የፌደሬሽን ምክር ቤት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የትግራይ ክልል አካሂደዋለሁ ካለው ምርጫ ጋር ተያይዞ ውሳኔ አሳለፈ

118851327 3648500808515102 982446124802356039 o 1የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ ከሕገ መንግስቱ የሚቃረን መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አስታውቋል፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባን ተከትሎ ያወጣው ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር የፓርላማ ዘመን 5ኛ አመት 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ ጎን በመተው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና አዋጁን መሰረት አድርጎ ያቋቋመው የምርጫ ኮሚሽን፣ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና የፈፃማቸው ተግባራት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ እንዲሰጥበት በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ተጣርቶ ለመጨረሻ ውሳኔ ለምክር ቤቱ በሕገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች በኩል በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱም ላይ በእስከ አሁኑ ሂደት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትግራይ ሕዝብ ትልቅ ክብር ያለው መሆኑንና ህገወጥ አካላት በሚፈፅሙት ድርጊት ምክንያት በሕዝቡ ላይ ጉዳት ሊደርስበት አይገባም ብሎ የሚያምን መሆኑ እና በቀጣይም ችግሮችን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በሌላ በኩል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ እና የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በመጥቀስ የትግራይ ክልል እያካሄደ ካለው ህገወጥ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብት አለማክበር ተቀባይነት የሌለውና ሊታረም የሚገባው መሆኑ ከማስቀመጡም ባሻገር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን አገራዊ ምርጫ በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ እና የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ በደብዳቤ ሕገ መንግስቱና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲከበር የሰጡትን ማሳሰቢያ አለመቀበሉ ኢ-ሕገ መንግስታዊ ነው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሚከተሉትን የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔዎች በሙሉ አፅድቋል፡፡
1) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55(15) እና አንቀጽ 55(2)(መ) ጋር ይቃረናል፤
2) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012ን መሰረት አድርጎ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 102 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ስልጣን ይጥሳል፤
3) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት፣ አስፈፃሚ አካላት እና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ያሳለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ምክር ቤቱ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እነሆ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ነሐሴ 30፣2012 ባካሄደው 5ኛ ዙር የፓርላማ ዘመን 5ኛ አመት 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ ጎን በመተው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና አዋጁን መሰረት አድርጎ ያቋቋመው የምርጫ ኮሚሽን፣ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና የፈፃማቸው ተግባራት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ እንዲሰጥበት በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ተጣርቶ ለመጨረሻ ውሳኔ ለምክር ቤቱ በሕገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች በኩል በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ውይይት መደረጉን ተናግሯል።
በውይይቱም ላይ በእስከ አሁኑ ሂደት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትግራይ ሕዝብ ትልቅ ክብር ያለው መሆኑንና ህገወጥ አካላት በሚፈፅሙት ድርጊት ምክንያት በሕዝቡ ላይ ጉዳት ሊደርስበት አይገባም ብሎ የሚያምን መሆኑ እና በቀጣይም ችግሮችን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል፡፡
በሌላ በኩል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ እና የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በመጥቀስ የትግራይ ክልል እያካሄደ ካለው ህገ ወጥ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብት አለማክበር ተቀባይነት የሌለውና ሊታረም የሚገባው መሆኑ ከማስቀመጡም ባሻገር፣ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን አገራዊ ምርጫ በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ እና የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ በደብዳቤ ሕገ መንግስቱና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲከበር የሰጡትን ማሳሰቢያ አለመቀበሉ ኢ-ሕገ መንግስታዊ ነው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሚከተሉትን የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔዎች በሙሉ አጽድቋል፡፡
1) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55(15) እና አንቀጽ 55(2)(መ) ጋር ይቃረናል፤
2) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012ን መሰረት አድርጎ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 102 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ስልጣን ይጥሳል፤
3) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት፣ አስፈፃሚ አካላት እና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ያሳለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
EBC :

2 Comments

  1. በጣም የረጋ ሩቅ አሳቢ ውሳኔ። በዛ በኩል ያለውን ከፍተኛ የህዝብ ጭንቀት ያገናዘበ፣በዚህም በኩል ሊኖር የሚችልን የህዝብ በጎሣ መከፋፈል አደጋ ከግምት ውስጥ ያስገባ፣ወንድሞቻችን ህዋታዊያንም ወደልባቸው ተመልስው በጥሞና እንዲያስቡና፣ቢያንስ በዚህም ማዶ ለትግራይ ህዝብ የሚጨነቅ ወገን መኖሩንና፣ ብንደማመጥና ረጋ ብንል፣ ሁላችንም ኢትዮጵያዊ መሆናችን፣ ሀገራችንም ለሁላችንም የምትበቃ መሆንዋን ያስተማረ፣ ከዚህ አልፈው እንገንጠል የሚል አጉል ዕብሪትና ቅዥት ውስጥ ቢገቡ ግን፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም ባለው መላ ኢትዮጵያዊም ሆነ በዓለም አቀፉ ማህበረስብ ዘንድ የሞራልም የትግል ተቀባይነት ያለው፣ የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስ የሚስሩ የሀገሪቱን የለየላቸው ጠላቶች ከህዝቡ ነጥሎ በመምታት አደብ ለማስገዛት የሚያስችል ብልህ ውሳኔ ነው። በርግጥም እስከዛሬም ድረስ በመላው ዓለም እጅግ የሚሚከበረው የቻይናና የመላው ዓለም የሚሊታሪ ዶክትሪን አባት ተብሎ በሚታወቀው Sun Tzu በተባለው የሚሊታሪ ስትራቴጂስት በተፃፈው The Art of War በተባለው መፅሀፍ እንደተገለፅው፣’የጀግና የጦር መሪ የመጀመሪያ ምርጫ ጦርነትን ማስወገድ ነው’ ።

  2. ከላይ የሞራልም የትግል ተቅባይነት ትብሎ የተፃፈው፣ የአፃፃፍ ግድፈት በመሆኑ ‘የሞራልም የህግም ተቀባይነት’ ያለው ተብሎ ይነበብልኝ፣ ከይቅርታ ጋር።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.