ለኖቤል ሎሬት ዐብይ አህመድ የሻሸመኔው የዘር ፍጅት፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተደገመ! ደም በገበታ ለልማት! (ክፍል ሁለት) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

et 77‹‹አንድ ዘር የበላይ ሌላው ዘር የበታች የሆነበት ፍልስፍና እስካለ  ድረስ በመጨረሻውና ለዘለቄታ የሌለው ዋጋቢስና ቀሽም አስተሳሰብ ውጤቱ ሁሉም ቦታ ጦርነት ይሆናል፡፡  እናም በአንድ አገር  የመጀመሪያ ደረጃ ዜጋና ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ  የሚባል ነገር እስካለ ድረስ፣ ሰው በቆዳው ቀለም እስከተፈረጀ ድረስ የዓይኖቹ  ቀለማት በጣም አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ›› (ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ)

“Until the philosophy which holds one race superior and another inferior is finally and permanently discredited and abandoned, everywhere is war. And until there are no longer first-class and second-class citizens of any nation, until the colour of a man’s skin is of no more significance than the colour of his eyes. (Quote by Haile Selassie I)

ለኖቤል ሎሬት ዐብይ አህመድ የሻሸመኔው የዘር ፍጅት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተደገመሎት!!! የሪፓብሊካን ጋርድ ዎ አዲስ አበባ ላይ ቲያትር ከሚያሳይ ቤኒሻንጉል  ጉሙዝ ዜጎችን የሚያርዱ፣ ሴቶች የሚደፍሩ፣ ህፃናትን የሚገሉ ደም ጠጭ አጋንቶችን የማይፋለሙት ለምንድነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ደሞዝ እስካልከፈለው  የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ ሠራዊት  የህዝብ ፀጥታና ደህንነት  አያስጠብቅም፣ እባክዎ ዩኤን አርሚ እንዲሆን ለምኑለት፡፡  እስከዛ  ደም በገበታ ለልማት !!!

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡-  ከዘር ፌዴራሊዝም ወደ ደም ፌዴራሊዝም !!!  አጋንቱን አራጅ ከብልቃጡ ውስጥ ይዱሉት!!!

‹‹የአማራ ማስሚዲያ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ዜና መሠረት ጳጉሜ አንድ ቀን 2012ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዘር ተኮር ፍጅት (ጆኖሳይድ) በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ኤባር ተብሎ የሚጠራ ቀበሌ አማራና አገው ሰማንያ ዘጠኝ ተወላጆች ላይ በስም ዝርዝር ተጠቁመው አሰቃቂ ዘር ተኮር ግድያ ተፈፅሞል፡፡  በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ውስጥ የቤሻንጉል  ህዝብ ንቅናቄ (ቤህን)፣ ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉዴን) ከ ኦነግ ሸኔ ጋርና ከህወሓት ስውር እጅ ጋር በመጣመር የዘር ፍጅቱን አድርገዋል፡፡ የወረዳው ፖሊስ አስቀድሞ ቀበሌውን ለቆ ወጥቶ ነበር፡፡  በአለፈው ጊዜም ሃያ አምስት ሽህ የአማራና አገው ተወላጆች ተፈናቅለው እንደነበር የታወሳል፡፡ በ1983ዓ/ም ኦነግና ሻብያ የዛሬ ሠላሳ አመት በቤኒሻንጉል  አሶሳ ሆስፒታልና ትምህርት ቤት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው እንደተቃጠሉ በታሪክ ይታወሳል፡፡››1

‹‹ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡-  በመለስ ዜናዊ መንግሥት የተፈጠረ ተጠፍጥፎ ከጎጃም ክፍለሃገር ከነበረው መተከል እናም ከወለጋ ክፍለሃገር ተወሰዶ ክልል የሆነ ነው፡፡  ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሲሆን ከጎጃም ክፍለ ሃገር ከአባይ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኝ ሲሆን ከወለጋ ክፍለሃገር  ከአባይ ወንዝ በስተ ደቡብ የሚገኝ ቦታን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማለት አሶሳ ዋና ከተማ ተደረገች፡፡ በማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ 2007 እኤአ በተደረገ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መሠረት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የህዝብ ቁጥር 784345 ነበር፡፡ ከዚህ ውስጥ የብሄር ብሄረሰብ ስብጥር አማራ (25.41%)፣ በርታ (21.69%)፣ ኦሮሞ (13.55%)፣ ሺናሻ (7.73%)፣ አገው አዊ (4.22%) ነበር፡፡ ዋናዎቹ የክልሉ ቌንቌ በርታ (25.15%)፣ አማርኛ (22.46%)፣ ጉሙዝ (20.59%)፣ ኦሮሞ (17.69%)፣ ሺናሻ (4.58%) እና አዋንጊ (4.01%) ነበር፡፡ ሃይማኖትን በሚመለከት (44.7%) ኦርቶዶክስ ክርስቲያን፣ (33.3%)ሙስሊም፣ (13.53%) ፕሮቴስታንት፣ (7.09%) ባህላዊ እምነት ተከታዬች የሚኖሩበት ክልል ነው፡፡ ››2 ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ከአማራ፣ ከኦሮሚያ እንዲሁም ከሱዳን ጋር ይዋሰናል፡፡  ቤሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ በከፍተና ድህነት ውስጥ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡  በቤሻንጉል ጉሙዝ ህገ-መንግሥት መሠረት ሃገሩ የመጤና ሠፋሪ የሆኑትን አማራ፣ኦሮሞና አገው ሁለተኛ ዜጋ ሲሆኑ በአንደና ዜግነት  የበርታ፣ ሺናሻ፣ ጉሙዝ፣አዋንጊ  እንደሆኑ በህገ መንግሥቱ ተፅፎል፡፡

የዘውግ ፌዴራሊዝም በኢትዩጵያ፣ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የዘውግ ፌዴራሊዝም ማኒፊስቶ (የወያኔ ህገ መንግስት) በ1983 ዓ/ም በቌንቌ፣ ላይ ተመስርቶ ለሃያ ዘጠኝ አመታት በህዝብ ላይ የተጫነበት የኢኮኖሚ፣ ጆግራፊ፣ የባህል፣ የስነልቦና፣ ወዘተ ልዩነቶችና   በዘር ላይ በተመሰረተ ክፍፍል ብዙ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ከቀያቸው ተሰደዋል፣ ብዙ ኢስብዓዊ ድርጊቶች ተፈፅመዋል፡፡ ዛሬም በወያኔ የተቀበረ የጊዜ ቦንብ እየፈነዳ ይገኛል፡፡ በሶማሌ ክልል አንድ ሚሊዩን ህዝብ ተፈናቅለሎል፣ ከኦሮሞም ክልል ሶማሌዎች በመቶ ሽህ ተፈናቅለዋል፡፡ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አማራዎች መጤ ተብው እየተፈናቀሉ ይገኛሉ፣ በኦሮያም ሻሸመኔ አማራዎች የዘርኛ የኃይማኖት  ፍጅት (ጆኖሳይድ)  ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በደቡብ ክልል በጌዲዮና በኦሞ ክልል ጉጂ ዞኖች መካከል ግጭት ታስቅሶ በሺዎች ተፈናቅለዋል እንዲሁም በጉራጌ ዞን በጉራጌና ቀቤና ማህበረሰቦች ግጭት ተከስቶል፣ በሲዳማና ወላይታ ህዝብ መኃል ግጭት ተከስቶል፡፡ በትግራይና አማራ ክልሎች በወልቃይት ጠገዴ ግዛት ውዝግብ ቀጥሎል፣ በአማራና አፋር ክልል ግጭቶች ይስተዋላሉ፣ በሃረሪ ክልል የኦሮሞ ፣ሱማሎና አማራ ህዝብ የታፈነ ብሶት መፈንዳቱ አይቀሬ ሆኖል፡፡ በኢትዮጵያ የሃገር ግንባታ የነገሥታት ታሪክ አስተዳደር ‹‹ሃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው!!!›› በሚል ቃል ኪዳን የተሳሰረና ህዝቡ በሁሉም የሃገሪቱ ግዛቶች ንብረት አፍርቶና ሠርቶ ይኖርበት የነበረ ወርቃማ ዘመን ያሳለፈ ህዝብ ነው፡፡ ›› የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ከሰውነት ጥያቄ ወደ የማንነት ጥያቄ ተሸጋገሩ፡፡

የዘውግ ብሄርተኛነትና የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ተቆም ግንባታ (ብርሃኑ ጉተማ ባልቻ)

‹‹ በዘውግ ብሄርተኛነት ላይ የተመሠረተ ዋነኛ መሥፈርት  የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ፌዴራላዊ መዋቅር መስመር ነው፡፡ የዘውግ ብሄርተኛ ፌዴራሊዝም አደረጃጀት የሚተዳደሩ አገራቶች የሶብየት ህብረት፣ ዩጎስላቪያና ቺኮዝላቫኪያ ዘውግ ተኮር በቌንቌ ላይ የተመሠረተ  ፌዴራሊዝም ዘለቄታዊነት ተስፋ መቁረጥ  አስከትሎባቸዋል፡፡  በተፃራሪ ደግሞ ዘውግ ተኮር በቌንቌ ላይ የተመሠረቱ ፌዴራሊዝም ውጤታማ የሆኑ ህንድና ሲዊዘርላንድ የመሳሰሉት አገሮች በዘውግ/በዘር በተከፋፈለ ህብረተሰብ ውስጥ ዘለቄታዊነት ያለው ሃገረ መንግሥት መገንባት እንደሚቻል አሳይተዋል፡፡  የዘውግ ብሄርተኛ ፌዴራሊዝም ሃሳብ ሁለቱም አመለካከቶች ደጋፊና ነቃፊ ተችዎች የእራሳቸው ማስረጃና መረጃ በማጣቀስ ትክክለኛ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ የዘውግ ፌዴራሊዝም ደጋፊዎች ሃሳብ መሠረት፤- (1) የማህበረሰቡን ልዩነትና ክፍፍልን ይቀንሳል፣ (2) የእራስን በእራስ የማስተደዳደር መብትንያመቻቻል ፣ያረጋግጣል፣ (3) የዘውጌ ብሄርተኞች በሰላም አብሮ የመኖር መርህ ህብረት ያበረታታል፣ (4) የዘውጌ ብሄርተኞች የመገንጠል ጥያቄ ዝንባሌዎች ይቀንሳል››

በተቃራነ ደግሞ የዘውግ ፌዴራሊዝም ነቃፊዎች ሃሳብ መሠረት፡-(1) የዘውግ/ የዘር /ብሄር ልዩነቶችን በኢንስቲቲዩሽን ደረጃ ያስፋፋል ፣ (2) የግለሰብ የዜጎች መብቶች ያቀጭጭል፣ (3) የማዕከላዊ መንግሥት ስልጣን ለክልሎች መንግሥታት  ያከፋፍላል፣ ያልተማከለ ሥርዓት ይገነባል፣ (4) የዘውጌ ውድድር የዜሮ ድምር ጨዋታ   (5) የዘውጌ ፌዴራሊዝም አደገኛ ለሆነ የዘር ፍጅትና የዘር ማጽዳት መንስኤ አገር የመገነጣጠልና የማፍረስ ሂደት ይከውናል፡፡››

የማንነት ጥያቄ በኢትዩጵያ፣በኦሮሚያ ክልል ዛይ፣በአማራ ክልል ቅማንት፣ በትግራይ ክልል ራያና ወልቃይት፣ በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል ወለኔና ኮንሶን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ብሄር ብሄረሰቦች የንግድ መታወቂያ፣ የማንነት ጥያቄዎች መጨመር ዋናው ምክንያት የሚገኘው የፌዴራል መንግሥት የገንዘብ የበጀት ጥቅም ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑና በዛም ለብዙ የዘር አባላቶች የሥራ ዕድል የማግኘትና የደሞዝ ገቢ ምንጭ ዕድል ስለሚፈጥር የፊዴራል መንግሥት በሚያከፋፍለው በጀት የህብረተሰቡን ችግሮች ለመፍታት መንገድ፣ ትምህርት ቤት ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያ የመሳሰሉትን በመገንባት ስለሚያስችል ለዚህ ለመብቃት መታገል የግድና የህልውና ጥያቄ ይሆናል፡፡

‹‹የዘውጌ ብሄርተኛነት ፖለቲካ ባህል እና የማንነት ጥያቄ ፖለቲካ ዋናው አሽከርካሪ ሞተር በመሆን ለኢኮኖሚ ኃብት መቆጣጠሪያና ለፖለቲካ ሥልጣን መያዣ መሣሪያነት አገልግሎል፡፡ የፖለቲካ ትግል ቀስ በቀስ ወደ ዘውጌ ብሄርተኝነት ፍልስፍና ተቀየረ፣ በዘር ላይ የተመሠረቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ተፈጠሩ፣ በዘርና በብሄር ተኮር የሆኑ ክልላዊ መንግሥቶች ተመሠረቱ፣ የሃገሪቱ ድንበርና ግዛት በክልል መንግሥቶች ድንበርና ወሰን ተሸነሸነ፡፡ ይህ አዲስ ማህበራዊ ፖለቲካዊ አስተዳደር የብሄር ፌዴራሊዝም በመባል ይታወቃል፡፡ የዘውግ የብሄር ፌዴራሊዝም በአዋጅ በህገ-መንግሥት ሆኖ ፀደቀ፤  የሃገሪቱ ዋና መሰረታዊ  ህግ በመሆን ባህላዊ ህግ 1995 እኤአ ሆነ፡፡›› (ማሞና ፓፓዶ ፖውሎስ 2004፡ 9)

የማንነት ጥያቄዎች የመጨመር እንድምታ፣

{ሀ} ለክልልና ለፌዴራል መንግስታት የማንነት ጥያቄዎች ከአገሪቱ ከሁሉም አቅጣጫዎች እየጎረፉ ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶቹ በክልል ደረጃ መፍትሄ አግኝተዋል ቢባልም፣ ሌሎች ግን በይግባኝ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበዋል፡፡ ወለኔ፣ ዛይ፣ ኮንሶ፣ ራያና ወልቃይት በክልል ደረጃ የመጨረሻ ውሳኔ ገና ያላገኙ ናቸው፡፡ እንደ ቅማንት፣ መንጃና ኮንቶማ ያሉት ደግሞ በምክር ቤቱ በይግባኝ ከታዩት የሚካተቱ ናቸው፡፡ ለአንዳንድ ምሁራን በክልል ደረጃም ሆነ ለፌዴራል መንግስቱ ለማንነት ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሾች ወጥነት የሚጎላቸው ናቸው፡፡

{ለ} በሽግግሩ መንግስት ወቅት 63 ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለራሳቸው እውቅና ሰጥተው ነበር፡፡ ሕገ-መንግስቱ በ1987 ዓ/ም ሲፀድቅ 67 ደርሰው ነበር፡፡ በወቅቱ በደቡብ ክልል የነበረው ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቁጥር 46 የነበረ ሲሆን፣አሁን 56 ደርሶል፡፡ ነገር ግን እነዚህ አዳዲስ ብሄሮች ማንነታቸውን እንዴት እንዳገኙ መረጃ የለም፡፡

{ሐ} የማንነት ጥያቄዎች በአብዛኛው ለአዲስ ማንነት እውቅና በመጠየቅ፣ አዲስ አስተዳደር በመጠየቅ፣ ፍትሀዊ የሆነ የሃብትና የሥልጣን ክፍፍል በመጠየቅና በመሳሰለው ሊገለፅ ይችላል፡፡ የማንነት ጥያቄዎች በዋናነት የእውቅና ጉዳይ ነው፡፡ አንድ አካል እውቅና ሳይሰጠው መብት አይኖረውም፡፡ እውቅና ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

{1} በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {1.1} የስልጤ የማንነት ጥያቄ በደቡብ ክልላዊ መንግስት፣ የስልጤ ህዝብ በደቡብ ክልል ውስጥ ተከልሎ የኖረ ህዝብ ነው፡፡ ስልጤዎች ከጉራጌ የተለየ ማንነት ስላለን ተነጥለን ራሳችንን በራሳችን እንድናስተዳድር ይፈቀድልን ሲሉ ጥያቄዎች ለደቡብ ክልል አቀረቡ፡፡ የስልጤ ጉዳይ በ1992 ዓ/ም በደቡብ ክልል ውድቅ ሆኖ  በይግባኝ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀረበ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የስልጤ ማህበረሰብ በማንነቱ ላይ በመጋቢት ወር 1993 ዓ/ም በህዝበ ውሳኔው ውጤት ስልጤ ከጉራጌ ተለይቶ የራሱ ዞን ለማቆቆም በቅቶል፡፡{1.2} መንጃና ኮንቶማ የማንነት ጥያቄ {1.3} ኮንሶ የማንነት ጥያቄ {1.4} የቁጪ የማንነት ጥያቄ {1.5} የሲዳማ የማንነት ጥያቄ በሪፍራንደም አስረኛው ክልላዊ መንግሥት ሆነዋል፡፡ ለሪፈረንደሙ 750 ሚሊዮን ብር ወጭ ሆኖል፣ በገንዘቡ ለህዝብ የጉድጎድ ውሃ ቢቆፈርበት የተሸ ነው እንላለን፡፡  {1.6} የዎላይታ የማንነት ጥያቄ በሪፍራንደም አስራአንደኛው ክልላዊ መንግሥት ለመሆን በትግል ላይ ናቸው፡፡ {1.7} የጌዲኦ የማንነት ጥያቄ በደቡብ ክልላዊ መንግስት ይገኛሉ፡፡ ለክልላዊ መንግሥትነት አንድም ሰው መሞት አይገባውም!!!

{2} በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {2.1} የቅማንት የማንነት ጥያቄ በአማራ ክልላዊ መንግስት፣ የቅማንት ህዝብ በአማራ ክልል ውስጥ ተከልሎ የኖረ ህዝብ ነው፡፡የቅማንት ህዝብ በአማራ ክልል ከአማራ የተለየ ማንነት ስላለን ተነጥለን ራሳችንን በራሳችን እንድናስተዳድር ይፈቀድልን ሲሉ ጥያቄዎች ለአማራ ክልል አቀረቡ፡፡ የቅማንት ጉዳይ በ1992 ዓ/ም በአማራ ክልል ውድቅ ሆኖ  በይግባኝ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደቀረበ፣ በአማራ ክልል ምክር ቤት ጉዳዩን ዳግም ለማየት ተስማማ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመመካከር በመጋቢት 2 ቀን 2007 ዓ/ም ለቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር እውቅና ሰጥቶል፡፡ {2.2} የአርጎባ፣የአገው ህዝቦች፣ ምዕራብ አዊ የብሄረሰብ ዞኖች፣ የማንነት ጥያቄ በአማራ ክልላዊ መንግስት ይገኛሉ፡፡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ይፈታ!!! {2.3} ከጎንደር ጠቅላይ ግዛት በህወሓት የተወሰዱ ከፍታ ሑመራ፣ ወልቃይት፣ተገዴ፣ ጨለምት፤ ከወሎ ጠቅላይ ግዛት በህወሓት የተወሰዱ እንደመሃሪ፣ ወፍላ፣ ራያ/አዘቦ፣ አላማጣ፤ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ የነበረወች የአዲስ አበባ ከተማና የደራ ወረዳ ለኦነግ/ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ርስተ ጉልትነት በተላላኪው ብአዴን/አዴፓ ተላልፈዋል፡፡ {2.4} ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ ጠቅላይ ግዛቶች እራሳቸውን በእራሳቸው ማስተዳደር መብታቸው በትግላቸው መረጋገጡ አይቀሬ ነው እንላለን፡፡ በተለይ ተላላኪ የሆነው ኢህዴን/ ብአዴን/አዴፓ የነቀዘ ፈሪ ስብዕና ያላቸው መሪዎች የአማራ ህዝብን አንገት ያስደፉ ፍርፋሪ ለቃሚ መሪዎቹን እየተሸሙለት ስናይ አዘንን!!!

{3} በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {3.1} የራያና ቆቦ፣ በወልቃይት የአማራ የማንነት ጥያቄ በትግራይ ክልላዊ መንግስት፣ የአፋር የማንነት ጥያቄ በትግራይ ክልላዊ መንግስት፣ በደሜ፣ኢሮፕ፣ ጥያቄ በኤርትራ መንግሥትና በትግራይ ክልላዊ መንግስት፣ የወሰን ድንበር ግጭት ተከስቶል፡፡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ይፈታ!!!

{4} በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {4.1} የሲቲ ዞን የማንነት ጥያቄ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት፣በሶማልያና ኦሮምያ የድንበር ግጭት ተከስቶም ነበር፡፡ የተቀበረ ፈንጂ እዛም አለ!!!

{5} በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣{5.1} የኑዌር የማንነት ጥያቄ  {5.2} የአኝዋ፣ ንዌር፣ ማኦ፣ መጀንገር ፣ ኦፖ የማንነት ጥያቄ እራስን በእራስ የማስተዳደር መብት በማጎናፀፍ ይሻሉ፡፡

{6} በኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ {6.1} የዛይ የማንነት ጥያቄ በኦሮምያ ክልላዊ መንግስት {6.2} ወለጋ፣ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲ፣ አንቦ፣ ሸዋ፣ ሃረርጌ ወዘተ ጥያቄ በኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ራስን በራስ ማስተዳደር ይሻሉ፡፡

የዘውግ/የብሄርና ብሄረሰቦች የማያባራ ግጭቶች፣ በኢትዩጵያ ዘጠኝ ክልላዊ መንግስቶች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰት የማያባራ የድንበር ግጭት ምክንያት አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በጦርነት ቁም ስቅላቸውን እያዩ በምግብ እራሳቸውን እንዴት አድርገው ሊችሉ ይችላሉ? የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ስልጣን ከጨበጠ ከግንቦት 1983 ዓ/ም ጀምሮ በዘውግ ላይ በተመሰረተ የውሸት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ፌዴራልላዊ መንግስት የከፋፍለህ ግዛ አገዛዝ መዋቅር በመተግበር በሃገሪቱ ውስጥ የተከሰቱ የዘውግ/የብሄርና ብሄረሰቦች የማያባራ ግጭቶች የዕለት ተለት ክስተት ሆኖል፡፡ በስልጤና  በጉራጌ፣ በደቡብ ዋጋጎዳ የቆንቆ ግጭት፣ በሸኮና በመጀንገር ግጭት፣ በአኝዋክና ኑዌር ግጭት፣ በበርታና ጉሙዝ ግጭት፣ በጌዲኦና ጉጂ ግጭት፣ በኦሮሞና በአማራ ግጭት፣ በቦረናና ገሬ ግጭት፣ በአፋርና ኢሳ ግጭት፣ በኦሮሞና በሱማሌ ግጭት፣ በትግራይና በአማራ ግጭት ወዘተ በተከሰቱ የድንበር ግጭት ምክንያት አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የግብርና ሥራቸውን መስራት ባለመቻላቸው ተደጋጋሚ ድርቅና ርሃብ በሃገሪቱ ተከስቶል፡፡ የህወሓት  መንግስት ድርቅና ርሃብ በመሬቱ ላይ በመዝራት በዜጎች ርሃብና ችጋር ላይ በመነገድ የህዝቡን አንጡራ ሃብት ተቀራምቶል፡፡  የሃገሪቱ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታዊ አወቃቀር ላይ በውይይትና በስምምነት  አዲስ ህገ-መንግሥት ማርቀቅ ያስፈልጋል እንላለን፡፡

እንደ ጆን ማርካኪስ ጥናት መሠረት ‹‹በኢትዮጵያ የደም መፋሰሱ ለምንድነው? የዘር ግጭት ነው ወይ? የኃብትና ንብረት ግጭት ነው? የማንነት ጥያቄ፣ የባህልና እሴት  ግጭት ነው? የሄን ሁሉ ያጠቃልላል፣ ሌላም ይጨምራል፡፡››(Markakis 2003:446)  በኢትዮጵያ ለብዙ ክፍለ ዘመናት ጀምሮ ከብት አርቢዎች የግጦሽ ቦታ  ግጭት የነበረ ነው፡፡ ከሁለት አስርት ጀምሮ ሃገሪቱ ውስጥ  የብሄር ግጭቶች በተደጋጋሚ በመከሰቱ የዜጎች የስብዓዊ ጉዳትና ቀውስ ተከስቶል፡፡  በኢትዮጵያ ግጭቶችና የመንስዔቸው አዙሪት ድግግሞሽ ለውጥ የተለያዮ ምክንያቶች ውስጥ የከባቢ ዓየር ብክለት፣ የግጦሽ መሬት እጥረት፣ የዓየር ሁኔት ለውጥና የፖለቲካ አለመረጋጋት ይካተታሉ፡፡

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን (2008-2012እኢአ)፣ በአምስት አመታት ውስጥ የአገር ውስጥ ታክስና ታክስ ያልሆኑ ገቢ፣አንድ ትሪሊዩን ሦስት ቢሊዩን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ህወኃት /ኢህአዴግ በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ዶሴው ላይ ገልፆል፡፡ በእቅዱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 17 በመቶ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶል፡፡ የሁለት ዓመት ተኩል የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መንግሥት በቀጥታ የተበደረው የውጭ ዕዳ ክምችት በዚህ አመት 24.75 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር፡፡ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ በ2009 ዓ/ም 13 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ አገሪቱ ስታገኝ የነበረው የውጭ ብድር በኢንቨስትመንትና ለኢንቨስትመንቱ በሚያስፈልገው ቁጠባ መካከል የሚታየውን ልዩነት ለመሸፈን ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ አስታውቀው ነበር፡፡ ከ2004 ዓ/ም እስከ 2007ዓ/ም ድረስ ከታክስ ይገኝ የነበረው 15.2 በመቶ የነበረ ሲሆን ከ2008ዓ/ም እስከ 2009ዓ/ም 10.3 በመቶ ብቻ ማደግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በ2009ዓ/ም ታቅዶ ከነበረው የታክስ ገቢ 39 ቢሊዮን ብር መሰብስብ እንዳልተቻለ፣ በ2010ዓ/ም ታቅዶ ከነበረው የታክስ ገቢ 199 ቢሊዮን ብር ደግሞ 50 ቢሊዮን ብር እንደማይሰበሰብ ከወዲሁ መታወቁን ጠቁመው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የተለያዮ ፕሮጀክቶች ወደ በ2011 ዓ/ም እንዲሸጋገሩ መንግሥት  መገደዱን፣ ይህ ሁኔታም በመንግሥት ላይ የበጀት ጫና መፍጠሩን ገልፀዋል፡፡

የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ህገ መንግሥት መሠረት የፊዴራል መንግስት ለክልል መንግሥታት መደበኛው ባጀትና የክልሎች ድጎማ በብዙ ቢሊዮን ብር የሚቆጠር በጀት ለክልሉ የመንግስት ሠራተኛ ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ  ለክልሎች ሹማምንትና ካድሬዎች መኪና፣ ቤት፣ መሬት ወዘተ ጥቅማ ጥቅሞች ለማግኘት ቀበሌዎች ወደ ወረዳ፣አውራጃ፣ ዞን፣ ልዩ ዞንና ወደ ክልል መንግሥትነት ማደግ ይፈልጋሉ፡፡ የክልል እንሁን የማንነት ጥያቄ የበዛው ለዚህ ነው፡፡ ለምሳሌ በ1998/99 ዓ/ም በዋግህምራ ልዩ ዞን የካፒታል በጀት 7.9 ሚሊየን ብር የነበረ ሲሆን የዞኑ ቢሮዎች ግንባት፣ትልቅ ሆስፒታል ግንባታ፣ የቤቶች ግንባታ በሰቆጣ ከተማ ውስጥ ተስተውሎ ነበር፡፡ በተመሳሳይ የዋግህምራ ልዩ ዞን መደበኛ በጀት 18.2 ሚሊዮን ብር ሲሆን በዛን ጊዜ የህዝቡ ቁጥር ሦስት መቶ አስራስድስት ሽህ አምስት መቶ ነበር፡፡ ልዮ ዞን በመሆኖ ምክንያት የነፍስ ወከፍ ካቲታል በጀት ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቦል፣ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ሲነፃፀር፡፡

በዚህ የጥቅም ግጭት ይነሳል፣ ክልሎቹ እዚህ ግባ የማይባል ግብር እየሰበሰቡ፣ ከፌዴራል መንግስት የሚሠፈርላቸው በጀት ይባላሉ፡፡ በኢትዮጵያ 2000 ሽህ ከፍተኛ ግብር ከፋዬች በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ አዋሳ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር ወዘተ እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞችና ገበሬዎች ብቻ ግብር ከፋዬች ናቸው፡፡ ከነዚህ የሚሠበሰበው የግብር ከፋዩ ህዝብ ላብና ደም ለእነዚህ የክልል  ሹማምንትና ካድሬዎች ወጪ ይውላል፡፡ የክልል ሹማምንት የሙያ ክህሎትና የትምህርት ደረጃ ብቃት መመዘኛ የማያሞሉ ምላስ አደር የፖለቲካ ካድሬዎች በህዝቡ ጫንቃ ላይ ተቀምተው ህዝቡን ሲዘርፉ 27 አመታት ተቆጥሮል፡፡ በየቦታው የሚነሳ የማንነት ጥያቄ ማጠንጠኛው ወደ ክልል መንግሥትነት ብናድግ ከፍተኛ በጀት እናገኛለን በሚል የፖለቲካ ካድሬዎች ቅስቀሳ የተነሳ ነው፡፡ ለዚህ ነው በህገ-መንግስቱ የተቀመጠው በቌንቌ ላይ የተመሠረተ የክልሎች አከላል ግጭቶችን በየአካባቢው የሚጭረው፡፡ በደቡብ ክልል የሲዳማ፣ ወላይታና የጉራጌ ህዝብ ከ ከ3 አስከ 4 ሚሊዩን ህዝብ እያለን ለምን ክልል አንሆንም ጥያቄ ተቀስቅሶል፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪና፣ ቤኒሻንጉል ክልል ህዝብ ከሃያ ሽህ እስከ 200 ሽህ ብቻ ሆነው እኛ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር እያለን ለምን ክልላዊ መንግስት አንባልም የሚል የማንነት ጥያቄ ህገ-መንግስቱ የሰጠን የእኩልነታና የፍትህ ጥያቄ ይከበር እያሉ ነው፡፡ የወያኔ ህገ-መንግሥት ሃገሪቱ ልትወጣው ወደማትችልበት የማያባራ ጦርነት ከመግባታችን በፊት ህገ-መንግሥቱ በአፋጥኝ መቀየር ግድ ይላል፡፡

‹‹የሃረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት 9,374 (ዘጠኝ ሽህ ሥስት መቶ ሰባ አራት) የህዝብ ቁጥር ያለው ሲሆን ጠቅላላው በክልሉ ውስጥ የሚኖረው ህዝብ ቁጥር  131,139 (አንድ መቶ ሠላሳ አንድ ሽህ መቶሥላሳ ዘጠኝ) የነበሪ ሲሆን ሃረሪ ህዝብ በታሪክ፣ በሃይማኖት፣ በጥንታዊ ባህልና በከተማ ቅርስነት ትታወቃለች፡፡  በክልሉ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ  ከፍተኛ ቁጥር አላቸው፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ ህገመንግሥት የእኩልነት መርህን የሚፃረር፣ የዓለም አቀፍ  የዜጎች የመምረጥ መብት የሚጥስ (principle of equal and universal suffrage) ከዘር፣ ብሄር፣ ኃይማኖት፣ ፆታ፣   ማህበራዊ ሁኔታ፣  ኃብትና ገቢ ደረጃ ፣ ምንም ዓይነታ ተፅዕኖና አድሎ የሌለበት መብት የተጣሰው በሃረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምሥረታ ነው፡፡ በህወሓት/ኢህአዴግ የህገ-መንግሥት ሳይንሳዊ ያልሆነ ምህታታዊ አሰራር በዚህ ዓይነት አሠራሩ ይገለፃል፡፡››

የክልሎች ልዩ የፖሊስ ኃይል እና የሚሊሻ

የትግራይ ክልል አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽህ ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ ሲኖሩት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ለ ሠላሣ አንደኛ ጊዜ ቁጥሩ ያልታወቀ ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ መልምለዋል፡፡ የአማራ፣ የጋምቤላ፣ የአፋር፣ የሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሃረሪ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ ክልላዊ መንግሥት ከሆኑ በሳምንቱ አንድ ሽህ ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ መልምለው አስመርቀዋል፡፡ ኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የክልል ሥልጣንና ተግባር ‹‹የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል ፣ይመራል፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፡››  ይላል አንቀጽ 52፡፡ በህገ-መንግሥቱ  መሠረት ክልሎች የፖሊስ ሠራዊት ኃይል ብቻ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡  ከህወሓት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራን ለመበጣጠስ የወያኔን ህገ-መንግስት በአዲስ ተክቶ ይሄን የአባላሽኝ ዘመን አልፈን አዲሲቶን ኢትዮጵያ በእውነትና በሃቅ መምራት ይጠበቅብናል፡፡

1ኛ/ ከክልል ፖሊስ በስተቀር ያሉ የክልል ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀትች ሙሉ በሙሉ ከክልሎች እጅ አውጥቶ በፌደራል መዋቅር ስር ማድረግ፣

2ኛ/ በብሔር የተዋቀረውን የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ በመበታትን ወደ ሁሉም የአገሪቷ ክፍል ማሰባጠር እና በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ ያለው ታጣቂ ኃይል ከሁሉም ብሔር የተወጣጣ እንዲሆን ማድረግ፣

3ኛ/ በየክልሉ ያለውን ስብጥር ኃይልን በበላይነት የሚመሩትንም አዛዦች እንዲሁ በተሰባጠረ መልኩ ማዋቀር፣

4ኛ/ ይህን ኃይል በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አይምሯቸው ውስጥ ያለውን የብሔረተኝነት ስሜት በሂደት እንዲቀይሩና ያለመድሎ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ደህንነት ዘብ እንዲቆሙ ማድረግ።

ክልሎችም ያንጃበበውን አደጋ ከወዲሁ አጢነው ለዚህ ለውጥ መሳካት ካልተባበሩ በዘር ያደራጁት የታጠቀ ኃይል ተንሸራቶ አክራሪዎች እጅ የወደቀ ዕለት የመጀመሪያዎቹ የጥቃት ኢላማዎች እነሱ መሆናቸውን ሊያጤኑት ይገባል። በዘር ተደራጅቶ በዘር የታጠቀ የዘር ፍጅትን ያፋጥናል። ይህን ለማድረግ ግን ወሳኙ ነገር የአገዛዝ ሥርዓቱ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ያንጃበበውንም አደጋ በበቂ ሁኔታ መረዳትን ይጠይቃል። ይሄን የተጠመደ ፈንጂ ሳያመክኑ በጀርባ አዝለው እየዞሩ ኢትዮጵያ አትፈርስም ማለት ብቻውን አደጋውን አያስቀረውም።›› የብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር አብይ አህመድ ይሄን ምክር ተጠቅመው የኢትዮጵያን እናቶች፣ ህጻናትና፣ ሁሉን ዜጎች ከዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀኖሳይድ) ሊታደጉት ይገባል እንላለን፡፡

የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበር!!!

ባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ እንዲሁም ልደቱ አያሌው፣ ይፈቱ!!!

የአስራት ጋዜጠኞች በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብር፣ ምስጋናው ከፋለኝ፣ ዬናታን ሙሉጌታ ይፈቱ

አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ክልላዊ መንግሥትነት ይገባቸዋል!!!

 

 

ምንጭ

{1} https://www.youtube.com/watch?v=qk8rZigR9dc/Ethio 360 Zare Min Ale “በቤኔሻንጉል ጉምዝ አማራን የማጥራት ዘመቻ” Tuesday Sep 15, 2020

{2} https://en.wikipedia.org/wiki/Benishangul-Gumuz_Region

{3} https://www.youtube.com/watch?v=WNke6uMkOKc/እንግዳችን – “የአዲስ አበባ ወጣት ሲነሳ የሻሸመኔው ቀልድ ይሆናል” ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም | Prof Mesfin Woldemariam | Abbay Media

{4} The post 1991 ‘inter-ethnic’ conflicts in Ethiopia: An investigation (Lubo Teferi) Department of Law, Adama Science and Technology University, Adama, Oromia State, Ethiopia. E-mail: mailto:[email protected]. 12 March, 2012

{5} Journal of Law and Conflict Resolution Vol. 4(4), pp. 62-69, April 2012/ Available online at http://www.academicjournals.org/JLCR DOI: 10.5897/JLCR11.045 ISSN 2006-9804 ©2012 Academic Journals

መስከረም 5ቀን 2013ዓ/ም

2 Comments

 1. This article seems to try to say clan based or race based federalism could work. We have seen it all in our eyes and it does not work. Like Empror Haile Selassie said it beautifully all of man kind should be equal and should be judged on their humanity and that is what we should aspire for. In theory, principle and practice one can not make so many non irreconcilable factors reconcile. Any patch to the race formula simply elongates the pain rather than cure it. Honestly we need a cure and that is make race a non factor.

 2. የአማራ አደገኛ እና አጥፊው ጠላቶች በቅደም ተከተል ሲገለጹ፤
  1ኛ፤ ኢህዴን/ብአዴን የትህነግ ምንጣፍ ጎታች ወይም አዴፓ/ኦነግ የኦነግ ምንጣፍ ጎታችና የአብይ ገረድ
  2ኛ፤ ጉማሬው ከርሳሙ እና የአይምሮ ዝግመት ያለበት ደመቀ መኮንን
  3ኛ፤ ጭቃ ፊቱ የኦነግ ካልሲና ሙታንታ አጣቢ ቤት አጽጅ ተመስገን ጥሩነህ
  4ኛ፤ መሃይሙና የሳጥናኤል አምልኮ/መለስ ዜናዊዝም/ ተክታይ አገኘሁ ተሻገር
  5ኛ፤ ወዘተ
  6ኛ፤ የበታችነት እና የዝቅተኛ አስተሳስብ ሲንድሮም ተጠቂ የሆንችው ወያኔ/ትህነግ
  7ኛ፤ በተመሳሳይ ሲንድሮም የተጠቃው ኦነግ
  8ኛ፤ ድህነት ናችው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.