‹‹በአገልግሎት ወቅት ለተፈጠሩ ቅሬታዎች ይቅርታ እንጠይቃለን››… ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ

Abebe 1በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ያሰናዳው የጳጉሜን አንድ ‹‹ የይቅርታ ቀን›› እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዚህ ወቅት መልእክታቸውን ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ የጳጉሜን ወር በትርጓሜው የምህረት ወር ተብሎ እንደሚታወቅ አስታውሰው ዛሬ ላይ ስለ ቅርታና ምህረት ማውራት ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡
ይቅርታ የትላንትን ስህተት፤ በበደልና ቁርሾ በመተው ዛሬን በጥበብ ለመኖር የሚያስችለን መንገድ አንደመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎት ወቅት ለተፈጠሩ ቅሬታዎች የከተማዋን ነዋሪዎች ይቅርታ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል፡፡
‹‹አዲስ አበባን እንደስሟ ውብና ማራኪ ለማድረግና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ የነዋሪዎቿን ድጋፍ እንፈልጋለን፤ ያለ ከተማዋ ነዋሪ አጋርነት ምንም መስራት አይቻልም›› በማለት ነው ያስረዱት፡፡
የታሪክ ምሁራን የቆየውን የኢትዮጵያውያንን የይቅርታ ባህል መልሰው እንዲያስተምሩ፣ ፖሊተከኞችም ከቂምና ጥላቻ ይልቅ ይቅርታን፤ አብሮነትንና አንድነትን እንዲሰብኩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ፣ የሀይማኖት መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ወርሀ መስከረምን በአዲስ ተስፋ ለመቀበልና ለፈጣሪ የምናቀርበው ልመና እንዲሰማ በይቅርታ የታደሰ ልብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በበቀል የሰለለን አጥንት የሚያለመልመው ይቅርታ በኢትዮጵያውን ዘንድ በግጥም፤በንግግር፣ በጫወታ በሃል እንደሚነሳና የየእለት ሕይወት አካል መሆኑን ጠቅሰው የይቅርታ አድራጊ ልብ ለሌሎች ይተርፋል ነው ያሉት፡፡
አዲሱን አመት ከበቀልና ጥላቻ ስሜት ርቀን በተስፋ በመቀበል ኮቪድን የምናሸንፍበት እንዲሆን እመኛለው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

3 Comments

 1. .Really ? Of course it is not surprising but it is painfully sad to witness how the people of Ethiopia have become mere subjects of these politicians of EPRDF/Prosperity whose hands are badly stained with the blood of countless innocent citizens .Yes, the blood of innocent compatriots is crying hard and will continue to do so until the day of true and just verdict reveals itself as the result of the realization of true democratic system..
  .Yes, it is deeply disturbing to witness these politicians and cadres keep playing an extremely stupid but brutal political drama on the very lives of more than one hundred million people..
  .This so called day of forgiveness or apology clearly shows that this generation is totally failing to be a generation of freedom and justice, and made the heavy price it paid for so long just kind of useless or garbage stuff.. Deeply sad! Yes, if we have to call a spade a spade , this is what is happening right on the ground and right now. Unfortunately, we are not fortunate enough to have a generation that patriotically say enough is enough !
  .It seems that these notoriously hypocritical and criminal politicians have concluded that this generation is miserably failed to challenge them and bring about a fundamental democratic change and make its is destiny a reality ! painfully sad!
  . I felt a very horrible disgrace when I watch religious leaders being parts and parcels of this very dirty or cynical or extremely feck gathering of ruling circle politicians and their puppets who stick together as long as their wildly self-centered interests go together . It makes our stomachs turn when we hear the very head of the Ethiopian Orthodox Church ( the Patriarch) reading verses from the bible as if this stupid political drama reflects the teachings of Jesus Christ . Alas! What sham and disgrace is this?
  .The people of Ethiopia are really in a very serious trouble of witnessing both politicians and religious leaders have totally lost their basic common senses . Yes, to orchestrate or perform this kind extremely disingenuous and deadly political show is a compete lose common senses !
  .Like it or not, if we do not firmly stand with those truly patriotic compatriots such Eskindir Nega and the like, we are going to count another three decades of brutally instituted ethno-centric political game led by those who replaced their former master (TPLF).
  ..The choice is for this generation whose destiny is being damaged or aborted by those politicians of EPRDF/Prosperity who have the blond of innocent citizens in their hands during their three decades political journey.
  .So, the question should be give me my death or my freedom ! If this generation is seriously concerned about its destiny of a democratic country, this is the way it should be !!!

 2. ሰው በቁሙ ሲታረድ ጆሮ ዳባ ያለ የይቅርታ ግብዣ ምን የሚሉት ነው? በመንግሥት ደርጃ “የይቅርታ” ፕሮግራም እያዘጋጁ ያላግጡብናል፡፡ አይን ቀቅሎ የበላ እንደ ወያኔ አሳፋሪ አስተዳደር ነው፡፡ ሰው እያረዱ፣ ህዝብ እያፈናቀሉ፣ አዲስ አበባን በዘር እየቸበቸቡ መድረክ ይዞ ይቅረታ መቼ ያመጡት ጭዋታ ነው?

  ይሄ አስተዳደር ይቅርታ እያለ ህዝብ ላይ ከሚላላጥ፣ የህዝብን አስተሳሰብ ከሚያቃልል የኢትዮጵያን ህልውና ቁጭ ብሎ በደንቆሮዎች ስብስብ መፋቁን ትቶ፣ የዘር፣ የክልል የጎሳ አስተዳደሩን አጥርቶ አንድ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ቢጅምር ጥሩ ነው፡፡

  አበቤ መቀላመድሽን ትተሽ በአዲስ አበባ ነዋሪነትሽ ሳይሆንን በኦሮሞነትችን ያገኘሽውን ሹመት በተግባር ተግብሪ፡፡ 20 ዓመት መኖርሽ አዲስ አበቤ አያደርግሽም፡፡ የሆነች ቅል እራስ ናት እሷም እንኳን አዲስ አበባን የሚያህል ከተማ የቀበሌ እድር የመምራት ችሎታዋን ያስጠርጥራል፡፡ ያው ዘመነኛና ትረኛ ስልሆነች በማንነቷ እስቲ የሱም ዘመን ፈልቶ እስኪገነፍል ትንቦጫረቅበት፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.