በእነአቶ ጃዋርና በእነአቶ እስክንድር መዝገብ ክስ ይመሰረታል፣ በድርድርና ሽምግልና የሚለቀቅ ተጠርጣሪ አይኖርም – ጠ/ዐቃቤ ህግ

Tsegaw በድርድርና ሽምግልና የሚለቀቅ ተጠርጣሪ አይኖርም ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ። ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በመግለጫቸው ወንጀልን በሽምግልና የምንፈታበት ህግም ስልጣንም የለንም ነው ያሉት። በአደባባይ ሰው የገደሉና ውድመት እንዲፈጠር ያደረጉ ተጠርጣሪዎች ሳንመረምር አናስርም የሚል የለም ማስረጃውን መዝኖ ለህግ የማቅረብ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
 የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በመፈጸምና ግድያውን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ተብሎ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ክስ እንደሚመሰረት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።
ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ፍቃዱ ጸጋ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።
በሰጡት መግለጫ ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸውንና አብራው በነበረችው ግለሰብ ፣ በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብና በእነ አቶ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ እስከ ፊታችን ሀሙስ ድረስ ክስ እንደሚመሰረት ገልፀዋል።
በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ያሉት በአብዛኞቹ ላይ ምርመራው ተጠናቋል ተብሏል።
አቶ ፍቃዱ ጸጋ በመግለጫው ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያለውን አቅም ተጠቅሞ ጥፋተኞችን ለፍትህ የማቅረብ ሂደት በሻለ ሁኔታ ተፈጻሚ እየሆነ ነው ብለዋል። ኤፍ.ቢ.ሲ

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከ ጃንዋሪ 13 እስከ 14፤ በዋሽንግተን ዲሲ በጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የኢትዮጵያ ኃይሎች ምክክር ጉባኤ ይካሄዳል

2 Comments

  1. ይህ እጅግ የሚደነቅ ጉዞ ነው:: በሽምግልና ይለቀቃሉ እያለ ትህነግ የሚያሰራጨው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ጎማ ያስተነፍሳል:: የኦሮሚያ ብልፅግና በማያዳግም ሁኔታ ፀረ ኢትዮጵያ የጃዋርን አንጃ ከራሱ ድርጅት ፀድቶ ያውጣ:: የአማራ ብልፅግናም ከኦሮሞዎች ጋር እየተናበባችሁ ስሩ:: የሽመልስ ባህር ዳር መገኘት መልካም ጅምር ነው:: ስህተትን ተወያይቶ በይቅርታ ማለፍና ወደ 2013 በሰላም መሻገር ወቅቱ የሚጠይቀው ነው:: ትህነግን ይህ እንቅልፍ እንደሚነሳቸው ይታመናል:: ይንጨርጨሩ::
    በዚህ አጋጣሚ ኢዜማና ባልደራስ እንዲዋሀዱ በዚህ አዲስ ዓመት የአማራ ብልፅግና ና አብን በ2013 እንዲዋሀዱ ምኞቴ ነው:: ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል::!

  2. በ እነ እስክንድር ላይ ክስ መመሥረት ፍርደ ገምድልነትን በ ግልጽ ማወጅ ማለት ነው። እራስን መከላከል ወጀል ነው ማለት ነው። የ ባልደራስ አመራሮች ሌላ ወንጀል ከሌለባቸው በስተቀር ወጣቶችን እራሳቸውን እንዲከላከሉ ማደራጀት ወንጀል ነው ማለት ቁጭ ብላችሁ ቄሮዎች ይረዷችሁ ማለት ነው። ይህ ሁኔታ ተቀባይነት የለውም፤ ወደፊትም አይሆንም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.