እባካቺሁ ባለጊዜዎች እምነት ካላችሁ በምታመልኩት አምልኮ ወይንም ፈጣሪ አምላክ ተለመኑ ( ከድሉ ዘገዬ )

PP 2ምድርቱን በንጹሀን ደም አታጨቅዩ ምክንያቱም በሞራል ፣ በፈጣሪና በሰው ሰራሽ ህግ ያስጠይቃልና ፤ ሕዝቦቿንም አታስለቀሱ ማቅም አታልበሱ እንባውን የሚያብስ አምላክ አለውና ፤ አታደህዩት የእለት ጉርሱንም አጣሳጡት ግፉ ለልጆቻችሁ ይተርፋልና ፤ አትቀሙት ፣ አትዝረፉት ስርቶና ለፍቶ አፍርቷልና ፤ ከቀዬው አታፈነቅሉት ርስት ጉልቱ ናትና ፤ አትቆምሩብት ቁማርተኛ አይደለምና ፤ አታደናግሩት የህይወት ውጣ ውረዱ ድንግርግር ይበቃዋልና ፤ ለስልጣንና ለጥቅም ብላችሁ አትከፋፍሉት አንድ ሕዝብ ነውና ።

ባለጊዜዎች ነግ በኔን እወቁ ፤ ጨለማና ብርኃን መፈራረቁ የተፈጥሮ ህግ በመሆኑ የሚያቆመው የለም ፤ ዛሬ የነጋላችሁ መስሏችሁ የምትፈነጩ ነገ እንደሚጨልምባቸሁ ብትገነዘቡ መልካም ነው ። የሰው ልጅ ሁሌም ታሪክ ሰሪና የታሪክ ተማሪ እንጂ የታሪክ እስረኛና ምርኮኛ አይደለም ስለሆነም አዲሱን ትውልድ በፈጠራ ትርክት አታሳስቱት ። ሕብረተሰብ በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ፣ ለውጥና እድገት ውስጥ እንደመሆኑ መጠን ጊዜውን የዋጀ አዳዲስ ተግባራትን በመከወን የኑሮውን ክብደት ያቀላል እንጂ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ወገኔን እንዴት አድርጌ ብገለው ስቃዩን አበዛበታለሁ ፣ እንዴት ቢዘርፍው ይደሄያል ፣ እንዴት አድርጌ መግቢያና መውጫ ባሳጣው ቀዬውን ጥሎ ይጠፋል ፣ እንዴት ቆምረንና አደናግረን አገር እናፍርስ ሕዝቡንም እንበታትን ብሎ ማሴር የሰይጣን እንጂ የሰው ልጅ ተግባር ሊሆን አይችልም ።

 

ተረኞች እባካችሁ ከስህተታችሁ ተማሩ

ብልህ ከሰው ስህተት ይማራል ጅል ግን ከራሱም ስህተት አይማርም ይባላልና አሁን በለውጥ ስም የያዛችሁት የተረኝነት ጉዞ ካሁን በፊት ከህወኃት ጋር ሆናችሁ ያላዛለቃችሁ መንገድ ነው ። ያላዛለቀው ህወኃት በመምራቱ ሳይሆን የተከተሉት የጎሣ ፖለቲካና ማስፈጸሚያው ሕገመንግሥት ተብዬው በዓለም የለሌ ሀገር አፍራሽና ዘረኛ በመሆኑ ነው ። አሁንም አያዛልቃችሁም ምክንያቱም ከህወኃት ዕንቁላል የተቀፈቀፋችሁ ጫጩቶች በመሆናችሁ ያልዘሩት አይበቅልምና ጉዟችሁ ሁሉ ለማንም የማይጠቅም እያዩ ገደል ነው ። መስሏችሁ እንጂ ቆምሮና አደናግሮ የተወሰነ እርቀት አብሮ ተጉዞ አያ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ ብሎ ሽኝቶ የምትመለሱበት አካሄድ አይደለም ። ከሆነም የሚሆነው ተያይዞ ገደል ነው ። እባካችሁ ከስህተታችሁ ተማሩ ።

 

መልእክት ለክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አህመድ

ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ያክብሮት ሰላምታዬ ይድረስዎ እኔ አንድ አገሩን እንድሚወድና ለአገሩ እንደሚጨነቅ ዜጋ የለውጡን ጉዞ በሚገባ እከታተላለሁ መልካም ሲሰሩ እመካብዎታለሁ ሲያበላሹ እሳቀቃለሁ ምክንያቱም በገቡልን ቃል መሰረት ኬት መጡ ማናቸው ሳልል በኢትዮጵያዊነትዎ አምኜ በመቀበል ነበር ። ነበር ያልኩት አለምክንያት አይደለም በዚች አጭር የስልጣን ዘመንዎ ተአምር አልፈጠሩም ብዬ የጅብ ችኩል ከመሆን በመነጨ አመክኒዮ አልባ እሳቤ አይደለም ነገር ግን ነበር ያሉክት እንደ መሪ የሰሩትን መልካም ተግባራትና መስራት ሲገባዎት ያላደረጉትን ፣ የመንግሥትዎ ተቀዳሚ ተግባር የሆነውን ህግ ማስከበር መቻል አለመቻልዎትን ፣ ለሕዝብ ህይወትና ንብረት ውድመት የሚሰጡትን ትኩረትና ቸልተኝነት ፣ ለስራዎ የሚሰጡትን ቅደም ተከተል ( ለከታማ ማስዋብና ለሰው ህይወት ያልዎት ቅደም ተከተል ) ፣ ነጌ አገርቷን ሊያበለጽጉ የሚችሉ የደንብዶሎ የዩኒቬርስቲ ተማሪዎች ጠፉ ካላችሁን 9 ወር አልፎታል ሌላው ቢቀር እንደ አገር መሪ አንድ ቀን መግለጫ ሳይሰጡን እንደ ቱሪስት ጋይደር ማይክራፎን ይዘው ፓርክ ሲያስጎበኙ ቪዲዮ አስቀርጸው ለቀውልናል ።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር የአዲስ አበባ መስተዳድር ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግሥት ሲሆን እርሶም ስልጣንዎን ተጠቅመው ከህግ ውጭ ኢንጂኔር ታከለ ኦማን በምክትል ከንቲባነት ሹመውታል ግለሰቡም ስልጣኑን ተገን በማድረግ በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የክህደትና የዘረፋ ውንጀል መፈጸማቸው ከእርስዎ እውቅና ውጭ ነው ማለት አይቻልም ። ግለሰቡን ከቦታው ማሸሽዎና ሌላ ሥልጣን መስጠትዎ የወንጀሉን መዋቅራዊነት የሚያረጋግጥ ነው ።

ዶክተር አብይ የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ማስተካከያ ፣ የመሬት ወረራና የቁጠባ ቤቶች ዘረፋ በእርሶ በሚመራው የኦሮሚያ ብልጽግና በእቅድ ተይዞ የሚተገበር አጀንዳ መሆኑን ኦቦ ሺመልስ አብዲሳ የአዋጁን በጆሮ ሹክ በማለት አረጋግጠውልናል የእርሶንም ዝምታ እንዳስለመዱን እየበሉ ዝም ፣ እየጠጡ ዝም ፣ የጋን ወንድም ብለን ወደማይሞላው ትዝብት ኮሮጇችን ከተነዋል ።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ የት እንደሚያደርስዎት የሚያውቁት እርሶ ንዎት ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው አይበሉኝና ሕዝባዊ መሰረትዎ ተንዶ አልቆ ባዶዎትን ከሚቀሩ በቅን ልቡና ለሕዝብ የሚታገሉ ፣ ሌቦችን የሚያጋልጡ ንጹህ ዜጎችን የባልድራስ አመራሮችን በማሰር የሚመጣ ለውጥ ባለመኖሩ ይፍቷቸው ። የሰው ህይወት ያጠፉ ጽንፈኞችን በእነ እስክንድር ስም አብሮ ለመፍታት የተሸረበ ሴራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለተረዳው አይጠቅምዎትም ወንጀለኞች በወንጀላቸው ይጠየቁ እነ እስክንድርን ይልቀቋቸው ።

የችግራችን መጀመሪያና መጨረሻ ህገመንግሥቱና የጎሣ ፌደራሊዝሙ ስለሆነ አሁን እርስዎ ባስጀመሩት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በሚያደርጉት የድርጅት ፕሮግራም ንትርክ የሚፈታ አይደለም ። በእውነት እርስዎ አገር አቀፍ እርቅ ምን ማለት እንደሆን ፣ እንዴትና በማን ተሳትፎ እንደሚደረግ አጥተው አይመስለኝም ነገር ግን ብሔራዊ እርቁ ህወኃት ሥልጣን ከተቆናጠጠበት ጊዜ አንስቶ በአገር ወዳዱ ዜጋ ሲጠየቅና መንግሥት ሲያጣጥለው እንደቆየ እርስዎም የሚያቁት ሲሆን አሁን እርስዎ በተራዎ እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው አይነት ውይይት ተብሎ ንትርክ የተካሄደበትን ድራማ እንድናይ ያደረጉበት ምክንያት ግልጽ ነበር ይሄውም ለፓርቲዎች መድረክ አዘጋጅተን ልስማሙ አልቻሉም በማለት ፓርቲዎችን ለማሳጣትና ብሔራዊ እርቁም እንደማይሰራ ለማሳየት የታቀደ ነው በመሆኑም እንዲህ አይነቱን የሴራ ፖለቲካ ትተው ብሔራዊ እርቁንም ሆነ በህገመንግሥቱና በጎሣ ፌደሬሺኑ ላይ ሁሉ አቀፍ ውይይት ማድረግ አርቆ አስተዋይነት ነው ።

የኢትዮጵያ በተለይም የአዲስ አበባ ሕዝብ ዝምታውን መስበር አለበት እንደ ህጻን ልጅ በብልጭልጭ ነገር ሳይሸወድ ተደራጅቶ ለህገ መንግሥታዊ መብቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሳይታገል ከተረኞች ነጻ መውጣት አይችልም ።

 

2 Comments

 1. . How many times should we keep saying please and please and please and please to those whose hands are terribly stained with the very blood of innocent people of Ethiopia for a quarter of a century ?
  .For how long should we keep begging and begging and begging those brutally ethnocentric politicians who served their master ,TPLF for a quarter of a century and continued not only business as usual but a much more cynical and horrible way of doing political business under the hegemony of OPDO/OLF ?

  .Is it not stupid enough to keep begging and begging and begging , and crying and decrying instead of helping the people to say enough is enough and engage those criminal politicians of EPRDF /Prosperity with any appropriate and effective method of struggle ?

  .Don’t we feel that it is totally nonsensical to try making a real change by repeating the same stupid way of doing politics over and over and over and over again ?

  .Didn’t we have enough to know who is Abyi Ahmed and what he is standing for and how he will be taking things to a much more worse consequences?
  . Are!t we really tired of wetting statements and letters of begging to those politicians who totally lost their basic moral and political senses during their deadly or bloody political game of three decades ? Totally nonsensical for us not to either understand or being stupid about this very clear and straight forward reality !!!
  So, it is time to tell the people the very bitter truth that those politicians of a rotten and poisonous political system of EPRDF/Prosperity will never be agents of a fundamental democratic change ! They instead not only prolong the untold suffering of the people but they will destroy the country and make it the massive grave land of this century . This may sound despair and pessimism . Like it or not , the way we are behaving and doing politics over and over and over and over again does not feasibly show hope and optimism in a real sense of the terms !
  The only way to avert despair and pessimism is to engage the very stupid but dangerous political agents of a deadly ethnocentric system of EPRDF/Prosperity with a well determined and coordinated way of struggle for the realization of a true democratic system !

 2. God bless you T.Goshu. Dear writer the frustration you are going through is real and is shared by many. But as T. Goshu mentioned begging or as some sad people say gentleness does get any any where time to call for collective action for the emancipation of Ethiopia and Ethiopians.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.