ተደጋጋሚ ሹም ሽሮች እና የሹማምንት ሽግሽጎች በቅጡ መርጋት በተሳነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል?

lema 1ሹም ሽር መሪዎች የካቢኔ እና የፓርቲ ፖለቲካን ከሚዘውሩባቸው መሳሪያዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ምኒስትሩ ከሚኖሯቸው ቁልፍ ሥልጣኖች አንዱም ይኸው የመሾም እና የመሻር ኃይል ነው። መሪዎች ታማኞቻቸውን በሹመት ያበረታሉ ተቃዋሚዎቻቸውን፣ ተገዳዳሪዎቻቸውን በሽረት ገለል ያደርጋሉ። በመንግሥት ውስጥ ጥምረት የሚያበጁበት በርከት ያሉ አንጃዎች ወይም ጎራዎች ሲኖሩ ደግሞ ሥልጣን በመስጠት የፓርቲ ፖለቲካን የሚቆጣጠሩበት መንገድ ነው።

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባሎችን ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ወይም ለሥራው ብቃት ካላቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርቦ ሹመታቸውን ያጸድቃል” ሲል ይደነግጋል።

ባለፈው ሳምንት በአስር የኢትዮጵያ መንግሥት ተቋማት ሹም ሽር ተካሔደ። ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ያክል ለማ መገርሳ ከመከላከያ ምኒስትርነት ተነሱ። ጌድዮን ጢሞቴዎስ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆነዋል። አዳነች አቤቤ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግነት ወደ ከንቲባነት ተዘዋወሩ። ከንቲባው ታከለ ዑማ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ታከለ የተኩት አቶ ሳሙኤል ኡርካቶን ነው። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ሲይዙ የማዕድን እና ኢነርጂ ምንስትርነትን የተሾሙት ሳሙኤል አሁን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ቦታን ይዘዋል። ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሆነዋል።

በፌድራል መንግሥቱ ውስጥ ከተደረገው ሹም ምር በኋላ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተመሳሳይ እርምጃ ተወስዷል። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሐሰን በክልሉ ካቢኔ የአዲስ አመራሮች ሹመት እና ሽግሽግ ማድረጋቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የኮምዩንኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በደቡብ ክልል የወላይታ ዞን ከኃላፊነታቸው በተነሱት ዳጋቶ ኩምቤ ምትክ አዲስ አስተዳዳሪ ተሾሞለታል። የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ባለፈው አርብ ባካሔደው ስብሰባ አቶ እንድርያስ ጌታ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: "እነሱ ለዓላማቸው ፈንጂ መርገጣቸውን ሲነግሩን ነበር እኛ ደግሞ የእነሱን እስርና ድብደባ ፈርተን ወደ ኋላ አንልም.." - አቶ ሃብታሙ አያሌው (ቃለ-ምልልስ)

በፓርቲው ውስጥም ተደጋጋሚ ሹም ሽሮች እና የሹማምንት ሽግሽጎች እየታዩ ነው። በሳምንቱ መጀመሪያ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊነታቸው ተነስተው በአቶ መለስ ዓለሙ ተተክተዋል። አቶ መለስ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እንዲሁም የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ነበር። ተደጋጋሚ ሹም ሽር የምን ምልክት ነው? በቅጡ መርጋት በተሳነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይስ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል? በዚሁ ጉዳይ ላይ ለተደረገው ውይይት ጋዜጠኛ ጸዳለ ለማ፣ ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ እና የፖለቲካ ተንታኙ ሰላሐዲን እሸቱን ጋብዘናል።

DW

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.