ግልጽ ደብዳቤ ለኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም

ለክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ
የኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
አዲስ አባባ ፣ ኢትዮጵያ

abiyኢትዮጵያ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ጎሳዎና፣ ነገዶች፣ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎችና ኃይማኖቶች በጋራ ተባብረውና ተፋቅረው የሚኖሩባት፣ የአብሮነት፣ የፍቅርና የአንድነት እሴቶች መገለጫ የሆነች ውብ፣ ታላቅና ጥንታዊት አገር ናት። የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ ጊዜያት የተነሱበትን የውጭ ወራሪዎች በአንድነት በመቆም የተዋጋና፣ በክቡርነተዎ መልካም ንግግር እንደተገለጸው “ሲኖር ኢትዮጵያዊ ሲሞት ኢትዮጵያ” ሆኖ አንድነቱንና ነፃነቱን አስከብሮ፤ የውጭ ጠላቶቹን የመከፋፈል ስውር ደባ ሲያከሽፍ የኖረ ጀግና ሕዝብ ነው።

ይሁን እንጅ በህወሐት ሲመራ የነበረው የኢህአዴግ መንግሥት የአገሪቷን መንበረ ሥልጣን ተቆጣጥሮ በነበረበት 27 ዓመታት ውስጥ እነዚህ ለረዥም ጊዜ የቆዩ እሴቶች አደጋ ላይ እንዲወድቁ ተደርገዋል። ሕዝቡን በዘር፣ በቋንቋና በሃይማኖት በመከፋፈል ታላቅ የጥላቻ ግንብ ገንብቶ በአገሪቱ ሕልውናና በሕዝቧቿ አንድነት ላይ ከባድ አደጋ እንዲፈጠር አድርጓል። የህወሐት አገዛዝ ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨት ብቻ ሳይወሰን የማሕበረሰብ መሰረት በሆነው ቤተሰብም ወስጥ ሳይቀር ሰርጎ በመግባት ባልና ሚስትን በማፋታት ትዳር በትኗል፣ ወላጅና ልጅን አጣልቷል፣ ወንድምን ከወንድም አጋሏል፣ በአጠቃላይ የማሕበረሰቡን የቆዩ እሴቶች እንዲናዱ በማድረግ ኢትዮጵያዊነትን ለማዳከም ብዙ ሰርቷል።

ዛሬ በእርሰዎ የሚመራውን የለውጥ ኃይል ተገዳዳሪ ሆኖ፣ የጀመሩት ኢትዮጵያን “ወደ ነበረ ክብሯ” የመመለስ ጉዞ እንቅፋት የሆነብዎ ይኸው ህወሐት ፈጥሮ ያሳደገው ችግር መሆኑን እንገነዘባለን። ዛሬ ይህንን አቤቱታ ለእርሰዎ እንድናቀርብ ያስገደደን ሁኔታም ህወሐት በአማራ ብሔራዊ ክልል በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሐገር ውስጥ “የቅማንት የራስ አስተዳደር” በሚል አንድ ሆኖ የኖረውን የጎንደርን ሕዝብ ቅማንትና አማራ ብሎ ለመለያየት የተከለው መርዝ እያደረሰ ያለውን በደልና ጥፋት የተመለከተ ነው።

የቅማንት ማህበረሰብ ለረዥም ዘመናት ወንድሙ ከሆነው የአማራ ሕዝብ ጋር ከሌሎች ብሔረሰቦችና ጎሳዎች በተለየ ሁኔታ በደም፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በሥነ ልቡናና በመልካ ምድር አቀማመጥ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆኖ የኖረ ማህብረሰብ ነው።

ከዚህ ሐቅ ተፃራሪ ህወሐት የተባለው የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ሥልጣን ከያዘበት ከ1983 ዓ. ም ጀምሮ በእራሱ ቁጥጥር ስር በነበረውና ብአዴን ብሎ በሰየመው የአማራ ክልል መንግሥት ወሰጥ በከፍተኛው የአመራር እርከን ላይ በአስቀመጣቸው አባላቱ አማካኝነት የቅማንትንና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል ተደጋጋሚ ሙከራዎችን በማድረግ የተለያዩ ደባዎችን ፈጽሟል። የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ተዋቂ ግለሰቦችንና ሙህራንን በቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ሰበብ ለማደራጀት ቢሞክርም በቆራጥ የቅማንት ተወላጆች እቢተኝነት ቅዠቱ መክኖ ቆይቷል።

ይሁን እንጅ አበው “ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይለቅም” እንዲሉ ህወሐት የአማራ ክልልን የማዳከምና ከክልሉ በጉልበት ቀምቶ ወደ እራሱ ያካለላቸውን የወልቃይት፣ የጠገዴንና የራያን የማንነት ጥያቄዎች አስመልክቶ ከአማራ ክልል ሕዝብ የሚነሳበትን ጥያቄ ለማድበሰበስና የክልሉን ሕዝብና መንግሥት ትርምስ ወስጥ ለማስገባት ሲል የራሱን ቅጥረኞች በመዋለ ነዋይና ሥልጣን በማባበል ‘የቅማንት የራስ አስተዳደርና የማንነት ኮሚቴ’ የሚባል ቡድን በማደራጀት በህዝባችን ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ሲያደርስ ቆይቷል።

እርሰዎም እንደሚያውቁትና ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ‘የቅማንት ኮሚቴ ነኝ’ ባዩን ቡድን አንድ ጊዜ በጽህፈት ቤትዎ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ በጎንደር አካባቢ ተገኝተው በነበረበት ወቅት ጉዳዩን በሰላም እንዲፈቱት ምክርና መመሪያ እንደሰጡ እናስታውሳለን። ይሁን እንጅ “ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች” እንደሚባለው ከክልሉ ማዶ በሚያገኘው የገንዘብ፣ የማቴሪያል፣ የሞራልና የፕሮፖጋንዳ ድጋፍ ልቡ ያበጠው ‘የቅማንት ኮሚቴ ነኝ’ ባዩ ቡድን ምክርዎንም ሆነ መመሪያዎን ካለመቀበልም አልፎ በመሸፈት በሕዝባችን ላይ እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ወንጀሎች እንዲፈጸሙ አድርጓል። በተነሳው ሁከት ከሁለቱም ወንድማማች ሕዝቦች በኩል የብዙ ወገኖቻችን ሕይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል፣ ቤተሰብ ተበትኗል፣ የብዙ ወገኖቻቻን አካላቸው ጎሏል፣ ከስራቸውና ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ትምህርት ቤቶችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተዘግተዋል።

ይህ ሁሉ ጥፋት ከደረሰ በኋላም ቢሆን በእርሰዎ የሚመራው የፌዴራሉ መንግሥትና የአማራ ክልል መንግስት ጉዳዩን በሰላም ለመፍታት ‘የቅማንት ኮሚቴ ነኝ’ ለሚለው ሽፍታ ቡድን ምህረት በመስጠት የወሰደውን የሰላም አማራጭ እኛ በስሜን አሜሪካ የምንኖር የቅማንት ተወላጆች ስብስብ እጅግ የምናደንቀው ከመሆኑም በላይ ምስጋናችን ለመግለጽ እንወዳለን።

ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን ያለ ሕዝቡ ይሁንታና ፍላጎት እንዲሁም በሕገ መንግሥቱ ከተቀመጡት አንቀጾች ውጭ በፖለቲካ ውሳኔ በ69 ቀበሌዎች የቅማንት የራስ አስተዳደር እንዲመሰረት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንቃወማለን። የምንቃወምበትን ምክንያቶችም ለክቡርነትዎ እንደሚከተለው እናቀርባለን።

1- ‘የቅማንት የራስ አስተዳደር’ የተባለው ጥያቄ የቅማንት ማህበረሰብ ፍላጎት አለመሆኑና ለህበረተሰቡ ሌሎች አማራጮች በነፃነት ቀርበውለት ተወያይቶበትና ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎበት ያልተወሰነና የአንድን ወገን የፖለቲካ ፍላጎት ብቻ መሰረት አድርጎ የቀረበ በመሆኑ፤

2- ‘የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር’ ጥያቄ የቀረበለት የአማራ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ጊዜያት ኮሚቴዎችን በማቋቋምና ጉዳዩን በማስጠናት ብዙ ውይይቶችን አድርጎ፤ ምክር ቤቱ በ4ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ጥያቄው የህገ መንግስቱን መስፈርቶች የማያሟላ ሆኖ በመገኘቱና ውድቅ በማድረጉ፤

3- የቅማንት ማህበረስብ በመላው የጎንደር ክፍለ ሐገር በሰላም የሚኖርና ከላይ እንደገለጽነው ከአማራ ወንድሙ ጋር በጋብቻ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በሥነ ልቦናና በመልካ ምድር በጣም የተሳሰረ ስለሆነ ማሕበራዊ ኑሮው ስለሚመሳቃቀልና ቤተሰብ ስልሚበተን የጉዳዩን አሳሳቢነት ግምት ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ ነው ብለን ስለምናምን፤

4- ይህ ጉዳይ በቅማንትና አማራ ማህበረሰብ መካከል ጸንቶ የቆየውን የቤተሰባዊነት ስሜት የሚያዳክምና ለማያባራ ግጭት መንስኤ ሊሆን ይችላላ ብለን ስለምንሰጋ፤

5- ይህ አካባቢ አገራችን ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የምትዋሰንበትና በተለያዩ ጊዜያት የወሰን ውዝግቦችና ግጭቶች የሚነሱበት አካባቢ በመሆኑ የሁለቱም ማህበረሰቦች መለያየት ለጠላት መጠቀሚያ ሊሆን እንደሚችል በማሰብ፤

6- የቅማንት ማህበረሰብ በ69 ቀበሌዎች ተከልሎ መኖር እንደማይፈልግና እንደ ጥንቱ በትውልድ አገሩ በጎንደር

(በኢትዮጵያ) ተዘዋውሮ፣ ሠርቶና ሀብት አፍርቶ በሰላም ከወንድሙ የአማራ ሕዝብ ጋር መኖርን የማይደራደርበት

አቋሙ መሆኑን በየጊዜው ከቤተሰብ፣ ጓደኛና ዘመድ ጋር በምናደርጋቸው ግንኙነቶችና፣ አንዳንዶቻችንም ለውጡ

በፈጠረልን የተመቻቸ የፖለቲካ ሁኔታ ተጠቅመን ለረዥም ጊዜ ወደ ተለየናት አገራችንና ቀያችን በመሄድ ስለሁኔታው

ከታዘበነውና ከተመለከትነው ለመረዳት ስለቻልን፤

7- ሕዝቡ በተለያዩ ጊዜያት ከክልሉና ከአካባቢው ባለሥልጣናት እንዲሁም ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ባደረጋቸው ስብሰባዎች ስሜቱን በተለያዩ ሚዲያዎች በመመልከታችን፤ ለምሳሌም የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት የነበሩት የተከበሩ ዶክተር አምባቸው መኮነን በ2010 ዓ ም ገንደዋ በተባለው የወረዳ ከተማ ሕዝቡን ስብስበው ባነጋገሩበት ወቅት ከሕዝቡ ይሰማ የነበረውን የአንድነት ስሜት እንደ ማስረጃ መጥቀስ በቂ በመሆኑ፤

‘የቅማንት የራስ አስተዳደር’ ተለይቶ እንዲቋቋም በአማራ ክልላዊ መንግሥት በኩል የሚደረገው ጥድፊያ ተገቢ ነው ብለን አናምንም።

በህወሐት ግፊት ራሳቸውን አደራጅተው፣ የእጅ አዙር ተልእኮ ተቀብለው ኣካባቢውን በሚያውኩ፣ ሆን ተብሎ በተሠራ የቅጥፈት የመብት ጥያቄ አንጋቢዎች ፍላጎት ብቻ ተነስቶ፣ በጥድፊያ በአብሮነትና በአንድነት የኖረውን የጎንደርን ሕዝብ መለያየት ተገቢ ስላልሆነ፤ የዓለም ሕዝብና መንግሥታት ስጋት የሆነው የኮቪድ 19 ወረሽኝ በሽታ ተውግዶ ሕዝቡ ወደነበረበት የሰላም ኑሮ ተመልሶ፤ የቅማንት ማህበረሰብ የተለያዩ አማራጮች በነፃነት ቀርበውለት ዕጣ ፋንታውን እራሱ ተወያይቶ እንዲወስን እስኪደረግ ድረስ ‘የቅማንት የራስ አስተዳደር’ የሚባለው መስተዳድር እንዳይመሰረት መመሪያ እንዲሰጡልንና ክትትልም እንዲያደርጉልን በታላቅ አክብሮትና ትህትና እንጠይቃለን።

በመጨርሻም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ለማዳንና ወደ ነበረ ክብሯ ለመመለስ ለሚያደርጉት ዕረፍት አልባ ጥረትዎ የበኩላችን የምንወጣ ሲሆን እርስዎንም እግዚአብሔር እንዲረዳዎት የዘወትር ፀሎታችን መሆኑን ለመግልፅ እንወዳለን።

ኢትዮጵያ በአንድነቷ ጸንታ ለዘላላም ትኑር!!!

ፀጋዬ ታደስ

በሰሜን አሜሪካ የምንኖር የቅማንት ተወላጆች ዋና አስተባባሪ

ሰሜን አሜሪካ (USA)

ግልባጭ

• ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባሕር ዳር

5 Comments

 1. Well, if your letter of complaint could make sense if it could be addressed to a leader of a country who came to power either for genuine reason or honest objective which is of course making a fundamental democratic political change by making the bloody ethno-centric system of EPRDF history . Yes, it could have been great if he was willing and able to get rid of a system which he himself was one of the most important cadres of it by being the boss of the intelligence and security agency that was instrumental to hunt down those innocent citizens who stood against the brutal ruling circle .
  It is self evidently true that this guy came to power after he and his hypocritical and conspiratorial colleagues planed how to remove the hegemony of TPLF and replace it with the hegemony of the Oromo elites who had and have the goal of Oromization of the country very much similar to the 16th century of the Oromo migration and invasion . And this has been proven true in these two years of of the called reforming EPRDF by renaming it Prosperity . This has already been proven by both official and confidential words of those Oromo elites such as Shimeles Abdesa .
  Did the prime minister say and do anything about all what his colleagues are talking and doing ? Ugly enough , nothing ! Did he say and do anything serious during the last two years of blood shed and untold suffering caused by his social and political base called Qerro ? Absolutely nothing ! Did he say or do anything about the plight of Addis Ababa which has been ruled by a guy he made him its mayor through very cynical and conspiratorial way doing things ? Absolutely nothing! Did he say and do anything about those large territories of the Amahara ? Absolutely nothing ! Did he say and do any meaningful words and actions with regard to those young students of Denbedolo university students who have been missing for so long ? Absolutely nothing !
  He instead keeps playing a very stupid and dangerous political drama including the photo up of talking about beautifying Addis . I hate to say but I have to say that this kind of an extremely misleading or hypocritical drama of politics is much more dangerous than those dictators who make their rulings unquestionable .

  I have to say that whatever you try to appeal and re-appeal or beg , the issue you are talking about will never be addressed and resolved under this system of EPRDF ! What is the right thing to do is helping the people to continue their struggle against these brutally stupid politicians of EPRDF/Prosperity ! No less than this struggle brings about a true democracy and any other sound resolution !

  • Well said.
   This p/m is got to go. We need revolution.Period! It’s enough to look around & listen his elected ignorant officials? Sickening This p/m is destroying Ethiopia in a very surgically done manner.
   Our people are dying left and right, but his priorities are planting flowers around Addis. It’s a crock of shit.

 2. Ethiopia is a failed state under Abiy Ahmed’s administration. Ethiopia failed in all aspects including in international relations. The begging scientists of Ethiopia are not succeeding as they used to. Abiy Ahmed’s administration is a candidate for UN sanctions due to the wide spread Crimes Against Humanity it commits.

  Abiy Ahmed should free all political prisoners and form a transitional government within the next couple of months otherwise Abiy’s administration should know the people of Ethiopia got no other choice but to remove his administration from power. There is no reason to tolerate the Abiy Ahmed’s state terrorism anymore because Abiy’s state terrorism is escalating as time went on, expected to reach a stage of biblical proportions if it continues in the same pace.

 3. በአማርኛ ጋዜጣ ላይ በእንግሊዝኛ አስተያየቶችን የሚጽፉ ሰዎች ደካማ አእምሮ አላቸው
  የራሳቸውን ቋንቋ ችላ በማለት ግን የቅኝ ገዥውን ቋንቋ እያስተዋውቁ ነው
  ወፍራም ጭንቅላት!

 4. በአማርኛ ጋዜጣ ላይ በእንግሊዝኛ አስተያየቶችን የሚጽፉ ሰዎች ደካማ አእምሮ አላቸው!!!!
  የራሳቸውን ቋንቋ ችላ በማለት ግን የቅኝ ገዥውን ቋንቋ እያስተዋውቁ ነው!!!
  ወፍራም ጭንቅላት!!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.