የብልጽግና መንገድ ሳርና በሬ – ከተማ ዋቅጅራ

PP Partyበሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ የመሰለ ነገሮች ከለውጡ ማግስት እየተመለከትን ነው። ከክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በምንሰማው የተስፋ ቃል ተውጦ ገደል ገብተው የቀሩ በጥቂቱ ሳይሆን አስደንጋጭ በሚያስብል መልኩ የጠፉ ዜጎችን ተመለከትን። የሚያስደነግጠው ህዝባችን የተነገረው የብልጽግና ተስፋ መጨለሙ ብቻ ሳይሆን የብልጽግና ሰዎች ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጀምሮ የክልል መንግስታትና የከተሞች ከንቲባዎች ዝምታ እንጂ። በስተመጨረሻም ዘግይተውም ብቅ ብለው እውነትን ከመግለጽ ይልቅ ገደሉ ላይ የጭድ ወሬ ሲከምሩ ስናይ ከፊታችን ከፍተኛ እና ከባድ የመከራ ግዜ እንዳለ በማወቅ ሁሉም ማህበረሰብ በንቃትና በተጠንቀቅ የሚሰሩትን ስራዎች መከታተልና እራሳችንን መከላከል እንዳለብን ይሰማኛል። በተለይ የሸዋ ኦሮሞ፣ አማራው፣ ጉራጌው እና የኦርቶዶክስ ክርስትያን አማኞች ሁሉ እንደ አይን ጥቅሻ በመግባባት አገርና ህዝብን ከጥፋት ልንታደግ ይገባል።
የሸዋ ኦሮሞ ጉዳይ በሚቀጥለው ጹሑፌ በሰፊው እመጣበታለው ጠብቁኝ። የሸዋ ኦሮሞ አክቲቪስቶች፣ ጦማርያኖች፣ ፖለቲከኞች፣ ሙሁራኖች፣ አርቲስቶች ግዜው ዝም ብለት ወይንም ተድብቀህ የምታመልጥበት ግዜ አይደለምና ሳይረፍድ የሸዋ ኦሮሞን በማንቃት እራሱን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም ሊያድን እንደሚችል አውቀን በስሙ ኦሮሞ እያሉ ወደ ጥፋት የሚወስዱትን እንዲለይ የማድረጉ ስራ የሁላችንም ነውና ለነገ ሳናሳድር ወደ ስራ መግባት አለብን።
ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ምስቅልቅል ህውአት( የመርገም ጨርቅ) ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናት። የተከተለችው የመከፋፈል መንገድ እርስ በእርስ ይበላላሉ ብትልም እንዳሰበችው ሳይሆን እራሳ በቆፈረችው ጉድጓድ በኢትዮጵያን ሁሉ ተጠልታ የመቀበሪያዋን ቀን እየጠበቀች ነው። ይቺ የመርገምት ጨርቅ ጣሯ ግን በዛ።
 አሁንም ተረኝነት በሚመስል መልኩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚያሳዩት ያልተገባ ንግግርና እንቅስቃሴ ነገ ልክ እንደ መርገምት ጨርቋ(ህውአት) የኦሮሞን ማህበረሰብ እና የፖለቲካ አመራሮችን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍል ከወዲሁ ማሳሰብ እወዳለው። አሁን እየተሄደበት ያለው መንገድ በምንም ተአምር የኦሮሞን ህዝብ አሸናፊ አያደርገውም እንደውም በሌሎች ብሔረሰብ እንዲጠላ እና ጠላት አድርጎ እንዲሳል ከማድረግ ውጪ የሚያመጣ አንዳች ትርፍ የለውም።
ሰውን በግድ እየገፋን ዘረኛ እንዲሆን ካደረግነው አደጋው የከፋ እንደሚሆን እሙን ነው። በዘረኝነት መስመር 27 አመት ስልጣኑን ይዞት የነበረው የህውአት (የመርገም ጨርቋ) መንግስት እራሷን ሸምቀቆ  ውስጥ ከታ የተወለደችበት ደደቢት ገብታ ሞቱንም በዛው እየተጠባበቀች ነው። የመርገም ጨርቋ መንገድ የሰው ህይወትን ከመቅጠፍ የኢትዮጵያ ህዝብንም ወደ ከፋ ችግር ከመክተት ውጪ ያመጣች አንዳችም ለውጥ የለም። አለ ብሎ  የሚከራከር ካለ ልቦናው በጥቅም የታወረ እና እውነት በውስጡ የሌለ ብቻ ነው። በዘር የተመሰረተ ስርዓት ለውጥ አያመጣም። ለዚህም ምስክራችን የመርገም ጨርቋ  ናት።
 በዘር የተመሰረተችው የመርገም ጨርቋ  ያመጣችብን  ጣጣ ለብዙሃኑ ሞትና እንግልት እስራት እና ስደት መንስኤ ሆኗል። ይህ ሁሉ የሰበአዊ መብት ጥሰት የመጣው የራሴ ዘር ገዢ፣ የራሴ ዘር ባለሃብት፣ የራሴ ዘር ተፈሪ፣ የራሴ ዘር ፈራጅ አድርጎ ሌላውን ህብረተሰብ ለጥ ሰጥ አድርጌ እገዛለው በሚል በዘር ፖሊሲ  ህግ መሰረት በመመራታቸው የተከሰተ አደጋ ነው። ወደፊትም የከፋ ጥፋትና እልቂት የሚያስከትል አካሄድ ነው። ብልጽግናም በፍጥነት እንደ መርገም ጨርቋ ግዜህ ሳያበቃ በወሬ ሳይሆን በተግባር ስራ መስራት ቢቻል ጥሩ ነው። አይ ስልጣን ላይ ያለ የሚያይ አይን ያሳውራል የሚሰማ ጆሮን ይደፍናል የሚያስተውል ልቦናን ይደፍናልና ግዜ የኛ ነው ከሆነ በናንተ ለይ የከፋ እንጂ የተሻለ ነገር እንደማይመጣ ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል።
በዘር የተመሰረተ አገዛዝ ከጥፋት ውጪ ምንም ልማት የለውም። ከመተላለቅ ውጪ ምንም ስምምነት አይኖረውም። አደገኛነቱ ደግሞ  በዘር ፖሊሲ የሚያምኑት አካሎች ከፍተኛ አደጋ ሲያደርስ ብቻ የሚነቁ መሆኑ ነው። ለምሳሌ ገዢው ፓርቲ ብልጽግናም የቀድሞ ገዢ ፓርቲ የመርገም ጨርቋ የዘር ፖሊሲን የሚከተሉ ናቸው። ስለሆነም ለአማራው የራሱ የሆነ ካርታ እና ባንድራ፣አማራ የሆነ ተወካይ መሪዎች አድርጎ አስቀምጧል። ለኦሮሞ የራሱ የሆነ ካርታ እና ባንድራ፣ ኦሮሞ የሆነ ተወካይኣ መሪዎች አድርጎ አስቀምጧል። ለደቡቡ እንደዚሁ። ለሱማሌም፣ ለጋንቤላ፣ ለአፋር፣ ለቤንሻጉል ጉምዝ እንደዚሁ የራሳቸው ካርታ እና ባንድራ ሰጥቶ አስቀምጧል። እውን ይሄ አካሄድ 27+2 አመት በቆየበት ሰዓት ሲፈተሽ ያመጠው ….ምን ያህል ሰዎች በዘራቸው ምክንያት ተገድለዋል፣ ምንስ ያህል ሰዎች በዘራቸው ተለይተው ወደ እስር ቤት ታግዘዋል፣ ምንስ ያህል ሰዎች በዘራቸው ምክንያት መኖር አትችሉም ተብለው የሚወዷትን አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፣  ምንስ ያህል ሰዎች በሐይማኖታቸው ምክንያት ተገለዋል፣ ተፈናቅለዋል።እውነቱን ለመናገር ከፈጣሪ በቀር ትክክለኛውን ቁጥር ማወቅ አይቻልም። የንጹሃን ደም ግን እንደሚፋረዳቸው  ላስገነዝባቸው እወዳለው። የዘገየ ቢመስልም በክፋት መንገድ እና በጥፋት ስራ የተሰማሩት ሁሉ የእጃቸውን ዋጋ የሚያገኙበት ግዜ ይመጣል። ያኔ ጥርስ ማፏጨት ብቻ ይሆናል። በዘር ምክንያት ተለይተህ ሲጎዱበት እንጂ ሲጠቅም አልታየም።
በኢትዮጵያ ዘግናኝ ክንውኖችን እያየን እና እየሰማን የተሻለ ግዜ ይመጣል በማለት አሁን ያለንበት ግዜ ደርሰናል። የዘረኝነት ፖሊሲ የዘራው የመርገም ጨርቋ ምርቷን የምታይበት ግዜ ደርሷል እና ለመቀበል ተዘጋጁ። ዘረኝነቱ ሲፈነዳ አፈናቃይ ሳይሆን ተፈናቃይ፣ ገዳይ ሳይሆኑ ሟች፣ ዳኛ ሳይሆኑ ተዳኚ፣ ገዢ ሳይሆኑ ተገዢ፣ እንዳለ የምታውቁበት ግዜው ደርሶ  ነገሮች ተገልብጠው ስታዩት የዘረኝነት ፖሊሲ  ዘግናኝነቱን  እና ክፋቱን ትረዱታላችሁ። የሰው ልጅ ብልጡ ከታሪክ አልያም በትምህርት ይማራል። ሞኝ ግን በራሱ ይማራል። የሚል አባባል አለ። ነገም ነገሮችን ሳይረፍድ በግዜ በፍጥነት ካላስተካከለ የፊተኛው ሄዴ የኋላውም የተሻለ ስላልሆነ እሱም ሄደ የሚባልበት ግዜ እሩቅ እንደማይሆን አትርሱ። የሚሰማ ካለ ለማስታወስ ነው።
የዘር ፖሊሲ አደገኛነቱ በሰላም ይኖር የነበረውን ሰው በጥላቻ ይቀሰቀስና ሌላውን ዘር እንዲጠላ ይደረጋል። ይሄንን ጥላቻ አዘል ሲነገረው ወደ ፍጹም ቂም አዘል ይለወጣል። እውነተኝነት በሌለው ነገሮች ይሞላና የሌላውን ዘር ወደ መጥላት እና ወደ ማጥፋት ይነሳሳል። ዘረኛ ያልነበረው በሰላም ሲኖር የነበረው ህዝብ በግድ ተገፍቶ ዘረኛ እንዲሆን ይደረጋል የዚህን ግዜ ሁሉም ብሔር  ውስጥ ዘረኝነት ይፈጠራሉ አደጋው አንዱ በራፍ ብቻ ሳይሆን  ሁላችንም ላይ ይመጣል። ወደ አልተፈለገ ግጭቶችም ይገባል። ቀድሞ የጥላቻ መልእክት ስለተላለፈ ለመጎዳዳት ምንም ነገር አያግዳቸውም። ያሸነፈ ግዛቱን የማስፋት የተሸነፈ ደግሞ ግዛቱን የመልቀቅ ነገሮች ይፈጠራሉ። ይሄንን ግጭት እንደ ቀላል ማየት ግን ፈጽሞ ሞኝነት ነው።
1ኛ፡ ለዘራችን ቆመናል የምንል የራሳችን ወገን በብዛት ይረግፍብናል
2ኛ ለግዜው የተሸነፈው ቆይቶ በቀሉን ለመመለስ መነሳት መቻሉ ተረጋግቶ ለመኖር አያስችለንም
3ኛ፡ ፍጹም ዘላቂ በሚመስል መልኩ የትኛውም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የተረጋጋ ኑሮ  መኖር ወደ ማይችልበት የሁል ግዜ የአዘን ቤት እንድትሆን ያደርጋል
4ኛ፡ የሁሉም ዘሮች የራሴ ግዛት ወደሚሉት የመሬት ይዞታ ካርታ አውጥተው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ። ይሄንን አቅልለኸው ካየኸው እንደ ፍሊስጤም አገር አልባል ስትሆን ያኔ ይገባሃል።
የራሴ ወገኖች የሚላቸውን አስፍሮ የሌላ ወገን የሚለውን ገድሎ አልያም አባሮ  የራሴ ለሚላቸው በመስጠት ግዛቱን በማስፋፋት ኢኮኖሚውንና ፖለቲካውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር የዘረኝነት ውጤት ነው። ይሄም ደግሞ  ሊከፍሉት የማይቻለውን ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል አለመረዳታቸው ያሳዝናል።
አሁን ባለው የዘር ፖሊሲ ከቀጠልን በመጀመሪያ ከፍተኛ እልቂት የሚፈጸመው በደቡብ ነው። 52 ብሄር አለ 52 ጦርነት ይደረጋል ማለት ነው። ሌላው ኦሮሚያ ወሎን ጨምሮ እስከ ራያ ድረስ የኔ ግዛት ነው ይላል እዚህ ጋር የሚፈነዳ እልቂት አለ ማለት ነው። አማራ ወለጋን፣ ሸዋ ጨምሮ ሃረር ድረስ የኔ ግዛት ነው ይላል እዚህ ጋርም የሚፈነዳ እልቂት አለ ማለት ነው። ሱማሌ ቦረና፣ ባሌን ጨምሮ እስከ አዋሽ ድረስ የኔ ግዛት ነው ይላል እዚህ ጋርም ሌላ የሚፈነዳ እልቂት አለ። ትግራይ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ራያ የኔ ግዛት ነው ይላል እዚህ ጋር የሚፈነዳ እልቂት አለ። ሲዳማ ቦረናን ጨምሮ አዋሳ ድረስ የኔ ግዛት ነው ይላሉ እዚህ ጋር ሌላ እልቂት አለ። በሁሉም አቅጣጫ የተጠመደ ፈንጂዎች አሉ ማለት ነው። ሁሉም ሊያተኩርበት የሚገባው ለዘሬ ቆሚያለው ዘሬን ብቻ ነጻ አወጣለው የሚል አካል ካለ ከላይ በጥቂቱ የገለጽኳቸውን አደጋ ለራሱ እንደመጋበዝ ነው። ምክንያቱም ወደ ይገባኛል ከተኬደ ወደ ፊት ልንጋፈጠው እና አይቀሬ አደጋዎች እና ጥያቄዎች እነዚህ ናቸውና።
ለኢትዮጵያ የዘላቂ መፍትሄ ህዝባችንን የሚጨቁነውን እና የሚገድለውን ሳይሆን እኩልነትና በዘር የተካለለውን ክልል በማፍረስ ለህዝብ እኩልነት እና ነጻነት የቆመ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት ሊያስተዳድር የሚችል ስርዓት መፍጠር ያስፈልገናል። ይሄንን  የሚያደርግ ማንም ኢትዮጵያዊ ለወገኑ የሚያስብ ሃላፊነት የሚሰማው ሰው እንደሆነ ልጠቁም እወዳለው። አይ የለም በዘራችን የምንል ከሆነ ግን ዘረኛ በሆንን ቁጥር ሌላ ለኛ ጠላት ሊሆኑ  የሚችሉ አደገኛ ዘረኛን እንደምንፈጥር ልናውቅ ይገባናል።
ከተማ ዋቅጅራ
03.09.2020

5 Comments

 1. Thank you Ketema Waqjira. What you said is the absolute truth and everybody who has a stake should take notice and act now. The proper name for Abiy’s party is Poverty of the Mind Party.Prosperity is a misnomer.

 2. ዕውነት ነው ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል። ጥላቻም ግጭትን ያመጣል። ግጭትም ወደ መተላለቅ ሊያመራ ይችላል። የ አገራችን ሁኔታ ወደ እዚህ አስከፊ ሰቆቃ እንደአያመራ በ አስቸኳይ መፍትሔ መፈለግ አለበት። ከ ፖለቲከኞች ምንም አይነት መፍትሔ ሊጠበቅ አይገባም። ለ ብሔር እንጂ ለ አገር አልቆሙምና። የ ፖለቲካ ሥልጣን ምኞት የሌላቸው የ ሃይማኖት አባቶች ብቻ ናቸው አገራችንን ከ መተላለቅ ሊያድኗት የሚችሉት። የ እነሱም ጥረት ሊሳካ የሚችለው የ ኢትዮጵያን አንድነት የሚፈልጉ ከ ጎናቸው ተሰልፈው ውሳኔያቸውን ሊተገብሩ ዝግጁ ሆነው ከተገኙ ብቻ ነው። አለበለዚያ አገራችን የ ትርምስ ቀጠና እንደምትሆን ምንም አያጠራጥርም። በተለይ ግብጽ አሁን አለመረጋጋት ለ መፍጠር እየሞከረች በአለችበት ጊዜ በቀላሉ ህዝባችን ሊባላ ይችላል።
  ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን እግዚአብሔር ይጠብቃቸው።

 3. ብልጽገና ቀርቶብን በሰላም ቆሏችንን በበላን! መጀመሪያ አገር ሲኖር እኮ ነው ብልጽግና የምንመኘው፡፡ በዚሁ ፕ/ሚሩ ትብዬው መሪነት የኢትዮጵያን ህልውና ለማጥፋት ጠዋት ማታ ለ3 ዓመት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ሰቆቃ ነውያመጣብን፡፡ ፓርላማ ወንበር ላይ ተቀምጦ በወሬ ሆዳችንን ይነፋል ወ እዛው ወንበር ላይ ተቅምጦ ሲያችሟጥጥ ነው የሚታየው፡፡ ሰው በሰላም ወጥቶ ካልገባ ሰላምና መረጋጋት ከሌሌ የመንግሥት መኖሩ አስተዋጽዎው ምንደነው?
  ክልል፣ ኦሮምያ ገለመሌ እያሉ መበላቀጣቸውን አቁመው ህዝብን የሚከፋፍለውን ህገ መንግሥት አስተካክሎ የክልል መሪ ሳይሆን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድር መሪ ይሄው አዛባ መሪ ወይ እራሱን አስተካክሎ ለውጥ ያድርግ ካልሆነም ችሎታ ያለው፣ በወሬ ሳይሆን የኢትዮጵያን ፍቅር በተግባር የሚተገብር መሪ ለማግኘት አብዮት ያስፈልጋል፡፡
  ፕ/ሩ የብስክሌት መለማመጃ ጎማውን ማውለቂያው ጊዜ ተላልፎበታል፡፡ በጭፍን 3 ዓመት በንጋ የወደደውም ተቀብሎት የእኔ ቢጤውም ትንሽ ጊዜ ይታይ ለወያኔ ተላላኪ ሆኖ ጥርሱን የነቀለበት ስርአት ሰውዬ ጊዜ ይፈልግ ይሆናል በማለት ይሄው አይተን ሰምተን የማናውቀውን እልቂትና ሰቆቃ ዳርጎናል ጭራሽ የኢትዮጵያን ህልውና እንደነጃዋር አገር አጥፊ ጫታም ግለሶችን በብቱ አቅፎ እንደ ኦነግ ጸረ ኢትዮጵያ ስብስቦችን እሹሩሩ እያለ ለጥፋት እዚህ አደርሶናል፡፡ አረቦቹን በቅይ ምንጣፍ እየተቅበለ የሚያደርገውን እናንሳው እንዴ? ሰውየው አላወቅውም እንጂ አገራችንን ወደማናውቃት ወደማናስታውሳት ገደል እያሽቆልቆለን ነው፡፡ I think this p/m is got to go! Enough is enough! ቢጠፋ ቢጠፋ መናፈሻና ችግኝ የሚተክል ሰው አናጣም፡፡

 4. ወንድሜ አቶ ከተማ እግዚአብሔር ይባርክህ እውነት ብለሃል፡፡
  ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል፡፡ እኛ እና እናንተ መባባላችን በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት መጀመሪያ በቋንቋ ወደ ክልል ቀጥሎ ደግሞ በሃማኖት በአካባቢ(በጎጥ) በመለያየት ወደማያባራ ትርምስ እና መጠፋፋት እንደምንሄድ አዋቂ መሆንን አይጠይቅም፡፡ የትኛውም ብሄር ብሄረሰብ ብለን ትክክለኛ ትርጉሙ የማይታወቅ መለያ ታርጋ የለጠፍንለት ህዝብና በቋንቋ ላይ ተመስርተን የፈጠርንለት ክልል ከሌሎች አንጻር ሲታይ አርተፊሻል የሆነ አንድነትና ማንነት የፈጠርንለት ቢመስለንም በውስጡ ግን ለጊዜው የተዳፈኑ ነገርግን በሀብትና በስልጣን ክፍፍል ወቅት እንዲሁም በሌሎች ብዙ ስነልቡናዊ እና ታሪካዊ ምክንያቶች የተነሳ ፈጠው የሚወጡ ብዙ ማንነቶች ስላሉ ክፍፍሎሹ ማባሪያ የሌለው መሆኑን አለመረዳት ሁላችንንም ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
  አቶ በቀለ እንደነሳኸው ብዙ ማረጃዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ለወሎው ኦሮሞ ከወለጋው ኦሮሞ ይልቅ ለብዙ መቶ አመታት አብሮት የኖረው የወሎ አማራ በስነ ልቡናም ይሁን በአኗኗር ለልቡ ይቀርበዋል፡፡ ለሸዋው አማራም በባህሉ በትውፊቱ በአለባበሱ በአኗኗሩ በአመጋገቡ በስነልቡናዊ አወቃቀሩ ከጎንደሩ ከጎጃሙ አማራ ባላነሰ አንዳንዴም በበበለጠ የሸዋው ኦሮሞ ጉራጌው እና ሌሎችም ይቀርቡታል ይመስሉታል፡፡ መቅረብም ብቻ አይደለም ተዋልዶ ተጋምዶ ተደባልቆ በመኖር በሀገር ምስረታም ይሁን አገርን በመከላከል አብሮ ዘምቷል አብሮ በየጦር ሜዳው ወድቋል፡፡ ኦሮሚያ ብለን አንድ የወል ክልል የፈጠርንለትም ህዝብ ቢሆን አርቲስት ሀጫሉ እንዳለው፣ ከልምድ እንዳየነውና ብዙ አስተዋይ ሰዎች እንደሚሉትም ወደውስጡ ሲገባ ብዙ ተፎካከሪ አካባቢያዊና ሃይማኖታዊ ክፍልፋዮችን ማቀፉን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በየክልሎቹ ውስጥ ሀገሬ ብሎ ለዘመናት የኖረውንና በአሁኑ አስተሳሰብ ዘረኞች መጤ የሚል መለያ የለጠፉለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተጋረጠበትን ስጋት እና ቀጥሎም ሊያነሳ የሚችለውን የመብት ጥያቄ ስንጨምርበት ደግሞ የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ያመለክተናል፡፡ በቅርቡ ክልል የሆነው ሲዳማም ውስጣዊ አውራጃዎችን በዘመኑ አጠራር ዞኖችን የሚጠራበት የሚያስማማ ስም በማጣቱ የአቅጣጫ ስሞችን ለመስጠት ተገዷል፡፡
  በትክክል እንዳልከው አክራሪ የዘር ፖለቲከኞቻችን ጥላቻን በመንዛት በአቋራጭ ወደስልጣን ስለሚመጡበት ሁኔታ እንጂ በዚህች ሀገር ውስጥ እንዴት አብረን እንደምንኖር አያሳስባቸውም፡፡ የህዝብ ቁጥር እና የመሬትየቆዳ ስፋት እሱም ቢሆን እንደ ሸረሪት ድር የተጠላለፈ መሆኑን ሳንዘነጋ አሸናፊ ያደርገናል ብለው ካሰቡ እጅግ ተሞኝተዋል፡፡ ሑሉም ቤት እሳት አለ፡፡ ከሁሉም በላይ ግን አሸናፊነት ከፍትሃዊነት እንጂ ከጉልበት እንደማይመነጭ አለመገንዘብ ጅልነት ይመስለኛል፡፡
  ለማንኛውም የሀገሪቱ እምብርት ስለሆነው ሸዋ እና ስለአስተሳሳሪነቱ ስለአያያዥነቱ ያነሳኸውና ወደፊት እጽፍበታለሁ ያልከው ነጥብ እጅግ አስፈላጊ ነውና በርታ፡፡ ሀገራቸውን የሚወዱ ከጎሳ በላይ ከማንኛውንም የዚህች ሀገር ዜጋ ጋር አብረው የኖሩ አሁንም በዚሁ መንገድ ለመኖር የሚሹ ሸዌዎች(ኦሮሞው ሃድያው ጉራጌው ከምባታው አማራው አርጎባው እና ሌላውም) ስላሉ ለሀገራችን ለራሳችን የሚበጀውን ለማድረግ ዝም እንደማንል ላረጋግጥልህ እወዳለሁ፡፡

 5. ወንድሜ አቶ ከተማ እግዚአብሔር ይባርክህ እውነት ብለሃል፡፡
  ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል፡፡ እኛ እና እናንተ መባባላችን በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት መጀመሪያ በቋንቋ ወደ ክልል ቀጥሎ ደግሞ በሃማኖት በአካባቢ(በጎጥ) በመለያየት ወደማያባራ ትርምስ እና መጠፋፋት እንደምንሄድ አዋቂ መሆንን አይጠይቅም፡፡ የትኛውም ብሄር ብሄረሰብ ብለን ትክክለኛ ትርጉሙ የማይታወቅ መለያ ታርጋ የለጠፍንለት ህዝብና በቋንቋ ላይ ተመስርተን የፈጠርንለት ክልል ከሌሎች አንጻር ሲታይ አርተፊሻል የሆነ አንድነትና ማንነት ያለው ቢመስለንም በውስጡ ግን ለጊዜው የተዳፈኑ ነገርግን በሀብትና በስልጣን ክፍፍል ወቅት እንዲሁም በሌሎች ብዙ ስነልቡናዊ እና ታሪካዊ ምክንያቶች የተነሳ ፈጠው የሚወጡ ብዙ ማንነቶች ስላሉ ክፍፍሎሹ ማቆሚያ የሌለው መሆኑን አለመረዳት ሁላችንንም ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
  አቶ ከተማ እንዳነሳኸው ለዚህ ብዙ ማረጃዎችን ማሳየት ይቻላል፡፡ ለወሎው ኦሮሞ ከወለጋው ኦሮሞ ይልቅ ለብዙ መቶ አመታት አብሮት የኖረው የወሎ አማራ በስነ ልቡናም ይሁን በአኗኗር ለልቡ ይቀርበዋል፡፡ ለሸዋው አማራም በባህሉ በትውፊቱ በአለባበሱ በአኗኗሩ በአመጋገቡ በስነልቡናዊ አወቃቀሩ ከጎንደሩ ከጎጃሙ አማራ ባላነሰ አንዳንዴም በበበለጠ የሸዋው ኦሮሞ ጉራጌው እና ሌሎችም ይቀርቡታል ይመስሉታል፡፡ መቅረብም ብቻ አይደለም ተዋልዶ ተጋምዶ ተደባልቆ በመኖር በሀገር ምስረታም ይሁን አገርን በመከላከል አብሮ ዘምቷል አብሮ በየጦር ሜዳው ወድቋል፡፡ ኦሮሚያ ብለን አንድ የወል ክልል የፈጠርንለትም ህዝብ ቢሆን አርቲስት ሀጫሉ እንዳለው፣ ከልምድ እንዳየነውና ብዙ አስተዋይ ሰዎች እንደሚሉትም ወደውስጡ ሲገባ ብዙ ተፎካከሪ አካባቢያዊና ሃይማኖታዊ ክፍልፋዮችን ማቀፉን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በየክልሎቹ ውስጥ ሀገሬ ብሎ ለዘመናት የኖረውንና በአሁኑ አስተሳሰብ ዘረኞች መጤ የሚል መለያ የለጠፉለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተጋረጠበትን ስጋት እና ቀጥሎም ሊያነሳ የሚችለውን የመብት ጥያቄ ስንጨምርበት ደግሞ ችግሩን የበለጠ ያወሳስበዋል፡፡ በቅርቡ ክልል የሆነው ሲዳማም ውስጣዊ አውራጃዎችን በዘመኑ አጠራር ዞኖችን የሚጠራበት የሚያስማማ ስም በማጣቱ የአቅጣጫ ስሞችን ለመስጠት ተገዷል፡፡
  በትክክል እንዳልከው አክራሪ የዘር ፖለቲከኞቻችን ጥላቻን በመንዛት በአቋራጭ ወደስልጣን ስለሚመጡበት ሁኔታ እንጂ በዚህች ሀገር ውስጥ እንዴት አብረን እንደምንኖር አያሳስባቸውም፡፡ የህዝብ ቁጥር እና የመሬትየቆዳ ስፋት እሱም ቢሆን እንደ ሸረሪት ድር የተጠላለፈ መሆኑን ሳንዘነጋ አሸናፊ ያደርገናል ብለው ካሰቡ እጅግ ተሞኝተዋል፡፡ ሑሉም ቤት እሳት አለ፡፡ ከሁሉም በላይ ግን አሸናፊነት ከፍትሃዊነት እንጂ ከጉልበት እንደማይመነጭ አለመገንዘብ ጅልነት ይመስለኛል፡፡
  ለማንኛውም የሀገሪቱ እምብርት ስለሆነው ሸዋ እና ስለአስተሳሳሪነቱ ስለአያያዥነቱ ያነሳኸውና ወደፊት እጽፍበታለሁ ያልከው ነጥብ እጅግ አስፈላጊ ነውና በርታ፡፡ ሀገራቸውን የሚወዱ ከጎሳ በላይ ከማንኛውም የዚህች ሀገር ዜጋ ጋር አብረው የኖሩ አሁንም በዚሁ መንገድ ለመኖር የሚሹ ሸዌዎች(ኦሮሞው ሃድያው ጉራጌው ከምባታው አማራው አርጎባው እና ሌላውም) ስላሉ ለሀገራችን ለራሳችን የሚበጀውን ለማድረግ ዝም እንደማንል ላረጋግጥልህ እወዳለሁ፡፡
  ሸዋን ገረመው

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.