ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም የሚያስቸግረኝን ከውስጤ ላውጣው

Mesfinእአአ ዛሬ 8/31/2020
ከሌሊቱ በኢት. ሰዓት አምስት ሆነ፤ እንቅልፍ አሻፈረኝ ስላለ የሚያስቸግረኝን ከውስጤ ላውጣው፡፡
ኢዜማ በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጸመውን የመሬትና የቤት ዝርፊያ በማስረጃ የተደገፈ መግለጫ ማውጣቱን ሰማሁ፤ መግለጫው እንዳይሰማ በተደረገው ሕገ-ወጥ ጉልበተኛነት በመከልከሉ በቢሮው ውስጥ እንዳሰማው ሰማሁ፤ ብዙዎቻችን ስንጠረጥረውና በሀሜት ደረጃ ስናወራው የነበረውን ኢዜማ ገሀድ አወጣው፤ ኢዜማን የደሀ አምላክ ይባርካችሁ፤ የእውነት መሪዎች ያድርጋችሁ፤ ብዬ አልፈዋለሁ፡፡
የኢዜማን መግለጫ ከነቆሻሻው የብልጽግና ፓርቲ ወደደደም ጠላ ይረከበዋል፤ ያቃጥላልና ሊይዘው አይችልም፤ ሊተወውና ቆሻሻው ተስፋፍቶ አገሩን እንዲውጠው ማድረግ አይችልም፤ ብልጽግና ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው፡ አስቸኳይ አብዮታዊ እርምጃ መውሰድ!
ብልጽግና በአብዮታዊ እርምጃ ካልጸዳ ብልጽግና እንደጣና ባሕር በእምቦጭ ይወረራል! ይህንን ቆሞ የሚያይ ሕዝብ ካለ እንዳለ አይቆጠርም፤ ቆሻሻውን ተሸክመን ወደ2013 ዓ.ም. መግባት አዲሱን ዘመን ማቆሸሽ ነው፡፡ አልጨረስሁም!
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከጋምቤላ ታግተው የተወሰዱት 125 ህፃናት ያሉበትን ቦታ መክበቡን አስታወቀ

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.