እነዚህ አቢያውያን እንደዚያ ቀልደኛ እረኛ እንዳይሆኑ እፈራለሁ! – አምባቸው ደጀኔ

abiy“በጎቼን ቀበሮ በላብኝ” በሚል የውሸት ወሬ መንደርተኛውን እያስደነገጠ ሲደርሱለት ይስቅባቸው የነበረውንና በኋላ ግን ነገሩ እውነት ሆኖ የቀበሮ መንጋ በጎቹን ሲገነጣጥልለት ቢጮህ የሚደርስለት ያጣውን እረኛ የማያስታውስ በተለይ ምራቅ የዋጠ ዜጋ አይኖርም፡፡

የአቢይ አህመድን ሀሰተኛ ነቢይነት በተመለከተ ብዙ ተብሏልና አሁን አላነሳም፡፡ ሰሞኑንም አንድ ታዛቢ እነዚህን የመሪያችንን ቱሪናፋዎች ሰብሰብ አድርጎ ኢትዮሪፈረንስ ድረገጽ ላይ አውጥቷቸዋልና እዚያ ላይ ማየት ይቻላል፡፡

“ካለበት የተጋባበት” እንዲሉ በትናንትናው ዕለት ከንቲባዋ ተናገረችው የተባለው የአምስት ዓመት ዕቅድ ግን በአስፈጋጊነቱ ወደር የለውምና በርሱ ላይ ትንሽ ማለት ወደድኩ፡፡ ይህ የአክራሪ ኦሮሞዎች አገዛዝ ሥርዓት ልክ እንደቀደመው የወያኔዎች አገዛዝ ሁሉ ኅልውናው የቆመው በውሸት ወሬና በሀሰት መረጃ ላይ ነው፡፡

“በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የአዲስ አበባን ሥራ አጥ ቁጥር ዜሮ እናደርጋለን፡፡” ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡፡

በዚህ ንግርት ማለቴ ንግግር ያልሳቀ ምንም ነገር ሊያስቀው አይችልም፡፡ ይህን መሰል ዕቅድ አደጉ የተባሉ ሀገሮችም አያደርጉትም፤ ለሆነ  ስህተት የሆነ ቀዳዳ ወይም ክፍተት ይተዋሉ፡፡ ማይምነትና ድንቁርና ግን እስከዚህ ድፍረት ይሰጣል፡፡ ከዜሮ በፊት እኮ ብዙ አማራጭ ቁጥሮች ነበሩ፡፡ በሲሦ፣ በሩብ፣ በግምሽ … የሚባል ነገርም አሉ፡፡ ተንደርድሮ ግን ዜሮ አስገባለሁ ማለት ዕብደት ነው፡፡ ውሸት መልክና ልክ አለው፡፡ ግን  በውሸታምነትና በቆርጦ-ቀጥልነት ከአለቃው ምንዝሩ እያስከነዳ የመሄዱ ምሥጢር አልገባህ ብሎኛል፡፡ የአንድ ዘመን መሪዎች በሥነ ቃል እንደሚነገረው ልክ እንደባልና ሚስት ሁሉ ከአንድ ምንጭ የሚቀዱ ናቸው ማለት ይሆን?

የውሸት አስተማሪ አባቷ አቢይ በዚያ ሰሞን ከአምስት ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከሉንና ይህም መጠን ዓለም በአንድ ዓመት ከምታጣው አንድ ሦስተኛውን እንደሆነ ቅንጣት ሳያፍር ተናግሯል፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን በየትኛው ጥናቱ እንዳረጋገጠው ባላውቅም ያን ያህል መጠን ያለው ችግኝ አሜሪካም ሆነች ቻይና እንዳልተከሉ ገልፆኣል፡፡ አዎ፣ ውሸትንና ቅራሪን ጭልጥ ነው፡፡ አቢይ የሚያፍረው እውነትን ቢናገር ነው፡፡ በስህተት እውነትን ቢናገር የሚያቅረው ይመስለኛል፡፡

አሁን የኔ ፍራቻ – እነዚህ አቢያውያን ሳት ብሏቸው እውነት ቢናገሩ ማን ያምናቸው ይሆን? ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡

የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ብአዴን አማራን አጋድሞ እያረደው ነው፡፡ ብአዴን በሠርጎ ገቦች እንጂ በአማራ የሚመራ ድርጅት አይደለም፡፡ በዚያ ውስጥ ያላችሁ አማራ ነን የምትሉ ምንም መልካም ነገር ለሀገር መሥራት ካልቻላችሁ በቶሎ ራሳችሁን ለዩ፤ ግለ-ታሪካችሁንም ከውርደት አድኑ፡፡ በዚህ ወንጀለኛ ድርጅት ውስጥ ሆናችሁ በኋላ ማቄን ጨርቄን ብትሉ ታሪክ አይሰማችሁም፡፡ “እንዲህ ላደርግ ብል እንዲህ ተብዬ፤ እንዲህ ላደርግ ስል እንዲህ ሆኖብኝ…” ማለቱ አያዋጣምና አሁኑኑ ከዚህ ወንጀለኛ ድርጅት፣ ከዚህ የከሃዲዎች ስብስብ፣ ከዚህ የድኩማንና የሆዳሞች ጥርቅም፣ ከዚህ የኦህዲድና የወያኔ ተላላኪ ወንጀለኛ ተቋም በአፋጣኝ ውጡ፡፡ ላስቲክ ሆዳችሁ በልቶ አይጠረቃምና ለሆዳችሁ ስትሉ አማራን እያስፈጃችሁ ያላችሁ የብአዴን አባላት ዛሬውኑ ተመለሱ፡፡ ነገ ጊዜ ላይራችሁ ስለሚችል አሁንን ተጠቀሙባት!

ፀረ አማራውን ሽመልስ አብዲሣን ባህር ዳር ወስዶ መሸለም ምን ይባላል? በመተከልና በልዩ ልዩ ሥፍራዎች የሚያልቁ አማሮችን ዜና እንኳን እንዳይዘገብ መከልከል ምን ይባላል? አማራና ኦርቶዶክስን ለመፍጀት አራት ኪሎ ለተሰየመ የሰይጣን መንግሥት አድሮ ሕዝብን መፍጀት የዞረ ድምሩ ምን ሊሆን እንደሚችል መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ አልኩ ለማለት አልኩ እንጂ ክፉ ዐመል ካላስገደለ እንደማይለቅ አጥቼው አይደለም፡፡ መልምም የጭንቅ ዘመን ያድርግን!

 

 

3 Comments

 1. አምባቸዉ በሁለቱም ሀሳቦች የሰጠኸዉ ምልከታ መልካም ነዉ እኔን ደግሞ የገረመኝ ከነዚህ ሰዎች የተሻለ ሹመኞች አጥቶ ነዉ ወይስ ምን ታመጣላችሁ የሚለዉ ነዉ? እነዚህ ሰዎች ከእኛ ይልቅ እሱኑ ወደ ጥልቁ የሚወስዱት ናቸዉ በሀሳብ አይረዱትም ሀሳብም የላቸዉም ተናግረዉ ሰዉ አያሳምኑለትም ዉስጣቸዉ ምንም ስለሌለ ያላቸዉ ነገር ቢኖር እራሳቸዉን ለጊዜዉ ኦሮሞ ነን ሁሉም ይገባናል ከማለታቸዉ በስተቅረ ከሁሉም ነገር ሌጣ ናቸዉ። ለጊዜዉ ያልኩት የዘረ መል ምርመራ ይደረግና የኦሮሞነታቸዉም ትርክት ወደ ፊት ሊቀር ይችላል የሚል ግምት ስላለኝ ነዉ። መቼም እነሱንም እኛንም እያሞኙ አይዘልቁም ትክክለኛ ቁጥራቸዉም መቼም ሳይንስ አይዋሺም 6 ሚሊዮን በመሆኑ።
  አብይ ከ110 ሚሊዮን ህዝብ ይረዱኛል ብሎ የመረጣቸዉ (አባ ዱላ ገመዳ፤ሌንጮ ባቲ/ለታ፤አርከበ እቁባይ፤አዳነች ሀቤቤ፤ታከለ ኡማ፤ሺመልስ አብዲሳ፤ሱሌማን ደደፎ፤ሬዱዋን ሁሴን፤ንጉሱ ምናምን በጓሮ በር ደግሞ አረጋዊ በርሄ፤ብርሀኑ ነጋ፤ዲማ ነገዎ፤አህመዲን ጀበል እስራኤል ዳንሳም አለ መሰል… እያለ ይቀጥላል። አረ ዶ/ር አብይ አብዛኛዉ የሚጽፈዉ የሚንገበገበዉ ኢትዮጵያዊ አገር አገር ሁና እንድትቆይ እንጂ ለፖለቲካ አላማዉ አድርገህ አጣመህ አትመልከተዉ። ከዚህ በዘለለም ላንተ በማሰብ ነዉ እነዚህ ሰዎች እንኳን ለሀገራዊ ግምባታ ሊረዱህ ቤታቸዉንም ያልገነቡ ሰዎች ናቸዉ ከማንም በላይ ይዋል ይደር እንጂ መከራዉ ላንተ ነዉ። ከላይ ትግሬ ቀን ይጠብቅልሀል ደቡብ አባዱላና ጁዋርን ልከህ ያተራመስከዉ ጥርስ ነክሶብሀል፤የአማራዉን አናንሳዉ በመላዉ ሀገሩ እንደ አዉሬ ሲታደን አላየሁም እያልክ ታላግጥበታለህ ወይም ደግሞ ይበሉት እያልክ ነዉ። ኢሳይያስ አፈወርቅ እንኳን ላንተና ለጓደኞቹ ለልጁ የማይሆን አረመኔ ነዉ ከጀርባህ ያሰበዉን አስቦብሀል። አረ ወዳጂህ ማን ሊሆንን ነዉ ለነገሩ አስተካክላለሁ ብትልስ ለመመለስ ትችላለህ ወይ? ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ብለህ የታፈረች የተከበረች ኢትዮጵያን ልታመጣልን ነዉ ስንል ነገሩ ሌላ ሆነ።
  የብአዴን ጉዳይ እንዲህ ባንድ ብጣሽ ወረቀት ወይም በአንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራም የሚዳሰስ አይደለም በክልሉ የሚኖር ወጣት ምን እንደተደገሰለት ተረድቶ ዝግጅቱን ያጣድፈዉ እንግዲህ 40 አመት ጠብቋል ምንም ጠብ ያለለት የለም አሁን ደግሞ አበረ አዳሙን የብርሀኑ ነጋን ሰዉ ሹመዉለታል ምርጫ ከተካሄደ እነዚህ ሰዎች እስካሉ ድረስ ማንም የአማራ ድርጅት አማራ ክልል 5% የምርጫ ወረቀት አገኛለሁ ብሎ ባይጠብቅ ይሻለዋል። የአማራ ወጣት መሪዎቼ ለምን ተገደሉ ብሎ ይጠይቅ። አምባቸዉ እንደ ሁልጊዜዉ ስለ ጥልቅ ምልከታህ እናመሰግናለን።

  • አመሰግናለሁ ሠመረ ስለገምቢ አስተያየትህ። ይህ መቅሰፍት በርግጠኝነት ያልፋል። የወጣ የሚወርድ፣ የወረደም የሚወጣ የማይመሥላቸው ገልቱዎች ይህ ዘመን እንዳለ የሚቆይ ሊመሥላቸው ይችላል። ግን የፍርድ ቀን መቅረቡን በብዙ ምልክቶች እያየን በመሆኑ ተሥፋችን የለመለመ ነው። እርግጥ ነው – ነፃነት ውድ ናት። ለዚህም ነው ንጹሓን ዜጎች ወደውና ፈቅደው ባልተወለዱበት የዘር ሐረግና በሃይማኖታቸው ምክንያት በዐረመኔው የናቡከደነፆር የአቢይ ቅልቦች እየተጨፈጨፉ ያሉት።…

 2. የአማራ አደገኛ እና አጥፊው ጠላቶች በቅደም ተከተል ሲገለጹ፤
  1ኛ፤ ኢህዴን/ብአዴን የትህነግ ምንጣፍ ጎታች ወይም አዴፓ/ኦነግ የኦነግ ምንጣፍ ጎታችና የአብይ ገረድ
  2ኛ፤ ጉማሬው ከርሳሙ እና የአይምሮ ዝግመት ያለበት ደመቀ መኮንን
  3ኛ፤ ጭቃ ፊቱ የኦነግ ካልሲና ሙታንታ አጣቢ ቤት አጽጅ ተመስገን ጥሩነህ
  4ኛ፤ መሃይሙና የሳጥናኤል አምልኮ/መለስ ዜናዊዝም/ ተክታይ አገኘሁ ተሻገር
  5ኛ፤ ወዘተ
  6ኛ፤ የበታችነት እና የዝቅተኛ አስተሳስብ ሲንድሮም ተጠቂ የሆንችው ወያኔ/ትህነግ
  7ኛ፤ በተመሳሳይ ሲንድሮም የተጠቃው ኦነግ
  8ኛ፤ ድህነት ናችው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.