አዳነች አስናቀች! “በከፈትሽው መንገድ ምሪበት!!! ተባረኪ‼️ – መስፍን ወልደ ማርያም

Mesfin፣ ጳጉሜን 2012
===============
አዲስዋ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች የእውነትን በር ከፈተች! ቃል በተግባር ከተደገፈ ወይዘሮ አዳነች ጠቅላይ ሚኒስትሩንም፣ አገሪቱንም፣ ብልጽግናንም አድናለች፤ አዳነች ለወላጆቿ ምስጋና ይድረሳቸውና! ይህ እውነት ሆኖ ከያዘ ስም ወደተግባር ይመራል የሚባለውም እውነት ይሆናል፤ በከፈትሽው መንገድ ምሪበት! ተባረኪ!

የሚመርር ቢሆንም እውነትን መቀበልና ስሕተትንም ሆነ ጥፋትን ከመሸፋፈንና ከማድበስበስ ይልቅ ፊት-ለፊት መጋፈጡ ወንድነት ነው፤ ለወይዘሮ አዳነች ስል ወንድነት ማለቱን በመሻር ሴትነት እለዋለሁ! ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ሲሆን የተደረገውን ጥፋት የማረሙ ሁኔታ እንዲሁ በይፋ እንድናውቀወ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ፤ ይህ ጥፋት ማዘጋጃ ቤቱን ሳያበላሽ፣ ብልጽግናን ሳያበላሽ፣ አገሩን ሳያበላሽ፣ አገሩ በብልሽት ሳይፈርስ ወይዘሮ አዳነች ቁልቁለት የጀመረውን የኢትዮጵያ ፖሊቲካ ወደዳገት እንደምታወጣው እንጠባበቃለን፡፡

በዚህ ሁሉ ውስጥ ኢዜማ እንደፖሊቲካ ቡድንም ሆነ እንደየነቃ ዜጋ ያቀረበው ጥናትና ያጋለጠው ጥፋት በአሉባልታ ብቻ የሚንጫጩትን የፖሊቲካ የሚያስተምር በመሆኑ የሚያስመሰግነው ይሆናል፡፡
ለወይዘሮ አዳነች ከመጽሐፈ ምሳሌ በአሥራ አንድና በአሥራ ሁለት ምዕራፎች ላይ የሚገኙ አንቀጾችን ልጥቀስላት፡–

አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው
መልካም መክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል፤ ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፤ ዘለፋን የሚጠላ ግን ደንቆሮ ነው፤ ሥልጣን ላይ ያሉ ሁሉ በሰሎሞን ምክር ቢመሩ ጠቃሚዎች ይሆናሉ፤ አደራ ከመብላት ይድናሉ፡፡

ወይዘሮ አዳነችን ይበልጥ የማመሰግናት የከንቲባነቱን ወንበር ስትለቅ ሳትማስን የቀረች እንደሆነ ነው፤ እግዚአብሔር ይጠብቃት!

ተጨማሪ ያንብቡ:  እውነትም ስምን መላክ ያወጣዋል - ደጀን ከተማና አካባቢዋ ያሳዩት ኢትዮጵያዊነት! - ግርማ በላይ

3 Comments

  1. The same woman gave omn over 50 million from public coffers. Professor we love you and respect you but dont be quick to shower praise because of talk. As you know talk is cheap action is different, haven’t you learned anything from lemma and abiy. You should be patient and wait, your life experience demands that. You should preach wait and see rather than rush and be disappointed.

  2. Here we go over and over again ! Prof. , if you got a great deal of personal favor , you need to offer your blessings accordingly , not in the name of the people who have been terribly cheated and continued being so by the very hypocritical and conspiratorial political drama of Abyi and his comrades in arms .
    Didn’t you learn from your very misleading idea of yours that went to the extent of claiming that Abyi is the savior of Ethiopia sent from the heavenly world ? I hope you do . If so ,Why you keep doing the same without at least taking time that is necessary to come up with comments that could reflect the reality in the ground ?
    This generation desperately needs intellectuals who live by example !

  3. ግራ የገባ ነገር ነው ፕሮፌሰርን ከማንጠልጠል በላይ በዘመናዊ ትምህርት ሌላ የትምህርት ደረጃ ምን አለ? የተሰረቀ መሬት አለ ብላ መናገሯ ይሄን ያህል ሙገሳ ያስፈልጋታል? ይህች ሴት ሌላው የሚያውቃት በሌላ ታሪኳ ነው። በታረዱት፣ በተገደሉት፣ በተጋዙት ዜጎች ላይ ቀጥተኛ ሀላፊነት ሲኖራት ግፍን ባለመቃወሟ ደግሞ ዳግም ተጠያቂ ነች። ስንት የነጠሩ መሪዎችንና ባለስልጣናት በቅርበት የተመለከት ፕሮፌሰር አለም አቀፍ መለኪያን ያሟሉ ባለስልጣናት በነበሯት ሀገር አዳነች ሀቤቤን፣ታከለ ኡማን ፣ወርቅነህ ገበየሁን፣አባ ዱላን፣ሱሊማን ደደፎን ….የመሰሉ ሰዎችን ስልጣን ላይ ማስቀመጥ ምሩ ለማለት ሳይሆን ወምበሩ ላይ ቁጭ ብላችሁ አቆሺሹት ማለት ነው። በሁዋላም ለኢንተርናሽናል ስራ ይጠቅማችሁዋል ከሚል እሳቤ ነው። እንደ ቴድሮስ አድሀኖም፣ወርቅነህ ገበየሁ፣ሰየ አብረሀ ይቀጥላል።ቴድሮስ አድሀኖም በችሎታ ማነስ እንዲህ ነብስና ስጋው ሲላቀቅ ድርጅቱ ለውድቀት ሲዳረግ በክብር ይሰናበት ነበር እሱ ግን ክብር ለምኔ ብሎ የሚወረውሩለትን እያሰበ ትችቱ ምንም ሳይመስለው ቁጭ ብሏል። የአብይ ሹመት ድልድሉ ተንኮል ላይ የተመሰረት በመሆኑ አገሪቱ ቀና ብላሽትሄዳለች ማለት ዘበት ነው። እስቲ እንለፈው ሌላውን ከግምት በመክተት።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.