ማስጠንቀቂያ ለኦርቶዶክስውያን እውነት ጀዋር ነው በቤተክርስቲያን መሪዎች ግድያ ያቀደ? – ሰርፀ ደስታ

relgionየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና ምዕመኖቿ በአሁኑ ጊዜ በዋናነት በመንግስት መዋቅር በሚታገዙ አካላት ጥቃት እየደረሰ እንደሆነ እያየን ነው፡፡  የዚህ መሠረታዊ ምክነያት ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱና ተከታዮቿ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እስከዛሬ መቀጠል ዋነኛ ተዋናዮችና ቁልፍ መሆናቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኦርቶዶክስን ማጥፋት ግድ እንደሆነ ስለሚታመን ሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና ተከታዮቿ ላይ ቢያነጣጥሩ ለምን አይባልም፡፡  ጣሊያን አገራችንን በወረረና ሁለት ጊዜ አየቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ የተባረረው በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምክነያት እንጂ በተራ ጦርነት እንዳልሆነ በደንብ ስለተረዳ አማራና ኦርቶዶክስ ካልጠፉ ኢትዮጵያን በጦርነት ማሸነፍ እንደማይቻል በግልጽ ተናግሮ ነበር፡፡ ይሄን የጣሊያንን ምክር እንደወረደ ነው የባንዳ ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን፣ ተከታዮቿና በልዩ ሁኔታ ደግሞ አማራ ወይም የአማራ ወዳጆችን ላይ ከፍተኛ ዘመቻ የከፈቱት፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን አቅም ከኢትዮጵያም በላይ ብዙ ሌሎች የዓለምን ሕዝብ ሳይቅር  ተጽኖ እንደሚያሳድር ብዙዎች ያውቃሉ፡፡ ከዚህች ደሀና አፍሪካዊት አገር እንዲህ ያለ ተጽኖ የሚያሳድር የእምነትና የፍልስፍና አቅም መኖሩ የሚያበሳጫቸው ብዙዎች እንዳሉ ሆኖ ግን ኢትዮጵያን በጠላትነት ለሚያይዋት ቤተክርስቲያኒቱ ከምንም በላይ አደጋቸው እንደሆነች ያውቃሉ፡፡  የዚህች ቤተክርስቲያን መታወቅም ከኢትዮጵያ መታወቅ ጋር አንድ ናቸውና፡፡ በዚህች ቤተክርስቲያን በኩል የሚነሰው የኢትዮጵያ ሥም እንደምንታወቅበት ረሀብና፣ ድህነት ሳይሆን የክርስትናው እምነት ሚስጢር መከማቻ የሆነቸውን አገር ነው፡፡ ከአንድ አፍሪካዊት ደሀ አገር ዓለም የክርስትናውን ታሪክ ማመሳከሪያ ለማግኘት መረጃዎች በዚህች ቤተክርስቲያን እንዳሉ ያውቃል፡፡ ክርስትናው ብቻም ሳይሆን የኦሪታዊው አሁድ እምነት ያላቸውም አዚህችው ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ታሪካቸው እንዳለ ያውቃሉ፡፡ ሆኖም ከእነሱም ቢሆን ታሪኩ የኢትዮጵያ መሆኑ የሚያበሳጫቸው ይኖራሉ፡፡ ለዚህም ታሪኩን የራሳቸው ቢሆን ስለሚፈልጉ ቤተክርስቲያኒቱና የምትጠራባት አገር ኢትዮጵያ ባለቤት ስለሆኑ ቤተክርስቲያኒቱ ከጠፋች ባለቤት የመሆን እድል ይኖራቸው ይሆናል፡፡ ይህ በትውልድ ብዛት ሊደረግ የሚችል ነው፡፡

በሌላ መልኩ የእስልምናው ዓለም በዛ አፍሪካ ቀንድ አካበባ ትልቋና በራሷ መሬት ላይ ያለችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አካባቢው ሁሉ ወደ እስልምና ለመቀየር የሚያሰቡትን ሐሳብ ከጥንት ጀምሮ ገድቦ ይዞባቸዋል፡፡  የዚህች ቤተክርስቲያን አስተምህሮትና ፍልስፍና ለኢትዮጵያ ክርስቲያን መሪዎች መርሀቸው ስለነበረ ማንንም በማስተማርና በማሳመን ከአልሆነ በቀር እምነት እንዲቀይር አያስገድዱም፡፡ ወደምድራቸው የመጣ የትኛውንም እምነት የሚከተል ሰብዓዊ ፍጡር በስላሴ አርዓያ የተፈጠረ ብለው ስለሚያምኑ በእምነቱ ምክነያት አይሳደድም፡፡ ይልቁንም ቦታ ሰጥተው እንደ እንግድነቱ ያኖሩታል እንጂ፡፡ ይህ ነበር የእስልምና ቀዳማይ ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው በመጡ ወቅት ንጉሱ በእምነታቸው ምክነያት ሳይጠየፋቸው ቦታ ሰጥቶ ያስተናገዳቸው፡፡  በዚህ ሁሉ ታሪክ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሁሉ ኢትዮጵያን እንዲያከብሩ በነብያቸው ሳይቀር ቢታዘዙም እንኳን የሌሎቹ የራሷ የኢትዮጵያ እስልምና ተከታዮችም ብዙዎች ለኢትዮጵያ ያላቸው ጥላቻ ቀላል የሚባል አደለም፡፡ አለመታደል ሆኖ እንጂ ኢትዮጵያዊው አስላምን ሊያኮራው የሚገባው ኢትዮጵያዊ በመሆኑ እንጂ አረባዊነት ባልሆነ ነበር፡፡ ምን ዓልባትም እንደክርስትናው ሁሉ በእስልምናውም የኢትዮጵያን ፍልስፍና ለዓለም እስልምና ተከታዮች ሁሉ ማድረስና በዓለም የእስልምና መድረኮችም ከሌሎቹ በላይ በእምነቱ የተከበረ በሆነ፡፡ ይህ አልሆነም፡፡ ኢትዮጵያ በክርስቲያን መሪዎች ስትመራ በመቆየቷ ይሄው እስከዛሬም የእስልምናው እምነት በኢትዮጵያ ትልቅ ቦታ ኖሮት ይኖራል፡፡ በተቃራኒው ግን ኢትዮጵያ በታሪክ በእስልምና እምነት ተከታዮች ስትመራ ብትኖር እንድም ክርስቲያን በዚህች ምድር እንደማይኖር ግልጽ ነበር፡፡ በእስልምናው አጋጣሚውን ያገኙ ሁሉ የመጀመሪያ ኢላማው ይህች ቤተክርስቲያን ነችና፡፡ የጥቅምቱም የሰኔውም ክርስቲያኖችን ማጥቃት የዚሁ አንዱ መገለጫ ነው፡፡

ከሁሉ በከፋ ደግሞ በአብዛኛው ቢያንስ ወላጆቻቸው ከዚህችው ቤተክርስቲያን የነበሩ ዛሬ እነሱና ዘራቸው ሁሉ ከዚህች ቤተክርስቲያን ወጥተው የፕሮቲስታነት እምነት ተከታዮች የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክ እብድ ያደርጋቸዋል፡፡ ከየትኛውም እምነት በላይ የጴንጤ እምነት ተከታዮች ይችን ቤተክርስቲያን ለማጥፋት ትልቅ ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለው ቡድን በሕቡዕም በይፋም በዚህች ቤተክርስቲያን ላይ መንግስታዊ መዋቅሩን በመጠቀም ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ ይገኛል፡፡  ሆኔታዎችን ሁሉ ቤተክርስቲያቱና ተከታዮቿ በሚጠቁበት መልኩ እያመቻቸ እናየዋለን፡፡

ሰሞኑን ጀዋር መሐመድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቃነ ጳጳሳትና የቤተክርስቲያን መሪዎች ላይ ግድያ ዓቅዶ ነበር የሚል ክስ እየሰማን ነው፡፡ ይህ ክስ ከምንም በላይ እውነትነቱ መረጋገጥ ያለበትና እንደተባለውም ግለሰቡ ይሄን አቅዶ ከሆነ እንዴትና በማን በኩል እንዳቀደው መጣራት አለበት፡፡ ብዙዎች ከሳሽ የሆኑት የሚሉት ተቀብለው ሌላውን ነገር  እየዘነጉት ያለ ይመስላል፡፡ በመጀመሪያ እካሁን የነበሩትን የአረመኔያዊ ድርጊቶች በጀዋርና ቄሮ በተባሉ አረመኔ ቡድን በኩል በሕዝብ ላይ እልቂት እየፈጸመ ያለው እራሱ ሥልጣን ላይ ያለው የጴንጤ ብልጽግና ቡድን እንደሆነ ሁሉም ሊረዳው ይገባል፡፡ ጀዋር መሐመድም ሆነ ቄሮ የተባለው ቡድን የጴንጤ ብልጽግናው ቡድን መሳሪያ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ዛሬ ላይ በእነሱ ሥልጣን የመጣ ስለመሰላቸው እንጂ፡፡ ሽመልሽ አብዲሳ ይሄን በደንብ ተናግሮታል ወዲያው እንዘነጋለን እንጂ፡፡  እንግዲህ የጳጳሳቱና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ግድያ እንደተባለው ታቅዶ ከሆነ ይህች አሳብ ቀድሞ ከማን መነጨች የሚለው መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆኑ ያሉት የሽብር ጥቃቶች ዋና ሐሳብ አመንጭ በስልጣን ላይ ያለው የጴንጤው ብልጽግና ቡድን ወይስ እነቄሮና ጀዋር የሚለው አሁን ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ ጀዋርንና ቄሮን እየተጠቀመ ያለው ማን ነው? ጀዋር በአገሪቱ ሁሉ እየተዘዋወረ ሽብር እንዲፈጥር የመንግሰትን ሐብት መድቦ ሲያንቀሳቅሰው የነበረው ማን ነው? አንዘናጋ! ሲጀምር ጀዋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት መሪዎች ላይ የተባለውን አይነት ወንጀል ለመፈጸም በጣም ሩቅ ነው፡፡ የሐሳቡ አቅራቢዎችና የነገሮች አመቻቾች ጀዋርና ቄሮ ሳይሆኑ የጴንጤ -ኦሮሞ ብልጽግና ሴረኞች እንደሆኑ አለማሰብ ስህተት ይመስለኛል፡፡  ምን ዓልባትም ይህችን እነሱ ያሰቧትን ሐሳብ ዛሬ በስልጣናቸው ስለመጣ ጀዋር ላይ ለጥፈውበት እንደሆነ አስባለሁ፡፡ እንዲህ ያለውን ድራማ የጴንጤው(ኦሮሞ) ብልጽግና ቡድን ከአሳዳጊው ወያኔ በደንብ ወርሷልና፡፡ በዚህ ጎዳይ ኦርቶዶክሳውያን መወናበድ እንዳይኖርባቸው አሳስባለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አደገኛው ጠላት የጴንጤ ብልጽግናው ቡድን እንደሆነ ሁሉም ልብ ሊል ይገባል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ሊለው የሚገባ ጉዳይ የጴንጤ-ኦሮሞ ብልጽግና ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቀን ከሌሊት እየሰራና ዛሬ አማራና ኦርቶዶክስ ላይ ቢሆንም ቀጥሎ ኦሮሞና ጴንጤ ያልሀነን ሁሉ ለማጥፋት እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ይህ እውነት የእስልምና ተከታዮችም ይመለከታል፡፡ በኦሮሞነት ብዙዎች ከነበረ እምነታቸው በተቃራኒ ዛሬ የኢሬቻ አምላኪ እንደሆኑ አስተውሉ፡፡ የጴንጤ-ኦሮሞው ቡድን እምነት ክርስትና ሳይሆን እምነት አልባ የሆነ እንደፈለገው የሚዘውረው ኦሮሞነትን በአገሪቱ ማስፈን ነው፡፡ የክርስትናውም የእስልምናውም እምነት የኢሬቻን አምልኮ እንደማይቀበል እሙን ነው፡፡ ሆኖም በኦሮሞነት ዛሬ ኢሬቻ ከሌላው እምነት ሁሉ ልዮ ቦታ ተሰጥቶት እናያለን፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለዘመናት የነበሩ የጥምቀትና የመስቀል ቦታዎቿን እየተነጠቀች ነው፡፡  የእስልምናው እምነት እስከዛሬም ዓመታዊ ባዕላቶችን መውሊዲን የመሳሰሉ የሚያከብርበት ሥፍራ የለውም፡፡ የኦሮሞ-ኢሬቻ፣ የኦሮሞ-ጴንጤ ቡድን ሥልጣን ስለያዘ በመሐል አዲስ አበባ ቦታ ተሰጥቶት እናያለን፡፡ በአዲስ አበባና አካባቢዋ እንኳን ኢሬቻ ኦሮሞ ታሪክ የለውም፡፡ ሸዋ የእነ አቡነ ተክለ ሀይማኖት ዘሮች እንጂ ኦሮሞ የሚባል ዘር በደሙ የለም፡፡ ሲጀምር ኦሮሞ የሚባል ነገር ከአለ፡፡

ሁሉም እንዲያስተውለው የሚፈለገው በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን፡፡ ኢሬቻ በቀጥታ የሰይጣን አምልኮ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ እንደቀልድ ለመመሳስ በሚል እየተሳተፋችሁ በራሳችሁና በቤታችሁ አደጋ እያመጣችሁ እንደሆን ልብ በሉ፡፡ ኢሬቻ መከበር እየገዘፈ በመጣ ቁጥር ምን እየሆነ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ከዚህ አምልኮ ራሳችሁን አውጡ፡፡ የእስልምናውም እምነት ተከታዮች ያለእምነታችሁ በኦሮሞነት የኢሬቻ አክባሪ መሆናችሁን አስቡበት፡፡ ይህ አገርንና ትውልድን የሚጎዳ የክፉ አምልኮ እንደሆነ በይፋ አውቁ፡፡ የጴንጤ-ኦሮሞው ቡድን ዋና ሥራው ይሄን አምልኮት በኢትዮጵያ ምድር ትልቅ ቦታ እንዲኖረው ነው፡፡ ጴንጤ-ኦሮሞ በአብዛኛው ዛሬም ባይሆን በሂደት የሄን እምነት እንደሚቀላቀል ታዘቡ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

3 Comments

 1. ነገሩ በሚገባ ንው የገባህ!
  ይሄው የኦንግ ነጭ ለባሽ፣ የጲንጤ ሃይማኖት ተከታይ ፕ/ሚር ከደንቆርነቱ የተንሳ እያደረገ ያለው የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ከሃይማኖት ጋር ሳይሆን የሚያየው የአትዮጵያ ባህል አድረጎ ነው፡፡ መድፈር አይሁንብኝም እንጂ ከሪቻጋርም እኩል የሚያየው ነው የሚመስለኝ በሚይሳያየን ድንታ የለችነት፡፡
  ለዛም ነው ክጅጅጋ ቢተክርስቲያን መቃጠል ጀምሮ እስከአሁን ለሁለት ዓመት ቢተክርስቲያናችን ሲጋይ፣ ቀሳውስቶች ሲታረዱ እሱ ቁጭ ብሎ ችግኝ ነው የሚተክለው፡፡ ጭርሽ በቅርቡ የሰጠው ኢንተርሺው ለአዲስ ዓመት ቢተክርስቲያናችንን ይወቅስ ነበር፡፡ ሰውየው ኢትዮጵያን ቁጭ ብሎ በላጵስ ማጥፋቱን ነው የተያያዘው፡፡ አሁን ደግሞ አስተዳደሩ የበለጠ ቤትክርስቲያናችንን የማጥፍት ዘመቻቸውን በግላጭ ለማድረግ ክዚህ ከጫታም ጃዋር ጋር ያስተሳስርሉ።
  የጥንቆላ ሃይማኖት ለመጀመርያ ጊ ዜ ንው በዘመናችን በእውቅና ሲከበር ያየነው፡፡ We need to get rid off this guy. He’s no good, I don’t know how the majority people feel, but this guy is destroying Ethiopia.. We need to vote and throw this sb out.
  .

  • ከ ኦርቶዶክሳዉያን የበለጠ ባእድ አምልኮ አምላኪ አለ አንዴ ኢትዮጲያ ዉስጥ፧ የተጠረበ እንጨት የሚያመልኩ፥ ኢሬቻ አምላኪ ደግሞ በሂወት ያለ ዛፍ ያመልካል፥ ሁለታችሁም አንድ – THE WALKING DEAD ናችሁ::

   • ምን ሃይማኖት እንደምትከተል የራስህ ጉዳይ ነው እዛ ላይ ችግረ የለብኝም ሆኖም መጀመርያ ሃይማኖቱን ስታውቅ ነው መትቸት የምትችለው፡፡ ስለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጨቅላ ትመስላለህ እና የማታውቀውን ሳተቅባጥረ ዝም ብትል ይመርጣል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.