የአግ7 ታጋዮች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ቡፌደራል ፖሊስ ተከለከሉ

facebook 1600673398487 6713710837968837436የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት ዴሞክራሴ ንቅናቄ በወረታ ካምፕ የሚገኙት ታጋዮች የጀርመን መንግስት የገባልንን ቃል የፌደራል የአዳጋና መከላከል እና መንግስት ያቋቋመው IOM የተባለ NGO የተገባልንን ቃል ተግባራዊ አላደረገም በማለት ለሚመለከትው የፌደራል መንግስት እና የጀርመን ኢምባሲ አካላት አቤቱታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ ከወረታ ካምፕ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ እየሄዱ እያለ እንጦጦ ላይ የፌደራል ፖሊስ ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ብሎ አቁሟቸዋል

መንግስት መፍትሔ መስጠት ባለመቻሉ ታጋቹ ላልተፈለገ ወጭ እና እንግልት ተዳርገዋል ። በትናንትናው እለት ባህርዳር የሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቶ እንደነበር የሚታውቅ ነው። ሰልፉ ባይደረግም የክልሉ መንግስት  መፍትሔ በቅርቡ እንሰጣለን ታገሱን ማለቱ የሚታወስ ነው።
 
ከወረታ ካምፕ የሚመጡት ታጋዮች ጉዳዩን በበላይነት ይዞ ይከታተል ከነበረው የግ7 መስራችና ዋና ፀሃፊ (የነፃነት ፣ ፍትህ፣ አንድነት እና የዴሞክራሲ ታጋይ) አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር በመሆን በዚህ ሳምንት አንድ ነገር ላይ ይደርሳሉ የሚል ተስፋ አለ።
 
ከጀርመን መንግስት የተገኘው ድጋፍና የተገባላቸው ቃል በስርአት ሊተገበር ይገባል። የአብይ መንግስትና የክልል አመራሮች የተገባውን ቃል ማክበር እና መፈፀም ተስኖት ብዙዎችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ጥርጣሬ እና የቀደመው የአገዛዝ እሽክርክሪት እንዳይመልሰን ስጋት ደቅኗል።
Mengistu Amare

3 Comments

  1. አይ አርበኞች ግምቦት 7 አይ ስም አወጣጥ።
    አንዳርጋቸዉ ጽጌ፤ ነአምን ዘለቀ፤ብርሀኑ ነጋ፤ኤፍሬም ማዴቦ ይክፈሏችሁ አዲስ አበባ የምትሄዱበት ምክንያት የለም ወይም ደግሞ ወደ አስመራ ሂዱ። እንደዉ ትንሺ እፍረትም ጠፋ ማለት ነዉ? ለኢሳይያስ ዳጉሳ ስትቆርጡ አዲስ አበባ ለመድረስ ሳምንት ነዉ የቀረን ስትሉን፤ በየምክንያቱ ስታልቡን፤ አሁን የጀርመን መንግስት ብር ሊሰጥ ነዉ የሚለዉን ሰማችሁ ልባችሁ ቆመ እንቅልፍ አጣችሁ። ከግምቦት 7 ያልተወራረደ ብዙ ሂሳብ አለ ዝም ብትሉ ነገር ይረሳሳ ነበር። ቦታ ቢሰጧችሁ እንደ አበረ አዳሙ ህዝቡን ቁም ስቅል ታሳዩ እንደሆን እንጂ ከዚያ የተሻለ ነገር ከናንተ አንጠብቅም።

    ብርሀኑ ነጋ ታፔላ ለዉጦ ኢዜማ ነኝ ብሏል እሱ ድሮም ብልጥ ነዉ መዉጫዉን ነዉ ቀድሞ የሚያየዉ። አንዳርጋቸዉ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ተሰጥቶት አሁንም ክፉ ስራዉን እና ኢትዮጵያን ጥላቻዉን የሚነዛበት እንደ ጁዋር ኦ ኤም ኤን የሚያጭበረብርበት እና ትልቅ ሰዉ መስሎ የሚታይበት ኢሳት የተባለ መገናኛ ተሰጥቶል ክፉ ስራዉ እስኪጥለዉ በድሮዉ ልምዱ ይቀጥላል አዲስ ነገር ለመማርም ለማሰብም ተክለ ስብእናዉ አይፈቅድለትም። በተረፈ ባላችሁበት ቁጭ ብላችሁ ንስሀ ግቡ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.