ኢህዴን/ብአዴን/አዴፓ የአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህርዳር ሆና ስትመረቅለት፣ አዲስ አበባን ለኦነግ / ኦህዴድ/ ኦዴፓ ሸጠ! (ክፍል አንድ) ሚሊዮን ዘአማኑኤል

et 8በ2013ዓ/ም ኢህዴን/ብአዴን/አዴፓ የባንዳ ባንዲራ ይውረድ፣ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በአማራ ክልል ይውለብለብ!!!  ኢህዴን፣ብአዴን የአማራ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ ባህርዳር ሆኖ  ሲመረቅለት፣ አዲስ አበባን ለኦነግ/ ኦህዴድ የሸጠ ድርጅት ነው!!! የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ፡-

{1} የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዲስ አበባን ከተማን ለኦነግ/ ኦህዴድ አሳልፈው የሸጡትን የኢህዴን/ብአዴን የፖለቲካ ሴረኞች ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ የሙሉ ዓለም አበባና የጀነራል አሳምነውና ጎዶቹ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ የክልሉ መንግሥት በአዲስ አበባ ጥያቄ ላይ ግልፅ አቆሙን መግለጫ አውጥቶ ያሳውቅ፡፡ በሃገሪቱ የሚገኙ ክልላዊ መንግሥቶች ያለአንዳች ፍርሃት በአዲስ አበባ ከተማ የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ መሆኖን በመግለጫ ያሳውቁ፡፡

{2} የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ለጎንደር፣ ለወሎና ለሸዋ ራሳቸውን በእራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በጎንደር፣ ባህር ዳር፣ በደሴና ደብረብርሃን ከተሞች የኢንቨስትመን፣ የዳኝነት፣ የግብር ወዘተ የመሳሰሉት ጉዳያቸው በዛው በከተማቸው እንዲካሄድ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደራዊ መብታቸው እንዲከበር ይደረግ፡፡ በህር ዳር ድረስ እየሄዱ ጉዳይ ማስፈፀም ዘመን ያለፈበት  የገባሪና አስገባሪ ጸረ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲወገድ ትግላችን ይቀጥላል፡፡ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር ለጎንሬው፣ ለወለዬውና ለሸዌው እኩል የስራ ዕድል፣ የሥልጣን ደረጃ፣ ለተገቢው ቦታ በትምህርትና እውቀት ላይ የተመሠረተ ውድድር በማድረግ የሰው ኃይል ያለአንዳች አድሎ በግልፅነት እንዲሰራ ተደማሪ ፀረ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎችን ይታገላሉ፡፡ እስካሁን ያለው የክልሉ የሰው ኃይል አመዳደብና መዋቅራዊ አሰራር እንዲሁም  ሹማምንት ድርሻ  በመረጃ ቀርቦ እንዲገመገምና አድሎዊ ምደባና ግልፅነት የጎደለው አሰራር እንዲወገድ መታገል፡፡

{3} የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አሁን ያለውን የኢህዴን/ብአዴን ሰንደቅ ዓላማ  ቀይሮ ጥንታዊውን አረንጎዴ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቃላማው እንዲያደርግ በህዝብ ሰላማዊ ሠልፎች በየጊዜው ተውለብልቦ እያየ በፍርሃት ርዶ ሲንቀጠቀጥ ይስተዋላል፡፡ የአማራ ህዝቡና የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠይቀው የጥንት የጠዋቱን ስንደቅ አላማ እንዲውለበለብለት ነው፡፡ የኢህዴን/ብአዴን ባንዲራ ህዝብ አውርዶት ታይቶል፣ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ አንግቦ በየሠላማዊ ሠልፉ ሲያውለበልብ ተስተውሎል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰንደቅ ዓላማ ሪፈራንደም እንዲያደርግ መታገል ያስፈልጋል፣ እስከዛው የአማራ ህዝብ ሪፈራንደም አድርጎ በክልሉ እንዲያውለበልብ መታገል ያሻል፡፡

{4} የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በጀት ድልድል ፍህታዊነት በመረጃ እንዲቀርብ፣ የበጀቱ ክፍፍል ለመደበኛና ለካፒታል በጀት ድርሻ ለመሠረተ ልማት ፍህታዊ ድልድል ወዘተ ለጎንደር፣ ለጎጃም፣ ለወሎና ሸዋ ህዝብ ባለፉት ሦስት አስርቶች እንዴት እንደነበር በመረጃ ማቅረብ ያሻል፡፡ ለዩኒቨርሲቲዎች መረጃዎቹን ይፋ በማድረግ የአስተዳደር፣ የምጣኔ ኃብት ምሁራንና  አጥኝዎች እንዲተቹበት ማድረግ ዘመናዊነት ነው፡፡

{5} የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ሥራ በገለልተኛ ኮሚሽን ተቆቁሞ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና ሸዋ ውስጥ የተሰሩትን መሠረተ ልማቶች መንገድ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት ወዘተ በመረጃ እንዲቀርብ ህዝብ በትግሉ ይጠይቃል፡፡ በ2013ዓ/ም ኢህዴን/ብአዴን/አዴፓ የባንዳ አመራሮችን በማስወገድ የአማራ ክልላዊ መንግሥትን  ዳግም ማዋቀር ግድ ይላል፡፡

{6} የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች የሦስት አስርት ሥራዎች በገለልተኛ ኮሚሽን ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወሎና ሸዋ የተዋቀረ ኮሚሽን በመረጃ ተጣርቶ ለህዝብ እንዲቀርብ በትግሉ ይጠይቃል፡፡

{7} ለክቡር ዶክተር አስራት ወልደየስ ለመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) መሥራች በአዲስ አበባ ኃውልት እንዲቆምላቸው ህዝባችን በትግሉ ይጠይቃል፡፡ በመአህድ አባላቶች ላይ የተፈፀመ ወንጀል ተጣርቶ ወንጀለኞቹ ለፍርድ ይቅረቡ፡

{8} የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አዲስ አበባን ለኦነግ/ ኦህዴድ/ኦዴፓ እንደሸጠ ሁሉ፣ ዛሬ ለባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ ልደቱ አያሌው፣    እንዲፈቱ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ ንስሃ እንዲገባ!!!

 

የሃገሪቱ ወርካዎቹ አፄ ቴዋድሮስ፣ አፄ ዮሃንስ፣ ዳግማዊ ሚኒሊክ፣ እቴጌ ዘውዲቱ፣ ልጅ ኢያሱ፣ ቀ.ኃ.ሥ.፣መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ መለስ ዜናዊ፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዶክተር አብይ አህመድ ወዘተ ገድለ ታሪክ  ወደድንም ጠላንም የአገራችን ታሪክ ነው፡፡ በትግራይ አክሱም ፣ በጌምድር ጎንደር፣ በወሎ ላሊበላ፣  በሸዋ አንኮበርና አዲስአበባ የኢትዮጵያ ዋና መዲና ሆነው አገልግለዋል፡፡ በ1889 እኤአ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና መዲና ሆና በዳግማዊ ምኒሊክ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያና ግርማዊት ንግሥተ ነገሥታት እቴጌ ጣይቱ ቡጡል ተቆረቆረች፡፡  አዲስአበባ  የዛሬ 131አመታት በፊት በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና ተቆረቆረች፡፡ የሸዋ ክፍለሃገር ዋና መዲና ተባለች፣ በሸዋ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ወዘተ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና ናት፡፡  ሸዋ ልዩ ጥቅም ግን ጠይቆም ተሰጥቶትም አያውቅም፡፡  ሻብያ ወያኔና ኦነግ ለኢትዮጵያ ህዝብ የመቶ አመት የቤት ሥራ በመስጠት ኤርትራን በማስገንጠል፣ ኢትዮጵያን ለዘጠኝ ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች ከፋፈሉ፡፡  የአማራ ክልል መንግሥት ዋና ከተማነት ባህርዳር ስትመረጥ ኢህዴን/ ብአዴን ኢህአዴግና አዴፓ ብልፅግና ፓርቲ  የፖለቲካ ሴራ አዲስ አበባን ለኦነግ ኦህዴድ ኦዴፓ አሳልፎ እንደሸጡ  የድብቁ ስምምነታቸው አካል ነበር፡፡

1889 እኤአ አዲስ አበባ የኢትዮጵያና የሸዋ ዋና መዲና ሆና በእቴጌ ጣይቱ ከተቆረቆረች መቶ ሃያ ሦስት አመታት ተቆጥሮል፡ የኢትዮጵያ ዜጎች በሃገሪቱ ባሉ አስራ አራት ጠቅላይ ግዛቶችና ዋና ከተማቸው  (ኤርትራ(አስመራ) ፣ትግራይ(መቐለ)፣ ወሎ(ደሴ)፣ በጌምድር(ጎንደር)፣ ጎጃም(ደብረማርቆስ)፣ ወለጋ(ነቀምት)፣ ኢሉባቡር(ጎሬ)፣ አርሲ(አሰላ)፣ ሸዋ(አዲስ አበባ)፣ ሀረርጌ(ሃረር)፣ ከፋ(ጂማ)፣ ጎሞጎፋ(አርባምንጭ)፣ ሲዳሞ(ሃዋሳ)፣ ባሌ(ጎባ) ይባሉ ነበር ) በእያንዳንዱ ጠቅላይ ግዛቶች ውስጥ በጋራ የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ ሲሆኑ በጆግራፊ፣ በኢኮኖሚና በታሪክ መስተጋብራቸው ተከፋፍለው በህግ፣ በነጻነትና ሠላም  ይተዳደሩ የነበረበት ወርቃማ ዘመን ነበር፡፡

 

1984ዓ/ም የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ፖለቲከኞች ሃገሪቱን ለዘጠኝ የዘርና ልሣን ክልሎች ከፋፈሉ፣አዲስ አበባ የሃገሪቱ ዋና ከተማ በማድረግና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ በማለት የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ያጋጩበት ለሃያ ዘጠኝ አመታት በከፋፍለህ ግዛ ዘይቤ የገዙበት የፖለቲካ ሴራ ሚስጢር ነው፡፡ የዚህ ፖለቲካ ሴራ ዋና ጠንሳሽ ደግሞ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ መለስ ዜናዊና ሌንጮ ለታ  ነበሩ፡፡  የአማራው ክልል በሽግግሩ መንግስት ጊዜና በህገ-መንግስቱ ማርቀቅ ላይ እንዳይካፈል ተደረገ፡፡ የወያኔ ተላላኪ ኢህዴን/ ብአዴን አመራሮች ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምዖን፣ ተፈራ ዋልዋ፣ አዲሱ ለገሠ፣ ህላዊ ዬሴፍና በአማራ ህዝብ ስም ሠላሳ አመታት ነገዱ፣ ህዝቡን አሰሩ፣ ገረፉ፣ አሰደዱ፡፡  ኢህዴን/ብአዴን አባላት በህዝብ ዘንድ ‹‹የአህያ ባል፣ ከጅብ አያስጥል!!!›› ይባሉ ነበር፡፡

 • አንደኛው መፈንቅለ መንግሥት በሙሉ ዓለም አበበ 1983 እስከ 1885 ዓ/ም (Mulu Alem Abebe 1991-1993) የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበረ የኢህዴን ታጋይ ሲሆን የመጀመሪያው  የፖለቲካ ሴራ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የተከሰሰ   ሙሉዓለም ለምን እንደተገደለ እስከዛሬ ድረስ የብአዴን አዴፓ ድብቅ ሚስጢር  ሆኖል፡፡ ሚስጢሩ ግን ሙሉ ዓለም አበበ የመለስ ዜናዊን የወያኔን የኢትዮጵያ አዲስ ካርታ አዲስ አበባን ለኦህዴድ ኢህአዴግ ተደርጎ የተካለለውን የፖለቲካ ሴራ በማጋለጡና አልቀበልም በማለቱ በመለስ ዜናዊ ትእዛዝና በጎደኞቹ ኢህዴን/ ብአዴን በግፍ ባህርዳር በቦንብ የተገደለ መሆኑን ታሪክ ያወጣዋል፡፡ ሙሉዓለም  ቤተ-እስራኤላዊ/ ፈላሻ ስለሆነ ከእስራኤል ሞሳዶች ጋር ተመሳጥሮ መንግሥት ለመገልበጥ ያሴር ነበር በሚል የውሸት ክስ መስርተውበት ነበር፡፡ ስለሙሉ ዓለም አበበ የጠየቁ የኢህዴን  ጎዶቹ እነ አንዳርጌ ወዘተ  በግፍ ተገድለዋል፣ ታስረዋል ወይ ተሰደዋል፡፡ አንድ ቀን የብአዴን አመራሮች ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡
 • በሁለተኛው በነጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ጀነራል አለበል አማረ፣ ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ ሌሎች የብአዴን አባላቶች ከግንቦት ሰባት ጋር የተሳተፉበትና የ2001 ዓ/ም (2009 )በመለስ ዜናዊ የወያኔ መንግሥት ላይ የተሞከረ መፈንቅለ መንግሥት   ‹‹ህዝባዊ ጋርድ›› በሚል ህቡዕ ድርጅት ሥር የተደራጁና የተመራ ነበር፡፡
 • ሦስተኛው መፈንቅለ መንግሥት የሰኔ 16 ቀን 2011ዓ/ም በአማራ ክልላዊ መንግስት አመራሮች ላይ ባህር ዳር የተፈጸመ ግድያ የዶክተር አንባቸው መኮንን፣ ምግባሩ ፣ እዘዘው፣ ብርጌደር ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጄኔራል ገዛዒ አበራን በመኖሪያ ቤታቸው በጠባቂያቸው በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል የተባሉት ወንጀለኞች እስከዛሬ ለፍርድ አልቀረቡም፡፡ ሦስተኛው በስመ መፈንቅለ መንግሥት ስም ጀነራል አሳምነው ፅጌ የተማከኘ  የፖለቲካ ሴራ ነበር፡፡

 

ምንሊክንና የእቴጌ ጣይቱ ቡጡል የመሠረቶትን አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማና  የሸዋ ክፍለ ሀገር  መዲና  ሆና አገልግላለች፡፡  ኢህዴን/ብአዴን/ኢህአዴግ  ለኦነግ/ኦህዴድ አሳልፈው እንዲሰጡ  በማድረግ ህወሓት/ኢህአዴግ ከበርሃ ሳሉ የተስማሙበት የፖለቲካ ሴራ ውስጥ በአማራ ግዛት ውስጥ የነበሩትን ቦታዎች ወደሌላ በመከለል ህዝብን ከፋፍለው በማጋጨት ከተደረጉት የከፋፍለህ ግዛ ሴራዎች ውስጥ ከሚጠቀሱት፡-

 • ጎንደር ክፍለ ሃገር ስር ይተዳደር የነበረውን ወልቃይት፣ ጠለምት፣ መተማ፣ ሁመራ ወዘተ ለህወሓት አሳልፈው ሸጡት የአማራ ከልል የማንነትና የወሰን ጥያቄ በአማራ ክልል ማፕ ላይ እንኮን አልተካተተም፣ ክልሉ እንዴት የእኔ ግዛቶች ናቸው ብሎ በካርታው ላይ እንኮን ግዛቱን አላካተተም፡፡ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ/ም  ሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ከተማን ተቆጣጠሩ፡፡
 • ጎጃም ክፍለ ሃገር ስር ይተዳደር የነበረውን መተከል ግዛት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ አስተዳደር ተከለለ
 • ወሎ ክፍለ ሃገር ስር ይተዳደር የነበረውን ራያ፣ ሃሸንጌ ኃይቅ፣ አላማጣ ወዘተ ለህወሓት ክልላዊ አስተዳደር የተከለለ
 • ሸዋ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ የነበረውን አዲስ አበባ እንዲሁም በሸዋ ስር ይተዳደር የነበረውን ደራ ለኦህዴድ በኦሮሚያ ክልላዊ አስተዳደር የተከለለ
 • በህወሓት ኢህአዴግ በሌሎች ክልላዊ አስተዳደሮች በግፍ የተከለሉ ግዛቶች አንዱን ህዝብ ከሌላው በማጋጨት ከፋፍለው ለመግዛት የተጠቀሙበት በዘር ላይ የተመሠረተ ግዛት፣ የፖለቲካ ሴራ ህዝቡን ለሞት፣ ለግጭት፣ ለስደት ለመፈናቀል ዳርጎታል፡፡

የታሪክ ምሁራን ስለ አዲስ አበባ ከተማ ታሪክ ለህዝብ ማሳወቅና አዲስአበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማና፣ የሸዋ ክፍለሃገር ዋና መዲናነቷን ካጣች 29 ዓመታት ተቆጥሮል፡፡ አዲስአበባ ከተማ የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ዋና መዲና የአፍሪካ አንድነት ዋና ከተማ በመሆን ለአንድ ክፍለ ዘመን በላይ አገልግላለች፡፡

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ/ም ህወሓት/ኢህአዴግ  አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ብሎም በ1987 ዓ/ም ባጸደቁት ህገመንግሥት መሠረት ኢትዮጵያ በዘጠኝ ክልሎች ተሸንሽና አዲስ አበባ በመጀመሪያ በክልል አስራ አራትነት በኃላም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ ዋና ከተማ፣ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ወዘተ ሲባል አመታት ተቆጠረ፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት ዋና ከተማነት ባህርዳር የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን) የህወሓት ቡችላ ተበረከተለት፡፡ የዳግሞዊ ሚንሊክና የእቴጌ ጣይቱ ቡጡል የቆረቆሮት ዋና ከተማ አዲስ አበባ ለኦሮሞ ክልል መንግስት፣ ለኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ)  አዲስ አበባ ተሸጠች፡፡

Ethiopia is a federation subdivided into ethn o-linguistically based Regional States (plural: ክልሎች kililoch; singular: ክልል kilil) and chartered cities (plural: astedader akababiwach; singular: astedader akabibi). This system of administrative regions replaced the provinces of Ethiopia in 1992 under the Transitional Government of Ethiopia and was formalised in 1995 when the current Constitution of Ethiopia came into force.

 • በ1991 ሻብያና ወያኔ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ተቆጣጠረ፡፡ መንግስቱ ኃ/ማርያም ዚምባዌ ተሰደደ፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ በ1993 እኤአ ኤርትራ ከኢትዮጵያ አስገነጠለ፡፡
 • በ1994 በኢትዮጵያ አዲስ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፌዴራላዊ የዘውጌ መንግስት ተመሠረተ፡፡››1
 • መለስ ዜናዊና የትምህርት ሚኒስትሮ ገነት ዘውዴ (ጉዲት) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት 40 መምህራንን አብዛኛዎቹ አማራ በመሆናቸው የተባረሩ ሲሆን ግፉ ዘሬ ተዘንግቶ፣ ሃገር የማፍረስ ተልእኮቸውን ግን ያለ አንዳች ፀፀት ቀጥለውበታል፡፡

የደሃ ፖለቲካኞች ሽሮ መብልያ ጥያቄ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ክልልና ዓለም አቀፍ የውጭ ግንኙነት ዕይታ፡-  በኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች፣  የኦሮሚያ ክልል፣  የአማራ ክልል፣ የትግራይ ክልል፣ ሱማሌ ክልል፣ ደቡብ ክልል፣  ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ጋምሌላ ክልል፣ ሃረሪ ክልል፣ አፋር ክልል የዘረኛ ምሁራን የፖለቲካ ሥልጣንና የፖለቲካ ሽሮ መብያ ጥያቄ መሆኑን እናረጋግጥላችኃለን፡፡ የወያኔ ህገ መንግሥት የሣር ጉዝጎዝ ያህል ዋጋ በማጣቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ አዲስ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ህገመንግስት ማርቀቅ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ መሆን ይኖርበታል፡፡ ዜጎች በሃገራቸው ውስጥ ተዘዋውረው የመስራት፣ በሃገሪቱ ውስጥ ሃብት ማፍራት የመምረጥና የመመረጥ መብታቸው ተረጋግጦ አንዱን ባለአገር አንዱን  መጤና ሠፋሪ የሚል ፍረጃ ታሪክ ሆኖ የሚቀርበት ሥርዓት መመሥረት የአዲሱ ትውልድ ጥያቄ ነው፡፡

{I} በኢትዮጵያ የክልል መንግሥት ድንበሮች/ ወሰኞች፣(Regional state borders) የኦሮሚያ ክልል 9 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአማራ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የአፋር ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የሱማሌ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የደቡብ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የጋምቤላ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የሃረሪ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣የአፋር ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣  የክልሎች የድንበር ግጭቶች  የማያባራ ጦርነት ያስከትላል ኢትዮጵያ ብቻ ድንበርና ወሰን ሲኖራት በውስጦ የሚገሙ ክልላዊ መንግሥቶች ድንበርና ወሰን ሊኖራቸው አይገባም እንላለን፡፡
በፈቃድ ከመጣ ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!! (‘No slavery is more disgraceful than that which is self-imposed’Seneca) ይሄ አባባል ለእኛ ‹‹በፈቃድ ከመጣ የልሂቃን ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› ቢባል ያስኬዳል፣ የኢትዮጵያ ልሂቃን ከባህር ማዶ የቀሰሙትን ትምህርት ከሃገራቸው ተጨባች ሁኔታ ጋር ባለማዛመድ እንዳለ በመቃዳትና በመተርጎም ከስልጣኔ ማማና ከምሁራን ጎራ ቢደመሩም ለሃገራቸው የፖለቲካ፣ ምጣኔ ኃብትና ምህበራዊ ጉዳዮች የሰጡት መፍትሄ አጠያያቂ ነው፡፡ በወያኔ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የህብለ በራሄ (ዲኤን ኤ) ፌዴራሊዝም ፖለቲካ ከተጫነብን 29 አመታት ተቆጠረ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ህዝቡን በልሳን ከፋፍሎ ለሞት፣ እስራትና  ስደት  ዳረገው፡፡ በኦሮሞና ሱማሌ፣ በአማራና ትግራይ፣ በሲዳማና ወላይታ፣ ወዘተ በተከሰተው የዘር ግጭት የሃገር ውስጥ ተፈናቃዬች ቁጥር ከሁለት እስከ ሦስት ሚሊዮን አሻቅቦ ነበር፡፡ የህወሃት አመራር በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ተካሄደበት፣በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፀመብን  ‹ኢንተር ሃሞይ!› ብለው እንደጮሁት ዛሬም ድራማ እየሰሩ ናቸው ታዲያ እነዚህን ቦዘኔ ሌባ የወያኔ አመራሮች ‹‹በፈቃድ ከመጣ የወያኔ አመራር ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› ልንላቸው ይገባል፡፡ ማንም ሰው ከህግ በላይ መሆን ስለማይችል መቐለ የመሸገው ፀረ-ዴሞክራቲክ ኃይል ለፍርድ መቅረብ ይገባዋል እንላለን፡፡ ከ2012 ዓ/ም  የጵጉሜ አራት የትግራይ ክልል ምርጫ ህዝቡን በስብዓዊ ጋሻነት በመያዝ ጦርነት ለመጫር ወያኔ አሲሮል፡፡ በትግራይ ህዝብ አልገዛም ባይነትና እንቢተኛነት ወያኔ ከሥልጣን መንበሩ ያለአንዳች ጦርነት ከሥልጣን ይወርዳል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ (የሹማምንት ዝውውር፣ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለ ግንኙነት ማገድ)፣ የኢኮኖሚ(በጀት እቀባ)ና የአገልግሎት(ኢንተርኔት፣ ስልክ) ማዕቀብ በጥናት በማድረግ ከትግራይ ህዝብ ጋር በጋራ በመቆም ወያኔን ማስወገድ፡

 

በዘር ግጭት! የሃገር ውስጥ ተፈናቃዬች! የማንነት ጥያቄ ሠለባዎች፣ ባለፉት 29 አመታት ወያኔ ባጸደቀው በዘርና ልሳን በተከለለ ፌዴራላዊ ክልላዊ አስተዳደር የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁም ስቅሉን በማየት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ በወያኔ ከፋፍለህ ግዛው የአባላህኝ ዘመን ከክልላቸችን ውጡ፣ ቅስቀሳ የተነሳ የሃገራችን ዜጎች በሁሉም የሃገሪቱ ግዛት ውስጥ ተዘዋውሮ የመስራት መብቱንና ክብሩን አጥቶል፡፡ በዚህም የተነሳ ከአንድ ሚሊዩን 500 ሽህ ህዝብ በላይ የኦሮሞና ሱማሌ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለው ነበር፡፡ በጉጂ ኦሮሞዎችና በሲዳማ ጊዴኦ የዘር ግጭት የተፈናቀሉ ከ750 ሽህ እስከ አንድ ሚሊዮን ወገኞቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለው ነበር፡፡ በሲዳማና ወላይታ በተከሰተው  የዘር ግጭት ከ20 እስከ 30 ሽህ ህዝብ ተፈናቅሎል፡፡ ለዚህ ነው ህገ-መንግሥቱ ይቀየር የምንለው!!!

{1} የትግራይ  ህዝብ ተፈናቃዬች፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና የትግራይ መንግሥት የትግራይ ተፈናቃዬችን 8 ሽህ 510 ሰዎች ከሚኖሩበት ቀዬ ከአማራና ኦሮሞ ክልል ተፈናቅለው ነበር፡፡ የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት የሆኑት አብዲ ኢሌ 10 ሚሊዮን ብር እርዳታ መስጠት በዜና ማሰራጫ ቀርቦ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የትግራይ ርዕስ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዬን በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ተደረገ በማለት ከመቐለ በማቅራራታቸው ይታወሳል፡፡ እናቱ የማተችበትም፣ ወንዝ ውሃ ለመቅዳት የወረደችበትም ህፃን እኩል ያለቅሳል እንደሚባለው ዓይነት የኢትዮጵያን ህዝብ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡  ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ እንዳልሆነ የትግራይ ወጣቶች አረጋግጠዋል፡፡ የትግራይ ወጣቶች በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ በነፃነት መንቀሳቀስ መቻላቸውን አገራግጠዋል፡፡ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ከሽፎል፡፡ ወያኔ የትግራይን ህዝብ በስብኣዊ ጋሻነት ጠርንፎ ይዞል፡፡ የትግራይ ወጣቶች በትግላቸው ነፃ ይወጣሉ፡፡

{2} አማራ ህዝብ ተፈናቃዬች፣ ከጉራፈርዳ በመለስ ዜናዊ ዘመን በሽፈራው ሽጉጤ አስፈፃሚነት በአንድ  ጊዜ ብቻ ከ78000 በላይ ቁጥር ያላቸው አማራዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ከአማያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ውስጥ የሚገኝ ሥፍራ በህወሃት/ኦህዴድ  አስፈፃሚነት ከ5000 በላይ ቁጥር ያላቸው አማራዎች ተባረዋልበ 1992 ዓ/ም ከ12000 በላይ ተባረዋል በኢሰመጉ ከ1983 እስከ 2009 ዓ/ም ድርጊቱ ተጋልጦ ነበር፡፡በወያኔ ትእዛዝ ሰጪነት ፣ በኦህዴድ አስፈፃሚነት ከምስራቅ ወለጋ ጊዳ ኪራሙ አካባቢ ቤትና ንብረታቸው ተቃጥሎ፣ ቤተክርስቲያን ተቃጥሎ፣ በቤት ንብረታቸው ተዘርፎ ሰብላቸው እንዲቃጠል ተደርጎ ወደ አማራ ክልል አዊ ዞን ውጥ ጃዊ በረሃ ተጥለው ለወባና ሌሎች በሽቶች ተዳርገዋል ለሞት በቅተዋል፣ ቤተሰቦች ተበትነዋል፡፡ቤኒሻንጉል ከክልል መተከል አውራጃ ዲባ ጤናና ማንዱራ ጉንጉዋ በተባለው ወረዳዎች ውስጥ የቤኒሻንጉል ነፃ አውጭ ድርጅት በሚባል ኃይል ፈፃሚነት 6000 በላይ አማራዎች ሲፈናቀሉ፣ 270 ሰዎች ተገድለዋል፡፡6833 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ ቤት ንብረታቸው የቤት እንሰሳቶቻቸው ተወስደዋል፡፡ ከተለያዩ ክልሎች ከ500 ሽህ በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች በወያኔ ሴራ በግፍ ተፈናቅለዋል፡፡ በቅርቡ በሻሸመኔ፣ በአርሲ፣ በጅማ፣ በባሌ ወዘተ በአማራ ህዝብ ላይ የሃይማኖትና የዘር (ጆኖሳይድ) ጭፍጨፋ መፈጸሙን ልብ ይበሉ፡፡ ጥቃቱ ሌሎችንም ህዝብ አካቶል፡፡

{3} በጉጂ ኦሮሞዎችና በሲዳማ ጊዴኦ የዘር ግጭት የተፈናቀሉ ወገኖቻችን፣ ከ740,000 ቁጥር ያላቸው የጊዴኦዎች እና ከ 178,000 በላይ ቁጥር የጉጂ ኦሮሞዎች ተፈናቅለዋል፡፡ በመቶዎች  የሚቆጠሩ  ኢትዮጵያውያን ሞተዋል፡፡ የጊዴኦ በደቡብ ክልልና ጉጂ በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ የሚኖሮ ወገኖች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ የውስጥ ተፈናቃዬች ቁጥር በአሁኑ ሰኣት 970 ሽህ መድረሱ ተገልፆል፡፡ 30,000 በላይ ቁጥር ያላቸው ሲዳማዎች የአክራሪ ብሄርተኛነት ፖለቲካ ውጤት በሆነው የነገድ ማንነት መሰረት ያደረገ  ውዝግብ እናንተ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ተብለው ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ተባረው ነበር፡፡

{4} በኦሮሚያ ክልልና በሱማሌ ክልል ወሰን አንድ ሚሊዮን የተፈናቀሉ ወገኖች፣ በኦሮሚያ ክልልና በሱማሌ ክልል ከ800,000 ኦሮሞዎችና ከ200,000 በላይ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ሶማሌዎች ተፈናቅለው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በሃገር ውስጥ የተፈናቃዮች ቁጥር 1.7 ሚሊዮን ህዝብ በተለያዩ አካባቢዎች በኦሮሚያና በደቡብ ክልል በተቀሰቀሰ የዘር ግጭትና በድርቅ የተነሳ ተፈናቅለው ሠፍረው ነበር፡፡

{5} በአዲስ አበባ፣ በቡራዩ፣ አስኮ፣ በጉራጌ፣ በስልጤ፣ በአርባ ምንጭ ወዘተ የተከሰተ የዘር ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የተፈፀመ አሳዛኝ ድርጊት ነበር፡፡ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እስካሁን አልቀረቡም!!!

{6} የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት መሪዎችና የኦሮሞ ክልላዊ መንግስት መሪዎች በጋራ ተጠያቂነት ጅዋር መሃመድ ተከብቤለሁ ባለ ምሽት ሰማንያ ስድስት ሰዎች በግፍ ተገድለዋል፣ በአረመኔ ቄሮዎች ታርደዋል ፍርድ ግን አልተገኘም፡፡ ቀጥሎም  በሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በሻሸመኔ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ጅማ የመቶ ሰማንያ ሰባት ሰዎች ግድያና የንብረት ውድመት አረመኔ ወንጀለኞች ለፍርድ አልቀረቡም፡፡  የዘር ተረኞቹ አንድ ቀን እራሳቸው ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡

አይነኬ የወያኔ ወንጀለኞች ለህግ ጥሰት ፈር ቀዳጆች ናቸው!!! ህወሓት የተከለው የህብለ በራሄ (ዲኤን ኤ) ፖለቲካ ሥር ሰዶ ትልቅ ወርካ ዛፍ ሆኖል፡፡ ህብረ ብሄር ፓርቲዎችና የብሄር ድርጅቶች ተቻቻሉ!!! አይነኬ የህወኃት ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!! ወያኔ ከመቐሌ ሽብር ስፖንስር ያደርጋል፡፡ ወያኔን በኢኮኖሚ መአቀብ መጣል ይቻላል

 

የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበር!!!

ባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ እንዲሁም ልደቱ አያሌው፣ ይፈቱ!!!

አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ክልላዊ መንግሥትነት ይገባቸዋል!!!

2013ዓ/ም መልካም አዲስ አመት ለመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ይሁንልን!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.