“የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 240ሺ ካሬ መሬት መዘረፉን አረጋግጠናል” አዳነች አቤቤ

abbebeየአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 240ሺ ካሬ መሬት መዘረፉን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ አሁን የመሬት ስራዎችን አቁመናል ብለዋል፡፡ሆኖም አሁን እሳቸው ስልጣን በያዙበት ጊዜ እንኳ በ15 ቀን ውስጥ ወደ 8ሺ ካሬ ይዘናል ብለዋል፡፡ 124 ህገወጥ ካርታዎችን አምክኛለሁ ብለዋል፡፡ ስንት ህገወጥ ካርታ ሳይያዝ እንደቀረ ስንት፡መሬትም አሁንም እየታጠረ እንደሆነ እንግዲህ እግዜር ይወቀው፡፡ካርታ አዳዮች እና መሬት አከፋፋዮች ግን አሁንም ቢሮ እና ማህተም ይዘው ቀጥለዋል፡፡


አብደናል እንዴ…?
ለምን ሁልጊዜ እንደ አዲስ እብድ እንጮሃለን ። ዱሮም ኮንዶሚኒየም እንመዘገባለን እንጅ መቼ ደርሶን ያውቃል ። ህወሐት ለማን ነበር የምታድለው ? አሁንስ የታደለው ለማነው ? ነገስ?
በ1997 ተመዝግበን አስቡት 17 ዓመት ጠብቀን ዛሬም ወፍ የለም ። ህወሐት ኢህአዴግን ፈጠረች ። ኢሀዴግ ደግሞ ብልጽግናን ፈጠረ ። በእርግጥ የንግድ ስያሜ ተቀይሯል ።
ህወሐት ደርግ 17 ዓመት ጨቆነኝ ብላ ለተፈናቀሉ፣ ለተጎዱ ፣ለአካል ጉዳተኝች ወዘተ በማለት መሬትም ኮንዶሚኒየምም ሌላም አደለች ። ልጅ ደግሞ ወረሰና በመሬታቸው ላይ ፎቅ ለተሰራባቸው ተሸካሚ ለሆኑ ለተፈናቀሉ 20000 ቤት ሲያንሳቸው ነው አሉን ። አይጣል ነው እንጅ ደርግም እኮ የተሰራን ቤት ነጥቆ ቤት ለሌላቸው ምስኪኖች አከፋፍሏል ።
ተረኝነት አለ ይቀጥላል ።
እኔ ግን እራሴን ያሳመንኩት ህወሐት 40/60 እና 20/80 ከ20000 በላይ ላራሷ አዘጋጅታ እንደነበር እና እንደተወረሰች አድርጌ ነው ።
“አዳራሹ ሰፊ በሩ እልጠበባችሁ
በተራበ ተራ ምነው መግባታችሁ”
ብሏል ባለቅኔው ።
በእውነት አብደናል !
ለማንኛውም ሲያንስ ነው ተብለናል ።
ከዚህም በላይ እንደሚኖር ምንም ጥርጥር የለውም ። ምን አልባት ከንቲባው አልደፍር ያለውን የሚደፍር ተተክቶበት ቢሆንስ ? ለማንኛውም አዲስ እብድ አንሁን ።በዛ ላይ መጭው መስከረም ነው እንደ አዲስ የምናብድበት ።

Image may contain: outdoor

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.