የአሜሪካ ኮነግረንሶች ደብዳቤ ይዘትና ቁማራዊው ጫወታ – ሰርፀ ደስታ

የአሜሪካ ኮንግረንሶችን ደብዳቤ ተከትሎ ብዙ የማሳከሪያ ዜናዎችን ስንሰማ ቆይተናል፡፡ እርግጥ ነው ደብዳቤው ሲጀምር ይዘቱ ሌላ እንዲሆን በፈለጉ ሰዎች ነበር፡፡ ሆኖም በአገርና ሕዝብ ወሳኝ ልጆች ክትትል በሴረኞች የተጀመረው ደብዳቤ ትክክለኛ አግባብነት ያለው ሆኖ እንዲስተካከል ተደርጓል፡፡ ሰሞኑን እየሰማን ያለንው ውዥንብር ግን የተለመደው ድራማዊ ቁማር እንደሆነ እየታዘብን ነው፡፡ አልፎም ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ አይነት ሆኖብናል፡፡ የሚከተሉት ማሳከሪያዎች በስፋት እየተሰራጩ እንደሆነ እየተመለከትን ነው፡፡

ጀዋርና በቀለ ገርባ እንዲለቀቁ ተጠየቀ፡– በደብዳቤው በአንድም መስመር ላይ የግለሰቦችን ሥም ጠርቶ እከሌ ይለቀቅ የሚል ሐረግ የለም፡፡ በትክክልም በፖለቲካ አመለካከታቸውና ለሕዝብ መረጃ በማቀበላቸው የታሰሩ መኖራቸውን ይጠቁማል፡፡ ይሄ ማለት እነ ጀዋርን ማለት ነው ብሎ ለማሳከር የሚሞከረው ሙከራ እስካሁንም እያየንው ያለንውን እንጀዋርን በትክክለኛ ወንጀላቸው ከመክሰስ ይልቅ የሐጫሉን አስከሬን አስመልሳችኋል በሚል ነው እየተከሰሱ ያለው፡፡ እኛ ምን እናድርግ ኮንግረንስ ነው ያስገደደን በሚል ሊለቋቸው ምክነያት እየፈጠሩልን እደሆነ በግልጽ ሊስተዋል ይገባል፡፡ የኮንግረንስ አባላቱ በእርግጥም መጀመሪያ በኦሮሞ (እስላማዊ) አክራሪዎች እንዲህ ያለ ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሁሉም የኮንግረንሱ አባላት በግልጽ በኦሮሞ ክልል ውስጥ ለተደረገው ጭፍጨፋ ምን አይነት ቅድመ ዝግጅት ሲደረግ እንደነበረና ጀዋርን ጨምሮ ሌሎች ብዙዎች ለዚህ ዋና ቀስቃሽ እንደነበሩ በማስረጃ ተደግፎ ስለቀረበላቸው የኦሮሞ አክራሪዎች እንዲሆንላቸው ያሰቡት አልተሳካም፡፡ ሆኖም በግልጽ የኮንግረንስ አባላቱ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንዳች ግንኙነት የሌላቸው የፖለቲካ አመራሮችና ጋዜጠኞች መያዛቸው ተረድተዋል፡፡ በደንብ ተነግሯቸዋል፡፡  የደብዳቤው መንፈስም ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸውና መረጃ በመስጠታቸው ታስረዋል የሚለው ከዚህ አንጻር እንጂ ከእነ ጀዋር መያዝ ጋር እንዳልሆነ ግልጽ ሊሆንልን ይገባል፡፡ ይችን ቁማር እየቆመረ የሚገኘው ቀድሞውንም በቀጥታ ወንጀላቸው ላለመጠየቅ እያቅማማ የነበረው የኦሮሞ-አብይ አስተዳደር ሴራ እንደሆነ ሊታወቅ ይባል፡፡ ኮንግረንሶቹ መጀመሪያ መረጃ ብዙም ባይኖራቸውም ኋላ ላይ ግን በግልጽ የሆነውን ሁሉ አውቀውታል፡፡ ሆኖም ከፈራሚ ኮንግረንሶቹ አንዳንዶች እያወቁ ይሄ በመጨረሻ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የገባውን ደብዳቤ ይዘት ለመቀየር ሞክረው ሁሉ ነበር፡፡ በዚህ ደብዳቤ በግልጽ ኮንግረንሶቹ እንደነ እስክንድር ነጋና የመሳሰሉት በትክክለም የፖለቲካ እስረኞች እንደሆኑ ተረድተዋል፡፡ በርካታ ስለጭፍጨፋው ሲዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞችም እንደታሰሩ አውቀዋል፡፡ የደብዳቤውም መንፈስና ይዘት ከዚህ አንጻር ነው፡፡

የአየሁድ ኮንግረንሶች ሴራ ነው፡- ይሄ ሌላው እየሰማን ያለንው ማሳከሪያ ነው፡፡ አንዳንዶች ሚዲያን ለግል ፍላጎታቸው በማዋል ሕዝብን ለመረጃ ሥካር በመዳረግ ያለውን የአብይ አህመድን ቁማር ሊከልሉ ሲሞክሩ አይተናል፡፡ አብይ አህመድ በኢትዮጵያዊነት ራሱን ጀቡኖ አደገኛ የሆነ አካሄድ እየሄደ እንደሆነ በተግባር ባየናቸው እውነታዎች ታዝበናል፡፡ የሆነ ሆኖ አሁን የምናየው ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ አይነት ቁማር ነው፡፡ ሲጀምር የዚህ ደብዳቤ ጠንሳሽ አይሁዶች ሳይሆኑ ሌሎች ናቸው፡፡ አንዳንዶች የሚኒሶታዋን የሱማሌ ተወላጅ ኮንግረስ አባል ይላሉ፡፡ በእርግጥም የመጀመሪያ አነሳሱ ይች ኮንግረንስ አባል የምትደግፈው ነበር፡፡ ኋላ ላይ ግን እሷም በአሰበቸው አልሆንም እንጂ፡፡ የአይሁድ ዝርያ ያላቸው ኮንግረንስ አባላት ፈርመው ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም የዚህ ደብዳቤ ይዘት ከአባላቱ የዘር ማንነት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ፍትህና እውነትን በፈለጉ ኢትዮጵያውያን ሐሳባቸው እየተጠየቀና መረጃ እየሰጡ የተዘጋጀ ነው፡፡ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ በእርግጥ ነው ሚኒሶታ አካባቢ ያሉ ተወካዮች ፍላጎት ሌላ ነው፡፡ የሚኒሶታዎቹ ሴናተሮች ሰሞኑን የተናገሩት ከኮንግረንሱ ደብዳቤ ይዘት ጋር የሚገናኝ ሳይሆን ቀድሞውንም የኮንግረንሱ ደብዳቤ ይዘት እነሱ የተናገሩት እንዲሆን ብዙ ሲጥሩ ከነበሩ ጋር በሚሰሩት የኮንግረንስ አባላትና የኦሮሞ (እስላማዊ) አክራሪዎች ቁማር ነው፡፡ ሴናተሮቹ እውነቱ እየተነገራቸው ነው፡፡ የኮንግረንሶቹ የደብዳቤ ይዘት ግን የትክክለኛ ኢትዮጵያውያን ሐሰብ ነው፡፡   አንዳንዶች የኩለማቻርና ለፕሬዘዳንትነት እጩ እንደነበረች በማንሳት ይሄን ጉዳይ ትልቅ ሊያደርጉት ሞክረዋል፡፡ ትልቁ ጉዳይ ግን የሴናተሮቹ ሳይሆን የኮንገረስ አባላቱ ደብዳቤ ነው፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር አገራችንንና ሕዝቧን ከክፉዎች ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

The full letter to Secretary Pompeo and the list of Congressional signatories can be read here.

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.