ማሳሰቢያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና እስልምና እምነት አባቶች! መታለሉ ይብቃ! – ሰርፀ ደስታ

በቅድሚያ ለመላ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሉ እንኳን ለ2013 ዓ.ም በሠላም አደረሳችሁ! አሁንም የዘመናት ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር ዘመኑን ባርኮልን አገራችንና ሕዝባችንን ከክፉ ሁሉ እንዲጠብቅልን እንጸልያለን፡፡

Orthodox Islam በእምነት አባቶች በኩል የብልጽግና ፕሮቲስታነት እምነት ቁማር፡- በመጀመሪያ ብልጽግና በገንዘብ የሚያመልኩ የፕሮቲስታነት እምነት ተከታዮች የእምነት ተቋም እንጂ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው ፓርቲ እንዳልሆን ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ይሄን ብዙ ሰው እየተረዳ አይመስለኝም፡፡ ዛሬ በርዕሴ እንደምታዩት ለማንሳት ከፈለግኳቸው ዋነኛ ነጥብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስና እስልምና እምነት አባቶችን ማሳሰብ ነው፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው ባለፉት ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ገደማ ለውጥ ተለወጠ ብለን ሁላችንም ደስ ብሎን ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ ለበርካታ ዓመታት ተከፍላ በሁለት ሲኖዶስ ስትመራ የነበረችው ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና በተመሳሳይ የኦርቶዶክስንም ያህል ባይሆን ለብዙ ዓመታት ተከፍሎ የነበረው የእስልምና እምነት መሪዎች ጉባኤ ወደነበሩበት የመመለስ እድል በመፈጠሩ ለእነዚህ ሁለት የእምነት ተከታይ ምዕመናን ከፍተኛ ደስታ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ለዚህም የለውጥ መሪ ነኝ ያለው ዛሬ አገራችንን በተተኪ ወራሪነት እየመራ ያለው ቡድን ለአብያተ እምነታቱ ወደ ቀድሞ አንድነታቸው ለማምጣት አስተወጽኦ ነበረው በሚል ዛሬ ላይ በተለይ የእምነታቱ መሪዎች የአገርንና የሕዝብን ጉዳይ ዘንግተው ውለታ ተሰርቶልናል በሚል አመለካከት የአገር አጥፊዎችና በአገራችን ከመቼውም ጊዜ በከፋ በለየለት ወሮበላ በሆነ ቡድን በመታለል ላይ እንዳሉ ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ በተለይም ደግሞ ዛሬ ጠ/ሚኒሰቴር ነኝ የሚሉት  የቡድኑ መሪ የብልጽግና ማኒፌስቶ ብለው በሰነድ በአስቀመጡት እንደምናየው ኢትዮጵያ ውስጥ ከፕሮቲስታነት እምነት ውጭ ያሉት ለአገርና እድገት እንቅፋት እንደሆኑ ነግረውናል፡፡ ይሄን ጉዳይ እንደቀላል የተመለከቱት ብዙዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ጉዳዩ ቀልድ ሳይሆን የአገር ፖሊሲ ሆኖ ብልጽግና የተባለው ቡድን መርሆው እንደሆነ አለሰማስተዋል ትልቅ ስህተት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሁለት መከፈሏ ሴረኞችን ለፍርድ ለቤተክርስቲያኗ ግን ትልቅ እድገት ነው፡-በእስልምና እምነት ምን እንደተከሰተ ሙሉ መረጃው ስለሌለኝ መናገር አልችልም፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ላይ የተከሰተውን ግን እኔ የምረዳው አብዛኛው ሰው ከሚያስበው በተለይ እንዳይሆን እፈራለሁ፡፡ እኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ በሁለት ሲኖዶስ መከፈል የክፉዎች ሴራ ቢሆንም የልዕል እግዚአብሔር ልዩ እቅድም እንደሆን በጽኑ አምናለሁ፡፡ እኛ በጎ ብንሰራ ለራሳችን ነው፡፡ ክፉ በመስራታችን ለክፋታችን ከመጠየቅ አንድንም፡፡ ሆኖም በክፎዎችም የሚሰራውን ሥራ እግዚአብሔር እሱ ለፈቀደው በጎ ነገር ሊያደርገው እንደሚችል ካስተዋልኩባቸው ክስተቶቸው አንዱ ቢሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ለሁለት መከፈል ነው፡፡ ዛሬ ቤተክርስቲያኒቱ በውጭ ሐገራት በተለይም ደግሞ በሰሜን አሜሪካ ትልቅ መሠረት አላት፡፡ ይህ የሆነው ሲኖዶሱ ከሁለት በመከፈሉ የተነሳ በተለይም በውጭ የነበረው ሲኖዶስ ትልልቅ መሠረቶችን በመጣሉ ነው፡፡ ደግ ባለመስራታችን ለእኛ ይቀርብናል እንጂ እግዚአብሔር ከአቀደው ነገር አይቀርም፡፡ በእልህም ተሰራ በፍቅር ዛሬ ግን በግልጽ በሚታይ ሁኔታ ለቤተክርስቲያኗ ትልቅ አቅም በመሆን በውጭው ዓለም መሠረቷ ደርጅቶ እናየዋለን፡፡ ይህ አንድ ሲኖዶስ ቢሆን አይታሰብም ነበር፡፡  ይህ ከጥንት ጀምሮ የቤተክርስቲያኒቱ እውነት ነው፡፡ ሊያጠፏት በሞከሩ መጠን የመስፋፋቷ፡፡ ግልጽ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንጂ ሰው አደለምና መሪዋ፡፡ ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊተዋት ይችላል እግዚአብሔር ለፈቀደው ለሌላ ሕዝብ ልትሰጥም ትችላለች፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ ኢትዮጵያ አገሯን ወክላ በትላላቅ የሰሜን አሜሪካ ከተሞች ግዙፍ ሆና የምትታይ ሆናለች፡፡ አብይ አህመድ እንደሚለው ለእድገትም ሆን ብልጽግና እንቅፋት ሳትሆን በበለጸጉትም አገራት በክብር መሪዎች ጭምር የሚጎበኟት ኢትዮጵያዊ ተቋም (በተቋምነት) ብትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነች፡፡ በማችበርበርና በማታለል ገንዘብ ከሕዝብ የሚቀሙ ፓስተሮች የሞሉበት ፕሮቲስታነት አደለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማናንስ ህዝብ ሆነን: ሳለን ሆሎዶሞር! የስታሊን ፍሬ! -ገለታው ዘለቀ

የቡድኑ መሪ አብይ አህመድ ከጅምሩ ጀምሮ በእነዚህ ሁለት ጥንታውያን የአገሪቱ ሕዝብ እምነቶች ላይ ትልቅ ትኩረት አድርገው ሲሰሩና ባለውለታ ለመሆን ቀደምት ሆነው ለመታየት የሄዱበት ሁሉ ርቀት በኋላ እሳቸውና የወሮበላው ቡድናቸው ላሰበው ስኬት ለማምጣት ቅድሚያ የእነዚህን እምነት አባቶች ማታለል ተገቢና ወሳኝ እንደሆነ ስለአመኑበት ነው፡፡ ይሄን በእርግጥም ብዙ ሊቆይ የሚችል አይመስለኝም እንጂ በብዙ ነገር እስካሁን ተሳክቶላቸዋል፡፡ እንደወረደ ይህ ቡድን እየተጫወተ ያለው የራሱ ዓባላት እንደተናገሩት ቁማር ነው፡፡  በማሳመንም በማደናገርም የአለሙትን ከማድረግ ላይመለሱ ተማምለው የገቡ ስብስቦች እንደሆኑ በግልጽ እናያለን፡፡ ይሄን ጉዳይ አገርና ሕዝብ የሚያሳስባችሁ ሁሉ አስተውሉት፡፡

ሰሞኑን የቡድኑ መሪ አብይ አህመድ ከዚህ በፊትም ከሚያደርጉት በበዛ ሁኔታ ሕዝብን ለማጭበርበር የሚንቀሳቀሷቸውን እንቅስቃሴዎች ለታዘብ ሰዎቹ አሁንም ለራሳቸው እንኳን አስበው ከድርጊታቸው መታቀብንና ወደ ልቦናቸው መመለስን የፈለጉ አይመሰልም፡፡ ብልጽግና ሲጀምር የእምነት ድርጅት እንጂ ፓርቲ እንዳልሆን ሁሉ ሊረዳ ይገባል፡፡ በአላወቅንው ነገር የጠላት አጃቢ ባንሆን እላለሁ፡፡ የዚህ ሐሳብ ዋና ተዋናዮች ገንዘብ የፈለግንው ቦታ ያደርሰናል ብለው የሚያምኑ ግልጽ የሆነ የፕሮቲስታነት እምነት ተከታዮች እንደሆኑ እናያለን፡፡ ይሄ የእነሱ እምነት ፍልስፍና ነው፡፡ ከይቅርታ ጋር እዚህ ጋር የሁሉም ፕሮቲስታነት እምነት ነው ብዬ አላምንም፡፡ የብልጽግና ፓርቲ መሪዎች የሚከተሉትን እምነት ማለቴ ነው፡፡ እምነት ስል በእርግጥም የአምልኮ ተቋም ማለቴ እንጂ ዝንም ብሎ የሰዎች አመለካከት ማለቴ እንዳልሆነ ልብ ይባልልኝ፡፡  ገዘብ እስከተገኘና እነሱ መኖር እስከቻሉ ድረስ የትኛውንም ወንጀል ከመስራት ወደኋላ የማይል አስተምሮት ያላቸው ናቸው፡፡ ለዛም ነው በየራሳቸው እምነትንና ስነምግባርን የሚያስተምሩትን እምነቶች (ኦርቶዶክስና ሙስሊምን) የብልጽግና እንቅፋት እንደሆኑ በማኒፌስቶ ጽፈው የተነሱት፡፡  ከዘረፋና ከአሳቃቂ ወንጀሎች በተጨማር የማህበረሰቡትን እሴቶች ሁሉ ማጥፋት ሌላው ውጥናቸው ነው፡፡ ሁሉም ያስብበት፡፡

ሰሞኑን አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ፓትሪአርክ የሆኑትን አቡነ መርቆሪዎስን፣ አረጋውያንን፣ ሌሎችም መጎብኘት የሚገባቸውን ሲጎበኙ ተመልክተናል፡፡ ይህ እንደመሪ መልካም በሆነ፡፡ ሆኖም አብይ አህመድና ቡድናቸው እንዲህ ያሉ ነገሮችን በግልጽ ለወጠኑት ሴራ መሳካት እየተጠቀሙባቸው እንደሆነ አይተናል አሁንም እያደረጉ ያሉት ለዚሁ ግብዓት እንዲሆናቸው እንጂ ፓትሪያርኩን ከማክበር ለድሆችና ለተጉዱ ከማዘን እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ እናውቃልን ስንል እናውቃለን፡፡ ያ ሁሉ ሕዝብ በረመኔዎች የተጨፈጨፈባቸውን ቦታዎች እንኳን በአካል ቦታው ላይ ተገኝቶ ያ ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ የደረሰባቸውን ወገኖች ማጽናናት ይቅርና በሚዲያ እንኳን ስለሁኔታው ለመናገር ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ በአፋር ያ ሁሉ ሕዝብ በጎርፍ ተጥለቅልቆ ጭራሽ የሚዲያ ትኩረት እንኳን እንዳያገኙ የአገሪቱን ሚዲያዎች የኢትዮጵያ ልክ በሚል የድራማ የማስታወቂያ ፊልማቸው ተቆጣጥረውት አይተናል፡፡  ከእነዛ ይልቅ አነሰም በዛም ዘወትር የሚመግቧቸው ኢትዮጵያውያን ያሏቸውን አረጋውያን መጎብኘት ብልጫ አላው ብሎ በጭፍኑ እውነትን ከመካድ ካልሆነ፡፡  እንዲህ አይነቱን ድራማ ባይቀጥሉበት ለራሳቸውም ጥሩ ነበር፡፡ ጥሩ ሆኖ አላየሁትም፡፡

የእነ እስክንድር ነጋ ክስ፡-ሌላው ሰሞኑን ያየንው በእስክንድርና ሌሎች ንጹህ ኢትዮጵያውያን ላይ የቀረበው ክስ ነው፡፡ ጀዋርንና ሌሎቹን በምን ክስ እንደከሰሷቸው እስካሁን የሰማሁት የለም የሐጫሉን አስከሬን አስመልሰሀል ከሚል በቀር፡፡ ቀድሜም ስለዚህ ጉዳይ ተናግሬ ነበር፡፡ ከጀዋር ይልቅ እስክንድር በፈጠራ ወንጀል ሊከሱት እንደሚችሉ፡፡ የእስክንድር ዛሬ አውሬዎች እጅ ለመግባት ምክነያቱ በእምነቱ (ሐይማኖቱ)ና በአለው ግልጽ የፍትሐዊነት አቋሙ በተለይም ደግሞ አዲስ አበባ ላይ እየተደረገ ያለውን ግልጽ የወሮበላ አሰራርን ፊትለፊት መጋፈጡ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እስከዛሬም በምን አሳበው እንደሚያስሩት ግራ ገብቷቸው ነው፡፡ ዛሬ የእስክንድርን የዘመናት ውትወታ ኢዜማ አንስቶ የሕዝብ ቀልብ መሳቢያ ያደረገው የአዲስ አበባ ጉድ እስክንድርና ቡድኑ በተወሰነም ቢሆን ባይገታው ከዚህ በከፋ ብዙ በሰማን ነበር፡፡ እስክንድርን አርሲና ባሌ ለተጨፈጨፉት ኦርቶዶክሳውያን ምክነያት ለመሆን ክነጀዋር ጋር በቅንጅት ይሰራሉ ነበር ያለችን ዛሬ አዲስ አበባን ለመዝረፍ የተረከበቸው አዳነች አቤቤ፡፡ ዛሬ ድረስ ግን ጀዋር ከሐጫሉ አስከሬን አስመልሰሀል ከሚል ክስ ውጭ ሌላ ክስ ትንፍሽ አልተባለም፡፡ ኢላማ የነበረው እስክንድር እንጂ ጀዋር አደለም፡፡ የሐጫሉን አስከሬን ማስመለስ ይሄን ያህል ትልቅ ወንጀልም አደለም፡፡ በዳኛ ፊት ደግሞ ስሜትና አለመረጋጋት ነበር በሚል ሊጣል የሚችል ቀላል ክስ ነው፡፡ ይሄን ተከትሎ ታቅዶና ታልሞ ስለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ማንም ተጠያቂ ወንጀለኛ የለም፡፡ የሐጫሉንም ገዳዮች የሶስት ጎረምሶች የግድያ ወንጀል ብቻ አድረገውት እናያለን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ ኃይለ ማርያም ምን ነካካቸው?

የሕወሐት ምርጫና ሕጋዊነት፡- ሌላው የሰሞኑ ድራማ የትግራይ ክልል ምርጫ ነው፡፡ አብይ አህመድና ቡድኑ የቡድኑና የእሱ የግል ጥቅም እስካልተነካ ድረስ ማንም የፈለገውን ወንጀል ሊሰራ መብት አለው፡፡ እኔ የትግራይ ክልል ምርጫ እንደ አካሄድ ሕገ ወጥ ለመሆኑ ምንም አይነት የሕግ ማሳያ ማቅረብ አልችልም፡፡ አንድ ነገር ግን እታዘባለሁ ሕገ ወጥ ነው ከተባለ ሕግ የማስከበር ኃላፊነት የማን ነበር? አብይ አህመድና ቡድኑ የወላይታን ሕዝብ ሰላማዊ ሠልፍ ወጥተሀል በሚል ወታደር አስምተውበት አይተናል፡፡ ያ ዜጎች በአረመኔዎች ሲታረዱ ትዕዛዝ አልደረሰኝም ያለ ወታደር ወላይታ ላይ በፍጥነት ትዕዛዝ ተሰጥቶት ሰላማዊ ሰልፈኞችን ሲገድል ነበር፡፡ የአሁኑ የሕወሐት ምርጫ ከሕጋዊነቱ ይልቅ አሳሳቢ የሚያደርገው በክልሎ የሚንቀሳቀሱ ወሳኝ ፓርቲዎች አለመሳተፋቸው ነው፡፡ እንግዲህ እንደተባለው ምርጫ ወደፊት ከአለ ያኔ በዛ ክልል ምርጫ አደርጋለሁ ብሎ ማለት ምን ችግር ሊያመጣ እንደሚችል ታዘቡ፡፡ አንዳንዶች የትግራይን ክልል አዲስ አበባ ፓርላማ ያለመቀመጫ ያስቀረዋል ይላሉ፡፡ ቀልዱን ትተን የሕዝብ መከራና ስቃይ ከገባን ግን አብይና ወያኔ እርስ በእርስ ይተዋወቃሉ ችግሩ ግን ለትግራይ ሕዝብም ከመድረስ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ሲጀምር ምርጫው ሕጋዊ አደለም ለማለት ሕጋዊ ሆኖ ያለ አካል ሲኖር ነው፡፡  የሕግ ጉዳይ ከተነሳ ደግሞ ክልሉ የተከተለው ሕጋዊ አደለም ለማለት የሚያስችል የሕግ አግባብ ሊኖር ይገባል፡፡ ለማንኛውም በኮንቪንስና ኮንፊውዥን ስልት የት እንደሚደረስ አላውቅም፡፡

አዲስ አበባ ፓርክ፡- እኔ ስለዚህ ጉዳይ ከጅምሩ ሰው እንዲያስተውል እያሳሰብኩ ነበር፡፡ ወታደራዊ ተዕይነት በመናፈሻ ምረቃ የባስ አለና አገርህን አትልቀቅ ነው፡፡ ለእኔ ይሄ የመናፈሻና የፓርክ ሥራ የአዲስ አበባ ከተማ የእቅዱ ቅንጣት እንጂ ለከተማውም ትልቅ ሥራ አደለም፡፡ ይሄን የምለው እኔ ከ8 ዓመት በፊት አቅጄው የነበረውን የአዲስ አበባን የወንዞች ማስዋብ ሥራ መሥራት የሚያስችል ሐሳብ አቅርቤ በብዙዎች አስተሳሰብ ገንዘብ እንጂ ሐሳብ ቡታ እንደሌለው ታዝቤ ነበር፡፡ ሐሳቤ የነበረው ግን ከመንግስት አመስት ሳንቲም ሳይወጣ የመስራት እቅድ ነበር፡፡ ከከተማው ፈለጌ የነበርኩት ሐሳቡን እንደሚሰራ አምኖ እውቅና መሥጠትን ብቻ ነበር፡፡ ዛሬ አብይ አንስቶ ድራማ እየሰራበት ያለው ፕሮጄክት በጠቅላይ ሚኒስቴር ደረጃ ቀርቶ በማዘጋጃ ቤቱም በቅንጅት ለመስራት ካልሆነ ክፍለከተሞች ሊሰሩት የሚችሉት ነው ከሕዝቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር፡፡ እግረ መንገድም የማህበረሰብን አስተሳሰብ በመቀየር ሕወትን የተሻለ በማድረግ፡፡ አሁን የምንሰማው እስከአሁንም ለመናፈሻ 5 ቢሊየን ብር ወጥቷል፡፡ የዚህ ገንዘብ አወጣጥ በራሱ ምን ያህል ሕጋዊ እንደሆነ አጠያያቂ ሆኖ የገንዘቡ መጠን ግን በእቅድና በአስተዋይነት ቢሆን ብዙ ሥራ በሰራ ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ልክ በአዲስ አበባ መናፈሻ በሚለኩ ጭንቅላቶች ተሰርቶ ምን ያህል ገንዘብ እንደወጣ አስቡት፡፡ አዝናለሁ፡፡ በመናፈሻ ልክ የሚያስበው ቡድን ይሄው አሁን ጭራሽ ወታደራዊ ትዕይነት በማሳየት የብሔራዊ ስኬት አድርጎት ቁጭ ብሏል፡፡  በማጭበርበር የኖቤል ተሸላሚ የሆነ ግለሰብ አኔኑነ በጨው አጥቦ ስኬት ነው ቢለን አይገርምም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለመፈንቅለ መንግስት እንኳን “ያልታደለች” ሀገር!

የአረንጓዴ አሻራ ጉዳይ፡- ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአብይ አህመድ የአስተሳሰብ ልክን የተዘብንበት 5 ቢሊየን ዛፍ በመትከላችን ዝናብ ጨመረ ዓለማያ ሐይቅ ተመልሶ መጣ ይሉናል፡፡ እንዲህ በሚያስቡ አገር እየተመራች አገር የመሆኗ ነገር ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ ሲጀምር 5ቢሊየን የሚባል ነገር በሌለበት ቁጥር መብታችን ነው በሚል 5 ቢሊየንን እውነት ነው በሚል ይሄው ብዙ ሕዝብ አሳምነዋል፡፡ አዝናለሁ፡፡ እኔ ባለሙያ ነኝ፡፡ የትም አገር ጠይቁ፡፡ ሕንድ በቢሊየን ተከለች ሲባል ሰምተን ይሆናል፡፡ ሕንድ አህጉር የምታክል አገር ከመሆኗም በላይ የአለምን አንድ አራተኛ የሚጠጋ ሕዝብ የያዘች ነች፡፡ ባሕላቸውም ለዛ ያግዛል፡፡ የ5ቢሊየኑን ቁጥር ተራው ሕዝብ ብቻም ሳይሆን ባለሙያ ነን የሚሉ ሳይቀሩ አብረው ሲጨፍሩ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ቀደም ባሉት መሪዎች ከሚተከለው የተለየ ተከላ እንደሌለ እንደባለሙያ መናገር እችላለሁ፡፡ በቴሌቪዥን ለማስታወቂያ ቢጠቀሙት የቀደሙት የተሻለ ተከላ አድርገው ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ ሆኖ እንኳን ቢሆን አምና የተከልኩት ችግኝ ዛሬ ተዓመር ሰርቶ ይሄው ዝናቡን በዚህ እጥፍ ጨመረና ዓለማያን ሞላ አይነት ሌላ አሳዛኝ ቁማር ያቺን ተከላ ተከልን ሲሉን የቱጋ ብለን ስላልጠየቅን አሁን በዚህ ድራማ ቢመጡ አይገርምም፡፡  ዓለማያ እንደማንኛውም የሐቅ ቦታ ረባዳ ስለሆነ በክረምት ውሀ ቢያጠራቅም አይገርምም፡፡ ሐረር ያሉ ወንዞች በአብዛኛው በክረምት እንጂ በበጋ አይፈሱም፡፡ የሐይቁ መሠረታዊ ችግርም የዝናብ እጦት ሳይሆን በደለል መሞላት ነውና የአካባቢው ገበሬዎችም ለጫት ውሐውን በብዛት መጠቀም ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ እስካሁን የዝናብ ችግር የለባትም፡፡ ይሄንንም ስል አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ የዝናብ እጥረቶችን ሳልረዳ ቀርቼ አደልም፡፡ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዓመታዊ ዝናብ ከሚያገኙት ነች፡፡ ከፈለጋችሁ የዝናብ መጠን ክርታዎችን ከጉግልም ማየት ትችላላችሁ፡፡ ችግራችን የዝናብ ሳይሆን የሚያስብ አእምሮ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እራሷን ይቅርና የእሷን አምስትና ከዛ በላይ እጥፍ የሆነ ሕዝብ የመመገብ አቅም አላት፡፡ አቅም ስል ፖቴንሺያል እንደሚባለው ሳይሆን ቀጥተኛ በቀላሉ የሚደረስበት ማለቴ ነው፡፡ ይህ እንዳይሆን ግን አገር እየተመራች ያለቸው እንደነ አብይ  ባለ ጭንቅላት ነው፡፡  የኢትዮጵያ ውሀማ አካሎች ከፍተኛ አደጋ እየሆነ የመጣው የዝናብ እጦት ሳይሆን መሬቱ በመራቆቱና አላግባብ በሆነ አጠቃም በአፈር መከላትና ደለል መሞላት ነው፡፡ ዛፍ ትከሉ የሚባለው በቀዳሚነት መሬቶ እንዳይሸረሸርና የሚዘንበው ውሀ ወደ መሬት እንዲገባ እንጂ ዝናብ ያወርድልናል ብለን አደልም፡፡ ከዛ ይልቅ የኢትዮጵያ ተራራማ መልክዓ ምድር በራሱ የዝናባማ አየሮችን የመያዝ ትልቅ አቅም ስላለው ዝናብ ይስባል፡፡  እርግጥ ነው ተራሮቹ በተሸፈኑ ቁጥር የዝናብ አዘል ንፋሶችን የማጥመድ አቅሙ ይቸምራል፡፡ የመልከዓ ምድራ እንክብካቤ ደግሞ ችግኝ ከመትከል በተሻለ መልክክዓ ምድሩን ከንክኪ ቢከለለው ተፈጥሮአዊና አስተማማኝ በሆነ በዝሀነት  ጭምር መሬቶ ራሱን ያድናል፡፡ ለማንኛውም የአብይ አህመድ አስተሳሰብ ፍጹም የማያፈር ፈጣጣ በመሆኑ እንጂ ሕጻን ልጅም ይሄን የማይረዳ ሆኖ አደለም፡፡ አዝናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር አገራችንንና ሕዝባችንን ከክፎዎች ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

2 Comments

  1. ወንድሜ አንተ ነገሩ የገባህ ነህ!! የኢትዮጵያ ህልውና ባልተለመደ ሁኒታ አይናችን ሰር እየጠፋች ናት፡፡ ወደድንም ጠላንም ኢትዮጵያን ደርና ማግ አድርጋ ኢትዮጵያ የሚያስብላት የ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ናት፡፡ ለአገር መሪ እንኳን የምትጸልይ ታላቅ ኦርቶዶክስ የአገርም አገር ናት፡፡ ዐቢይ ጮሌው የአገር ምሳሌ የሆነችውን ቢተክርስቲያናችንን ያስብላታል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ እስካሁን ያየነው እንድትጠፋ አረንጓዴ መብራት ቁጭ ብሎ እያበራላት ነው፡፡ ሰውየው ሰላምና ደህንነት ሊይስጥብቅ የሚችለው ህገመንግስቱን ሲያሻሽልና ህግ እንዲሰፍን ሲያደርግ ብቻ ነው፡፡ እስከአሁን ለድረስብን ጥፋት ዝምታው ተባባሪ እንደሆነ ነው ማስረጃው የሚያሳየን፡፡ለፓርቲ የቆመ መሪ ነው፡፡ በቋፍ ላይ ያለ መሪ ነው፡፡ የትግራይ ወያኔ በዓልም ሚዲያ እያሳቀበት ያለ መንግሥት ነው፡፡ በአገሩ መሪ እንደሊለ በግልጽ የሚታይበት ቲያትር ነው፡፡

  2. በመጀመሪያ አንተ ራሲ ጺሁፉን ከመጻፍህ በፊት ራሲህን ማጥራት አለብህ

    ማለተ ጠቅላይ ሚኒስትር የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ስለሆኑ እምነቱን መንካት ከአንድ አውቀዋለሁ ብሎ በሚድያ ከምፅፍ ሰው ይሄ አይጠበቅም፡፡

    በነገረቸን ላይ አትዮጰያን እስከ ዛረ የጠበቃት አመንኪም አላመንኪም እግዚአብሄር ነው እንጂ የእምነት ተቁዋም አይለም፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.