የገዳ ሥርዓት ‘ጅብ ከማይታውቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ!’ – በገ/ክርስቶስ ዓባይ        

Geda ጳጉሜን 2 ቀን 2012 ዓ/ም

የመርገም ጨርቅና እና ሽንፍላ ቢያጥቡት አይጠራም የሚባለው ፈሊጣዊ አነጋገር እውነት መሆኑን የሚያረጋግጡ በርካታ ሁኔታዎች እየታዩ ነው። አንዳንድ የበታችነት ሕመም ስሜት የሚያሰቃየው ፖለቲካኛ ነኝ ባይ ተማረም አልተማረም ምንም ዓይነት የባህርይ ለውጥ ሊያሳይ አይችልም። የዶክተርነት (PhD) ወይም የፕሮፌሰርነት የተከበረ ማዕረግ ተሸክመው ያላቸውን ደረጃ፤ ኅሊናቸው የማይቀበልላቸውና ሁልጊዜም የበታች መሆናቸውን አምነው እየተብሰለሰሉ፤ ራሳቸውን ጎድተው የሌላውንም ወገኖቻቸውንና ጓደኞቻቸውን ሕይወት የሚያጨልሙ ጥቂቶች እንዳልሆኑ ለማረጋገጥ ብዙ ማስረጃ አይጠይቅም።

የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አህመድ ሕዝብን በሚያስደምም ሁኔታ ባልታሰበ ወቅት ለሥልጣን በቅተው ያደረጉትን ንግግር ስናዳምጥ ፈጣሪ አምላክ የኢትዮጵያውያንን ችግርና ዕንባ ተመልክቶ እኒህን ሰው እንደሰጠን አድርገን በደስታ ተቀብለናቸው ነበር። ነገር ግን ምንም እንኳ ሥልጣኑን ቢጨብጡም ኢትዮጵያውያንን ማስተዳደር የሚያስችል ጥበብና ብቃት ያላቸው አልመስላቸው ስላለ፤ እንደ ቀድሞዎቹ አለቆቻቸው የሕወሃትን ያረጀና ያፈጀ የ17ኛው ምዕተ ዓመት ፍልስፍና ሙጥኝ ብለው እንደ እስስት የተለያየ መልክ ተላብሰው እየተሠቃዩ መሆናቸውን ሕዝብ የተረዳላቸው አይመስልም። በገሐድ ‘የማሻግራችሁ እኔ ነኝ’ በማለት፤በችግኝ ተከላውና በመዝናኛ ፓርክ ግንባታ፤ እንዲሁም የተረሳውን ቤተ መንግሥት ሕዝብ እንዲጎበኘው አድርጌአለሁ በማለት የገጽታ ግንባታውን (cosmotic make up) ትኩረት ሰጥተው እየሠሩበት ናቸው።

ይህንን እንደ ማደንዘዣ ሲጠቀሙበት፤ በሌላው እውነተኛ ፊታቸው ደግሞ፤ በፈጠራ ትርክት የተገነባውን የአኖሌን ሐውልት እንደ አርማ እየተንከባከቡ፤ በውሾቻቸው አማካይነት በጋምቤላ፤ በቤንሻንጉል፤በሰሜን ሸዋ እና በአዲስ አበባ የዲሞግራፊ ለውጥ (Social Engineering)፤ዕጣ የወጣባቸውን የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና የቦታ ዘረፋ ፤ሕዝብን ከሕዝብ የሚለያይ፤ ዘር ተኮር ማፈናቀልና የጎሣ ፖለቲካ እያራመዱ መናቸውን ሕዝብ የማያውቅ መስሏቸዋል። ይህንኑም ዕቅዳቸውን የሚያከናውኑላቸው የአንድ ጎሣ ሰዎችን በባትሪ እየፈለጉ ቁልፍ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን በሞኖፖል ጠቅልለው ይዘዋል። በዚህ አካሄዳቸው ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ በማንም ተገፍተው ሳይሆን በራሳቸው ቅሌት፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ እራሳቸውን አውጥተዋል።

ይህም የሚያሳየን ጠ/ሚንስትሩ በምርጫ የማያምኑና ሕዝብን በኃይል እረግጠውና አፍነው፤ በአምባ ገነንነት  ለመግዛት ዝግጅታቸውን እያደረጉ መሆኑን በየሳምንቱ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን የጦር ኃይሎች እንቅስቃሴ እያሳዩ በማስፈራራት ላይ መሆናቸውን ማስታወሱ ተገቢ ነው። በመሠረቱ የጦር ኃይሎች ሥልጠና እና ልምምድ ለጠላት ግልጽ እንዳይሆን በከፍተኛ ምስጢር መጠበቅ ሲገባው በይፋ በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ መሆኑ ሕዝብን ለማሸበርና ለማስፈራራት ታቅዶ እየተካሄደ መሆኑን ሀሁ የቆጠረ ሁሉ የሚያውቀው ነው። በዚህ ርዕስ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዓባላት ዘርዘር ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡበት እንጠይቃለን።

ቀድሞ በኢንዱስትሪ አብዮት ዋዜማ ወቅት፤ የአውሮፓ ነገሥታት፤ የሠራተኛ ሰው ኃይል፤ ለፋብሪካ የሚሆን ጥሬ ዕቃ፤ እና ገበያ፤ ለማግኜት እንዲረዳቸው ግዛታቸውን ለማስፋፋት ሲሉ እ.ኤ.አ. ከ1618-1648 ዓ/ም ድረስ ሠላሳ ዓመታት የዘለቀ ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ገብተው እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል። እንዲህ ያለውን ዘግናኝ የሰው ፍጅት በወቅቱ በነበረው የባዮሎጂካል መሣሪያም ሲጠቀሙ ስለነበር ከሕፃን እስከ አዋቂ በርካታ ሰዎች አልቀዋል። በመጨረሻም ይህንኑ ተከትሎ በተከሰተው ከፍተኛ የሆነ ረሃብ፤ የሰው ልጅ እርሙን እስከ መብላት (cannibalism) ደርሷል።

ያኔ ነው የአውሮፓ ነገሥታት ወደ ኅሊናቸው በመመለስ ጦርነቱን የሚያካሂዱት ለምን እንደሆነ መመርመር የጀመሩት። በኋላም የግዛት ሉዓላዊነትን የሚያስክብር ስምምንት ጀርመን በምትገኘዋ በዊስትፋሊያ ከተማ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 1648 ዓ/ም የግዛት ማስፋፋቱን ጦርነት ለማቆም የተፈራረሙት። እንግዲህ በጦርነት አሸናፊም ሆነ ተሸናፊም እንደሌለ መገንዘብ ይቻላል። ልዩነቱ አንዱ ወገን ብዙ ጉዳት ሲደርስበት ሌላኛው ደግሞ ያነሰ ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል ግን የሚያጠያይቅ አይሆንም።

ይህንን ትንሽ ማብራሪያ ለግንዛቤ ካቀረብን በኋላ ወደ እኛው አገር ፖለቲካ እንመለስ። የኦሮሞ ማኅበረሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አሁኗ ኢትዮጵያ የገባው በ1521 ዓ/ም ነበር። በወቅቱ በነበሩት የአፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት የቱርክ ኦቶማን ኢትዮጵያዊውን ግራኝ አህመድን በባንዳነት በመጠቀም፤ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ የክርስትና ሃይማኖት ለማፍረስና አገሪቱን የእስላም አገር ለማድረግ ከፍተኛ ጦርነት የከፈተበት ወቅት ነበር።

በዚህ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የገቡት ሁለት ወንድማማች ኦሮሞዎች ነበሩ። እነርሱም ቦረና እና ባረንቱ የሚባሉ ነበሩ። ከታሪክ እንደምንረዳው በኦሮሞ ማኅበረሰብ ባህል የወላጆቹን ሀብትና ንብረት የሚወርሰው የመጀመሪያ (የበኩር) ልጅ ብቻ ሲሆን፤ ሌሎች ግን እራሳቸው ጥረው ግረው ሕይወታቸውን መምራት ይጠበቅባቸዋል። ቦረና ታላቁ ሲሆን ባረንቱ ደግም ታናሽ ነበር። ባረንቱ ታላቅ ወንድሙን ቦረናን ከአለው ሀብት እንዲያካፍለው ይጠይቀዋል። ታላቅየው ቦረናም ባህሉን መሠረት በማድረግ ሊሰጠው አልፈለገም። በዚህ ጊዜ የተናደደው ባረንቱ የወንድሙን ማለትም የቦረናን ልጅ በመግደል ሸሽቶ በአሁኗ ኬንያ አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትምህርት ሰጭ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ * - ከእሸቴ ውለታው

ቦረናም በልጁ መሞት በመናደድ ለበቀል የባረንቱን ኮቴ በመከተል ወደ ኢትዮጵያ ይገባል። በአጋጣሚ ባረንቱ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ በመሄድ በባሌ ክ/ሀገር መዳ ወላቡ በተባለው አካባቢ ይሠፍራል። ቦረና ደግሞ ከብቶቹን እየነዳና ግጦሽ እየፈለገ ይጓዝ ስለነበር ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በመሄድ ወንድሙን ሳያገኘው ይቀራል። ከዚህም የተነሳ ወደ ምሥራቅ የዘመተው ባረንቱ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ሲሆን ወደ ሰሜን ምዕራብ የዘመተው ቦረና ደግሞ የክርስትናን ሃይማኖት ይቀበላል።

እንግዲህ ከላይ እንደተጠቀሰው በኦሮሞ ባህል የወላጆቹን ንብረት የሚወርሰው ታላቁ ልጅ ነው ብለናል። ሌሎቹ ልጆች ከወላጆቻቸው ሀብት የመውረስም ሆነ የመካፈል ዕድል ስለሌላቸው ኑሮአቸውን ለማስቀጠል የሚያስችል የገዳ ሥርዓትን ፈጥረዋል። የገዳ ሥርዓት በአጭሩ የዘረፋ ሥርዓት ነው። ሥርዓቱ ከወላጆቻቸው ሀብትና ንብረት መውረስ የማይችሉትን ለማቋቋም የታቀደ ሥርዓት ነው። አደረጃጀቱም እንደሚከተለው ነው። በገዳ ሥርዓት የሰዎችን ዕድገት በስምንት ዋና ዋና ደረጃ ይከፍላል። የእያንዳንዱ ደረጃ የስምንት ዓመት ጊዜ አለው።

1ኛ. ዱባሌ ከ1-8 ዕድሜ ልጆች በቤት አካባቢ የሚውሉ

2ኛ. ጋሜ ዲዲቆ 9-16 ዕድሜ ወጣት ከብት ጠባቂዎች

3ኛ. ጋሜ ጉርጉዳ 17-24 ዕድሜ ዘራፊ ቡድን

4ኛ.  ኩሳ 25-32 ዕድሜ ስካውቶች (ሰላዮች)

5ኛ. ራባ ዶሪ 33-40 ዕድሜ አባ ዱላ የዘረፋ ጦር መሪ

6ኛ. አባ ገዳ  41-48 ዕድሜ የመሪነት ተግባር የሚጫወተው ነው።

7ኛ. ዩባ 49-80 ዕድሜ አማካሪዎች

 

8ኛ.ገደ ሞጂ ሴራ ከ81 ዕድሜ በላይ አባ ሙዳ (ጡረተኞች)

ከላይ እንደ ተገለጸው አባ ገዳ የተባለው መሪ ሲሆን፤ በተጨማሪም እሱን የሚያገለግሉ የተለያዩ ማዕረጎች አሉ። እነርሱም አባ ዱላ የዘረፋው መሪ ሲሆን፤ አባ ቦኩ ደግሞ በአባ ገዳ ስብሰባ ጊዜ የተወሰነውን ውሳኔ የሚናገር የገዳው ቃል አቀባይ ነው። አባ ሴራ የሚባሉት በዕድሜያቸው የገፉና የሸመገሉ ሰዎች ሲሆኑ የአሳለፉትን የዘረፋ ሕይወትና ተሞክሮ፤ ለወጣቱ ትውልድ የሚያስተምሩና የሚመክሩ ናቸው። እነዚህ ወጣቶች በተለይ ከ17 ዓመት በላይ የሆኑት የጦር ልምምድና ሮጦ የማምለጥ ስልጠናዎችን እያደረጉ ይቆያሉ። ከኩሳ እና ራባ ዶሪዎች  መካከል ለእስካውትነት (ሰላይነት) ይመረጣሉ። ስካውቶች ቀደም ሲል በዘረፋ ወቅት የተካፈሉና በቂ ተሞክሮ ያላቸው ሲሆኑ በአካባቢው በነበሩ የአማራና የሐዲያ እንዲሁም የሲዳማ ብሔረሰብ በሚኖሩባቸው ቀየዎች በመሄድ የእግዜር እንግዳ መስለው ይጠጉና የሰዎችን ብዛት፤ ያላቸውን የጦር መሣሪያ፤ እንዲሁም የሀብታቸውን መጠን በማጥናት ለላካቸው ለአባ ዱላ ሪፖርት ያቀርባሉ።

አባ ዱላም በቀረበለት ሪፖርት ተመርኩዞ፤ ማጥቃት የሚያስችል ኃይል በማሰለፍ በድንገት በሌሊት ሄዶ ሰዎችን በማፈናቀልና ወንዶችን በመስለብና በመግደል፤ ሴቶችን በመማረክ፤ ከብቶችንና ሀብታቸውን በመዝረፍ ወደ በረሃማው ክፍል ይሸሻል። የገዳ ሥርዓት እንዲህ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ሀብትና ንብረት ለመውረስ ያልቻሉትን ኦሮሞዎች ለዝርፊያ እንዲደራጁና እራሳቸውን እንዲችሉ የሚያደርግ የዘረፋ ሥርዓት እንደሆነ መታወቅ አለበት። እንዲህ ያለውን አስነዋሪና ኋላቀር ሥርዓት እንደ ትልቅ ነገርና እንደ ጀብድ ቆጥሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ አሁን ለመጫን የሚደረገው ሙከራ የሕልም እንጀራ ከመሆን የዘለለ አይሆንም።

ነገር ግን ይህንኑ መሰል ወረራና ዘረፋ በዚህም ዘመን በግልጽና በስውር በአቶ ለማ መገርሳ፤ በወ/ሮ ጠይባ ሐሰን፤ በኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ እና በአቶ ሽመልስ አብዲሳ አማካይነት በተባበረ መልኩ፤ የሌላ ጎሳ ናቸው የሚሏቸውን ንጹሐንን ከማፈናቀል ጀምሮ፤ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከልጆቻቸው አፍ እየነጠቁ ከአሥር ዓመታት በላይ እየቆጠቡ የተገነቡትን የኮንዶሚኒየም ቤቶች በሕገወጥ መንገድ በመዝረፍና የአዲስ አበባን ከፍት ቦታዎች እየሸነሸኑ ሲያድሉና ሲወሩ መቆየታቸው የአድባባይ ምስጢር ሆኗል።

በዚያ አስከፊ ሥርዓት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በአብዛኛው የአማራው ሕዝብ ሲሆን በተከታይም የሐዲያው ማኅበረሰብ ይገኝበታል። በተለይ የአማራው ሕዝብ አሰፋፈር እጅግ በጣም ተራርቆ ስለነበር ለመተጋገዝና ለመረዳዳት አልቻለም። የኦሮሞ ዘራፊዎች በቁጥር እጅግ በጣም በዝተው ስለሚወሩ በዚያች አካባቢ ከሚኖሩ ከአንድ ቤተሰብ የአማራ ልጆች ቁጥር ጋር ሲነፃጸር ሁሌም አጥቂዎች በመሆን አካባቢውን እያስለቀቁ ተቆጣጥረውታል። በተጨማሪም በኦቶማን ቱርክ የታገዘው የግራኝ አሕመድ ወረራ ለኦሮሞ ዘራፊዎች ታላቅ ድጋፍ ሆኖላቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሁለቱ ቅንብር የትግል ጉዞአቸዉ - ሙላት በላይ

ኦሮሞዎች በዚያን ጊዜ እንኳን ፈረስ መጋለብ ይቅርና ፈረስ አይተው አያውቁም ለማለት ያስችል ነበር። ነገር ግን አማራዎችና ሐዲያዎች ግን እጅግ የተዋጣለቸው ፈረስ ጋላቢዎች ስለነበሩ በኦሮሞ ወራሪዎች ላይ በተደጋጋሚ እራሳቸውን የመከላከልና ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውባቸው እንደነበረ ይታወቃል። በኋላም ቀስ በቀስ ኦሮሞዎች ፈረሶችን በመውሰድና የመጋለብ ልምድ እንዳዳበሩ ታሪክ ያስረዳናል።

ይሁን እንጂ በአፄ ገላውዲዎስ፤ በአፄ ሱስንዮስና፤ በኋላም በአፄ ፋሲል ጊዜ ኦሮሞዎቹ ልብስ የመልበስና በአንድ ቦታም ረግተው እርሻ የማረስ፤ ባህል እንዳካበቱ ሲታወቅ፤ ከዚያ በፊት ግን የሚመገቡት የበቆሎ ግንፎና የእንስሳትን አንገት የደም ሥር በጦር በመብሳት የሚፈስውን ደም ከቅል በተሠራ መጠጫ በመቅዳት ያንን በወተት በመቀላቀል ይመገቡ እንደ ነበር ተዘግቧል።

እንግዲህ እንዲህ ያለውን አሳፋሪ ታሪክ እንደ ጠንካራ ነገር ቆጥሮ ለሕዝብ ለማስረጽ የሚደረገው ሙከራ ‘ጅብ ከማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ’ ከሚለው የአባቶች ፈሊጣዊ አነጋገር ተለይቶ የሚታይ አይሆንም። የኦሮሞ ወጣቶች ለዝርፊያ ከመሠማራታቸው በፊት የዕድሜ ባለፀጋ ከሆኑት ከአባ ሙዳ ዘንድ በመቅረብ ቅቤ በመቀባት ይመረቃሉ። የሚለብሱት ልብስ ከከብት ቆዳ የተሠራ ሲሆን ሀፍረታቸውን ከመሸፈን ያለፈ አልነበረም። ወደ ሃይማኖቱ ስንመለከት ግን ታላላቅ ዛፎችን አድባር እያሉ የሚያመልኩና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቅቤ የሚቀቡ ዶሮ አርደው በዛፉ ዙሪያ የሚያንጠለጥሉ ባዕድ አምላኪዎች እንደነበሩ ይታወቃል።

እንደ እውነቱ ከሆነ ታሪክን ለመማሪያ ካልሆነ በስተቀር የቀደሙ አባቶች ሠርተውት ባለፉት ጉዳይ መከራከሩ አሁን ላለንበት ሁኔታና ለቀጣዩ ትውልድ ጠቃሚ ስለማይሆን የምንጠቅሰው ግን ተመሳሳይ ስሕተት እንዳንሠራ ለመጠቆም መሆኑን ማጤን ያስፈልጋል። ይህንኑም መሠረት በማድረግ አንድ መነሳት የሚገባው ዓቢይ ጉዳይ አለ። ይኸውም በሐረር አካባቢ ‘ሙላቱ ገዳ’ በመባል የሚታወቅ የገዳ ሥርዓት ነበር። ታዲያ በዚያን ወቅት ከፍተኛ ረሃብ ተከስቶ ነበር። ከዚህም የተነሣ ሙላቱ ገዳ የሐረሪ ሰዎችን እንደ ዱር አራዊት እያደነ እንደ ወሰዳቸውና እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ (cannibalism) እንደ ተጠቀመባቸው ታሪኩ ያስረዳል። እንግዲህ የገዳ ሥርዓት ምን ያህል ጨካኝ አረመኔና የዝርፊያ ሥርዓት ብቻም እንዳልሆነ ለመገንዘብ አይቸግርም።

እንግዲህ እንዲህ ያለውን የወረደና የዘቀጠ ታሪክ ተሸክሞ በራሥ መተማመን የሚባል ነገር በዚህ ማኅበረሰብ ልሂቃን ውስጥ ይመጣል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። የፎረንሲክ ሳይንስ ጠበብት እንደሚገልጹት የወንጀለኛ ልጅ የሆነ ሰው በዘር እንደሚተላለፍ ይጠቁማሉ። አሁንም የምናየው ከዚህ የተለየ አይደለም። ያለፉበትንና ያልደከሙበትን ሀብት የእኔ ነው በማለት ሲወስዱ ኅሊናቸው የማይሰቀጥጣቸው፤ ከዚህ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠሩ ተገቢ ይሆናል። የሥነ አእምሮ ጠበብት እንደሚሉትም የእጅ ዐመል (Kleptomania) ያለበት ሰው ተማረም አልተማረ መስረቁን አያቆምም። ከዘረፋው በተጨማሪ በዘር የሚተላለፍ የበታችነት ስሜት እግዚአብሔር ይማርህ የማይሉት ክፉ ደዌ መሆኑን መረዳት አዋቂነት ነው። የአለፈውንና የማይጠቅመውን ሥርዓት እንደ በጎ ነገር አድርጎ ወይንም ስኳር እንደተቀባ መርዝ እየኳኳሉ ለሕዝብ ለማቅረብ፤ በትምህርት ካሪኩለም ውስጥም ለማካተት መጣር፤ እጅግ በጣም የሚያስተዛዝብ መሆኑን መገንዘብ ሞኝነት አይሆንም።

መነገር ካለበት እርቃን የነበሩትን ልብስ እንዲለብሱ ያደረጋቸውን፤ የተሰረቀ የከብት ጭራ ተከትሎ በረሃ ለበረሃ ከመዞር ቤት ሰርተው በአንድ ቦታ እንዲኖሩ ምሳሌ የሆናቸውን፤ እርሻ በማረስ የተለያዩ የእህል ዘሮችን የማምረት ዘዴ ያስተማራቸውን፤ ከበቆሎ ገንፎ ይልቅ እንጀራ የመጋገር፤ ቦርዴ፤ሻሜታ፤ ጠላ የመጥመቅና ጠጅ የመጣል ጥበብ፤ ከእንሰት ቆጮና ቡላ ማዝጋጀት፤ ያሳያቸውን ማኅበረሰብ በማድነቅ ውለታውን ቀጣዩ ትውልድ እንዲያውቅ ቢያደርጉ የበለጠ የኅሊና እርካታን ያገኙ ነበር። እንዲህ የመሰለውን በጎ ተግባር በማስተማር ውለታው እንዲታወስና የኅብረትሰቡ ትስስር የበለጠ እንዲዳብር ማድረግ ሲገባ፤ የበታችነት ስሜት የሚንጣቸው በመሆኑ ግን፤ ያንን ትተው እኛም ዕኩል ነን ለማለት ሲባል ሰማይ መቧጠጥ ለመላላጥ ካልሆነ በስተቀር ውጤቱ ከቶ አያምርም።

በአጠቃላይ ግን በሠፊው የኦሮሞ ሕዝብ ውስጥ እንዲህ ያለው ስሜት እንደሌለ ብዙ ማረጋገጫዎች አሉ። ይኸውም ለብዙ ዓመታት የኖረው ከሌላው ማኅበረሰብ ጋር በመጋባትና በማዋለድ ሲሆን በማንነቱና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ዜጋ ሆኖ ነው።  ነገር ግን ሰላሙን እያመሱት ያሉት ጥቂት የኦሮሞ ልሂቃን ሲሆኑ፤ የበታችነታቸው ዋነኛ ምልክት ወያኔ የነደፈላቸውን ‘የመቶ ዓመት የቤት ሥራ’ በመቀበል የራሳቸውን ቋንቋ (የግዕዝ ፊደላትን) በመናቅ የላቲን ፊደል አምላኪ መሆናቸው ነው። በእነርሱ ቤት በላቲን ፊደል መጠቀማቸው እራሳቸውን ከሌሎች ዕኩል ያደረጉና ፈረንጅ የሆኑ መስሏቸዋል። ይህም የበታችነታቸው ዓይነተኛ መገለጫ መሆኑን የኦሮሞ ወጣትና ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያወቀው ይገባል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመጨረሻው መጀመሪያ - ማስተዋል በለጠ (አዲስ አበባ)

አንድ ሰው በርካታ ቋንቋ በማወቁ ሕይወቱን በመለወጥ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ይረዳዋል እንጂ፤ ተጎጂ እንደማያደርገው እየታወቀ፤የኦሮሞ ወጣት የአማርኛ ቋንቋ እንዳይማር የሚከለክሉት ከሆነ ምክንያታቸው አንድ እና አንድ ብቻ ነው። ይኸውም ቀጣዩ የኦሮሞ ትውልድ ወደ ማዕከላዊ መንግሥት ሥልጣን እንዳይደርስና በኦሮሞ ክልል ብቻ እንደ ከብት በበረት ተከልሎ እንዲቀር በማሰብ ነው። ለዚህም አሁን አማርኛ ቋንቋ የሚናገሩት የኦሮሞ ልሂቃን ልጆች፤ እንደ ልዑላዊያን ቤተሰብ በመሆን ቀሪውን የኦሮሞ ሕዝብ ደግሞ እንደ ባርያ የእነርሱ አገልጋይ እንዲሆኑ በማቀድ መሆኑን ማጤን ይገባል። በዚህ ረገድ የኦሮሞ ወላጆች የልጆቻቸው የወደፊት ሕይወት የተሻለ እንዲሆን፤ ከአሁኑ ጀምሮ የአገራቸውን የመግባቢያ ቋንቋ የሆነውን ‘አማርኛን’ እንዲያውቁ የማስተማር ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን።

የሕዝብ ሥልጣን አደራ ነው፤ አንድ ቀን በአልታሰበ ሁኔታ ከእጅ ሊያመልጥ ይችላል። በተጨማሪ የጤናም ሁኔታ አለ፤ ኅሊና የማይፈቅደውን እኩይ ተግባር በመሥራት የሰላም ዕንቅልፍ ተኝቶ ማደር ዘበት ነው። ይህም ቀስ በቀስ የሰውነት ጤናን ሁኔታ እየተፈታተነ በማወክ ለከፋ ደዌ ሊዳርግ ይችላል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የሰው ልጅ ሕይወት እንደ ሸክላ ዕቃ ነው። በምን ሁኔታና በምን ምክንያት እንደምንሞት አናውቀውም። ሟቹ ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ ረጅም ዕድሜ የሚቆዩ መስሏቸው በውስጣቸው የነበረውን የበታችነት ስሜት ለማካካስ ሕዝብን ከሕዝብ እርስ በእርሱ የሚያናቁር ፖሊሲ ቀርጸው፤ በችጋር አለንጋ እየገረፉ ሲያሠቃዩት ሳለ ድንገት ባልጠበቁትና በአላሰቡት ጊዜ ይህችን ዓለም በሞት ተሰናብተዋል።

አሁንም በሥልጣን ላይ ያሉት ጠ/ሚንስትር ዶ/ር ዓቢይ አህመድ ከዚህ ትምህርት በመውሰድ የሚናገሩትን እና የሚሠሩትን አራቦና ቆቦ በማድረግ ሕዝብን ለማታለል ከሚሞክሩ ይልቅ የአለፈውን እንደአለፈ ቆጥረው፤ አገሪቱ አሁን ከአለችበት ጀምሮ ዕድገቷን ለማፋጠንና የሕዝቦቿን የኑሮ ሁኔታ በመለወጡ ላይ ቢያተኩሩ የተሻለ በሆነ ነበር። ነገር ግን ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንዲሉ ኢንጂነር ታከለ ኡማን አንስተው ወ/ሮ አዳነች አበቤን መተካቱ እውነት አገር ለማሳደግ ታስቦና ታቅዶ የተሠራ ነውን? ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን።

ጊዜያዊ ሥልጣንን መከታ በማድረግ ለጥቂት ጊዜ ሕዝብን ማታለል ይቻል ይሆናል። ነገር ግን ፈጣሪ አምላክን መሸንገል በእውኑ ይቻላልን? በተለይ አሁን በአለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰውን ከደረጃው ዝቅ አድርጎ የሚያሳየው በዘር፤ በጎሣ፤ በጎጥ፤ በሃይማኖትና በቋንቋ ልዩነት ሲፈጥር ነው። ዓለማችን ከቴክኖሎጂ ዕድገትና ምጥቀት የተነሳ እያነሰች በሄደችበት ዘመን የጋራ ጠላት በሆኑት በልዩ ልዩ በሽታዎች ላይ በኅብረት በመነሳት ለመመከት ጥረት እየተደረገ መሆኑን እንገነዘባለን። በተጨማሪም እንኳን ኢትዮጵያውያን ይቅርና ፍቅር እስካለ ድረስ ሰዎች የሌላ አገር ሰዎች አያገቡ ተዋልደውና ተዛምደው ቋንቋውንም እየተናገሩ፤ በሰላም እየኖሩ መሆኑ እየታወቀ፤ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ ሕወሃት ወያኔ ይጠቀምበት የነበረውን የቅኝ ገዥዎችን የከፋፍለህ፤ አዳክመህ ግዛ ፖሊሲ ሳያስተካክሉ ሙጥኝ ብለው በመያዝ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስተዳድራለሁ ብለው መሞከራቸው፤ እራስን ከማታለል የዘለለ ሊሆን አይችልም።

‘ከመልካም ሽቱ መልካም ስም ይሸታል!’ እንዲሉ ዶ/ር ዓቢይ ሳይመሽ ወደ ቀልባቸው ተመልሰው ለሕዝብ የሚጠቅም ሥራ ቢሠሩ ታሪክ በጥሩ ሲያስታውሳቸው ይኖራል። ነገር ግን ከንቱ ውዳሴና ኮስሞቲክ ገጽታ ግንባታ ለዕድሜ ልክ ጸጸት ይዳርጋል (ያውም ዕድሜ ካለ ነው)። ምክንያቱም እነ ዶ/ር አምባቸው መኮንን፤ እነ ጄኔራል ሠዓረ መኰንን እና ጄኔራል አሳምነው ጽጌን ማስታወሱ አይከፋም። ሞት በሁሉም ደጅ ቆሞ ያደባልና! ሌላው ቀርቶ እነ በረከት ስምዖንንም ማሰቡ ይህች ዓለም ከንቱ መሆኗን ያስታውሳልና፤ ለማንኛውም ሁሉንም ጉዳይ ለሠፊው ሕዝብና ለቀጣዩ ትውልድ ጥቅም እየታሰበና እየታቀደ ቢሠራ መልካም ነው እላለሁ።

-//-

 

8 Comments

 1. በጣም እግዜር ይስጥልን የተሟላና አስተማሪ ጽሁፍ ነው ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ሰጥቷል ገ/ክርስቶስ አባይ ወደፊትም ዝም አይበሉ ነገር ተበላሽቷል ወደፊትም እንዲሁ ምልከታዎን ይስጡን። ጽሁፎ ማህደራችን ውስጥ ገብቷል።

 2. ወንድሜ ገ/ክርሰቶስ
  በፁሁፍህ ይዘት ከሞላ ጎደል እሰማማለሁ::ሆኖም ግን
  “…በዚያ አስከፊ ሥርዓት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በአብዛኛው የአማራው ሕዝብ ሲሆን በተከታይም የሐዲያው ማኅበረሰብ ይገኝበታል”

  ከላይ በተጠቀሠው ጥቅስ አልስማማም:: ምክንያቱም በኦሮሞ መስፋፋት ጊዜ ያልተጎዳና ብልቱ ያልተሰለበ ጥቂት ነውና::

  ለምሳሌ ጉራጌን : ከምባታና ሌሎች ደቡቦችን ሽዋ ውስጥ በመቁረጥ ወደደቡብ በመግፋት ህዝቡ ዛሬ በመጨናነቅ የስፈረበት ሁኔታ ተፈጥሯል:: ለምስክርነት oromize የተደረጉ በጉራጊኛ የሚጨፍሩ ግን ኦርምኛ የሚገሩ vise versa ህዝቦች ይገሉ:: ብዙ ያልጠና የቃል ታሪክ በነዋሪ ው መሃል ይገኛል (oral history) ከተፃፈው ውጪ::

  ጉዳዩ ያለፈው ጉዳይ ላይ ለመቸከል ሳይሆን የኦሮሞ “እብድ” መሪዎች ትርክታቸውን በማስቀየር ወደ መሃል አስመጥቶ ይህችን ትልቅ አገር ከወያኔ እብደትና ከዘር አባዜ አውጥቶ ትክክለኛ የስልጣኔና የእድገት መንገድ ማስያዙ ላይ ነው:: የእገሌ ባህል ይበልጣል የሚለውን ረስቶ ጎጂውን ባህል አስወግዶ : የተቀሩትን ለዩንቨርስቲ ጥናትና ለክልል ነዋሪ ፍላጉት : ለቱሪስትና business venture (commoditization) በመስጠት አገሪቱን በገዳ በምናምን ወደዲሞክራሲ እመራለሁ ከማለት አለም ያለፈበትን የተፈተነ ሳይንሳዊ መንገድ መከተል ነው:: የትምህርት ቤቶችን ከማዘመን የትምህርት ይዘተን ከማሳደግ ይልቅ ገዳ አዲስ አበባ አስተምራለሁ ማለት የተረኝነ አሰትእሳስብ ነው::
  የኢትዮዽያ ህዝብ የሚፈልገው:
  ሠላም
  አንድነት
  ዘረኝነት መጥፋት
  መከባበር
  እድገትና ብልጽግና
  የእውነተኛ ዲሞክራሲ
  ጥሩ ትምህርትና ሥራ ወዘተ ናቸው
  ይህ የስው ዘር ሁሉ የሚመኘው ነው::
  A noble leader should be noble enough to strive for these

 3. ይህ ሜድድያ አድሎአዊነት ይታይበታል የሚል ግምት አለኝ

  የለፋሁባቸው comments ብዙዎቹ ኣጥቻሉሁ::

  የሚያሳዝነው ሜዲያም በዘርና በሀይማኖት መሽንሽኑ ነው

 4. ስለ ገዳ ምንም ሳታዉቅ በኩንታል ወሬ መልቀቅህ ቀንደኛ የኦሮሞ ጠላት መሆንህን ከማሳየት ወጪ ምንም ለውጥ አያመጣም ።

  • Anonmous
   ልክ ነህ ያወቅነዉ ትንሹን ነዉ አሁን ግን መቆፈር ይዘናል ይኸኛዉ ካበሳጨህ የሚመጣዉ ምን እንደሚያደርግህ መገመት አይኸኛዉ ካበሳጨህ የሚመጣዉ ምን እንደሚያደርግህ መገመት አይከብድም አወናብደህ በተመድ ያስመዘገብከዉንም እስከ ወንጀሉ ስንነግራቸዉ አፍረዉ ቀደዉ ይጥሉልሀል። ለማንኛዉም ማሳሰቢያህን ተቀብለነዋል ስለ ገዳ በስፋት እናጠናለን።

 5. ቋንቋን በተመለክተ ኢትዮጵያን በዓለም ላይ ትልቅ ስፍራ ያሰጣት የረሳችን በራሳችን በቀል ቁንቁ ከንጽሁፉ አሳምሮ ለኛ ብቻ የምንኮራበትን ቁንቋ ፈርንጅ ለመማር ሲሻማ የአብይ ኦነግ ቄሮ መንግሥት ለማጥፋት ለምን ተራራ እንደሚቧጥጡ አይገባኝም፡፡ የአማርኛ ስነጽሁፍ በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኮራ የሚያደርገን ነው፡፡የኢትዮጵያን ህልውና የአእቢይ አስተዳደር ሲፍቅ ነው የሚውልው፡፡ አገር ትፋረዳቸው! ሊላ ምን ይባላል!

 6. ቋንቋን በተመለክተ ኢትዮጵያን በዓለም ላይ ትልቅ ስፍራ ያሰጣት የረሳችን በራሳችን በቀል ቁንቁ ከንጽሁፉ አሳምሮ ለኛ ብቻ የምንኮራበትን ቁንቋ ፈርንጅ ለመማር ሲሻማ የአብይ ኦነግ ቄሮ መንግሥት ለማጥፋት ለምን ተራራ እንደሚቧጥጡ አይገባኝም፡፡ የአማርኛ ስነጽሁፍ በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኮራ የሚያደርገን ነው፡፡የኢትዮጵያን ህልውና የአእቢይ አስተዳደር ሲፍቅ ነው የሚውልው፡፡ አገር ትፋረዳቸው! ሊላ ምን ይባላል!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.