ታከለን የአዲስ አበባ ከንቲባ ሲያደርገው፣ ታከለ እንዲሰራለት የፈለገው ሥራ ነበረ (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

adanech Abebeታከለ አልበደለም

አንድ ልጅ ሰፈር ውስጥ ሲጋራ፣ አረቂ፣ ጫት እየተሯሯጠ ሲገዛና ወደቤቱ ሲወስድ ብታዩት፣ ይሄ ልጅ በዚህ እድሜው እነዚህን ጎጂ ነገሮች ሲያመላልስ ይውላልና በደለኛ ነው ልትሉት ትችላላችሁ። ተግባሩን በወላጅ እየተላከ እንደፈጸመው ካወቃችሁ ግን ልጁ በደለኛ ነው አትሉም።  አባቱ መልእክትና ገንዘብ ሰጥቶ እየላከው ያደረገው ሁሉ በአባቱ ዘንድ የሚያስመሰግነው፣ ጎሽ የሚያስብለው ነው። በፍጥነትና በቅልጥፍና በመላላኩም በአባቱ ይመረቃል። በሱሱና ልጁን የሱስ እቃዎች አመላላሽ በማድረጉ መወቀስ ካለበት የሚወቀሰው አባትዬው ነው ማለት ነው። ላኪው እያለ ተላላኪውን መውቀስ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንደመደብደብ ያለ ነው።

ዶ/ር ዐቢይ ገና በሕዝብ ከፍተኛ የድጋፍ ማእበል ውስጥ እያለ፣ ለዚያ ሕይወቱን ሊሰዋለት ለተዘጋጀው ሕዝብ የአፍ ወዳጅ የልብ አራጅ በመሆን ሕግ ለውጦ (በሕገወጥነት) ታከለን የአዲስ አበባ ከንቲባ ሲያደርገው፣ ታከለ እንዲሰራለት የፈለገው ሥራ ነበረ። ያንን ሥራ በትክክል ሠርቶ ሲያጠናቅቅ ከአፈርና ድንጋይ ተቆጣጣሪነት ወደ ወርቅ፣ ነዳጅና የከበሩ ማእድናት በጅሮንድነት ሹመት ሰጥቶ መርቆ አሰናብቶታል። በትንሹ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ እንዳለ የመጽሐፍ ቃል።

ልጁ በተመደበበት የሱስ እቃዎች የማመላለስ ሥራ አንዳንድ ጥፋቶችን ሊያጠፋ እንደሚችል የሚያውቅ ትሑት ልጅ ነው።

ይቅርታም ጠይቋል። ወደ ሱቅ ሲሄድ መንገድ ላይ ሳያውቅ ገፍትሮ ያለፋቸው ካሉ፣ ቆሎ የደፋባቸው ካሉ፣ ሱቅ ሲደርስ ሌሎች ቀድመውት ወረፋ ይዘው እሱ ግን በኦሮምኛ ባለሱቁን አዋርቶ ሳያውቅ መጀመሪያ ተስተናግዶ ከሄደ፣ እንደዚህና እንደዚህ የመሳሰሉ በሥራው ላይ ሲተጋ ሳያውቅ ያስቀየመባቸው በደሎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ይቅርታ ጠይቋል።

ይቅርታም ሰጥቷል። መንገድ ላይ ያባቱን ሱስና ሐራራ አጣዳፊነት እና የሱን ችኮላ ሳይረዱ መንገድ አልለቅለትም ያሉ፣ “ኧረ ሲጋራና ሌላም የሱስ እቃ እያመላለሰ ነው” ብለው ያሳበቁ፣ “ጀርጀራ! ምን ይንቀዠዣል!” ብለው የሰደቡትን ሁሉ ይቅር ብሏል።

እርግጥ መንገድ ላይ ገፍትሮ የጣላቸውን ሕጻናት፣ ዜብራ ላይ የገጫቸውን ስዎች፣  መተዳደሪያቸውን ቆሎ ደፍቶ ጦም ያሳደራችውን አሮጊቶች ምናምን በጅምላ ሳይሆን በነጠላ ይቅርታ መጠየቅና መካስም ይኖርበታል። ይቅርታው የምር እንዲሆን።

“ይሄንን ልጅ ታደናቅፉትና ወዮላችሁ! ጠባችሁ ከኔ ጋር ነው! “ ብሎ ልጁ የሱን ተልእኮ ፈጻሚ መሆኑን በማያሻማ ቋንቋ ጠቅሷል አባትዬው።

እናም መወቀስ፣ መከሰስ ካለበት አለቃውና ላኪው እንጂ ተላላኪው አይደለም። እናስ? አንበሳ ድንገት ሳያስቡት እያደነ ጨፍቶ ሊፈጃቸው ሲል የዱር አራዊት እንደመፍትሔ ያቀረቡት እንደሚከተለው ይወሳል። “አንበሳ ቃጭል ምንኛ ያምርበት” ሲሉ “ማን ደፍሮ ይሠርለት?” ተባብለዋል አሉ የዱር አራዊት እና…

ዕንቁጣጣሽ!

 

እስክንድርና ልደቱ፣

ይፈቱ!

ሊያሳስር አይገባምና እውነቱ።

3 Comments

  1. Abdi Elle evicted Oromos killing some of them then Abiy Ahmed went to Somali region and stripped Abdi Elle from power brought the evicterd Oromos to Nazret Adama. The rescue mission of the Oromo victims was assumed successful until mass graves were found later on.

    Then to advance the OPDO’s Addis Ababa ownership agenda and chase non Oromos out of Addis Ababa , Abiy chose to transfer the evicted Oromos from Somali region to Addis Ababa after brief temporary rest stop in Adama Nazret area. Many of the attacked Abdi Elle’s victims Oromos did not want to move to the over populated Addis Ababa since they are not city dwellers so then Abiy started to recruit any Oromo who is interested to relocate to Addis Ababa whether they were Abdi Elle’s viictms or not. The demography change was expected to be possible by not moving these Oromos into Addis Ababa only but mainly demography change was expected to.be possible by inciting violence in Addis Ababa between the security apparatus and the Addis Ababa people who get their condos stolen from them..

    If Abiy wanted to arrest just Jawar and associates during the recent incident the day after Hachalu died Abiy could have arrested them within few minutes after hijacking Hachalu Hundessa’s body and also arrest the Querro hours before they Walked into Addis Ababa but Abiy let them come all the way to Mesqel square Adebabay hoping to involve the Addis Ababa people in violence hoping to massacre Addis Ababa people but the peaceful eskinder preached peaceful struggle denying Abiy his desire to massacre Addis Ababa residents in violence, so he arrested Eskindere and alike because Abiy was hoping he will get the chance to massacre Addis Ababa people that day when he let the Jawars Querro parade all the way I to Addis Ababa massacring whoever non Oromo they found on the way in Oromia and the surrounding Addis Ababa towns.

  2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮንዶሚኒየም ግንባታ ተበድሮ ያልመለሰው 50 ቢሊዮን ብር + የተወዘፈ ዕዳ እንዳለበት ታወቀ::

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.