ለዜጎች ደህንነት ግድ የማይለው መንግስት መንግስት አይደለም – ዶ/ር በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ

Nobel ethiopian registrarወያኔ/ኢህአዲግ ለ27 ዓመት ከሰራቸው መንገዶች እና የልማት ስራዎች ይልቅ በሰብዓዊ መብት ላይ ያደረገው ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጎልቶ ሲተረክ ይኖራል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ኦህዴድ/ብልፅግና እየሰራሁት ነው ከሚለው የዕድገት ቱርፋቶች ይልቅ በየክልሉ የሚሰሙት አሰቃቂ ግድያዎች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ስርዓቱን መንግስት አልባ አድርጎታል፡፡

በአይን ያልታዩ፣ በጀሮ ያልተሰሙ፣ በህሌና ያልታሰቡ የዕድገት ቱርፋቶች፡ ፓርክ፣ መዝናኛ፣ ግንባታ፣ ግድብ፣ መናፈሻ፣ ህንፃዎች፣ መንገዶች፣ ፕሮጀክቶች በሀገሪቱ ላይ ቢሰሩ እና ተሰርተዋል ብለን ብናስብ እንኳን ከሰዎች ህልውና ጋር የሚነፃፀሩ አይደሉም፡፡ ዜጎች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ እየተገደሉ፣ ሰዎች በማንነታቸው የጥቃት ሰለባ እየሆኑ፣ የሰው ልጅ ያፈራው ንብረት በመንጋ  ጥቃት አመድ እየሆነ እየታየ ገፅታ ግንባታ ላይ ማተኮር ብልህ አያሰኝም፡፡ የረከሰ ስራን የሚሰራን አሸባሪ ቡድን ፀጥ ማድረግ ያልቻለና የዜጎችን ህይወት ከአጥቂዎች መታደግ ያልቻለ መንግስት መንግስት አይደለም፡፡ እንዲሁም የረከሰ ስራን የሚሰራን አሸባሪ ቡድን ወደ ፍትህ አቅርቦ መቅጣት ያልቻለ መንግስት ቅቡልነት አይኖረውም፡፡ ለሰው ልጅ ወይም ለዜጎቹ ክብር እና ደህንነት ትኩረት የማይሰጥ መንግስት መንግስት አይደለም፡፡

 

Bekalu Atnafu Taye
Kotebe Metropolitan University, Addis Ababa, Ethiopia · Faculty of Languages and Humanities
B.Ed in English, MA in SNE, MA in Language Education, PhD in Language Education

1 Comment

  1. ዝምታው ለተደረገውም እየተድረገ ላለው ጥፋት ሁሉ ተባባሪነቱን ነው የሚያስረዳው፡፡ በኢትዮጵያ ሥም ነግዶ መደመር ምናምን እያለ በወሬ የህዝቡን ቂልብ ስቦ ኢትዮጵያን እያጠፋ ያለ መንግስት በየትኛወም የኢትዮጵያ ታሪክ ተድርጎ ያልታየ አሁን በዚህ የበሰብሰ አስተዳደር ነው የሚታየው፡፡ ከላይ እስከታች የሰገሰጋቸው ለኢትዮጵያዊነት ደንታ የሌላቸው፣ ህዝብ ሲያልቅ ፣ በእሳት ሲጋይ ቁጭ ብለው ጥርሳቸውን የሚፍቁ እንሰሳዎች ነው የሰበሰበው፡፡ የኦሮሞ ሥም የሌለበት ሰው ሥራ ላይ አለማስቀመጡ የሚያስረዳው እራሱ አብይ ተብየው የኦነግን አጀንዳ እያራመደ እንደሆነ ማስረጃ መጠየቅ ምንም አያስፈልገነም፡፡ እንደው በአገሩ ሌሳ ዜጋ እንደሌለ የሚያደርግው አይን ቀቅሎ የበላ ቅሌት በወያኔ ብቻ የታየ ነው፡፡ ደግሞ ለውጥ ይለናል ማፈሪያ ደንቆሮ! ውያኔን በኋላ በር አስወጥቶ ኦነግን በፊለፊት በር ነው አጅቦ ያስገባው፡፡ እንደው የኢትዮጵያ አምላክ እንኳን ምን ይለኛል የማይል ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለው አጭበርባሪ በህዝብ ላይ ቁማር የሚጫወት አስተዳደር ነው፡፡
    ወንድሜ እስከአሁን ካሳረደውና ካስፈጀው ህዝብ አይብሥም፡፡ ህዝቡ ከእንቅልፉ ነቅቶ ወደአዘቅት እየከተተ ያለውን መንግሥት አውጥቶ መጣል ነው ያለበት፡፡ እቺ ጥሬ ያደረች እንደሆነ አትቆረጠምም ብሏል ያገሬ ሰው፡፡ መንግሥት ተብዬው እንደሆነ ትናንት የምናውቃትን ኢትዮጵያ በትልቅ ላጲስ ጃግሬዎቹን በየቦታው ሰግስግሶ በማጥፋት ላይ ነው የተያያዘው፡፡ ቅዘንን ህዝብ ላይ የቀዘነ መንግሥት እንደዚህ አይነት ታይቶ አይታወቅም፡፡ ቤተመንግሥቱን ለአረብ አልቤርጎ ማድረግን እና ለፈረንጅ መናፈሻ መስራት መሪነት አይደለም፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.