ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይሄን ጉድ ያውቁታል? – ሃብታሙ ምናለ

abbebe

ኢ/ር ሰናይት ዳምጤ ከታከለ ዑማ ጋር በመመሳጠር የአዲስ አበባ ህዝብ ቆጥቦ የሰራውን ቤት ስታከፋፍል የነበረች የጋራ መኖሪያ ቤት ማጅራት መቺ ናት። ታከለ ዑማ ከሥልጣኑ ሊወርድ መሆኑ ስታውቅ ቤቶችን በፍጥነት ለምትፈልጋቸው በመስጠት፣ ቤቶቹን ለመረከብ ከወራት በላይ የሚወስደው ፕሮሰስ በአንድ ሳምንት ውስጥ እንዲያልቅ በማድረግ ርክክብ እንዲፈፀም አድርጋለች። ለዚህም ማሳያ ነሐሴ 8/2012 ዓ.ም በአንድ ቀን ለአንድ ቤተሰብ፣ ለሦስት ወንድማማቾች ባለሁለት መኝታ ቤቶችን በአጠቃላይ ሦስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሰጣቸው አድርጋለች። ታከለ ዑማም የአላማው ማሳኪያ መሳሪያ አድርጎ በጥሩ ሁኔታ ሲጠቀምባት ቆይቷል። ታከለ ብዙ ወንጀሎችን ቢሰራም ምን ያህል ሲዘርፍ እንደነበር በጥቂቱ አንዱ ማሳያ ነው።

ኢንጅነሯ አሁንም በቦታዋ ላይ ተቀምጣ የታከለ ኔትወርክነቷን እየተጠቀመችበት ማረግ የምትፈገውን እያረገች ትገኛለች።
እነዚህ ሦስት ቤተሰቦች የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፣ ከጻፈ በኃላ ቤቶች ኮርፖሬሽንም ለቦሌ ክ/ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመጻፍ በፍጥነት ቤቶቹ ለሦስቱም እንዲሰጣቸው ተደርጓል። የሰዎቹን መረጃ በጥቂቱ ላክልፍላችሁ:-

1. ሻሾ መኮንን የትውልድ ቦታ ምዕራብ ሸዋ፣ ዕድሜ 19 ደብዳቤው የተጻፈላቸው ቀን ነሐሴ 8/2012 ዓ.ም የደብዳቤው ቁጥር 1ሀ/አ/ቤ/ል/አስ/ቢ/5487/2021 ዓ.ም – ልማት ኮርፖሬሽን ደግሞ ለቦ/ክ/ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቁጥር 7207/12፣

2. ታደሰ መኮንን የትውልድ ቦታ ምዕራብ ሸዋ፣ ዕድሜ 25 ደብዳቤው የተጻፈላቸው ቀን ነሐሴ 8/2012 ዓ.ም የደብዳቤ ቁጥር 1ሀ/አ/ቤ/ል/አስ/ቢ/5485/2021 ዓ.ም – ልማት ኮርፖሬሽን ደግሞ ለቦ/ክ/ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቁጥር 7195/12፣

3.እንዳልካቸው መኮንን የትውልድ ቦታ ምዕራብ ሸዋ፣ ዕድሜ 36 ደብዳቤው የተጻፈላቸው ቀን ነሐሴ 8/2012 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር 1ሀ/አ/ቤ/ል/አስ/ቢ/5424/2021 ዓ.ም – ልማት ኮርፖሬሽን ደግሞ ለቦ/ክ/ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቁጥር 7201/12
ካሉት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም ውስጥ የመኖሪያ ቤት በልዩ ሁኔታ እንዲሰጣቸው ተወስኖ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።

ከስር የሦስቱንም ሰዎች መረጃ አያይዤያለሁ:

118777961 3134749313261034 3667869768391262381 n

118802301 3134749783260987 7255118560532548436 n 118702742 3134749583261007 6954280607491438897 n  118779920 3134749433261022 2173985327805777226 n

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.