ለሰዎች ልባዊ ይቅርታ በማድረግ አዲሱን ዓመት በንጹህ አዕምሮ እንቀበል… የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች

118944199 2739227849653010 1793603645746894952 n
ለሰዎች ከልብ የመነጨ ይቅርታን በማድረግ አዲሱን ዓመት በንጹህ አዕምሮ መቀበል እንደሚገባ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ጥሪ አቀረቡ፡፡
የሃይማኖት መሪዎቹ ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የይቅርታ ቀን ሆኖ እየተከበረ ያለውን የጳጉሜ አንድ እለት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
በዚህ ወቅት የሃይማኖት መሪዎቹ እንዳሉት ትውልድ በይቅርታ የሚያምን ከሆነ የአገር ሰላም ይበዛል ህዝቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ልማትም እየተፋጠነ ይመጣል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ባስተላለፉት መልዕክት “አዲሱን ዓመት ስንቀበል ጥላቻን በፍቅር ቀይርን ሊሆን ይገባል” ብለዋል፡፡
“ከአባቶች የተቀበልናትን አገር ቂም በቀልን ሳናለማምድ ወደ ሚቀጥለው ትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር በበኩላቸው “በሳለፍነው ዓመት የሰራነውን በደል ጥለን ወደ አዲሱ ዓመት ልንሸጋገር ይገባል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የምናደርገው ይቅርታም ከልብ የመነጨ እንጂ ከምላስ መሆን እንደሌለበት ተናግረዋል፡፡
” አዲሱን ዓመት ስንቀበል በተገባደደው የ2012 ዓመት ያስቀየምናቸውን ወገኞቻችንን ይቅርታ በመጠየቅ መሆን ይኖርበታል ” ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ ባስተላለፉት መልዕክትም “ጥላቻን አርግዘን፣ ቂም ይዘን እና ምሬትን ተንከባክበን ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገር አይገባም” ብለዋል፡፡
በመሆኑም የበደልናቸውንም ይሁን የበደሉንን ይቅርታ ልንጠይቅ ይገባል” በማለትም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት ዋቅሹም ኢዶሣ በበኩላቸው ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ይቅርታ አስፈላጊ መሆኑን ነው የተናገሩት።
“ብሩህ የሆነ አዲስ ዓመትን ለመቀበል ወንድሞቻችንን ይቅር ልንል ይገባል” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
“እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ይቅር እንዳለው ሁሉ እኛም እርስ በእርስ ይቅር ልንባብል ይገባል” ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ቃለ-ህይወት ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢያሱ ኤሊያስ ናቸው፡፡
ያለፈውን ምዕራፍ በይቅርታ ቁልፍ ዘግቶ በሰላም ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ፓስተር ታደሠ አዱኛ “ይቅርታ ተቀባይነት ሚያገኘው ከልብ ሲመነጭ በመሆኑ ከልብ ይቅር ልንባባል ይገባል” ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አምስቱ የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥተዋቸው የሚከበሩ ይሆናል፡፡
ኢዜአ
ተጨማሪ ያንብቡ:  በቤሩት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 333 ኢትዮጵያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

2 Comments

  1. These people are definetly do not care for their followers especially the orthodox church leader. The fact that he stands in unison with those that want and are doing their best to destroy his church is proof positive he is an agent of the regime. Shame on him to solicit forgiveness for those who are destroying the church he is supposedly to lead. He should pray for forgiveness for himself for this gross neglect of his duties. May god point him in the right direction. Orthodox christians should ask for his ouster.

  2. እኔ ለ ኢትዮጵያ ህዝብ ፈጣሪን ለ አዲሱ አመት የምለምነው ሰላምን፣ መረጋጋትን፣ ፍቅርን፣ ፍትህን፣ ከ ረሃብ መላቀቅን፣ ይቅር መባባልን እና በ ነጻነት መኖርን እንዲያድላቸው ነው። ይቅርታ ሰላምን ያወርዳል፤ ለ ግለሰቡም መንፈሳዊ እረፍት ይሰጣል፤ ስለዚህ ክቡር የ ሕይወት መተዳደሪያ ነው። ነገር ግን ሃይማኖታችን የገደለን ይቅር የሚል አስተምህሮ አያስተምርም። ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸመ ለ ወንጀሉ መጠየቅ አለበት። ይቅርታ የሚደረገው ዕቅድ አውጥተው በ አረመኔያዊ ተግባር ዘር እና ሃይማኖት ለ ማጥፋት ላልተሳተፉት ብቻ መሆን አለበት።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.