‹‹ከ2013ዓ/ም ምርጫ በፊት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቱ እንዲጠበቅ ህዝባዊ እንቢተኝነት ይጠራ!!!›› ክፍል አንድ ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

et23‹‹በባዬሎጅ የሥነ ህይወት ትምህርት ሃይድራ  በውኃ ውስጥ የሚኖሩ ህይወት ያለው ትናንሽ አካል (organisms)  በአንድ አካል ሁለት ጭንቅላት ያለው ፍጥረት ሲሆን  ፊለም ሲንዳሪያና ሃይድሮዞአ በመባል ይታወቃሉ፡፡ የሥነህይወት (ባዬሎጂስቶች) ተመራማሪዎች ጠበብት ሁለት ራስ ያለቸውን ሃይድራን በዋናነት በፍላጎት የሚያጠኑበት ምክንያት ሃድራ ዝርያውን ዳግም ማፍራት፣ ማብቀልና የመተካት ችሎታ የተነሳ የማይሞት ዘላለማዊ ህይወት ያለው የሚመስልና የማያረጅ  እርጅና ለምኔ፣ እድሜ ቁጥር ነው የሚል ይመስል ነበር፡፡›› ዊኪፒዲያ፡፡  ‹‹Hydra is a genus of small, fresh-water organisms of the phylum Cnidaria and class Hydrozoa. They are native to the temperate and tropical regions. Biologists are especially interested in Hydra because of their regenerative ability – they do not appear to die of old age, or indeed to age at all. Wikipedia››

‹‹ ሁለት ጭንቅላት ያለው የፌዴራልና ክልሎች መከላከያ ሠራዊት!!! ሁለት ጭንቅላት ያለው መንግሥትና ፓርቲ!

{1} ሁለት መንግሥት፡- ህወሓት/ኢህአዴግና  ብልፅግና ፓርቲ፣ በኢትዮጵያ ሁለት ጭንቅላት ያለው ሃይድራ መንግሥት ተፈጥሮል፡፡ የህወሓት/ ኢህአዴግ የአራት ፓርቲዎች ውህዱ ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን፣  ግንባር የነበረ ሲሆን ብልጽግና ፓርቲ ደግሞ ህወሓት ወጥቶ በሦስቱ ህብረት ተመሠረተ፡፡ በሃገሪቱ ህወሓትና  ብልፅግና ፓርቲ ሁለት ራስ ያለው ሃይድራ ፓርቲዎች በመሆን በአንድ ሃገር ሁለት መንግስት መሥርተዋል አንዱ ከአዲስ አበባና አንዱ ከመቐለ ሆኖ እየተዘወረ ለሠላሣ አመታት ቀጥሎል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግና  ብልፅግና ፓርቲ፣ ሞተ ሲባል ታድሶ፣ ፈረሰ ሲባል ገምቶ፣ አለቀለት ሲባል በጥልቅ ተሃድሶ፣ በሰበሰ ሲባል እየደረቀ  ሁለት ጭንቅላት ያለው ሃድራ የማያረጁና የማይሞቱ ጥገኛ ተዋሲያን በመሆን የሃገራችንን ህዝብ ረግጠው ሲገዙ ኖረዋል፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች ጠብ ያላቸው ይመስላሉ እንጂ ጠብ የላቸውም፡፡ በዋናነት ህገመንግሥቱን በጋራ ይደግፋሉ፣ የዘር ፌዴራሊዝም፣ የመሬት ጥያቄ፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ጥያቄ፣ የስብዓዊ መብትና የዴሞክራሲ ጥያቄ  ወዘተ ላይ አንድ ዓይነት አቆም አላቸው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ፕሮግራም ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በተረኛነት ማስቀጠል ነው፡፡

{2} ሁለት ፓርቲ፡-ብልፅግና ፓርቲ ሁለት  ጭንቅላት ያለው ሃይድራ ፓርቲ ሆኖል አንደኛው የዶክተር ዐብይ አህመድን ‹የመደመር› ፍልስፍና ተጠምቀው የተቀበሉ ናቸው፡፡ ሁለተኛው  የህወሓት/ኢህአዴግ የዶክተር ደብረፂዮን ገብረማርያም ‹የአብዬታዊ ዴሞክራሲን› ፍልስፍና የሚያምኑ የብልፅግና ፓርቲ በማስመሰል የተቀበሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ መሪዎቻቸው ዶክተሮቹ ዐብይና ደብረፂዮን ‹‹እንደ ሰው በምድር እንደ አሣ በባህር›› ገፀ ባህሪ በመላበስ የሚተውኑ ናቸው፡፡  የፓርቲ አባሎቻቸው ተክለ ሰውነት ግራና ቀኝ አካል አንዱ የህወሓት አንዱ የብልፅግና ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለም፡፡ አምቼ የተገጣጠመ ተክለ ሰውነት ያላቸው ሆድ አደር ቦዘኔ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡

{3} ሁለት መከላከያ ሠራዊት:-በሃገሪቱ ሁለት ጭንቅላት ያለው ሠራዊት ተገንብቶል፡፡ አንደኛዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት የመከላከያ ሠራዊት ሲሆን ሁለተናው ደግሞ የክልል መንግሥቶች ሠራዊት በልዩ ፖሊስ ኃይል፣ ህዝባዊ ሚሊሽያ ወዘተ የተገነባ ነው፡፡ በሃገሪቱ የሚገኙ ክልሎች በድንበርና ወሰን ግጭት ወደማያባራ የዘር ጦርነት ይሸጋገራሉ፡፡  በዚህ ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ወያኔ ኢህአዴግና ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ አንድ ናቸው፡፡

{4} ኖቤል ሎሬት ዐብይ አህመድ ቃለ ምልልስ እንዳሉት ‹‹ ዜጎች ኢትዮጵያ ውሰጥ በወንድሞቻቸው በእራሳቸው ወገን እየሞቱ ነው ያሉት፣ ሌላ ወራሪ ኃይል ከውጭ መጥቶ ጥቃት ያካሄደ የለም፡፡ መንግስት በእያንዳንዱ ቤተሰብ ቤት በር ላይ ዘበኛ ሊያቆም አይችልም፡፡ ለእያንዳንዱ ሃይስኩል (ት/ቤት) በር ላይ ዘበኛ ማቆም አይችልም፡፡ እያንዳንዱ ዜጋ ለእራሱ ሠላም ዘብ መቆም አለበት፡፡››   ብለዋል፡፡

ሪፐብሊክ ጋርድ፡- የሪፐብሊኩ ጥበቃ ልዩ ኃይል ሲሆን በቀጥታ የሚታዘዘው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፡፡ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ልዩ ኃይል የሚመሩት ብርጌዴር ጀነራል ብርሃኑ በቀለ ሲሆኑ ለመንግሥትና ባለሥልጣኖች፣ ለመሪዎችና ቤተሰቦቻቸው  ሌትና ቀን ዘብ መቆም ነው፡፡ ልዩ ኃይሉ የሚጠብቃቸው በዓየርና በምድር የጥበቃ ተግባሩን ለመከወን ባቃት እንዳለው ተገልፆል፡፡ የታጠቁጥ ማሽንገን በአንድ ደቂቃ ስምንት መቶ ጥይት የሚተፉ፣ ታጣፊ ታንኮች፣ በራሪ ሂሊኮፐተሮች፣ ጥይት የማይበሳቸው መኪኖች፣ የሥልጣን በእቅፌ፣ ቴክኖሎጂ በመዳፌ መንግሥትን ያስጠብቃሉ፡፡ በታሪክ የቀኃሥ ክብር ዘበኛ፣ የደርግ ቅልብ ጦር፣ የወያኔ አጋዚ ጦር፣ የብልጽግና ሪፐብሊካን ጋርድ ‹‹የአህያ ባል ጅብ አያስጥልም›› ሆነው አልፈዋል፡፡

{5} ኖቤል ሎሬት ዐብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደምሆን መለስ ዜናዊ እንኮን ያውቅ ነበር በሚለው ቃለ ምልልሳቸው ‹‹የዜጎች ህይወት ላይ የማመጣው ውጤት፣ የማረሰርሰው ጉሮሮ፣ የማስተምረው ጭንቅላት፣ ሥራ የምሰጠው እጅ ቁጥር ብዛት የእኔን መሆን ውጤት ይለካል፡፡››1 ብለዋል፡፡ ሆኖም በእውኑ ዓለም ያለው ሁኔታ ግን ‹‹ በሀገራችን ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት የለውም፡፡ በዜጎች ህይወት ላይ የሚያመጡት በህይወት እንዲኖሩ መብታቸውን ማስከበር ነው፡፡ የሚያረሰርሱት ጉሮሮ እየታረደ፣ የሚያስተምሩት ጭንቅላት እየተቀላ ፣ የሥራ እድል የሚሠጡት እጆች ቁርጥራጭ ቁጥር ብዛት በእርሶ አገዛዝ ዘመን የተከወነ የመንግስቶ ውጤት ይለካል፡፡ ኖቤል ሎሬት ዐብይ አህመድ የምኒልክ ቤተመንግሥት፣ የቀኃሥ ኢዩቤልዩ ገነተ ልዕል ቤተ-መንግሥትና ከአዲስ አበባ መናፈሻዎች ተጨማሪ የአንድነት ፓርክ፣ እንጦጦ ፓርክ፣ ወንድማማች ፓርክ  ሲገነቡ ሥራ በዝቶብዎ ካልሆነ ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ ጸጉሩ የሸበተ፣ እግሩ የሸበተና ልቡ የሸበተ መሪ ቢሆኑ ኖሮ አይዋሹም፡፡ በእለቱ ለሞቾቹ ቤተሰቦች እግዜር ያጥናችሁ በተደጋጋሚ ያላለ መሪ ግን አንድ ችግር፣ አንዳች የሚጎልዎ ነገር እንዳለ ያሳያል፡፡  እርሶ እራስዎን መሲሃ አድርገው ያያሉ፣ ከአፍዎ ቅባት፣ ከእጆዎ ዘይት፣ የሚያመነጩ አርገው ይቆጥራሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ ... ለአህመዲን ህክምና ስጡት ፣ ፍቱትም !

{6} ዶክተር ዐብይ አህመድ ስለ ኖቤል ሽልማታቸውና ስለምርጫ በቃለምልልሳቸው እንዳሉት ‹‹አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ፓርቲዎች ሰብሰብ ብለው ጠንከር ስላላሉ ለብልፅግና የሚያሰጋ ሃሳብም አደረጃጀትም አለ ብ አላስብም፡፡የተሸለ አደረጃጀት ያለው ብልፅግና ፓርቲ ስለሆነ በምርጫ እናሸንፋለን፡፡ ምርጫው ነፃ፣ፍህታዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን፣ ብልፅግናን ፓርቲን የሚወዳደር ተፎካካሪ የተደራጀ ፓርቲ አለ ብዬ አላስብም፡፡…በ2013 ዓ/ም ምርጫው ይካሄዳል ብዬ አስባለሁ፡፡›› ብለዋል፡፡  ዶክተር ዐብይ አህመድ             በሃገሪቱ የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን አግዝፈው ተራ በተራ ማጅራታቸውን እየመቱ ጥለዋል፡፡ በአንድ ድንጋይ ሁለትና ሦስት ወፎች መተው ጥለዋል በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሣ ግድያ በጁሃር መሃመድና በቀለ ገርባ የመፈንቅለ መንግስት የከሸፈ ሴራ

 • ኦፌኮ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከፍተኛ አመራር የነበሩት በቀለ ገርባና ጅዋር መሃመድ በሃገሪቱ ባስነሱት የተቀነባበረ የፖለቲካ ሴራ የብዙ ሰዎች ህይወት ተቀጥፎል ንብረት ዶጋ አመድ ሆኖል፡፡ ኦፌኮ ከምርጫና ከስልጣን መንበሩ ተቀጨ፣
 • ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በነጁሃር መሃመድ ወንጀል በአስራ አራት ሰዎች ግድያና በመቶ ሰማንያ አራት ሚሊዮን ብር የንብረት ውድመት ወንጀል ተከሰው በግፍ ወህኒ ገብተዋል
 • አብሮነት ፓርቲ ኢንጅነር ይልቃል ለእስር ተዳርጎል ፓርቲውም በምርጫ ቦርድ እውቅና ተነፍጎታል፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የብልፅግና ፓርቲ ብዙ መስፍርቶችን ሳያሞላ ከኢህአዴግ ወደ ብልፅግና ሙሉ የቅርጽ ለውጥ (Metamorphosis) ኢህአዴግን  ፈጭተው፣ አቡክተው፣ ጠፍጥፈው  በመጋገር ብልጽግና ፓርቲነት በመቀየር አጋፍረዋል፡፡
 • አቶ ልደቱ አያሌው ወህኒ ወርደዋልየኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት የወከሏቸውን ጠበቆች አሰናበቱ።የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በሁለት ሳምንት ውስጥ ክስ እንዲመሰረት በማዘዝ መዝገቡን ዘግቶ ነበር።
 • የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ኦቦ ዳውድ ኢብሣ የዝምታ መፈንቅለ መንግሥት ከቤታቸው ቁጭ ብለው ከመሪነት ተሰናብተዋል፡፡
 • ኦነግ ሸኔ የወለጋ ህዝብን በስብዓዊ ጋሻነት ጠርንፎ በመያዝ የኦሮሞ ህዝብን የጨፈጨፈ ሽፍታ ቡድን የዘርና የሃይማኖት ፍጅት በአማራው ህዝብ ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወንጀሉ ከደረሰ በኃላ በመድረስ እንደ ህንድ ፊልም በመተወን ላይ ይገኛል፡፡
 • የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ህዝብ በተለያዩ ክልሎች የሚደርስባቸውን የዘር ጭፍጨፋ በቅርብ ጊዜ በሻሸመኔና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የደረሰ በማውገዝና የህሊና እስረኞችና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡
 • ኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በምርጫ አሮሮጭነት (Pacemakers ) ብልፅግና ፓርቲ እንዲያሸንፍ ይደልላል፣ አንዴ አብይ ከሌለ የምፅዐት ቀን እንደሚመጣ ይሰብካል፣ አንዴ አብይ ካላሸጋገረን ለውጡ ይቀለበሳል በማለት አታጩሁት ተረጋጉ በሚል አመራራቸው ይታወቃሉ፡፡ በኢዜማ የውስጥ ትግልና ጥናት መሠረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የኢንጅነር ታከለ ኡማ በሥራ ዘመናቸው ዘጠና አራት ሽህ ኮንዶሚኒየም ክፍፍል በሙስና የተጨማለቀ፣ የቤት ቆጣቢዎችን ገንዘብ የዘረፈ ሥርዓት መሆኑን ሞግተዋል እንዲሁም የቢኒሻንጉል ጉሙዝ ጭፍጨፋን የብልጥግና ፓርቲን በማውገዝ የሰላ ሂስ በመስጠት የአቆም ለውጥ አድርጎል፡፡
 • ህወሓት/ ኢህአዴግ በትግራይ ምርጫ አካሄደ 98 በመቶ አሸነፈ:: ህወሓት የጦር አበጋዝ መንግስት ነው፡፡
 • ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ምርጫ በ2013 ዓ/ም 99 በመቶ ለማሸነፍ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን አፍንጫ እየሰነጉና ስንኮፋቸውን እየነቀሉ፣ ህዝቡን በሽብር ፍርሃት ውስጥ ዘፍቀው በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ፍርሃት ውስጥ ዶለውት፣ ዜጎችን አንዱን የእንጀራ ልጅ ‹‹መጤና ሰፋሪ›› ሌላውን ልጅ ‹‹ተወላጅ ባለአገር›› በማድረግ አንደኛና ሁለተኛ ዜጋ በክልሎች መንግሥት ህገመንግስት በተፃፈበት ሃገር ምርጫ ማድረግ ዴሞክራሲን ሳይሆን አንባገነንነትን ያሳያል እንላለን፡፡  በሁሉም ክልሎች ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብታቸው በህግ ሳይረጋገጥ  ምርጫ ማድረግ ከንቱ ውዳሴ ነው እንላለን፡፡

{7} ዶክተር ዐብይ አህመድ ሃገረ መንግስት ግንባታ ያልፀናው ተቆማቱ ሲገነቡ ተጠያቂነት፣ ቅቡልነት በዴሞክራሲያዊ መንገድ በምርጫ ስልጣን መያዝ፣ የህግ የበላይነት የፍትህና ርትህ አሰጣጥ  እንዲሁም የዴሞክራሲ ሃሳብ በህዝብ ውስጥ አለመስረፅ የተቆማት ግንባታው ደካማ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ሆኖም ጠንካራ የነበሩ መንግሥታዊና ሲቪል መዋቅሮች በመንግስት ጣልቃ ገብነት መዳከማቸው ሊካድ አይገባም፡፡ ህወሓት /ኢህአዴግ መንግሥታዊ መዋቅሩን በአንድ ዘር ተኮር በመጠቅጠቅ ሃያ ሰባት ዓመታት ገዛ፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በተረኛነት በአንድ ዘር መንግስታዊ ቢሮክራሲውን ስልጣን በማስጨበጥ ላይ ይገኛል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ መንግሥታዊ መዋቅሮች እየተጠቀመ የሁሉንም ክልሎች መንግስታዊ አስተዳደሮች፣ ዞን፣ አውራጃ፣  ወረዳ፣ ቀበሌ፣ መዋቅሮች በመጠቀም፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ፖሊስ ሠራዊት የፀጥታና የደህንነት ተቆማት በመጠቀም፣ የፌዴራልና የክልሎች መገናኛ ብዙሃን ሬዲዩና ቴሌቪዝን ጣቢያዎችን በመቆጣጠር የቅስቀሳ ተግባር በመፈፀም፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን በመቆጣጠር፣ የፍርድ ቤቶችን አስራር በመቆጣጠር፣ ለኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ፣ በአንድ ቀን አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊየን ብር ለፓርቲው የማሰባሰቡ እንቆቅልሽ የፌዴራልና ክልልሎች መንግስትን በመዳፉ ቁጥጥር አድርጎ ስለሚያስገብር ነው፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ‹‹ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ›› አድርጎ በመጠቀም ስለ ወደፊቱ ሀገረ መንግስትና መንግሥታዊ አወቃቀር  ዶክተር አብይ ለማስተማር ይዳዳሉ፡፡  ዶክተር ዐብይ አህመድ የብልፅግና ፓርቲ ዴሞክራሲን ከንፈር ወዳጁ ያደረገና  በተግባር የህግ ሉዓላዊነት ማስከበር ያልቻለ የሞተ የወንዴ ዘር ፈሳሽ ያለው የመከነ ፓርቲ ነው፡፡ ‹‹ከምርጫ በፊት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው!!!›› በአሁኑ ሰዓት አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሽህ ህዝብ ተፈናቅለው ለአስቸኮይ እርዳት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፣ መንግሥት ሊደርስላቸው ይገባል፡፡ ከ2013ዓ/ም ምርጫ በፊት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቱ እንዲጠበቅ ሠላማዊ ህዝባዊ እንቢተኝነት የቤት መቀመጥ አድማ ይጠራ!!!››

ተጨማሪ ያንብቡ:  በረከት ስሞንንም የተቃዋሚ ሀይሉ መሪ ለማድረግ ያቀደ የሚመስለዉ የባዶ ጮህት ፕሮፖጋንዳ:- 

 

ምንጭ

{1} https://www.youtube.com/watch?v=Cmjhbx2j6Wo&feature=emb_rel_end“ጠቅላይ ሚኒስትር እንደምሆን መለስ እንኳን ያውቅ ነበር” ዶ/ር አብይ/•Sep 9, 2020 ((መታየት ያለበት ዩቲዩብ))

{2} https://www.youtube.com/watch?v=UaFhvnoD7Qgዶ/ር አብይ አህመድ ሰለ ኖቢል ሽልማታቸዉ እና ሰለ ኤርትራ ያልተጠበቀ ምላሽ ሰጡ Ethio Eritrea Abiy Ahmed | Isaias Afwerki/•Sep 9, 2020 (መታየት ያለበት ዩቲዩብ)

                  ————————————–//——————————

ኢት-ኢኮኖሚ            /ET- ECONOMY

et23ዐብይ ሪፓብሊካን ጋርድ ገነባ!!! ለህዳሴ ግድብ የፌዴራል ጋርድ ልዩ ኮማንዶ ጦር አልገነባም!!!››

ክፍል ሁለት                             ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ግድቡ ከሱዳን ድንበር  አርባ ኪሎሜትር ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ በአማፂዎች የሚደረግ ተደጋጋሚ የዘር ጭፍጨፍ ቅጥረኞች ከግብፅ፣ ከሱዳንና ከሃገሪቱ ወዳጅ ያልሆኑ ሃገራት የፖለቲካ ሴራ የህዳሴግድቡ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ስለሚችል በአስቸኮይ እንደ ሪፓብሊካን ጋርድ፣ለህዳሴ ግድብ የፌዴራል ጋርድ ሊገነባ ይገባል እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ በላይ የወጣበት የሃገሪቱ አንጡራ ንብረት በመሆኑ በቆሚ በፌዴራል መከላከያ ሠራዊት ወይም በፌዴራል ጋርድ ጥበቃ ልዩ ኃይል በዓየርና በምድር የጥበቃ ተግባርን ለመከወን የሁሉም ክልሎች የሰው ኃይልና የጋራ በጀት መገንባት ይኖርበታል፡፡ የህዳሴ ግድቡ በአስተማማኝ የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ መገንባት አለበት እንላለን፡፡

የዐብይ ሪፓብሊካን ጋርድ እንደገነባ ሁሉ ፣ የህዳሴ ግድብ በፌዴራል ጋርድ ልዩ ኮማንዶ ጦር ሊገነባ ይገባል እንላለን ይህን ስንልም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሽምቅ ተዋጊዎች በተደጋጋሚ የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋ ስላደረጉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል ካለ ስለማይቆጠር  በሁሉም ክልሎች የተወጣጣ  አዲስ የፌዴራል ጋርድ እንዲቆቆም እንጠይቃለን፡፡ የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ የህዝብ አንጡራ ኃብት በመሆኑ ከደሃው ህዝብ በመዋጮ የተገነባ ግድብ በመሆኑ የግድቡን ፀጥታና ደህንነት መጠበቅና ዋስትና መስጠት የብልፅግና ፓርቲ  ቀይ መሥመር ነው እንላለን፡፡ በግድቡ ላይ ጥቃት እንዳይፈፀም በንቃት መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ በግድቡ አካባቢ ሽምቅ ተዋጊዎች እንቅስቃሴ መቆም ግድ ይላል፣ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲን መንግሥት የግድቡን ፀጥታና ደህንነት ያስጠብቅ እንላለን፡፡

የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ለሃገሪቱ የሚያስገኘው ገቢ ትንበያ (Revenue Projection) በግልፅ የተቀመጠ ጉዳይ ስለሆነ የፕሮጀክቱ ጥቅምና ጉዳት (Cost-Benefit Analysis) ስሌት በጥናቱ መሠረት ካልተተገበረ የአዋጭነትና ትርፋማነት ጥናቱ ከንቱ ሆኖ ስለሚቀር የግድቡ ፕሮጀክት የድርድሩ ቀይ መሥመር ለመንግሥትና ለተደራዳሪዎች አይነኬ ውሃልኮችን ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረግ የምሁራን ኃላፊነት ነው እንላለን፡፡ የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ፣  ከመጋቢት 24 ቀን 2003 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ/ም የዘጠኝ  ዓመታት ጉዞና እውነታዎች ውስጥ የሚያመነጨው የሃይል መጠን 6 ሺ 450 ሜጋ ዋት፣ለመገንባት የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን 80 ቢሊን ብር (ከ4-5 ቢሊዩን የአሜሪካ ዶላር በላይ)፣የሃል ማመን ዩኒቶች ብዛት 16፣ እንዳንዱ ኒት የሚያመነጨው የሃይል መጠን ከ 375 እስከ 400 ሜጋ ዋት፣ የዋናው ግድብ ከፍታ 145 ሜትር፣ የዋናው ግድብ ርዝመት 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር፣ የዋናው ግድብ ውፍረት የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ቻፍ ወይም የላይኛው ክፍል 11 ሜትር፣ ግድቡ ሚይዘው የውሃ መጠን 74 ቢሊዩን ኪዩቢክ ሜትር፣ግድቡ ሚሸፍነው የቦታ ስፋት 1 ሺ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር፣ሲጠናቀቅ ውሃ ሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር፣ ለግድቡ ግንባታ ከህዝብ ቃል የተገባ የገንዘብ መጠን 12 ነጥብ 8 ቢሊዩን ብር፣ቃል ከተገባው እስካሁን የተሰበሰበ ገንዘብ ብዛት 9  ነጥብ 6 ቢሊዩን ብር፣ግድቡን የጎበኙ ኢትጵያውን ብዛት 250 ሺ፣ ግድቡን የጎበኙ የውጭ ሚዲያዎች ብዛት 400፣ በ2023 እኤአ 1 ቢሊዩን ዶላር በዓመት ለሃገሪቱ የውጪ ምንዛሪ ከኤሌትሪክ ሃይል ሽያጭ  ያስገኛል ተብሎ ተተንቡዩል፡፡ (ምንጭ መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ) የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ያልተጠበቀ ምን  ይጠበቅ፡፡ ለዚህ ነው  የዐብይ እራሱን ለመጠበቅ ሪፓብሊካን ጋርድ እንደገነባ ሁሉ ፣ የህዳሴ ግድብ በፌዴራል ጋርድ ልዩ ኮማንዶ ጦር ሊገነባለት ይገባል እንላለን፡፡

በሌላ በኩል የአማራ ማስሚዲያ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ዜና መሠረት ጳጉሜ አንድ ቀን 2012ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዘር ተኮር ፍጅት (ጆኖሳይድ) በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ኤባር ተብሎ የሚጠራ ቀበሌ አማራና አገው ከሰማንያ ዘጠኝ እስከ መቶ ሠላሳ ተወላጆች ላይ በስም ዝርዝር ተጠቁመው አሰቃቂ ዘር ተኮር ግድያ ተፈፅሞል፡፡  በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ውስጥ የቤሻንጉል  ህዝብ ንቅናቄ (ቤህን)፣ ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉዴን)  እና ኦነግ ሸኔ  በመጣመር የዘር ፍጅቱን አድርገዋል፡፡ የወረዳው ፖሊስ አስቀድሞ ቀበሌውን ለቆ ወጥቶ ነበር፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትን የስነህዝብ (ዲሞግራፊ) ለመቀየር በሚደረግ የፖለቲካ ሴራ  እንደሆነ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እቅዳቸውን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

‹‹ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡-  በመለስ ዜናዊ መንግሥት የተፈጠረ ተጠፍጥፎ ከጎጃም ክፍለሃገር ከነበረው መተከል እናም ከወለጋ ክፍለሃገር ተወሰዶ ክልል የሆነ ነው፡፡  ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሲሆን ከጎጃም ክፍለ ሃገር ከአባይ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኝ ሲሆን ከወለጋ ክፍለሃገር  ከአባይ ወንዝ በስተ ደቡብ የሚገኝ ቦታን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማለት አሶሳ ዋና ከተማ ተደረገች፡፡ በማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ 2007 እኤአ በተደረገ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መሠረት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የህዝብ ቁጥር 784345 ነበር፡፡ ከዚህ ውስጥ የብሄር ብሄረሰብ ስብጥር አማራ (25.41%)፣ በርታ (21.69%)፣ ኦሮሞ (13.55%)፣ ሺናሻ (7.73%)፣ አገው አዊ (4.22%) ነበር፡፡ ዋናዎቹ የክልሉ ቌንቌ በርታ (25.15%)፣ አማርኛ (22.46%)፣ ጉሙዝ (20.59%)፣ ኦሮሞ (17.69%)፣ ሺናሻ (4.58%) እና አዋንጊ (4.01%) ነበር፡፡ ሃይማኖትን በሚመለከት (44.7%) ኦርቶዶክስ ክርስቲያን፣ (33.3%) ሙስሊም፣ (13.53%) ፕሮቴስታንት፣ (7.09%) ባህላዊ እምነት ተከታዬች የሚኖሩበት ክልል ነው፡፡ ››ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ከአማራ፣ ከኦሮሚያ እንዲሁም ከሱዳን ጋር ይዋሰናል፡፡  ቤሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ በከፍተና ድህነት ውስጥ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡  በቤሻንጉል ጉሙዝ ህገ-መንግሥት መሠረት ሃገሩ የመጤና ሠፋሪ የሆኑትን አማራ፣ኦሮሞና አገው ሁለተኛ ዜጋ ሲሆኑ በአንደና ዜግነት  የበርታ፣ ሺናሻ፣ ጉሙዝ፣አዋንጊ  እንደሆኑ በህገ መንግሥቱ ተፅፎል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እውነት ለፍርድ በር ላይ ደርሳለች!!! – ከተማ ዋቅጅራ

በአለፈው ጊዜም ሃያ አምስት ሽህ የአማራና አገው ተወላጆች ተፈናቅለው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በ1983ዓ/ም ኦነግና ሻብያ የዛሬ ሠላሳ አመት በቤኒሻንጉል አሶሳ ሆስፒታልና ትምህርት ቤት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው እንደተቃጠሉ በታሪክ ይታወሳል፡፡››

‹‹ከምርጫ በፊት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው!!!››

ብልፅግና ፓርቲ ሁለት ራስ ያለው ሃይድራ ፓርቲ ነው፡፡

 • የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) በኢስብዊ መንገድ በገጀራ፣ በጦር፣ በድንጋይ፣ በዱላ ወዘተ በቡድን የሚፈጸሙ ግድያዎች ድርጊት ፈፃሚዎች በህግ እንዲጠየቁና፣ ታድነው ተይዘው ለፍርድ ሲቀርቡ ከታየ በሌላ ቦታዎች ተመሳሳይ ወንጀሎች ይቀንሳሉ ብሎም የደቦ ግድያው ይቆማል፡፡
 • በኢትዮጵያ በሚገኙ ክልሎች ውስጥ በክልሎች ህገ-መንግሥት ዜጎች ‹‹መጤና ነባር›› ተብለው የተፈረጁ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች እንደተፈረጁ ተደንግጎል፡፡ ይህ ህገመንግሥት እስከአልተሰረዘ ድረስ በዚህ የህግ የመኖር ዋስትና ያጡ ዜጎች፣ ዋስተና ያጡ ኑዋሪዎች ይህ ህግ ተፈፃሚ ከሆነ በሚቀጥሉት ጥቂት ጊዜት ውስጥ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ይሆናል እንላለን፡፡ የዳክተር አብይ መንግሥት የህግ የበላይነትን መተግበር ባለመቻሉ የተነሳ ብዙ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ ልጃገረድ ሴቶችና እናቶች ተደፍረዋል፣ ሃብትና ንብረታቸው ተዘርፎል፣ ህጻናትና ወጣቶች የሥነ ዓዕምሮ ቀውስ ተዳርገዋል  እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ በመላ ሃገሪቱ ተፈናቅለዋል፡፡
 • የዳክተር አብይ መንግሥት የህግ የበላይነትን መተግበር ካልቻለ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመላ ሃገሪቱ ተዘዋውሮ መሥራት ካልቻለ፣ ሃብትና ንብረት ማፍራት መብት ከሌለውና በህግ ፊት እኩል ካልሆነ፣ ‹‹ጨዋታው ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ›› ተባብለን ወደ ዘር ስልቻችን በመታቆር፣ ‹‹የመጤና ነባር›› ትርክትን አስፈፃሚው በሰላም መጤውን ህዝብ ከሙሉ ክብሩ ወደ ክልሉ ማሰናበት ይኖርበታል፡፡ የሕወሓት/ኢህአዴግና የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ይህን ህገመንግሥት በህግ ሊሻርና አዲስ ህገመንግሥት ሊረቅ ይገባል እንላለን፡፡  ይህ ሳይተገበር ቀጣዩ ምርጫ ዘበት ይሆናል፡፡
 • ተፈናቃይ ህዝብ ዳግም ወደ መጡበት መልሶ የማስፈር እርቀ ሰላም የሚለው ፈሊጥ በተደጋጋሚ ለተፈናቃዮች ሞትና ስደት የዳረገ በመሆኑና ተፈናቃዬች ከገዳዬቻቸው ጋር እንዲኖሩ በመገደዳቸው ለከፍተኛ የሥነ አይምሮ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቀው በእውሸት እርቅ፣ ፍትህ ባልተሰጠበት፣ ፍርድ ባልተገኘበት ሁኔታ አንዱን ጠቅሞ፣ ሌላውን ጎድቶ የሚደረግ የይስሙላ የሽምግልና እርቅ በተደጋጋሚ ለብዙ ሰዎች እልቂት ምክንያት ሆኖል፡፡ በሁሉም ክልሎች የህግ የበላይነት ተፈፃሚነት ካላገኘ እርቀ ሰላሙ የውሸትና ከንቱ ነው መንስዔው መቅኒው ድረስ የዘለቀ የድህነት አረንቆ ውስጥ ህብረተሰቡ በመኖሩ የተነሳ የመጤውን መሬት ለመንጠቅ፣ ከብቶቹን ለመንዳት፣ ገንዘቡን ለመንጠቅ፣ ሴቶቹን ለመድፈር፣ ወዘተ መሆኑን አለመረዳት ለብዙ ሰዎች እልቂትን ያስከትላል እንላለን፡፡
 • አሰቃቂ ኢስብዓዊ ግድያ የፈፀሙ ወንጀለኞች በገጀራ፣ በጦር፣ በድንጋይ፣ በዱላ ወዘተ የጅምላ ግድያ ድርጊት የፈጸሙ በሃገሪቱ ህግ መሠረት ያለው የሞት ፍርድ ቢቻል በአደባባይ በገበያ መኃል ወንጀለኞችን በመስቀል የሰው መግደል ወንጀል እንደሚያስቀጣ ህብረተሰቡ ካልተረዳ በውሸት እርቀ ሰላም አይፈታም እንላለን፡፡
 • ህወሓት/ኢህአዴግ በአለፉት 27 አመታት በአደባባይ ሰው በስናይፐር አድኖ የሚገድል አውሬ በአደባባይ መሰቀል ሲያንሰው ነው፣ ያን ለበቀል ሳይሆን የህግ የበላይነትን በመላ ሃገሪቱ ያጠፋ፣ ወንጀለኞች ገድለው የሚኖሩበት የሽፍታ የከተማ መንግሥት ባህል ያስፋፉ በመሆናቸው ዛሬ በየቦታው የተከሰተው ወንጀለኛነት የተስፋፋው ለገዳዬች ፍርድ ስለማይሰጥ፣ ለፍርድ ስለማይቀርቡና ከገዳዬቻችንና ከገራፊዎቻችን ጋር አብረን እየኖርን ስለሆነ በፍርሃት ቀንበር ስር ህብረተሰቡ እንዲኖር ተገዶል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ በተረኛ ዘረኛ ስሜት በአለፉት ሦስት አመታት በሃገሪቱ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) በቅርብ ጊዜ እንኮን በሻሸመኔ፣ አርሲ ፣ጅማ፣ ባሌ፣ ቤኒሻንጉል ወዘተ ተፈፅሞል፡፡ ይህ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት የተፈጸመ ወንጀል  በነጻና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ እስካልቀረቡ ድረስ ህዝቡ ለሰላማዊ ህዝባዊ እንቢተኛነት ሥራ ማቆም፣ ቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ በተፎካካሪ ፓርቲዎች መጠራት ይኖሩበታል እንላለን፡፡
 • የታሠሩት የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበር እንላለን፡፡ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ እንዲሁም ልደቱ አያሌው፣ ይፈቱ!!! የአስራት ጋዜጠኞች በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብር፣ ምስጋናው ከፋለኝ፣ ዬናታን ሙሉጌታ ይፈቱ

 

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዐብይ አህመድ  ሪፓብሊካን ጋርድ ገነባ!!! ለህዳሴ ግድብ የፌዴራል ጋርድ ልዩ ኮማንዶ ጦር ከሁሉም ክልሎች የተወጣጣ ጦር መገንባት አስፈላጊ ነው እንላለን !!!››

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዘርና የኃይማኖት ፍጅትን ማስጠበቅ ያልቻለ መንግሥት ስለሆነ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፀጥታና ደህንነት ማስጠበቅ አይችልም!!! እውቀትም ብቃትም

 

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.