የአርቲስት ሀጫሉን ግድያ ተከትሎ ታስረው የነበሩት እንጂነር ይልቃል ከሁለት ወር እስር በኋላ ተፈቱ

Yilkal e1599139637754ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት አራት ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ከእስር መለቀቃቸውን ፓርቲው አስታወቀ፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል ምዕራፍ ይመር ለአል ዐይን እንደገለጹት ኢንጅነር ይልቃል ዛሬ በዋስትና ከእስር ተለቀዋል፡፡ ከሁለት ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩት ፖለቲከኛው ዛሬ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለምዶ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ ከሚጠራው ማረሚያ ቤት በዋስ ተለቀዋል፡፡

ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግዲያ በኋላ በነበረው እስር ከታሰሩት መካከል የሚጠቀሱት ኢንጅነር ይልቃል ከታሰሩ በኋላ ሕገ መንግስቱ በሚፈቀደው አግባብ መሰረት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቆየታቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው እንዳይጠይቋቸው እንደተከለከሉ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

(ምንጭ፦ አል አይን)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‎በደሴ‬ ከተማ ያሉ ነጋዴዎችና ባለሱቆች የስራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር)

7 Comments

  1. A care taker government is desperately needed. Engineer Yilkal should work to form a care taker government. He needs support from within the country and from outside the country so he can work to form a care taker government. Birtukan Midekssa needs to recognize or reinstate his political party ASAP.

  2. ተመልሶ ያው የሆነ የሙታን ፓለቲካ፡፡ አሁን ማን ይሙት እንጂኒየሩ ከሃጫሉ ሞት ጋር ምን አገናኛቸው? አቶ ልደቱስ ቢሆኑ ያው እንደ በፊቱ ፓለቲካውን ከመፓትለክ ሌላ ምን ሴራ ሸርበው ነው የታገቱት? የሚገርመው የዶ/ር አብይ አመራር እየቆየ ወያኔና የድርግን የእመሰለ መምጣቱ ያው ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንዲሉ ነው፡፡ ሰው አንገቱ ሲቀላ ራሱን መከላከሉ እንደ ወንጀል በሚቆጠርባት የኦሮሞ የፈንጠዚያ ሜዳ ኢትዮጵያ ስሟን ጠልተው ሃብቷን እንደ ወያኔ የሚሻሙባት የዘር የፓለቲካ ንግድ የጦፈባት ሆናለች፡፡ እስቲ እናስብ አሁን እስክንድር ነጋ በሃሳብ ከመሟገቱ ሌላ ክፋት ይሰራል? የአስራት ጋዜጠኞች የታገቱት ለጃዋር ጋዜጠኞች መታሰር ማጣጫ ነው? እንዴትስ በረቀቀ ሴራ ሰው አስገድለው እነርሱ ሲለቀቁ ሌሎች ታግተው ቀሩ? ይገርማል፡፡ እኔ ለምድሪቱና ለህዝቦቿ አዝናለሁ፡፡ ሰው እስር ቤት ሳይገባ የማይኖርባት ምድር!
    አሁን አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው የዶ/ር አብይ መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ ልክ መንግስቱ እንዳደረገው ማኖቋቸውን እየያዘ ለእስራትና ለእንግልት ወያኔና ተባባሪዎቻቸውን አልፎ ተርፎ በጥባጭ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ቢዳርግ ኑሮ ሃገሪቱ ሌላ ገልባጭ እስኪመጣ ድረስ እፎይ ባለች ነበር፡፡ አሁን በሰላም ጥሪ ገብተው ድልድይ የሚያፈርሱ ወስላቶች በአንድ በኩል ሲታኮሱት ስልጣን ተቀምተው በመቀሌ የመሸጉት የወያኔ አለቆችና ተከታዪች ጦርነት ናና ግጠመን እያሉ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ትእቢተኞች መውደቂያቸው ሲደርስ ጥርሳቸው ወልቆ አርጅተው ዛሬም አንበሶች ነን ሲሉ መደመጣቸው ነው፡፡ የሊቢያው ጋዳፊ፤ የኢራቁ ሳዳም፤ የባናማው ጄ/ ኖርዌጋ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ወያኔ ያላወቀው ዛሬ ትላንት አለመሆኑን ነው፡፡ አጀንዳ ሳናውቅ አንሰበሰብም አለ ወያኔ፡፡ ስንት አጀንዳው ሳይታወቅ ራሱ ለዘመናት ስብሰባ ያረግ እንደነበር ማወቅ እንዴት ተሳነው? ለብሄር ብሄረሰቦች ቆሜአለሁ የሚለው ወያኔ የብሄሮችን ጭቆና ያጧጧፈ፤ በከፋፍለህ ግዛው ክልል አበጅቶ ሰዎች እንዲጫረሱ ያደረገ ድርቡሽ ከግራዚያኒ የከፋ ቡድን ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን በውጭ ያሉ አፍቃሪ ወያኔዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው የወያኔን ባንዲራ ይዘው ሲወጡና ሲጯጯሁ ማየት ምንኛ ያማል፡፡ በትግራይ ህዝብ ለዘመናት የነገደ ድርጅት እንዴት ራሱን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ ሃገር ሆኜ እኖራለሁ ሲል አውሮፓና ስሜን አሜሪካ ላይ ተቀምጠው በዚህ ህሳብ ይጠለፋሉ? ግን ጉዳዪ የዘር ፓለቲካ በሽታ መድሃኒት አይገኝለትም፡፡ ሞት ብቻ ነው የሚገላግለን፡፡ የሃበሻው የዘር ፓለቲካ ስብእናን የካደ ለእኔ ብቻ የሚል ከሰው ባህሪ የወጣ የአውሬነት መግለጫ ነው፡፡ ለዚያም ነው አንገት ቆረጣው፤ ባንዲራ አስለብሶ ገደላው እና ቤትና ንብረትን በእሳት የሚለኩሱት፡፡
    ምድሪቱ ያም መጣ ያም ሄድ ባህሪያቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ ገደላ፤ አፈና፤ እስራትና እንግልት፤ ከስራ ማባረር፤ ለወገኔ ብሎ ነገርን በአድሎ መያዝ፡፡ ሌላው በረንዳ ላይ እየተኛ በጊዜአችን እንብላ በሚል ፈሊጥ በሚስት ስም፤ በልጅ፤ ስም፤ በቅርብና በሩቅ ዘመድ ስም እንዲሁም በሽርክና ይህ ነው የማይባል ሃብት በውጭና በውስጥ ማካበት የየጊዜው አለቆቻችን ባህሪ ነው፡፡ ወያኔ በዚህ እጅግ የተካነ ነው፡፡ በአሜሪካ፤ በቻይና፤ በአውስትራሊያ፤ በታይላንድ እና በመሳሰሉት ቦታዎች ከነዳጅ ማደያ እስከ ከራይ ቤት ያላቸው ወያኔዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ናቸው አሁን የትግራይን ህዝብ ተነስ ተከበሃልና ለውጊያ ታጠቅ የሚሉት፡፡ የትግራይ ህዝብ የታጠቀውን ወይም የሚታጠቀውን መሳሪያ በእነዚህ የደም ሰዎች ላይ አዙሮ የራሱን መብት በማስከበር ከወገኑ ጋር አብሮ ለመኖር ጊዜው አሁን ነው፡፡ መነሳት አለበት፡፡ እስከመቼ በስምህ ይነገዳል? 50 ኣመት አይበቃም?
    በመዝጊያው የዶ/ር አብይ መንግስት ሸር የሌለበት በዘርና በጎሳ ያለተመረኮዘ ፍትህና ርትእ ለህዝባችን መስጠት የሚችሉ ሰዎችን በስልጣን ላይ በማድረግ ህዝባችን ካለበት ሰቆቃ እንዲወጣ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ስም የሚነግድ ኤምባሲዎች፤ የካውንስለር ቢሮዎች የሚያራምድት የማንን ጥቅም ነው? የሃገርን ወይስ የዘር ፓለቲካን፡፡ ቀረብ ብሎ መርምሮ ማየት ያሻል፡፡ ስለሆነ የኦሮሞ ቄሮዎች ቆንጨራ ይዘው ሰው እያረድ በተንጫጩ ቁጥር ዝም ብሎ ሌላውን እያጋፈፉ እስር ቤት መክተትና ማሰቃየት ተገቢ አይሆንም፡፡ ኢንጂኒየር ይልቃልና ሌሎችንም ያሳሰራቸው የፈጠራ ፓለቲካ እንጂ አንድም ክፉ ነገር ሰርተው አይደለም፡፡ ያበድት የኦሮሞ ብሄርተኞች ናቸው፡፡ ሌላው ሁሉ ከወያኔ ድንፋታ ሌላ በትንሹም ቢሆን በጎጥና በዘሩ ዙሪያ ማቅራራቱን ጋብ አድርጓል፡፡ ህዝባችን ለአንድነትና ለህብረት ዋጋ ከፍሎ ሁሉም እንዳሻው የሚኖርባት ሃገር እስካላመጣ ድረስ ምከረው ምከረው አልሰማ ካለ ግን መከራ ይምከረው የሚለው የአባቶች ተረት እንደሚሆን የጠራ እይታ ያለው ሰው ሊገምተው የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ ዋ ጊዜ ለሁሉ እንደሆነ አንዘንጋ፡፡ ማንም ምንም ይሁን ከመበደል እንቆጠብ፡፡ የማማው ላይ ፓለቲካ ማብቂያ አለው፡፡ ሰው እንሁን፡፡ በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.