪክ መጻፍ የለም ብሎ ማስመረቅ(እኛም እንናገር ታሪክ አይደናገር መሰለኝ)። መጽሀፉ ላይ የተጠቀሱት ተረቶች አንድም እውነትነት ስለታጣባቸው ቴዎድሮስ ጸጋዬ በልመናም በልምምጥም በማባበልም ለማብራራት ቢጠይቀው አሻፈረኝ አለ ስራውን ስለሚያውቅ።
  ቢቸግረው አቻምየለህ ታምሩን እባክህ ይህን ጉዳይ እንደሚሆን አድርገው ይለዋል መቼም ጉድ ነው በጽሁፍ ተጽፎ አያልቅም። እኝህ መከረኛ ምንሊክ ቡኒ ከተባለው ከአንዳርጋቸው አያት 20000 ከብት እንደወሰዱባቸው በተረቱ ተካቶ ስለነበር አቻምየለህ ጉዳዩን ሲፈለፍለው ከቡኒ ዘመን እስከ አጼ ምንሊክ በ25 አመት ብቻ አባዝቶ ቡኒ የተወለደው በአጼ ምንሊክ አያት ዘመን ሁኖ ቁጭ አለ እግዜር ያሳይህ በ25 አመት ብቻ አባዝቶ ነው። ቡኒ 20000 ከብት አለው ወይ የሚለውን ይሁን ብለህ ውሰደው። የምንሊክ አያት ሳይወለዱ በምን ሂሳብ አጼ ምንሊክ የቡኒን ከብት ይዘርፋሉ? ይሄ ማለት በንጽጽር ወደፊት የሚወለደው ያንተ የልጅ ልጅ ልጅ አሁን ያለውን የአንዳርጋቸውን መኪና ወይም ላፕቶፕ መስረቅ ማለት ነው።

  ይቀጥልና በአድዋ ጦርነት እስላሞች እንዳይቀበሩ ትእዛዝ ተሰጥቶ ነበር ይላል ጉዳዩን ከየት አገኘው ሬይመንድ ከተባለ በስለላ ስራ ከተባረረ እንግሊዛዊ። ሬይመንድ ይህን ጉዳይ ከየት አገኘው ከአድዋ ጦርነት ከ5 ወር በሁዋላ ወደቦታው ከተጓዘ ተጓዥ ።አሁንም እግዚሀር ያሳይህ ነብስህ ሳትወጣ ጥንብ አንሳና አውሬ በሚቀራመትህ አገር ከ5 ወር በሁዋላ የጠመጠም እስላም ተንጋሎ ሲጠብቀው ለዛውስ ቄስ መሆኑንስ ፈረንጁ በምን ለየው ባንዳ ኤርትራዊ ቢሆንስ ግራ የገባ ነገር። የአእምሮው ደረጃ ልኩ ይሄ ስለሆነ ሌላው ሊመረምር ይችላል ብሎ ባለመገቱም ቴዎድሮስ ጸጋዩና አቻምየለህ ሰይፍ ላይ ወደቀ እልሀለሁ። ይህች በጥቂቱ ተቀንጭባ ነው ሳቅ ሲያምርህ እየሄድክ ማዳመጥ ነው። እኛን አንጫጫን ብለው እነሱው ተንጫጩ። ብርሀነ መስቀልም ደቀ መዝሙሩ እንደ መምህሩ እንዲሉ ባስተሳሰብ የተጎዱ ስለሆነ የተጎዳ አስተሳሰባቸውን ነው የሚለቁት ልልህ ነው። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ።ማንም ህይወት የበደለችው ሁሉ ተፍጨርጭሮ ሰው መሆን ይልቻለ መተዳደሪይውን ቸነፈር መቸርቸር አድርጎታል። ምናለ ታክሲ ሰርተው ወይ ጠርገው ወይ ለምነው ቢኖሩ የአምላክ ፍጡርን ከሚያምሱ?

  • ሠመረ ጥሩ ብለሃል። ዘመኑ የነማሞ ቂሎ በመሆኑ ጊዜያቸውን እሥኪጨርሱ እንዲሁ ከመንጨርጨር በዘለለ ምንም ማድረግ አልቻልንም። በውነቱ ከዚህ ዓይነቱ ፍጡር ጋር በአብድ ሀገር መኖር ይቅርና እንደሰው አብሮ መቆጠር ራሱ ምርጫ ማጣት እንጂ ይነድማል፤ እጅግም ያበሣጫል።
   በነገራችን ላይ ዶር. አሰፋ ነጋሽ የተባለ ወዳጄ አንድ ዕርማት በውሥጥ መስመር ሰጥቶኛል። እሱም የፀጋየ ገ/መድኅን አያት እኔ ያልኩት ዋቀዮ ሣይሆን ቀዌሣ መሆኑን የጠቆመኝ ነው፤ ወዳጄን በዚህ አጋጣሚ ማመሥገን እፈልጋለሁ።

   • በ”አብድ” የሚለው በ”አንድ” ለማለት ነው፤ እብድ ከሚለው ጋር ሊያምታታ ስለሚችል ነው ይህን መለያ አስተያየት መሥጠት የወደድኩት፤ ለነገሩ ልፋ ቢለኝ እንጂ ያው ነው – አገራችን ካበደች ቆይታለችም አይደል?
    በነገራችን ላይ ዛሬ ያረፈችውን የታዋቂዋን ከያኒ አልማዝ ኃይሌን ነፍሥ ይማር። አርቲስቶቻችንና ታዋቂ ዜጎቻችን ተተኪ ሣያገኙ እያለቁብን ነው።

 3. አምባቸው ምን ያላደረጉን አለ ብለህ ነው ጨርቃችንን ጥለን ያለመሄዳችን እኛ ሁነን ነው ዶር አሰፋ ለኢትዮጵያ ባለውለታ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው እድሜና መልካም ጤንነት ይስጠው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.