ከአማራ ክልል ወደ አ/አ የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ወደ ደጀን ከተማ እንዲመለሱ ተደረገ

dejen ከአማራ ክልል ወደ አ/አ የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ወደ ደጀን ከተማ እንዲመለሱ ተደረገ

በትናንትናው እለት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ወደ አማራ ክልል ደጀን ከተማ እንዲመለሱ ተደረገ የሚል መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ተሰራጭቷል፣ እኛም እንድናጣራ በርካታዎቻችሁ ጠይቃችሗል።

የደጀን ከተማ አስተዳድር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ይግረም ከበደ ሁለት አውቶብሶች ከኦሮሚያ ክልል ገብረ ጉራቻ ከተማ ወደ ደጀን ከተማ እንዲመለሱ መደረጉን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል። በሌሎች ተጨማሪ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ግን የተደረገ እገዳ አልነበረም ብለዋል።

ሁለቱ አውቶብሶች እንዲመለሱ የተደረጉት “በጥርጣሬ” እንደሆነ የገለጹት ኮማንደሩ ስለጥርጣሬው ምንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል። አውቶብሶቹና መንገደኞቹ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸውንም እና መንገዱም ክፍት መሆኑን ነግረውናል።

በተመሳሳይ በትናንትው ዕለት ሁለት አውቶብሶች ወደ ደጀን ከተማ እንዲመለሱ ስለመደረጉ መረጃ እንደደረሰው የደጀን ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ ገልጿል።

ኢትዮጵያ ቼክ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.