የታይታ ይቅርታ የሃገራችንን መከራ አያስቆምም                                                                                                                          በቻፕሊያን ኤዲ (አደፍርስ) ሃብቴ

በቻፕሊያን ኤዲ (አደፍርስ) ሃብቴ    September 7/2020                                                                                                            Abebe 1

ሃገራችን ኢትዮጲያ በብሉይም ሆነ በሃዲስ የክርስትና ሃይማኖት በአይሁድም ሆነ በሙስሊም ሃይማኖትና በባህላዊ ሃይማኖት  ጭምር የዳበረ ልምድ ያላት ሃገር ነች:: ይህ እሴት ተግባራዊ ሆኖ ሃገራችን ለሚፈለገው የዜጎቿ መልካም የህይወት ኑሮ ያለመብቃት ይባሱኑ የመከራ የረሃብ በቅርቡ ደግሞ በአለም ያልታየ የአሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋ ክቡር የሰው ልጅ  አካል ከተገደለ በኋላ አካሉ መበጣጠቅ የቀብር ስፍራው ሳይቀር  መነፈግና ሃውልት ማፍረስ የታየባት ለመሆን በቅታለች:: በዳያስፖራም በማንም ሃገር ያልታየ የራሱን ሃገር ይወደም የሚል  የማፈሪያ አክቲቪስቶች ፖለቲከኞችና የሃይማኖት መሪዎች ክፉ ዘር ፍሬ የሆነ ተውልድ ታይቷል::

በዚህ ሁኔታ ለቆሰለች ሃገርና ህዝቦቿ ትክክለኛ የእርቅና የሰላም ጉባኤ  በኮ/ል መንግስቱ የሃገር ጉዳይ የባልና ሚስት ጉዳይ ኣየደለም ተብሎ የተቀለደበት በግዮን ሆቴል ሲጀመር በህወአት መሪዎች የተወገዘና የተሳተፉበት ከምክር ቤት የታገዱበት አይነት ከማድረግ ይልቅ ወቅቱን ጠብቆ የሃይማኖት መሪዎችን ይዞ የይቅርታ ድግስ ማድረግ  ያሳፍራል ::ብዙ ስሞታ የቀረበበት የፓርቲ አጋሩ ኣዲሱ ረጋሳ በለማ መገርሳ የዲሞግራፊ ስብሰባ ላይ “በሚዲያ የማይነገር ብዙ የሚሰራልን ስራ ኣለ “የተባለው ታከለ ኡማ  የፌዝ ይቅርታ ማሰማቱ በሃገሬና በተጀመረው  ለውጥ ለማዘን በቅቻለሁ:: ይቅርታ ሊጠይቁ የሚገባቸው የተደባለቀ ህዝብን በቤተሃይማኖት በጋብቻ በገበያ ቦታ ሳይቀር ይለያይ ዘንድ የቀሰቀሱ አንዱን ዘር ወይም ብሄርሰብ ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ በማድረግ ለከፋ መተላለቅ ያበቁ ሲሆኑ ይህ የይቅርታ ድግስ ይህን ተገቢ ሀገራዊ የእርቅና የሰላም ጉባኤ ለማጨንገፍ የተካሄደ የይስሙላ ይቅርታ በመሆኑ ሊስተካከል በህዝባችን ላይ የደርሱ ስቆቃዎች በገለለተኛ አካል በሚገባ ተጣርተው በደለኞቹ ለተገቢ ፍርድ ሊቀርቡ ይገባል:: መንግስት ዋነኛ ሃላፊነቱ የሆነውን የህግ የበላይነት ማስፈጸም ይቀድም ዘንድ ህዝባችንን የሚያባሉ ማናቸውም የሚዲያ ድርጅቶች በፖለቲካ ተቀናቃኝነታቸው ሳይሆን በፈጸሙት የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ተገቢው የህግ ርምጃ ይደረገባቸው ዘንድ የሚዲያ ፈቃዱም በዘር መካሄዱ ያስከተለው ስቃይ ግምት ውስጥ ገብቶ የሚታገድበት ህግ ይዋቀር ዘንድ  ማሳስብ ፈልጋለሁ::

Screenshot 20200907 095104 Facebook

በዚህ አጋጣሚ ለወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳትም ሆነ ለሃገራችን ህልውና ወሳኝ የሆነው የቀደመ ስሟ ፊንፊኔ እንደነበር ታዋቂ የታሪክ ሰው ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ የመስከሩላት አዲስ አባባ የገጠማት ያላስፈላጊ የባላቤትነት ፉክክር የሚቀርፍ በተመድ   የቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ለምክር ላቀርብ እወዳለሁ:: በከተማዋ ዙሪያ የነበሩና ያሉ የተፈናቀሉ የተገፉ የወረገኑ ኦሮሞ ወገኖች ጉዳይ የፖለቲካ ፍጆታ እንዳይሆን ከተማዋ የሁሉም የኢትዮጲያ ዘሮችና ብሄረሰቦች በመሆን በነዋሪዋ የምትተደዳረበት ህግ ባስቸኳይ ይደነገግና የፌደራል መንግስቱ ጣልቃገብነት ይቆም ዘንድ አሳስባለሁ::

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.