የአዲስ ተስፋ ምኞት (ዘጌርሣም)

happy NewYearዘንድሮ አምና ሰዓታት ቀርቶታል
ተስፋ ያዘለ ዓመት ሊተካ ተቃርቧል
አዲስ የምሥራች ይመስላል ሊነግረን
ያለፈውን ችግር እርሱት ተውት ሊለን

ብዙ ችግር ታይቷል
ጥፋትም ተሠርቷል
ንፁሐን ሙተዋል
ህዝብ ተፈናቅሏል
የልማት አውታሮች ፍርስርስ ብለዋል
ሰራተኛውን ህዝብ ጦም አሳድረዋል
የሸማቹን ህይወት ምስቅልቅል አርገዋል

አዲስ ተስፋም ታይቷል
አባይ ተገድቧል
የውሃ ሙሊቱን በዓይናችን አይተናል

ሰላም ቢኖር ኑሮ
ከአምና ይሻል ነበር የያዝነው ዘንድሮ
ይህም ያልፋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን
ያገብኛል ብለን ተጋግዘን ከሠራን
እንተካዋለን የዘንድሮን ጥፋት
አዲስ ተፋን አዝለን ከቆምን ለልማት
በአንድ ላይ መቆሙ ባህር ያሻግራል
አንዱ ዋና ባይችል ሌላው ያግዘዋል
ዳገትም ሲወጣ ደገፍ ያደርገዋል

እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሰን እንበል
በፍቅር በደስታ በዕልልታ እንቀበል
ብሩህ ተስፋን ስጠን ብለን እንለምን
ሰላም በመሆኑ የልብ ምኞታችን

እንኳን በሰላም ለአዲሱ ዓመት አደረሰን
የኢትዮጵያ አምላክ ሁላችንም ይጠብቀን

1 Comment

 1. ለተወደዳችሁ የዝግጅት ክፍሉ ሀላፊወች
  በቅድሚያ እንኩዋን አድረሳችሁ እያልኩ ከላይ ከተቀመጠችው ግጥም
  ላይ ትንሽ ስህተት እንዳደረኩ ስለተረዳሁ የሚል ከሆነ ብታርሙልኝ ??

  ዘንድሮ አምና ሊሆን ሰዓታት ቀርቶታል

  ቢስተካከልልኝ ? የመጀመሪያዋን ስንኝ ይመለከታል
  አመሰግናለሁ

  ዘ-ጌርሣም

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.