አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አቅርቦ ጭብጥ አስመዘገበ

Jawar Mohamed አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብ በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አቅርቦ ጭብጥ አስመዘገበ።

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪዎቹ የቀረቡ ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ በ3ኛ፣ 13ኛ እና 14ኛ ተጠርጣሪዎች በድጋሜ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ የአዲስ አበባ እስረኞች አስተዳደር ተወካይ በባለፈው ቀርቦ አለማብራራቱን ተከትሎ ታስሮ እንዲቀርብ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ቀርቧል።

ተወካዩ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ እስረኞች መሆናቸውን ጠቅሶ በውሰት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መቆየታቸውን ይሁን እንጂ በዚያው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኮቪድ ምርመራ እንደተደረገላቸው ማብራሪያ ሰጥቷል።

ከዚህ በፊት ለምን አልቀረብክም ተብሎ በፍርድ ቤቱ ለቀረበለት ጥያቄ ተእዛዝ እንዳልደረሰው ገልጿል።
ፍርድ ቤቱም እነዚህ ተጠርጣሪዎች በድጋሚ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ይህ ካልተፈፀመ ፍርድ ቤቱ እንደሚቀጣው አፅንኦት ሰጥቷል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማቅረቡን ገልፆ የምስክሮችን ስም አስመዝግቧል።
በዚህም መሰረትም አቃቤ ህግ ተጨማሪ አራት ምስክሮችን አሰምቷል።

ይሁን እና ፍርድ ቤቱ አራተኛዋ ምስክር ላይ የተጀመረው የመስቀለኛ እና የማጣሪያ ጥያቄ ስላላለቀ በይደር ምስክሯ ቀርበው መስቀለኛ እና ማጣሪያ ጥያቄው እንዲቀርብላቸውና ሌላ ቀሩ የአቃቤ ህግ ቅድመ ምርመራ ምስክርን ለመስማት በይደር ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በአጠቃላይ አቃቤ ህግ እስከለ ዛሬ ድረስ ሰባት የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰምቷል።

ዛሬ ተጠርጣሪዎቹ ከ7 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ከ30 የነበረው የምሳ ሰዓት እረፍት ምግብ አለመመገባቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ቀ2ጣይ ምስርሮቹ ሙሉ ቀን ስለሚሰሙ ምምሳ ሰዓት ምገብ የሚመገቡበት ሁኔታ ፖሊስ ያመቻችላቸው ብሏል።

የዛሬው የምስክሮች ቃል ተገልብጦ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ አዟል።

ዐቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ ዘጠኝ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰምቷል።
ዐቃቤ ህግ 15 የቅድመ ምርመራ ምስክሮች ማዘጋጀቱን የገለፀ ሲሆን፥ ከ15 ምስክሮች ውስጥ 4ቱ በተለያዩ ምክንያቶች እና የምስክር ጊዜ ላለማራዘም ማሰማት አልፈልግም ሲል ለችሎቱ ገልጿል።
ዐቃቤ ህግ በ11ኛ እና 14ኛ ተራ ቁጥር ያስመዘገባቸው ቀሪ ሁለት ምስክሮች ስልካቸው ባለመስራቱ ለነሃሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነት ይሰማልኝ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በልደታ አዳራሽ የተገኙት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ የዐቃቤ ህግ ቀሪ ሁለት ምስክሮች ዛሬ ተሰምተዋል።
በዚህም ሂደትም ዐቃቤ ህግ የሚያሰማቸው እና የማያሰማቸው ቀሪ ምስክሮች ዝርዝር ይገለፅልን ሲሉ የተጠርጣሪ ጠበቆች ጠይቀዋል።
ዐቃቤ ህግም ለደህንነታቸው ሲባል ዝርዝራቸውን አልገልፅም፤ ከዚህ በፊት ምስክር የነበሩ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ሽጉጥ ጉዳት ደርሶባቸው ፓሊስ ጣቢያ ማደራቸውን ጠቅሶ በተለያዩ ጊዜ ምስክሮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰ በመሆኑ ለደህንነታቸው ሲል ዝርዝራቸውን መግለፅ እንደማይፈልግ አብራርቷል።
ተጠርጣሪዎችም የተለያዩ አቤቱታዎቻቸውን ለፍርድ ቤት አስመዝግበዋል።
አቶ በቀለ ገርባ የባንክ ሂሳባቸው መታገዱን እና የግል ተሽከርካሪያቸው እንዳልተመለሰላቸው አቤቱታ አቅርበዋል። እንዲሁም የማረሚያ ቤት አያያዛቸው እንዲስተካከል ጠይቀዋል።
አቶ ሃምዛ አዳነ በአንድ መፅሄት እንዲሁም በሌሎች ጋዜጦች ስሜ እየጠፋ ነው ሲሉ አመልክተዋል።
አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የተባሉ ተጠርጣሪም የጆሮአቸውን ህመም በሚፈልጉት የህክምና ተቋም እንዲታከሙ ፍርድ ቤቱ ያዘዘው ትዕዛዝ አልተፈፀመም ሲሉ በድጋሜ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል።
ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም በተነሱ አቤቱታዎች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት እና ሁለት የዐቃቤ ህግ ከመጋረጃ ጀርባ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለነሃሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ/ ኤፍ.ቢ.ሲ

 

1 Comment

  1. ፍርድ ቤቱ በጥይት ለተመቱት ምስክሮችን ለምን በእስር ቤት አቆያቸው?
    ግራ የተጋባው ፍርድ ቤት ወይም ዜና !!! ምንድነው?
    ማረሚያ ቤቱ እንደ ሆስፒታል ይቆጠራል?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.