ታከለ የሚባል ጮሌ ሲሄድ አዳነች አበቤ የምትባል ጩሉሌ መጥታለች ከመምጣቷ ቲቪውን ተቆጣጥረዋለች – ጌታቸው ሽፈራው

Abebeታከለ የሚባል ጮሌ ሲሄድ አዳነች የምትባል ጩሉሌ መጥታለች። ከመምጣቷ ቲቪውን ይዛዋለች። ቂሟን እንደማናውቀው መልካም ምኞት በማስተላለፍ ላይ ነች። ስንቱን ከየተቋሙ ገፍትራ በራሷ ሰው የተካች አግላይ አሁን ጥሩ እናት መስላ “ለሁላችሁም” ብላ መልካም ምኞት ማስተላለፍ ተያይዛዋለች። ባናውቃትኮ ጥሩ ነበር። ቂመኛና አግላዩዋ አዳነች አቤቤም አዲስ አመትን እንዲህ ጮሌ ስትሆንበት የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም የማይማር ነው የሚመስላቸው!
የጃዋር ቲቪ የዘር ፍጅት ጭፍጨፋ በሰበከ አየር ላይ ያልነበረውን አሥራትን ቁጥር አንድ አድርጋ የወነጀለኝ ቂመኛ “መልካም አዲስ አመት” ስትል እንደ ክፋቷ “አያድርሳችሁ” የምትል እየመሰለኝ ይቀፈኛል
እስክንድር ነጋ በርካታ ስጋት እያለበት በህዝብ መሃል ሲባክን ነው የሚውለው። ጥበቃ የለውም። መኪና የለውም። የሆነ ችግር ተፈጠረ በተባለ ቁጥር በእግሩ ይባክናል። እስክንድር በእግሩ የሚባክነው መኪና የሚሰጠው ሰው አጥቶ አይደለም። አይፈልግም። የእስክንድር ስብዕናና ትህትና አንዳንዴ ያስደነግጣል። ክፍለ ሀገር የሆነ ዝግጅት ያለው አካል ከጠራው ላለመቅረት ተከብዶም ቢሆን ሊገኝ ይችላል። ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ አለው። “ወጭዬን እኔ የምሸፍን ከሆነ ብቻ ነው።” ይላል። ጊዜ የለኝም ብሎ ለመቅረት የከበደው እስክንድር “አይሆንም ወጭውን እኛ እንችላለን” ካልከው ሳያመነታ “አልመጣም” ይልሃል። እስክንድር ጋር ሆኖ ወጭ መጋራት የተከለከለ ነው። እከፍላለሁ ካልክ እጅህን ይዞ ይለምንሃል። ወደቤት ስትገባ እሱ የመቅደም ግዴታ ይጥልብሃል። ታናናሾቹን ሳይቀር አስቀድሞ ይከተላል። የእስክንድር ትህትና እና ታታሪነት የሚያስደነግጥ ነው። በተለይ ቀርቦ ለማያውቀው!
በሌላ በኩል ደግሞ ታከለ ኡማ አለ። ሰሞኑን እንደታየው የፈለገውን እያነሳ ለሚፈልገው ሁሉ የሚሰጥ ነው። ዛሬ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የነገረንም ይሄውን ነው። ግን ሰው ሳያውቅ ተሳሳተ። አቶ ታከለ 8 ሚሊዮን በሚያወጣ የመንግስት መኪና እየከነፈ መንገድ ላይ እሰክንድርን በእግሩ ሲባክን ያየዋል። ይጠራውና “ለምን በእግርህ ትሄዳለህ? ይህን መኪና ልስጥህ?” ይለዋል። አይደለም ከገዥዎቹ ከጓዶቹ መቀበል የማይፈልገውን እስክንድርን ባያውቀው ነው። በተመሳሳይ አላማ ያሉ ሰዎች ጋር ሆኖ ወጭ እንዳይጋሩት የሚያደርገውን ጥረት ስለማያውቅ ነው። ሰዎች ለራሳቸው ስራ ሲጠሩት የመጀመርያ ቅድመ ሁኔታው “ወጭዬን እኔ ከሸፈንኩ ብቻ ነው” እንደሚል ባያውቀው ነው።
እስኬውን የማያውቀውና የቱንም እያነሳ በመስጠት አፍ ማስያዝ የሚፈልገው ታከለ ኡማ መኪና ልስጥህ ሲለው እስክንድር የመለሰለት በትህትና ነው። “ፈጣሪ ያክብርልኝ! አልፈልግም!” ነበር ያለው፣ ተመስገን ታከለን ጠቅሶ እንደፃፈልን። እስኬው ለጠላቱ (እሱ ቃል በቃል እንዲህ ብሎ አይናገርም) እንኳ ትሁት ነው።
እነዚህ ሁለት ሰዎች ናቸው እንግዲህ አዲስ አበባ ላይ እየሰሩ የነበሩት። ታከለ በአዲስ አበባ ላይ፣ እስክንድር ለአዲስ አበባ። የሚያሳዝነው ግን ሕዝብ በታከለ ሲታለል ይህን የመሰለ ስብዕና ያለውን እስክንድርን እንደ አላማው፣ እንደ ቅንነቱ፣ እንደ ቁርጠኝነቱ አልተረዳውም። ብዙውን ጊዜ ያላወቀ ሕዝብ ካለፈ በኋላ የሚቆጨው እንዲህ አይነት አጋጣሚ ነው። ተሸውዶ አንድ ሰሞን ያደነቀው የታከለ ኡማ ጉዳይ ዘግንኖት አይወጣለትም፣ እየሰራለት ያልደገፈው እስክንድር ጉዳይ “ወይኔ” ብሎ አይጠቅመውም።
ለራሱ ስልጣንና ጥቅም የሕዝብን ሀብት የሚጠቀመው ታከለ ኡማ ተጨማሪ ሹመት ሲሰጠው፣ ትሁቱ ለራሱ ሳይሆን ሕዝብን ለመጥቀም የሚታትረው እስክንድር ደግሞ ለወንጀለኞች ማናጆ በክፉ እስር ላይ ይገኛል። ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ ይሄን ይመስላል!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.