የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘር ማጥፋት (ጆኖሳይድ) ይቁም!!! ደም በገበታ!!! ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

ethio 45አንደኛ በእስክንድር ነጋና በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ  የአክራሪ ቄሮ የዘር ማጥፋት ወንጀልን በመተንበይ  ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቆማት አቅርበው ነበር፡፡ ሁለተኛ በሻለቃ ዳዊት ወልደጊዬርጊስ  ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘር ማጥፋት መከላከያ ድርጅት ፕረስ ኮንፍረንስ አድርገው ነበር (ምንጭ ላይ ያለውን ዩቲዩብ ይመልከቱ)1 ሦስተኛ በፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው  “የዘር ማጥፋት ይቁም” ዘመቻ 2 (መታየት ያለባቸው ዩቲዩብ) ሦስቱም በህብረት ተቀራርበው በህብረት ቢሰሩ የኢትዮጵያን ህዝብ ላ እየተፈፀመ ያለውን የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) በፍጥነት ለዓለም ህብረተሰብ በማሳወቅ ትኩረት ሊያገኝ ይችልል እንላለን፡፡

በኢትዮጵያ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ)

 • በ1982 ዓ/ም መግቢያ ላይ፣ ህወሓት ሥልጣን ከመያዙ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ፣ በአሶሳ ከተማ ኦነግና ሻዕቢያ የተሳተፉበት ክርስቲያኖችንና አማራዎች የሚሏቸውን ለይተው ቤት ዘግተው በእሳት ማቃጠላቸው የሕዝቡ መፃዒ ዕድል ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች አሰቃቂ ተግባር ነበር። በሻብያና በኦነግ የተፈፀመ የዘር ጭፍጨፋ ነበር፡፡ ሻብያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂና ሌንጮ ለታ በጆኖሳይዱ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
 • በ1984/85 ዓ/ም በአርሲ ሃገረ-ስብከት አርባጉጉ አውራጃ በ680 ካህናትና ኦርቶዶክሳዊያን በአሰቃቂ አረመኔዊ ተግባር ታርደዋል፣ ተቃጥለዋል ከገደል ላይ ተወርውረዋል፡፡ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ አርባ ሦስት ሽህ ምዕመናን ተሰደዋል፡፡
 • በምዕራብ ሐረርጌ ሃገረስብከት አሰቦት ገዳምና አቡነ ሣሙኤል ገዳም መነኮሳትና ምዕመናን በግፍ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡
 • 1998 ዓ/ም በህዳር 8 እና 9 ቀን፣ በአርሲ ሃገረስብከት ኮፈሌ ቆሬ ከተማ አይሻ ሰበካ ስድስት ምዕመናን ተገለዋል፡፡ ከመቶ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ተከታዬች ቤታቸው ተቃጥሎ ተሰደዋል፡፡ የማርያም ቤተከርስቲያን ተቃጥላለች፡፡
 • 1999 ዓ/ም ከመስከረም እስከ ጥቅምት አምስት፣ በሻሻ ዴዴሳና በሞናቶ  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተቃጥሎል፡፡ካህናትና ምዕመናን ታርደዋል፣ የምዕመናን መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡
 • በ2011 ዓ/ም የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ የ86 ሰዎች ሞት፣ ንብረት ውድመትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ወንጀሎች ተፈፅመዋል፡፡
 • በ2012 ዓ/ም ሃጫሉ ሁንዴሳ 187 ሰዎች ተገድለዋል የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮ ድርጅታዊ የዘር ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ!!! በዚህ የህቡዕ መፈንቅለ መንግሥት  የፖለቲካ ሴራ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተደገሠው የዘር ፍጅት ሁለት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት፣ ሁለት መቶ ሰዎች መቁሰል፣ ሁለት መቶ ሃምሳ መኪኖች መሰባበርና ሃያ መኪኖች መቃጠል፣ የአርባ  አምስት ፎቆች መቃጠል፣ ብዙ ሽህ ቤቶች መቃጠል፣ መሠረቱ በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊነትና ተጠያቂነት  መኖር አለበት እንላለን፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ዲያስፖራውን አስተባብረው አይሲሲ በገለልተኛ ተቆማት ፍርድ እንዲሰጥ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንላለን፡፡

 

‹‹በመሣሪያ የመጣ፣ በመሣያ ይወጣ!!!›› ‹‹ በኃይል የመጣ፣ በኃይል ይወጣ!!!››

 • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተቃጠለባቸው፣ ካህናትና ምዕመናን የተገደሉባቸው ስፍራዎች ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ አጣዬ ወዘተ በናሙናነት ይጠቀሳሉ፡፡
 • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዕምነት ቦታዎች የመስቀል ማክበሪያ ቦታዎች በኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በሚገኙ የእምነት ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ የተፈፀመ የሃይማኖት እምነት መብት ጥሰት ተፈፅሞል፡፡
 • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዕምነት ተከታዬች ካህናትና ምዕመናን ሰላማዊ ሠልፍ እንዳያደርጉ መታፈን ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሦስት ድርጅቶች በመነጋገር ሰላማዊ የእንቢተኛነት ትግል፣ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ቢጠሩ ህዝብ ተግባራዊ ያደርጋል እንላለን፡፡
 • ‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። በአብዲ ኢሌ የሥልጣን ዘመን ወደ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዜጎቻችን ከሶማልያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ተፈናቅለዋል። በተመሳሳይ መልኩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሌ ብሄረሰብ ዜጎቻችን ከኦሮሚያ ተፈናቅለው ለስቃይ ተዳርገዋል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የጌዲዖ ዜጎቻችንም በኦሮሞ ፅንፈኞች ተፈናቅለው በብርድና በዝናብ በመጠለያ ሥፍራዎች እስከ አንድ ዓመት ድረስ ኖረዋል። የፈረደባቸው የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ከቤኒሻንጉል በተደጋጋሚ ተፈናቅለዋል፣ እስከዛሬም ያላቆመ ክስተት ነው።››3
 • የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ› በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኜ፣ በዝዋይና በባሌ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የተካሄደው ጥቃት፣ ባመዛኙ የአማራና ሌሎችንም “መጤ” ተብለው የተሰየሙ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞችንና የዕምነት ቤቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው።

‹‹በመሣሪያ የመጣ፣ በመሣያ ይወጣ!!!›› ‹‹ በኃይል የመጣ፣ በኃይል ይወጣ!!!››

የዘመናችን የኦነግ አረመኔዊ ሽብርተኛነት፤-የዘመናዊ ሽብርተኛነት በፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰብ ደረጃ በስብዓናችን ላይ የሚከሰት ቀውስ እንደ (ሽመልስ አብዲሳ) የፖለቲካ ሥልጣን ጥማት ከፍተኛ ስሜት እንደ (ጅዋር መሓመድ)፣ የበታችነት ስሜት የሚንጸባረቅ የማንነት ጥያቄ እንደ (በቀለ ገርባ)፣ በራስን ማፍቀርና ማምለክ ስሜት ሁሉን አውቃለሁ ባይነት ስሜት መወጠር (ዶክተር ዐብይ አህመድ) እና ወይም የግብረገብነት ፈሪሃ እግዜብሄር ጋር ያለ ግንኙነት መላሸቅ  ስሜቶች አንዱን ሰማዕት አንግሶ ሌሎቹን ሰማዕታት አርክሶ፣ ዜጎችን እንደ ልጅና የእንጀራ ልጅ ለአንዱ ሃውልት ለአንዱ አመድ የሚሰጥ  መሪ በታልክ ተጠያቂ ነው፡፡

 • በኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት የሚመራ መንግሥት መር ሽብርተኛነት፣ በመንግሥታዊ መዋቅሮቹ በመጠቀም፣ በመከላከያ ሠራዊቱ፣ ፖሊስ ኃይሉ፣ በጸጥታና ደህንነት ድርጅቱ በጋራ የተቀነባበረ የሽብርተኛነት ድርጊት የተፈፀመ የዘርና የኃይማኖት ማጥፋትን ያሳያል፡፡
 • በኦኤምኤን የጅዋር መሃመድ የቴሌቪዝን ስርጭት ጣቢያው የተቃዋሚ ሽብርተኛነት ሚና ለብዙ አመታት ተጫውቶል፡፡ በተቃሚዎች የሚመራ ሽብርተኛነት ቡድን ሲሆን ኢላማውም የኦሮሞ በአማራና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዬች ላይ እርምጃ እንዲወስድ የመንግሥት  ባለሥልጣኖችና መንግስታዊ ተቆማት ላይ ጥቃት እንዲፈፅም ቀስቅሰዋል፡፡  እነዚህ ሽብርተኞች የፖለቲካና የኃይማኖት ዓላማዎችን በኃይል ማሳካት ነው፡፡
 • የኦሮሞ ፊዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባና ጅዋር መሃመድ  የፖለቲካ ርዕተ ዓለም ፍልስፍና አንዴ የግራ ፖለቲካ ሽብርተኛነትንና አንዴ ደግሞ የቀኝ ፖለቲካ ሽብርተኛ በማጣቀስ  የዘርና ኃይማኖት ፍጅት ሲያደርሱ ኦፌኮ ምንም መግለጫ አላወጣም፡፡
 • ህወሓትና ኦነግ ሸኔ በመናበብ በሃገሪቱ ውስጥ የኃይማኖታዊ ሽብርተኛነት፡-ዋልታ ረገጥ ወይም ፅንፈኛ ኃይማኖታዊ ሽብርተኛ ቡድን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና በሙስሊም የእምነት ተከታዬች ላይ የፈፅሙት ሽብር ይካተታል፡፡
 • በሃገራችን የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንብር በተለይ ኦነግ ሸኔ በወለጋ ውስጥ የሚፈጽመው የወንጀል ሽብርተኛነት የሰዎች ገደላና አፈና የሃያ ሦስት ባንኮች ዘረፋ ለአብነት ይጠቀሳል፡፡ ኦነግና ኦነግ ሸኔ ወንጀለኛ ሽብርተኞ ቡድኖች በወንጀል ድርጊት ኃብትና ንብረት የሚዘርፉ ቡድኖች ውስጥ ይካተታሉ፣ በዕፅ ንግድ፣ በመሳሪያ ሽያጭ፣ በሰዎች ዝውውር፣ በወሲብ ንግድ፣ በህጻናት ሽያጭና ህፃናትን በወታደርነት በመመልመል ፣ በገንዘብ ዝውውር በህገ ወጥ መንገድ የተሰማሩ ወንጀለኛ ሽብርተኛ ብድኖች ናቸው፡፡በዓለማችን የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኞች፣ የግራ ክንፍ ፖለቲከኞች፣ ብሄርተኛ ቡድኖች፣ ኃይማኖተኛ ቡድኖች፣ አብዬተኞችና ገዥው መንግሥት በአጠቃላይ፣ መንግሥትና ተቃዋሚ ቡድኖች በሽብርተኛነት ፅንሰ-ሃሳብ ላይ ተስማምተው ባያውቁም ሁሉም ዓላማቸውን ለማሳካት ሽብርተኛነትን ይተገብራሉ፡፡ ሁሉም የሽብር ድርጊቱን ፈፅመው ከደሙ ንፁህ ነን ይላሉ፡፡

 

የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበር!!!

ባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ እንዲሁም ልደቱ አያሌው፣ ይፈቱ!!!

የዘርና ኃይማኖት ፍጅት የሚቃወም፣ ሰላማዊ የእንቢተኛነት ትግል፣ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ  ይጠራ!!!

ነጻነትና መብት በልመና አይገኝም!!! በመሣሪያ የመጣ፣ በመሣያ ይወጣ!!!

 

ምንጭ

1-https://www.youtube.com/watch?v=v8knP7MvFBc /ጉዳያችን – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘር ማጥፋት መከላከያ ድርጅትፕረስ ኮንፍረንስ -Abbay Media-Ethiopia (መታየት ያለበት ዩቲዩብ)

2-https://www.youtube.com/watch?v=14gADx9LyRg/Ethio 360 Special program “የዘር ማጥፋት ይቁም” ዘመቻ Tuesday September 22, 2020 (መታየት ያለበት ዩቲዩብ)

3-ዴሞክራሲያ ቅጽ 48 ፣ ቁጥር 3 ነሐሴ ፣ 2012 ዓ.ም/የኢሕ አፓ መግለማ ጥላቻ፣ አክራሪነትና ዘረኝነት አንድም ሦስትም ናቸው! /by ዘ-ሐበሻ/ August 27, 2020

 

1 Comment

 1. በፎቶዉ ላይ የተካተቱት ቁርጥ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸዉ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናዬ ይድረሳቸዉ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ አንዴም አላሸለቡም። ገብሩ አስራት መለስ ዘራዊ አሺቀንጥሮ ሲጥለዉ በዉጭ የሚኖር ትግሬ አዲስ ማርቸዲስ ገዝቶ ሲልክለት እኛ ጀግኖቻችንን ከተንኳሾች እንኳን መሳሪያ ሳንይዝ ማስጣል እልቻልንም የማንም አፍ ማሟሻ እናስደርጋቸወለን ወይ ጸጸት። ደግነቱ እነሱም ለሀገራቸዉ እንጂ ከእኛ ምንም ስለማይጠብቁ ተግተዉ እየሰሩ ናቸዉ። እዚህ ላይ የቀሩት አቻምየለህ ታምሩ፤ጌታቸዉ ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) አቶ ገ/መድህን አርአያ ይመስሉኛል። አምላክ ብርታቱን ይስጣችሁ አገር ወዳዱ ልብ ዉስጥ ሀዉልት ተሰርቶላችሗል ክብር ለናንተ ይሁን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.