ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ፓሪቲ መሪዎች! – ከታምራት ይገዙ

መስከረም 2013 ዓ/ም
ከታምራት ይገዙ

መንደርደሪያ፤

eggየመጀምሪያዎቹ የክርስቶስ ተከታዮች የክርስትና ዕምነትን ለማስፋፋት በየአገሩ ተሰማሩ::  ጊዜውም የከፋ ስለ ነበር የሮማ ገዢዋች አሰደዱአቸው ሐዋሪያትም እንደምንም እየተሽሎክለኩ ደቀመዛሙርትን አፈሩ::  በየአገሩ ዞረው ዞረው ደቀመዛሙርትን ካፈሩ ቦሃላ እነዚያ መጀመሪያ ላይ ያፈሯቸው ደቀመዛምርትን እምን ደረጃ ላይ እንደደረሱ ላማየት ሲመለሱ ነገር ዓለሙ ተዘበራርቆባቸው ጠበቃቸው::  ዋነውን አሳዳጅ የሮማውን መንግስት ጨርሶ ረሱት ሊከተሉት የተጠመቁለትንም ክርስቶስን ረሱት::  ዓላማቸውን ስተው ተከፋፍለው ጠበቁአቸው: ያስተማሩአቸውን ሐዋሪያትን ብቻ ስም እየጠሩ “እኔ የጳውሎስ ነኝ::”  “እኔ የኬፋ ነኝ::” “እኔ የአጵሎስ ነኝ::” ” እኔ የክርስቶስ ነኝ::” እያሉ “የእኔ መምህር ከአንተ መምህር ይልቃል” በማለት ከዘጠኝ በላይ ተከፋፍለው ተጣልተውና ተኮራርፈው ጠበቁአቸው:: ይህንን ጉድ ያልጠበቀው ሐዋሪያው ጳውሎስ በጣም አዝኖ ተበሳጭቶና ተቆጥቶ ለቆሮንጦስ ሰዋች በመጀመሪያው መልዕክቱ “ክርስቶስ ተከፋፍላልን” አላቸው::

አገራችንን ኢትዮጵያን የኢሕአዴግ እኩይ ሃይል ጥፍንጎ ይዞአት ሊያጠፋት ለሀያ ሰባት ዓመታት ተግተው ቢሰሩም: ይህንን የኢሕአዴግ እኩይ ተግባር የተገነዘቡ ከአገርና ከህዝብ ጫቅና ለማላቀቅ በአገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና ድርጅቶች ከአገር ውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያኖችም ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ባለ በሌለ ሃይላቸው ጠንክረው ሲሰሩ ለውጡ አይቀሬ መሆኑን የተገነዘቡ የኢህአዴግ አመራሮች ኦሮ አማራ በሚል ተሰባስበው ቲም ለማ በሚል መጠሪያ ተዋግነው የለውጡን መምጫ ቀን መቁጠርና መጠበቅ ጀመሩ ለውጡም አይቀሬ ሆኖ ሰዓቱን ጠብቆ መጣ።

አሁን ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ እየመሩት ያሉትን ለውጥ ቲም ለማ ተባብለው የተሰባሰቡት የኢህአዴግ ሰዎችም “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” አሊያም “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” በማለት የመጣባቸውን ለውጥ እንደመጣላቸው አርገው ተቀበሉት መሪም ሆኑ። ይህው ይህንን የመጣባቸውን ለውጥ እንደመጣላቸው ሆነው ሲመሩት ሁለት መስቀል ተኮሰው ሶስተኛ ዳመራ ለመተኮስ እየተዘጋጁ አዲስ ዘመን ዋዜማ ላይ ይገኛሉ።

የሚገርመው ግን “እኔ የኦሮሞ ክልል ብልጽግና ነኝ፤ እኔ የአማራ ክልል ብልጽግና ነኝ፤ እኔ የደቡብ ክልል ብልጽግና ነኝ፤ እኔ የሱማሌ ክልል ብልጽግና ነኝ” በመባባል ተከፋፍለው ይታያሉ እውነት አገራችን ኢትዮጵያ ተከፋፍላለችን? ስንትስ ኢትዮጵያ ነው ያለችው? እናንት የክልልብልጽግና መሪዎች በተለይ ደሞ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ዐሕመድ በአዲሱ አመት እቅዳችሁ ላይ ግልጹን ንገሩን መልሱልኝ። በሌላ በኩል በቡዙ መሰዋትነት ከስልጣን የወረደውን ህወሓትን መስላችሁ መገኘታችሁ ህዝብ ያውቀዋል እናንተ የብልጽግና መሪዎች ይታወቃችሁ ይሆን?

ሁላችንም እንደምናውቀው የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም አገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድምቀት የሚከበር በዓል ነው:: ተወልደን ባደግንባት በአገራችን በኢትዮጵያም ደሞ ልማዳችንና ወጋችን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ጶጉሜ ከገበ ጀምሮ ሁሉም በየቤቱ እንደ አቅሙ አዲሱን ዓመት ለመቀበል ሸብ ረብ ማለቱ የቆየ ባህሉ ነው::

አዲስ ዓመት የሁሉ ነገር መጀመሪያ ነው ስለሆነም እያንዳንዱ አገር ባለው የቀን መቁጠሪያ ተመርኩዞ የተለያዩ እቅዶችን በአዲሱ ዓመት መግቢያ ወር ላይ የሚጀምረው ። ያቀደው ነገር በዓመቱ መጨረሻ ሊሳካ ወይም ላይሳካም ይችል ይሆናል ዋናው ቁም ነገር ግን በዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ለማሳካት የታሰበ እቅድ መኖሩ ላይ ነው። ለእቅዱ አለመሳካት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ እነዚህን ምክንያቶች ለይቶ ማወቅ በራሱ የእቅዱ አንድ አካል በማድረግ እንደገና ለመጪው አዲስ ዓመት ለተሻለ እቅድ ግባት ይሆናሉ::

የዘንድሮ የሁለት ሺ አስራ ሦስት የኢትዮጵያውያን አዲስ አመት ከግለሰባዊ አሊያም ከድርጅት ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ የለውጥ ፋይዳው የበዛ እንዲሆን የብልጽግና ፓሪቲ ከስሙ ጀምሮ ሊያሻሽላቸው የሚገባቸው ዘርፈ ቡዙ ስራዎች ይጠበቁበታል። ለምሳሌ ይህንን ጽሁፍ ስጀምር ተደራሽነቱን “ለኢትዮጵያ ብልጽግና ፓሪቲ” ያልኩበት ምክንያት ይህ “ብልጽግና” የሚባል አዲስ ስም ኢህአዴግን ሊተካ ነው ተብሎ በሃሳብ ደረጃ ሲወሳ ከብልጽግና በፊት “ኢትዮጵያ” የሚል እንዳለበት በሰፊው ናኝቶ ነበር ፓሪቲው ፓርላማ ቀርቦ ሲጸድቅ ግን “ኢትዮጵያ” የምለው ቀርቶ ብልጽግና ብቻ ቀርቦ ጸደቀ። ያን ግዜ ምነው “ኢትዮጵያ” የምትለው ቃል ወጣች የምትል ጽሁፍ ከቀድሞው ግንቦት ሰባት አካሄድ ጋር አመሳስዪ አንድ ጹሁፍ ከትቤ ነበር በአንዳንድ ምክንያት ጽሁፉን ግን ለህትመት አላበቃሁትም የዛ ጹሁፍ አጠቃላይ መልእክቱ እንዲህ ይል ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወያኔ ትግሬዎች በወሎ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ግፍ ሲጋለጥ

“ግንቦት ሰባት ኤርትራ ሲጓዝ በኤርትራ ውስጥ ከአስራ አምስት ዓመት በላይ ያስቆጠረ “የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር” የሚባል ድርጅት ነበረ። ግንቦት ሰባት ይህ ድርጅት በፈቃደኝነት ሳይሆን በጉልበት ከግንቦት ሰባት ጋር እንዲዋሃድ ሲያደርግ “ኢትዮጵያ” የምትለውን ስም አስወግዶ “አርበኞች ግንቦት ሰባት ሆኖ እንዲሰየም ሆነ። ይህ የሆነበት የኤርትራ መንግስት በፈጠረው ተጽኖ እና የግንቦት ሰባት አመራሮች ፈቅደው በመቀበላቸው እንደነበረ እንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች ይተቹት ነበር።

ብልጽግናም ኢትዮጵያ የምትለውን ቃል ከመጠሪያነት ያወጣው “የኦሮሞ ቤሄረተኞች” ተጽኖቸው አይሎ ወጥቶ ይሆን?” የሚል እድምታና ጥያቄ ያዘለ ጹሁፍ ነበር። የሚገርመው ብልጽግና የሚለው ስም እንደ ጸደቀ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በአንድ ጥያቄና መልስ ላይ ለምን “ኢትዮጵያ” የሚለውን ስም “ከብልጽግና” አወጣችሁ ተብለው ሲጠየቁ የሰጡት መልስ ውሃ የሚቆጥር አልነበረም።

ወደ ተነሳሁበት ስመለስ በኔ እይታ በሁለት ሺ አስራ ሦስት ብልጽግና እየጠራ ስለሚመጣ ያወጣትን “ኢትዮጵያ” በመጨመር “የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓሪቲ” ብሎ በፓርላማ እንድ ሚያጸድቅ ተስፋ አለኝ። ይህም በዋኝነት የሚጠቅመው ለደርጅቱና ለመሪዎቹ ህልውና ነው ምክንያቱም የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓሪቲ ስባል ብቻ ነው “እኔ የኦሮሞ ብልጽግና ነኝ”፤ “እኔ የአማራ ብልጽግና ነኝ”፤ እኔ የደቡብ ብልጽግና ነኝ” የሚባሉት ስሞች የሚከስሙትና አንድ አገር አቀፍ ፓሪቲ ሆነው የሚወጡት ያ ካልሆነ “ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም” እንደሚባለው ህውሀትስ ቢሆን ለሃያ ሰባት አመት አገርን የበዘበዘው ህዝብን እንደ ብረት ቀጥቅጦ የገዛው እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ በሰራቸው አራት ድርጅቶች አልነበረም ወይ ብሎ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የምርጫዋን ቀን በጉጉት በመጠበቅ በድምጹ “የኦሮሞን ብልጽግናን”፡ የአማራን ብልጽግናን”፡ እንዲሁም ሊሎቹን ብልጽግናዎች በድምጹ አይቀጠ ቅጣት እንደሚቀጣቸው የወቅቱ የብልጽግና መሪዎች ሆኑ ጠ/ሚ አብይ ከወዲሁ ሊገነዘቡ የግድ ይላል።

አባቶቻችን “ ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ” እንደሚሉት ጠ/ ሚ አብይ በሁለትሺ አስራ ሦስት ከመጀመሪያው ወር ጀምሮ ቡዙ ነገሮች ላይ ለውጥ ማድረግ ይገባቸዋል ከድርጅታቸው ስም ጀምሮ ይህንንም የሚያደርጉት እራሳቸው በጠ/ሚ ለመዝለቅ እና ለድርጅታቸው የወደፊት እጣ ፋንታ ሲሉ ነው። ጠ/ሚ አብይ በሁለት ሺ አስራ ሶስት ለወስዶቸው ከሚገባቸው ለውጦች ውስጥ።

በተለያዩ የኦሮሞ ክልሎች የደረሰው አሳቃቂና አሳዛኝ እልቂት መንግስታቸው ሳይፈራ ስሙን በመጥራት የዘር ማጥራት መሆኑን ማመን። ከዚያም መንግስትም እንደ መንግስትነቱ ለከሰተው እልቂት ይቅርታ መጠየቅ፤ በማስከተል ይህንን ወንጀል ያደረሱትን ለህግ ማቅረብ እና ይህንን ዓይነት ጥቃት ዳግም እንዳይፈጠር ጠንካራና ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት፤ ጠንካራ ህጎችን በስራ ላይ ማዋል፤ በተጨማሪ የሚመለከታቸው ተቋማትን ማናናቅ ሳይሆን አብሮ መስራት። በተለያዩ አካባቢ የተነሱት የይገባኛል ጥያቄዎች በህገ መንግስቱ መሰረት መመለስ አሊያም ህገ መንግስቱ ማሻሻል ያ ካልሆነ ሌላው ችግር ሆኖ ይቀጥልና በምርጫው ወቅት በድምጽ መቀጣትን አሊያም ከምርጫው በፊት በህዝባዊ መእበል ከስልጣን መውራድ ያስከትላል። ብልጽግና የግለሰቦችን ለውጥ ሳይሆን የተቋማት ለውጥን በግዜውና በወቅቱ ማምጣት ለዛ ተቋምም የሚመጥኑ እዋቂዎችን መመደብ ይጠበቅበታል ብልጽግና ፓሪቲ በአዲሱ ዓመት በታዋቂ ካዲሪዎች ሳይሆን በአዋቂ የድርጅት መሪዎች ካልተመራ ያ የሚጠበቅ ምርጫ ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለካድሬ የሚሰጠው ድምጽ እንደ ሌለው ከወዲሁ ሊያስቡበት ይገባ በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ የብልጽግና ድርጅት መሪዎች በሚያሳዩት አካሄድ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት በሚቻል ደረጃ የህወሀት መራሹን ኢህአዴግን ስናስወግድ ኦህዴድ መራሹ ብልስጽግና ተፈጠረ እያሉ እያማረሩ ሲሆን ጠ/ሚ አብይ ይህንን እየሰሙ የዝሆን ዦሮ ይስጠኝ ከሉ በድርጅቶት ላይ ለሚመጣው ሽንፈት ከወዲሁ ሊዘጋጁ ይገባል እንደ እውነቱ ከሆነ በአዲስ አበባ ላይ እያስቀመጦቸው ባሉት ከንቲባዎች ምክንያቱ እርሶ ጠ/ሚ ከአዲስ አበባ ኗሪዎች ልብ በልታሰበ ፍጥነት እየወጡ መሆኖትን ተገንዝበው በአዲሱ አመት ለአዲስ አበባ የሚመጥን ከንቲባ ካልሾሙ በአዲስ አበባ ላይ ምንም አይነት ወንበር እንደማያገኙ መጠራጠር የለቦትም። ይህ ብቻ አይደለም በሌሎችም ከተማዎች ላይ በአሁን ሰዓት ያሉት የኦሮሞ ብልጽግና፤ የአማራ ብልጽግና፤ የደቡብ ብልጽግና ካድሬዎች ከሆኑ የሚወዳደሩት እርሞትን አውጡ ለካድሬ ተመራጮች ድምጽ የሚሰጥ አለመኖሩን ከወዲሁ ሊገነዘቡ ይገባል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይህን ቪዲዮ የተመለከቱት 16,832 ሰዎች ብቻ ናቸው | ካላዩት ተመልክተውት አስተያየት ሊሰጡበት ይገባል

ጠ/ሚ የርሶ መንግስት በአዲስ አበባ በተፈጸመው የመሬ ቅርምት ሊጠየቁ የሚገባቸውን ባለስልጣኖች እና አቶ ታከለ ኡማን ጨምሮ እንዳይጠየቁ አለባብሰው ለማለፍ በሚመስል መልኩ on your Facebook page እንዲህ የሚል መለክት አስተላልፈዋል”እንደ አገር ግብ ከያዝን የአገራችን ህልውና የጋራ ድል እንደምንቀዳጅ ምንም ጥርጥር የለውም። ሁለት ተጻራሪ ዋልታዎች ላይ የሚንጠለጠሉ ፍላግጎቶች መቀራረብ አለባቸው እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ግትርነት የምናደርገው ጉዞ ሀፍት፤ ግዜና ጉልበትን ካማባከን ውጪ ምንም ጥቅም አይኖረውም…….”የሚሉ ትንተናዋች ይስተዋልባቸዋል በአባባሎት የምስማማ ሲሆን “እኔ ያልኩት ካልሆነ” የምትለው አባባል እርሶን የብልጽገናን አመራሮችን ጨምሮ ለሁሉም ገዢ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ።

ባብዛኛው ኢትዮጵያዊ እምነት አሁን በአገራችን ያለውን ችግር ለመፍታት በስልጣን ላይ ያለውን የብልጽግና መንግስት ወደ ውይይትና ከፍም ሲል ወደ እውነተኛ አገራዊ እርቅና አገራዊ መግባባት የሚመጣበትን መንገድ በቅንነት እና በግልጽነት መስራት ይጠበቅበታል ቅንነት እና ግልጽነት የምትለውን ቃል የጨመርኩበት ያለምክንያት አይደለም ሁላችንም እንደምናስታውሰው ለውጡ በመጣ ሰሞን በጠ/ሚ አብይ አቅራቢነት አገራዊ እርቅ እና አገራዊ መግባባት ላይ እንዲሰሩ ሃላፊነት የተቀበሉ የሐይማኖት አባቶች፤ አዋቂ ግለሰቦችና የፖለቲካ ሰዎች እንደ ነበሩ እናስታውሳለን እነዚህ ሰዎች በቅንነት እና በግልጽነት ስላልተሾሙ ስራቸው ሁሉ የጋን ውስጥ መብራት ሆኖ ቀርቷል የሚል ስጋት አለኝ። ለዚህ አባባሌ ሁለት ግለሰቦችን ስም በመጥራት ሃሳቤን እንዳላጠናክር ከይቅርታ ጋር ይፈቀድልኝ።

  • የቀድሞው ጠ/ሚ አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ። እኝህ ሰው ነፍሳቸውን ይማረውና ሞቹን ጠ/ሚ መለስ ዘናዊ የተኩ ጠ/ሚ ሲሆኑ ስልጣኑ ሳይሸራረፍ ነበር የተሰጣቸው እርሳቸው ግን ስልጣናቸውን ተጠቅመው ያመጡት ለውጥ የለም እንደውም ሲነግሩ የነበሩት የሞቹን ጠ/ሚ ለጋሲ አስቀጥላለው እያሉ ነበር ሲዋትቱ የከረሙት። በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ከተሰራው ግፍ አንዱን ላነሳ በሁለት ሺ ዘጠኝ ላይ እንዲት የኦሮሞ እናት በርበሬ እየሸጠ የሚያኖራቸውን ልጅ መንግስት በጥይት ተኩሶ መግደሉ ሳያንስ እኝህን እናት ልጃቸው አስክሬ ላይ እንዲቀመጡ ማድረጉ የቅርብ ግዜ ትዝትዝችን ነው ታዲያ እኝህ የቀድሞው ጠ/ሚ አቶ ሐ/ማርያም ደሳለኝ በስልጣን በነበሩበት ወቅት ለጠፋው ጥፋት ይቅርታ ጠያቂ መሆን ሲገባቸው በጠ/ሚ አብይ አገራዊ እርቁ ውስጥ አስታራቂ ሆነው መመረጣቸው እውነት አገራዊው እርቅ እንዲሳካ ታስቦ ነውን? ቅንነትስ የጎደለው ነው አያስብልም?

(ለ) ሌላው አገራዊ እርቅ ውስጥ የገቡ ተመራጭ ደሞ የወቅቱ የኢዜማ ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው ። ይህንን ሹመት ሥሰማ ጠ/ሚ አብይ ቅን ሆነው ነው ወይስ ተመራጮቹ ስልጣን እንደሚወዱ አውቀው እያላገጡባቸው ነው የሚል ጥያቄ ነው የመጣብኝ። ምክንያቱም ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በኢህአዴግ ፍርድ ቤት ከአንድም ሁለት ግዜ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሰው ስሆኑ እንደ እውነቱ ከሆነ ይቅርታ ተጠያቂ የሆኑ ሰው ነበሩ ታዲያ በተቃራኒው አስታራቂ የሆኑት እንዴት ነው? እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በተወሰነ ደረጃ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ምንም ጥፋት የለባቸውም ችግሩ የኢትዮጵያ የድርጅት መሪዎች ስልጣን ምን ያህል እንደሚወዱና ስልጣን ይሰጣቸው እንጂ ስልጣኑ እንዴት መጣ ብሎ የመጣበት መንገድ ተገቢ ነው ወይስ ተገቢ አይደለም ብለው እንደ ማያስተውሉ ከድርጅት መሪዎች ውስጥ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ማሳያ ናቸው። ምክንያቱም በወቅቱ በጠ/ሚ አብይ ለአስታራቂነት ቢታጩም፤ በመታጨታቸው ጠ/ሚ አብይን አመስግነው እርሳቸው ግን ለዛ ቦታ መታጨታቸው እርቁን እርቅ አይስብለውም ምክንያቱም እኔ በኢህአዴግ ፍርድ ቤት ከአንድም ሁለቴ ይሙት ባቃ የተፈረደብኝ ሰው ስለሆንኩ ይቅርታ ተጠያቂ እንጂ አስታራቂ ሆኜ መመረጥ የለብኝም ማለት ነበረባቸው ባይ ነኝ። ለዚህምይመስለኛል አገራዊ እርቅ እንዲያመጡ የተሾሙት ሰዎች በሁለት ዓመት ውስጥ ምንም አይነት ሪፖርት ለህዝብ ሊያቀርቡ ያልቻሉት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation)! ክፍል ሁለት - ከግርማ ሞገስ

በማስከተል በአዲሱ ዓመት በሁለት ሺ አስራ ሶስት ሁላችንም በአንድ ልብ መካሪ በአንድ አንደበት ተናጋሪ ሆነን እንድንነሳ ጠ/ሚ አብይ ትልቁን ድርሻ ወስደው በቅንነትና በግልጽነት እስከ ሚመጣው ምርጫ ድረስ አገራችንን እና ህዝባችንን በታማኝነት እንዲያገለግሉ በአክብሮት እጠይቃለው። ሁላችንም የሃገራችንን ሁኔታ ልብ ብለን ብንመለከተው ይህ ዘመን ከመቼውም ጊዜ የከፋና ይበልጥ የሚያስፈራ ሆኖ ይገኛል በተለይ ለውጥ ከመምጣቱ አንድ ዓመት በፊትና ለውጡ መጣ ከተባለ ጀምሮ ያለውን በጽሞና ስናጤነው በጣም ይሰቀጥጣል ብሎ ማለፉ ይበቃል። ለዚህ ችግር መሰረቱ የተረኝነት ፖለቲካ ነው እየተባለ በሰፊው ይተቻል። ይህንን የተረኝነት ብዥታ የሚሰማቸውን ካዲሬዎች ከድርጅቱ በማስወገድ ኮታ የሚባለውን አሰራር እስወግደው በእውቀታቸው የሚተማመኑ አመራሮችን ወደ ፊት ማምጣት ጠ/ሚ አብይ ይጠበቅቦታል ያን ግዜ ነው እውነተኛው የኢትዮጵያ ብልጽግና ድርጅት ሆናቹሁ አገርን እና ህዝብን መምራት የምትችሉት።

እንደ እውነቱ ከሆነ የብልጽገና ድርጅት መሪዎች የሚታዩትን ቅራኔዎችን መፍታት ሲገባቸው በእውቀት ማነስ አሊያም በአወኩሽ ናኩሽ ቂም ይዘው ያንን ቂም ባለመርሳትና ይቀር መባባልን እንደ ድክመት በመቆጠር አውቀው በድፍረት ስህቶቶችን ሲደጋግሙ ይታያሉ በኔ እምነት ወደፊት አዛኝ ነገር ግን አምባገናናዊ ወደ መሆን ሲያዘግሙ ይታያል የዚህም ማሳያ የሰሞኑ ሹመት ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል በብልጽግና ስር ያሉ ድርጅቶች እራሳቸውን አለመሆንና እንደ እስስት የተለያዩ ገፅታዎችን ማንጸባረቅና ዥዋዥዊ ሲጫወቱ ይስታዋልባቸዋል ይህን ዓይነት የድርጅት አወቃቀርና የማያውቁትን እንደ ሚያውቁ ያልሰሩትን እንደሰሩ ማቅረባቸውን ሲያበዙ ለዓገራዊ ቅራኔ ህዝቡን ሲገፋፉ ይስተዋላል ስለሆነም ይህንን ዓይነት አካሄ በግዜ መቅጨት የሁለት ሺ አስራ ሶስት የጠ/ሚ አብይ ተቀዳሚ ስራ ሊሆን ይገባል::

በማስከተልም በታሪክ እንደተማርነው ዳዊት ጎልያድን ያንጋለለው እንድ ጠጠር ድንጋይ በወንጪፍ አወናጭፎ ወይም ወርውሮ ግንባሩን ላይ መቶት ነው:: በሌላ በኩልም ምን የሚያክልን ትልቅ ተራራን እንዲት ትንሽ ወንዝ ሸርሽራ ትንደዋላች ይባላል:: የአንድ ሰው ጠጠር አልበግር ባዩን ጎልያድን ካንጋለለ ትንሽ ወንዝም ማን ይነካኛል ብሎ ተኮፍሶ የተቀመጥን ተራራ ሸርሽሮ ከናደ የኢትዮጵያ መቶ ሚሊዮን ህዛብ ቃል እንደተገባለት የማይመራ ከሆነ ወይኔ ለብልጽግና ከማለት ወዲያ ምን እላለው።

በመጨረሻም በአንድ ወቅት ሰለ አውቁ ኢትዮጵያዊ ሎሬት ጸጋዪ ግብረ መድን በአድንቆት ስናገሩ የርሱን ስራዎችም እንደሚያደንቁ በስብሰባ ላይ ለተገኙ የዘርፉ ባለሞያዎች ሲናገሩ ስለ ሰማው በዚህ አባባሉ የዛሬዪ ጹሁፍ ላጠቃልል “ቃል የእምነት እዳ እንጂ የናት አባት ርስት አይደለም” ፍቃዱ ተ/ማርያም እንድ ቴድሮስ !!

አገራችንን ኢትዮጵያን አግዚአብሔር ይጠብቅልን አሜን !!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.