ዝም የተባለው የአብይ አህመድ ጸረ-ኦርቶዶክስ ማኒፌስቶ – ሰርፀ ደስታ

abiy

ወያኔ ጸረ-አማራ መሆኑን በግልጽ በማኒፌስቶው ጽፎ እንደተነሳው እንዲሁ አብይ አህመድ በብልጽግና ማኒፌስቶው በግልጽ ጸረ-ኦርቶዶክስነቱን ጽፎ ተነስቷል፡፡ እርግጥ ነው ሙስሊሚም በመደረቢያነት ኢላማ ከተደረጉት ነው፡፡ አብይ-አህመድ ብልጽግና ላለው የማደንዘዣ ፓርቲ (እኔ ያልኩት ሳይሆን ሽመልስ የነገረን እውነት) ማኒፌስቶው የኦርቶዶክስ እምነት እንቅፋት እንደሚሆንበትና ለዛም ተራማጅ ባለው የፕሮቲስታንት እምነት መተካት እንደሚገባ ነግሮናል፡፡ በሌላ አገር ቢሆን በሕግ የሚያስጠይቀው በሆነ፡፡ የሆነ ሆኖ አንድም ሰው ለምን ይሄን ጻፈ ብሎ አልጠየቀም፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው ሁለት ሰዎች መንገድ ሲሄዱ ይውሉና ሲመሽ ከአንድ ዛፍ ስር ይተኛሉ፡፡ ጀብ ይመጣና የአንዱን እግር መብላት ይጀምራል፡፡ ሌላኛው የሆነ የሚቆረጠም ድምጽ ሲሰማ ምንድነው ብሎ እየተበላ ያለውን ጓደኛ ሲጠይቀው፡፡ እየተበላ ያለው ጓደኛው ዝም ብል ጅብ የእኔን እግር እየበላ ነው ይለዋል፡፡ ያኛው ጓደኛ እንዴ አንተን ሲጨርስ ወደኔ መምጣቱ አደል እንዴ ብሎ ከመኝታው ብድግ ሲል ጅቡ ድንግጦ ይሸሻል፡፡  የአብዛኞቻችን እውነት እየተበላ ያለው መንገደኛ ነው፡፡ የእነ አብይ አህመድ እቅድ ግልጽ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኦርቶዶክስን ማጥፋት በሚለው የቀጠለው የባንዳዎቹ ልጆች እነወያኔ አባቶቻቸው ከጌቶቻቸው ጣሊያኖች የነገሯቸውን ነው አብይ አህመድ የወያኔ ማደጎው እያስቀጠለ ያለው፡፡

አብይ አህመድ ትክክለኛ የአጭበርባሪ ጴንጤ ማሳያ እንደሆነ በብዙ ግዙ ነገሮች እያየን ነው፡፡  ሰውዬው በተቻለው አቅም አውቀት ያላቸውን ሰዎች ከራሱ በማራቅ ያው የተለመደው የጴንጤ ስልትን የሚጠቅም ነው፡፡ እንደነ እስራኤል ዳንሳ እስከሚሆን አንጠብቅም፡፡ የሆነ ሆኖ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል የፕሮቲስታንት እምነት ተከታዮች ከሌላው በተሻለ የእድገትና ብልጽግና አስተዋጽኦ ኖሯቸው አናይም፡፡ አብይ አህመድ ከየትም ያነበበው ከየትም የሰማው እውነት አደለም፡፡ ራሱ ፈጥሮ የተናገረው እንጂ፡፡ እርግጥ ነው የጅው እምነት ተከታዮች በብዙ ቦታዎች ስኬታማ ናቸው፡፡ አብይ አህመድ እዳለው ሳይሆን የአይሁዶች ስኬታማነት የሚመነጨው ከወግ አጥባቂነትና ትውልድን እያሰቡ ከመስራታቸው ነው እንጂ እንደ ፕሮቲስታንቲኒዝም ዘመናዊ ለመሆን በሚል የስብዕናን እሴቶች በመጣል አደለም፡፡ በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ፕሮቲስታንቲኒዝም ከዛም በከፋ የኢትዮጵያ ፕሮቲስታንቲነዝም በጣም አደገኛ በሆነ የማጭበርበርና ከስብዕና ይልቅ ገንዘብን የሚያስቀድም አመለካከትን የሚያራምዱት እንደእነ አብይ አህመድ ያሉት፡፡

እውነታው ይሄ ነው፡፡ በየትኛውም የዓለማችን ክፍሎች አደጉ የተባሉ አገሮች ጥብቅ የሆነ የእምት ሥርዓት ያላቸው ናቸው፡፡ እምነታቸው የቱም ይሁን የቱ፡፡ አብይ አህመድ ካነሳቸው ካቶሊክና ፕሮቲስታንት እንኳን ለማሳያነት ብንመለከት ዛሬ የዓለማችን ትልልቁ ሐብትም ሆነ ወሳኝ የእድገት ትልሞች የሚሰሩት በካቶሊክና የካቶሊክ ሌላው አይነት የኢቫንጀሊካል ተከታዮች ነው፡፡ እንግዲህ ዓለም የሚደነቅላት አሜሪካ በእነዚህ ሁለቱ፣ እንደተባለውም በአይሁዳውያን እጅ ነች፡፡ ዛሬ የዓለማችን ታላላቅ የተባሉ ባለሐብቶች ቢልጌትን ጨምሮ ካቶሊክ ናቸው (ከክርስትናው ማለቴ ነው)፡፡ በፕሮቲስታንቲኒዝም የምትታወቀው ጀርመን ከሌላው ፕሮቲስታነት ከሆነው የአገሪቷ ክፍል ይልቅ በካቶሊክ አክራሪነታቸው የሚታወቁት ባቫሪያን (ደቡብ ጀርመን) አብዛኛውን የአገሪቱን ሐብት የሚቆጣጠሩ ናቸው፡፡ ሐብት ብቻም ሳይሆን ሳይንሱንም፡፡ እንግዲህ የአብይ አህመድ መረጃ ከየት አንደሆነ የሚጠይቀው ስለሌለ ያው ጀብ የማያውቁት አገር ሄዶ… አይነት ነው፡፡ የእኛዎቹ ፕሮቲስታንቶች ደግሞ በተጨማሪ በይሉኝታቢስነታቸው ስለሚታወቁ ለአብይ አህመድ  ችግር የለበትም፡፡ ከዚህ በተረፈ የነባር መሠረት ያላቸው የትኞቹም እምነቶች የትኛውም ይሁን በዓለማችን ወሳኝ እንደሆኑ በግልጽ እያየን ነው፡፡ በሩቅ ምስራቅ አገራት የቡዲዝም፣ በሕንድ ሂንዱዝም፣ የዓለማችን የምጡቅ ሳይንስ ምድር የሆነቸው ራሽያ ደግሞ በኦርቶዶክስ ክርስትና የሚታወቁ ናቸው፡፡ ለብዙዎች የዓለማችን የምጡቅ ሳይንስ አገር ራሽያ ስል ግር እንዳይላችሁ፡፡ እውነት ነው፡፡ ያች አገር ቀደም ባሉት ዘመናት ተራማጅ ነን በሚል ከእምነት በወጣችባቸው ዘመኖች ብዙ ወደኋላ ሄዳ ነበር፡፡ አርግጥ ነው ሳይንሱ ቢኖርም ሥርዓት ስለጠፋ እምነት ስለተተወ አደጋ ላይ ነበረች፡፡ የሶሻሊስቷ ምድር ራሽያ ዛሬ የኬጂቢው አባል መሪዋ ዋና የቤተክርስቲያኗ አስቀዳሽ ነው፡፡ ይሄ ለራሽያ እንደገና ማንሰራራት አንዱ ነው፡፡ አሁን በዛች አገር እየሆነ ያለው የራሽያን ታላቅነት በአስተማማኝ ሁኔታ ሊያስቀጥል በሚችል ነው፡፡ ሁሉም ነገር በሥርዓትና በራሽያ የኖሩ እሴቶች ስለተገነባ፡፡ ቻይና በኮሚኒስት ብትመራም ከአባቶቻቸው የወረሱትን የቻይናን ባሕልና ወግ ተከትለው ቻይናዊነትን ትልቅ በማድረግ ዓላማ ነው የሚሰሩት፣ ጃፓን የወግ አጥባቂ ሥርዓት ተከታይ ናቸው፡፡ በእምነት በአብዛኛው የጥንታዊ የሺንቶና ቡዳህ እምነትናቸው፡፡ ሕንድም እንደዛው የጥንታዊ ሕንዱዝም ተከታዮች ዋና ናቸው፡፡ የሁሉንም ጥንታውያን እምነቶች አንድ የሚያደርጋቸው የሕብረተሰብን የመገንባትና  በአገር ላይ ባላቸው ከልብ የሆነ የባለቤትነት መንፈስ ነው፡፡ ይሄ አይነት ባሕሪ እንኳን በአፍሪካና በተለይም በኢትዮጵያ ይቅርና የፕሮቲስንታኒዝም እምነት በተፈጠረበት በጀርመንም የለም፡፡ የእኛው አገር ፕሮቲስታንቲኒዝም ትውልድን በማደንዘዝና በማጭበርበር ሕዝብና አገርን መዝረፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡  አዝናለሁ፡፡ አብይ አህመድ የሚለን ተራማጁ ፕሮቲስታንቲኒዝም በኢትዮጵያ ይሄን መሠል አደገኛ ቡድን ነው፡፡

አብይ አህመድ በፍጥነት መዋቅሮችን በኦሮሞና በጴንጤ መሙላት ተቀዳሚ ስራው ነበር፡፡ እርግጥ ነው ኦርቶዶክስ በፊትም ወያኔ አሳስታው ነበር፡፡ አብይ አህመድ የጴንጤ ሰባኪን በባትሪ እየፈለገ ነው በዚህ ሁለት ዓመት ሲሾም የነበረው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በፍጥነት ነበር በጴንጤ ያስወረረው፡፡ ያው እንደ ለመዱትም በዘረፋና በእርዳታ ሥም ከባንኩን መዝረፍ ትንሽም አላሳፈራቸውም፡፡ አሁን የጴንጤው ሥራአስኪያጅ ነገር ብዙ ጫጫታ ፈጠረ መሰለኝ አሁን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከአረቦች ጋር የሚሰራ ከኦሮሞ ባንክ አንድ ኦሮሞ ሙስሊም ሥርዓስኪያጅ መድቧል፡፡ በነገራችን ላይ የዳንኤል ክብረት ነገር እያጠያየቀኝ ነው፡፡ ለመሆኑ የዳንኤል ክብረት የሥራ ድርሻ ምን እንደሆነ የሚያውቅ አለ?

አስገራሚው ሌላው እውነት የአማራ ክልል ጉዳይ ነው፡፡ አማራ በአብዛኛው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ቢሆንም ከ60 በመቶ በላይ የክልሉ ባለሥልጣናት ጴንጤ መሆናቸው ብቻም ሳይሆን የማህበረሰቡን እሴቶች ማጥፋት ሥራዬ ብለው የሚሰሩ መሆናቸው በሰፊው እየተነገረ ነው፡፡ የጣና ጉዳይ የዚህ ሴራ አንዱ አካል እንደሆነም እየታዘብን ነው፡፡  ባሕርዳር ላይ በከንቲባነት ተመድቦ እየሰራ ያለውን የጴንጤ ዘራፊ ዝና ሥንሰማ ነበር፡፡

የጴንጤን አማኝ ነን የሚሉትን ብዙዎች ሰሞኑን ስንታዘብ ነበር፡፡ አንድ ደረጄ የተባለ የጴንጤ እምነት ተከታይ ሰሞኑን እንዴት አብይን ትተቻለህ ተብሎ የተከፈተበት ዘመቻ አስቂኝ ነበር፡፡ በአረመኔዎች አብይ አህመድ እንዲታረዱ ያስደረጋቸው ዜጎች ጉዳይ ለብዙ የእምነቱ ተከታይ ነን ለሚሉ ምናቸውም አደለም፡፡ በተለይ ደግሞ የታረዱት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መሆናቸው ደስታቸው ጭምር እንደሆነ ስሜታቸውን በይፋ አሳይተውናል፡፡ ደረጃ እስከዛሬ የት ነገር ይላሉ ሁሉም፡፡ አንዳንዶች ኦሮሞ ከሱማሌ ሲፈናቀል ምናምን እያሉ ያኔ አልተናገረም ይሉናል፡፡ ሲጀምር ኦሮሞ ከሱማ ድንበር የተፈናቀለው በሴረኛ ኦሮሞ እንጂ በሱማሌም አልነበረም፡፡ ከሱማሌ ድንበር ያፈናቀሉት በአዲስ አበባና በናዝሬት የዲሞግራፊክ ለወጥ እናመጣለን ላሉት እቅዳቸው እንጂ አብዲ ኢሌ አልነበረም አፈናቃዩ፡፡ ይሄን ከጅምሩ እናውቅ ነበር፡፡ በወቅቱም እውነቱን ጽፌ ነበር፡፡ ከጌዲዮም የሉናል፡፡ እርግጥ ነው ጌዲዮ ተፈናቅሏል፡፡ ለጌዲዮ ማን ደረሰለት? ኦርቶዶክስ ወይ ጴንጤ? እውነቱን እንነጋገር? እርግጥ ነው ጴንጤ ሆነው የሚደማቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ግን በአብዛኛው ጴንጤ የገንዘብ እርዳታ ነገር አይሆንለትም፡፡ አንዳንዱ እማ እባክህ የሞት መድሀኒት ነው አንድ ብር ቢሉት ድብን ይበል እንጂ እንድ ብር አላወጣም አይነት መንፈስ የተቆራኘው ነው፡፡ አንዳንዶች ሌሎች ባዋጡት ገንዘብ ቦታው ሄደው ስላሽቃበጡ የጌዲዮ ሕዝብ አዛኛ ሆነዋል፡፡  ያም ሆኖ ያም የሆነው በአብይ ሥርዓተ አልባ አስተዳደር ነው፡፡ የጥቅምቱና የአሁኑ የሰኔው የአረመኔነት ክስተት ግን ከየትኛውም ጋር ሊነጻጸር ባልጸገባ፡፡ በግልጽ አውሬነታችሁን ስለነገራችሁን ግን ጥሩ ነው፡፡ ደረጄ እስከዛሬ ዝም ብሎ ከሆነም ዝም ቢሊም ዛሬ መናገሩ ለምን ተናገረ ብሎ መጠየቅ ሳይሆን የሰውነት ባህሪ ቢኖራችሁ ሐሳቡን መደገፍ ብቻም ሳይሆን እናንትም ቀዳሚ በሆናችሁ፡፡ ስታሚኝ ሰሞሽ ስህተትሽን ያለው ዘፋኝ ትዝ ይበላችሁ፡፡

የሆነ ሆኖ ግን አብይ አህመድ በግልጽ በማኒፌስቶ የጻፈውን የጸረ-ኦርቶዶክስ የመርዝ ሴራ ዝም የተባለበት ነገር አልገባኝም፡፡ ይሄ ብቻም አደለም በየቦታው ጴንጤ እየመረጠ የሚያስቀመጠውንም ሥራውን ማን ነው የሚጠይቀው፡፡ እስከዛሬ ድረስ ኢትዮጵያ የተመራቸው በጴንጤ ወይም ሙስሊም ቢሆን እዛች አገር ሌላ እምነት ባልተገኘም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያን የምትወክል እምነት ነች፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኦርቶዶክስን ማጥፋት የሚለውን ሴራ ነው እየሆነ ያለው፡፡ አብይ አህመድ የመጀመሪያው የኖቤል ተሸላሚ በዓለም አቀፍ ወንጀል ተጠያቂ መሆኑም የሚቀር አይመስልም፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

7 Comments

 1. ሰርጸ ደስታ በእኔ በኩል ጥሩ ግንዛቤ አግኝቻለሁ ወደ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ርእዮት ሚዲያ ብትደርስ ይበልጥ ነብስ ትዘራ ነበር። እንግዲህ የሳይበር ጴንጤዎች እነ እውነቱ ደግሞ የተመደቡበትን ተቃውሟቸውን እጠብቃለሁ

 2. Abiy Ahmed is learning how to be a Prime Minister by using Ethiopian Orthodox as an experimental (guinea pig). If the Ethiopian Orthodox survives and his experiment brings life to the Ethiopian Orthodox then Abiy will implement his trial experimental leadership strategy on others claimed mg it was his brilliant strategy which he knew succeedes, if the experiment fails Abiy blames Alothers then the Ethiopian Orthodox will pay the burden while Abiy watches and learns if Orthodox survived and how the Ethiopian Orthodox survived ? What kind of resilience strategy others can learn will be observed.

 3. እግዚአብሔር ይስጥልን ፀርፀ ! for being a voice for the voiceless! the Goddamn so called p/m is destroying Ethiopia.

 4. “ሀገር የጋራ ነው ሀይማኖት የግል ነው” የሚለውን የጃንሆይን ንግግር አልሰማህም?
  ጽሁፍህ ጠባብነትህን፣ አርቆ ማሰብ የማትችል ፣ ጉግማንጉግ የጥፋት ሰው መሆንህን ያሳያል።
  ሰውን ማሽነፍ የሚቻለው በፍቅር እንጅ በጥላቻ ወ ይም በጉልበት አይደለም።

 5. “አብይ-አህመድ ብልጽግና ላለው የማደንዘዣ ፓርቲ (እኔ ያልኩት ሳይሆን ሽመልስ የነገረን እውነት) ማኒፌስቶው የኦርቶዶክስ እምነት እንቅፋት እንደሚሆንበትና ለዛም ተራማጅ ባለው የፕሮቲስታንት እምነት መተካት እንደሚገባ ነግሮናል፡፡ ”

  ማንም አይምሮ ያለው መሪ አንድን እምነት በሌላ ለመቀየር አቅዶ ይነሳሳል ብሎ መገመት በዚህ ምእተ አመት እብደት ነው ብዬ ስለማምን አስተያየትህን አላምንበትም:: ጠቅላይ ሚንስትሩ ወይም ሌሎች የግል አመለካከታቸው ሲገልፁ ህዝብን ስልሚወክሉ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል::
  ብዝሀ ሃይማኖት ባለበት አገር መንግስት ካዳላ እራሱ ገደል ይገባል::
  ስለዚህ ነው መንግስትና ሀይማኖት መለያየት ያለባቸው::
  ሁሉቱ የክርስትና ሀይማኖቶች ማቀራረብ እንጂ ማጋጨት አይጠቅምም!

  ኦርቶዶክስ የአማራ ሀይማኖት ብቻ እንዳልሆነ ዼንጤም እንዲሁ::

  በማንኛውም አካባቢና በማንም ስው ወይም ጎጂ ያልሆነ ሃይማኖት ላይ የሚፈፀም በደል ኢስብአዊ ነው::

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.