በ24 ሰዓታት 1 ሺህ 206 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ21 ሰዎች ሕይወት አልፏል

corona በ24 ሰዓታት 1 ሺህ 206 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ21 ሰዎች ሕይወት አልፏልአዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2012

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 25 ሺህ 158 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 206 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 58 ሺህ 672 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈ የ21 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 918 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 531 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ 307 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 44 ሺህ 0 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 58 ሺህ 672 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 36 ሺህ 445 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 308 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 21 ሺህ 307 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ918 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል። ኤፍ.ቢ.ሲ

 

1 Comment

  1. The border patrol soldiers of Ethiopia need to be able to do their jobs much better than they are currently forced to do due to failed regional politics, the policies administering the border patrol need to take the covid-19 pandemic into account.

    ” Somaliland’s new Cold War diplomacy ”

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.