ትልቅ ጥያቄ? በኢትዮጵያ የብር ኖት ላይ ላሊበላ አለ?  ገንዘብ ለማግኘት ግን ዋና ነው! – ሰርፀ ደስታ

ብር ኖት ተቀየረ ተብሎ በአንዳንዶች ዘንድ ልክ ተዓምር የተደረገ አስመስለውት አየሁ፡፡ ይሄ ሃሳብ ገና ሪፎርሚሰት ነን ብለው እንደገቡ ነበር እንዲያደርጉት የተጠየቁት፡፡ ምን አልባት እንግዲህ ሌቦች ወደ ዶላር ጨርሰው እስከሚቀይሩ ጊዜ ለመስጠትም ይሆናል፡፡ የሆነ ሆኖ የብር ዘረፋው ግልጽ ነው፡፡ 14 ሚሊየን የአንበሳ አውቶቢስ ብር በአንድ ተራ ሰው ወጣ የተባለ እለት ነው የኢትዮጵያን የባንክ አሰራር የታዘብኩት፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥው እንዳለው ከባንክ የሚወጣ ገንዘብ ገደብ መመሪያም ከብር ኖቶች ጋር አብሮ በአዲስ መልክ ሥራ ላይ እንደሚውል  ነው፡፡ ይሄ ጥሩ እርምጃ ነው፡፡ ሲጀምር አንድ ህጋዊ የሆነ ድርጅት ገንዘብ በጆንያ ከቦታ ቦታ የሚያንቀሳቅስበት ምክነያት ሊኖር አይችልም፡፡ ክፍያዎች ሁሉ በባንከ በኩል ለተቀባዮች እንዲደርስ ማድረግ ይቻላልና፡፡ ሌላው አሁንም ለግለሰብ በቀን 200 ሺ የተባለው ትክክል አይመስለኝም፡፡  በግለሰብ ደረጃ ከ50 ሺ በላይ ሊያውም ሲበዛ ነው ማውጣት አስፈላጊ አደለም፡፡

birrየገንዝብ እንዲህ በጆኒያ አየር በአየር መዟዟር ከምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራው ባሻገር ትልቅ የደህንነት ችግር እየፈጠረ ያለውም ይሆው ነው፡፡ አብዛኛው የጆንያ ገንዘብ አዟዟሪዎች እኔን እንደሚገባኝ የመንግስት ባለስልጣናት ከለላ የሚያደርጉላቸው ናቸው፡፡ ገንዘብም ሆን ተብሎ ከባንክ እንዲያወጡ እየተደረገ፡፡ እንግዲህ ይሄ አጋጣሚ ምን አልባትም ወንጀለኞችንም ለመያዝ ያስችል ይሆናል ቁርጠኝነቱ ካለ፡፡ መቼም ገነዝቡ በሶስት ወር ተጠናቆ ከተቀየረ የጆንያ ብር አዟዟሪዎች ገንዘቡን በአዲሱ ኖቶች ለመቀየር መሞከራቸው አይቀርም፡፡ እንግዲህ ከታወቀ የገቢ ምንጭ ያላቸው ወይም ከሚገመት በቀር ትልልቅ ምንጩ የማይታወቅ ገንዘብ ለመቀየር የሚሞክሩትን በዛው ምርመራ ማካሄድና የገነዘባቸውን ምንጭ ማጣራት ተገቢ ነው፡፡ ቢያንስ የተወሰነ ብር እስካሁንም በዶላር ያልተሸጠ ካለ ማለት ነው፡፡ ለነገሩ ለኦሮሞ ባለስልጣናትና ወያኔ ቀድመው አስበው ገንዘቡን ወደ ዶላር ቀይረው እንሚሆን እንገምታለን፡፡ ለዚህ ደግሞ ጠ/ሚኒስቴሩ ሳይቀር አንዱ እንደሚሆን እንገምታለሁ፡፡ እንገምታለሁ ሲባል ተራ ግምት አደለም፡፡  ጊዜ የተሰጠውም እንዲህ ያለ ማስተካከልና አስተማማኝ የሆነ ዘረፋ እስከሚካሄድ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡

ከገንዘብ ቅያሬው ጋር ግን እንድ እኔ የታዘብኩት ነገር ቢኖር የታሪክና የሰላም ምልክት ናቸው የተባሉ አንዳንድ ከዚህ በፊት ያልነበሩ ምስሎች በኖቶች ላይ ተደርገው አይቻለሁ፡፡ በአገሪቱ በአስደናቂነቱና በታሪካዊነቱ የሚታወቀውና ትልቁ የቱሪስት ገንዘብ ማስገኛ የሆነው ላሊበላን ግን ማየት አልቻልኩም፡፡ የላሊበላ ምስል በቀደሙት በየትኛዎቹ ኖቶች እንዳለ አላውቅም፡፡ አክሱምና ጎንደር አሉ፡፡ በኃይለስላሴ ኖት ላይ በእርግጥም የላሊበላ ቤተጊዮርጊስ ሕንጻ አንዱ ነው፡፡ ተዓምረኛው ንጉስ ዛሬ ዋጋ ለማግኘት ሁሏም እኔ እኔ የምትለውን የሕዳሴ ግድብንም በሃምሳ ብር የኢትዮጵያ ኖት ላይ አስቀምጠውት እናያለን፡፡ ገራሚ ነው! ራዕይ ያለው መሪ ነብይ ይሆናል ለአገሩ!  ከዛ በኋለ በደርግ ጊዜ የነበሩ ኖቶችን ለማየት ሞክሬ ሁሉንም ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ ምን ምን እንደነበረ አላውቅም፡፡ አሁን ያለው  ላሊበላን የሚያሳይ ኖት  መኖሩን እንጃ፡፡ ሚስጢራዊ ምስል ካልሆነ፡፡ አሁን አዲስ ታተመ  የተባለው ከታሪክ የሐረር ግንብን አካቷል፡፡ ላሊበላን ግን አላየሁም፡፡ የእትሞቹን ሁሉንም ገጽ ስላላየሁ መጠየቄ እንጂ አልተካተተም የሚል ድምዳሜ መስጠት አልችልም፡፡ ላሊበላ ሳይካተት ሐረርን ወይም ጎንደርን አልተካተተ እንደሆነ ግን ጉዳዩ ቀደም ብዬ በሌላ ርዕስ ካነሳሁት የጸረ-ኦርቶዶክስነት አንዱ ማሳየ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ በየትኛውም መስፈርት ጎንደርና የሐርር ግንብ ከላሊበላ የጥበብና የታሪክ ልዕልና ጋር ሊወዳደሩ የሚችሉ አደሉም፡፡ ጎነደርም ሆነ ሐረር ግንብ ከተራ የድንጋይ ካብ የዘለለ ጥበብ የሚታይባቸው አደለም፡፡ እነጎንደር ግንቦች ሲሰሩ በአውሮፓ ዛሬ ውብ የምንላቸው ከተሞች ተሰርተዋል፡፡ የጀጎል ግንብ የሚባለውም ያው ነው፡፡ በዓቅማቸው የዘመናቸው ታሪክ ምልከት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከላሊበላ ጋር ሲነጻጸሩ ግን ተራ የድንጋይ ካብ ከመሆን ያለፈ ታሪካዊም ጥበባዊም እሴት አላይባቸውም፡፡

ላሊበላን ኢትዮጵያውያን ሰሩት ሲባል ሌላ ተረት ያወራሉ፡፡ የእነሱን ተረት ታሪክ የእኛን እውነት ተረት እያደረጉ ብዙ ታሪክ አበላሽተዋል፡፡ ላሊበላ ከእነ አብረሀ አጽብሐ ጀምሮ የነበረ ጥበብ ትልቅ ደረጃ የደረሰበትን በቤተመንግስቱ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ የነበረ እንጂ የሌሎች ጥበብ እንዳልሆን ተመሳሳይ የሆን በዘመናት ርዝመት ሲሰሩ የኖሩ በትግራይ ተራሮች ላይ ያሉ ተመሳሳይ ሕንጻዎችን ማስተዋል በቂ ነው፡፡ ይሄ የ60 ለፈረንጅ የተሸጠ ጭንቅላት የያዘ ትውልድ ሲያፈርስ የነበረውን ታሪክ ዛሬ ላይ አስተማማኝ በሆኑ መረጃዎች እየመለስን እንገኛለን፡፡ ማንም እንደፈቀደ የሆነ ፈረንጅ ስለነገረው የሚያወራው ታሪክ ከዚህ በኋላ አይኖርም፡፡ እድሜ ለቴክኖሎጂ፡፡ ላሊበላን የሚመስል አሰራር በየትም ዓልም የለም፡፡ በኢትዮጵያ ግን ከትግራይ እስከ ደቡብ አዳዲ ማሪያም ድረስ ዘልቆ አሻራውን እናያለን፡፡ ይልቁንስ ጎንደርም ሆነ ሐረር የኢትዮጵያውያን ሥራ ድንጋይ ከማቀበል ያለፈ እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ ጎንደር በፖርቺጊዞች ሐረር ደግሞ በቱርኮችና ሌሎች ሙስሊም አከራት የተሰራ በመሆኑ፡፡  ይሄ ግልጽ የሆነ ታሪክ ነው፡፡ እንግዲህ በባርነት ተቀጥሮ ድንጋይ ማቀበልና ከራስ በወጣ ጥበብ የተሰራን ሥራ ማወዳደር በእነ እንቶኔ የኢትዮጵያን ልክ  እይታ ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡

በሌላ መልኩ፣ በእርግጥም ከታሪካዊና ጥበባዊ ልዕልናው የተነሳ ኢትዮጵያን ለማየት ከሩቅ የሚያስቡ ቢኖሩ ላሊበላን ለማየት እንጂ ጎንደርን ወይም ሐረርን ለማየት ብሎ የሚመጣ ምን ያህል እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ሊያውም ካለ ነው፡፡ ሲጀምር ምንም የሚታይ ነገር የለውም፡፡ ጎንደሬዎችን እንዳላበሳጭ እንጂ የጎንደር ግንብ  የሚያየው ላሊበላን፣ ራስዳሸንን ብሎ የመጣ እግረመንገዱን የሚያይ ጎብኝ እንጂ ጎንደርን ብሎ የሚመጣ አይደለም፡፡ ሌላው ቀርቶ በጥበቡም በታሪኩም የሚደነቀው አክሱም ከላሊበላ ጋር ሲነጻጸር ያንሳል፡፡ ዓለም ወደ ኢትዮጵያ ሊገበኘው የሚመጣን ታሪካዌ እሴት ትቶ የምናምን ዘመን ተራ የድንጋይ ካቦችን እንደልዩ የአገር ክብር በብር ኖቶች ላይ ማስቀመጥ አንድምታው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ ይሄን ሁሉ የምለው ካልተቀመጠ ማለቴ ነው፡፡ በጉልሕ አንዱን ብቻ ሳይሆን የተለያዩትን የላሊበላን ሕንጻዎች በኢትዮጵያ ብር ኖቶች ላይ ማስቀመጥ ከክብርም በላይ ያው ትልቁን የጎብኝ ገንዘብ ከማስገኘቱም ጋር ትልቅ ማስተዋወቅም ነው፡፡  ሆኖም አሁን በአየሁት ደረጃ በአንዱም ኖት ላይ ጎልቶ ይቅርና በጨረፍታም የትኛውንም የላሊበላ ሕንጻ ማየት አልቻልኩም፡፡  በአንዱም ከሌለ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነን የምትሉ የቱንም ያህል ገንዘብ እያመጣ ያለው ለአገር ቢሆን የእድገታችን ማነቆ ነች ያሏት ቤተክርስቲያን አሻራ በመሆኑ በብር ኖቶቹ ላይ ማኖርና እውቅና መስጥ እንዳልፈለጉ በደንብ አስተውሉ፡፡ ምና ዓልባት ኢሬቻ የሚያከብሩበትን ሆራን አስበውት ይሆናል፡፡  ይሄን እውነት ጠይቁ፡፡ አመሰግናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.